Bukayo Saka 07 fan ኢትዮጵያ

Bukayo Saka 07 fan ኢትዮጵያ

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bukayo Saka 07 fan ኢትዮጵያ, Sport & recreation, Dubai.

14/08/2025



✨ ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ

💒 ✨ ቅዳሴ ዘእግዝእትነ ማርያም ትርጓሜ ክፍል 1️⃣ ✨💒
𝗤𝗜𝗗𝗔𝗦𝗘 𝗠𝗔𝗥𝗜𝗔𝗠- 𝙏𝙃𝙀 𝘼𝙉𝘼𝙋𝙃𝙊𝙍𝘼 𝙊𝙁 𝙎𝙏. 𝙈𝘼𝙍𝙔
▬▬▬▬▬ ▬▬ ▬▬▬▬▬
(ጴጥሮስ አሸናፊ ከበደ)

፩. አኮቴተ ቍርባን ዘእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘደርሰ ላቲ በመንፈስ ቅዱስ አባ ሕርያቆስ ኤጲስ ቆጶስ ዘሀ ገረ ብህንሳ ጸሎታ ወበረከታ የሃሉ ምስለ ኵሎሙ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም አሜን ።

ሕርያቆስ ማለት ኅሩይ ማለት ነው ለሹመት መርጠውታልና።
አንድም ረቂቅ ማለት ነው ምሥጢረ ሥላሴን ይናገራልና። ከሊቃውንትስ ምሥጢረ ሥላሴን የማይናገር የለም ብሎ ከሁሉ ይልቅ እሱ አምልቶ አስፍቶ አጉልቶ ይናገራልና።
አንድም ፀሐይ ማለት ነው አብ ፀሐይ ወልድ ፀሐይ መንፈስ ቅዱስ ፀሐይ ብሎ ጽፏልና።
አንድም ብርሃን ማለት ነው የምዕመናንን ልቡና በትምህርቱ ብሩህ ያደርጋልና። ዘአብርሃ መንበረ ማርቆስ በብርሃን እንዲል።
አንድም ንሕብ ማለት ነው ንሕብ የማይቀምሰው አበባ የለም እሱም የማይጠቅሰው ሊቅ የለም።

ይህስ እንደምን ነው ቢሉ ሐዋርያት የተማረ ግብረ ገብ ይሾም ብለው ሥርዓት ሠርተዋል ይህስ አይደለም ሁለቱን አስተባብሮ የያዘ አይገኝም ብሎ የተማረ ከሆነ ይሾም ብለዋል። በትምህርቱ መናፍቃንን ተከራክሮ ይመልሳልና ብለው ግብረ ገብም ከሆነ ይሾም ብለዋል በጸሎቱ ይጠብቃል በትሩፋቱ ያጸድቃል ትምህርቱን ውሎ አድሮ ያደርገዋልና ብለው ሾሙት። ይህም አባ ሕርያቆስ ያልተማረ ግብረ ገብ ነው። ቢማርም ለጸሎት ለቅዳሴ ያህል ነበር በብህንሳ በእልፍ መነኮሳት በእልፍ መነኮሳዪያት ተሹሟል። በብዙም መሾም ልማድ ነው። አባ ሆርና አባ ኤስድሮስ በሽህ አባ አሞን በሦስት ሺህ አባ ጳኩሚስ በስድስት ሽህ አባ ሠራብዮን በእልፍ ተሾሙ።

ይህችም ብህንሳ ቅድመ ትሰይም አርጋድያ ወድኅረ መኑፍ ይላል ብዙ ጊዜ ስመ ተፋልሶ አግኝቷታል በፊት አርጋድያ ኋላም መኑፍ ተብላለች ዛሬም ብህንሳ ትባላለች። ሴትና ወንድ ያልተለየባት ገዳም ናት እንደ ዘጌ እንደ ቆራጣ እንደ ቀንጠፋሜ። እርሱም ግብረ ገብ ነውና ሥርዓት ቢያጸናባቸው ይጣሉታል ያልተማረ ነውና ይንቁታል። ከመጠምጠም መማር ይቅደም እንዲሉ ከመሾም መማር አይቀድምምን እያሉ እሱ ግን ወእቀውም ዮም በ ትሕትና ወበፍቅር ብሎ እንዲያመጣው እንደጠሉኝ ልጥላቸው እንደ ናቁኝ ልናቃቸው ሳይል በፍቅር እና በትሕትና ጸንቶ ያስተምራቸው ነበር።

ከዕለታት ባንዳቸው በምን ምክንያት እንሻረው አሉ ቀድሰህ አቍርበን ብለን በዚህ ምክንያት እንሻረው ብለው መክረው ቀድሰህ አቍርበን አሉት። የእሱ ግን ተምኔቱ እንደ ቅዱስ ኤፍሬም የእመቤቴ ምሥጋና እንደ ባሕር አሸዋ እንደ ሰማይ ኮከብ በዝቶልኝ እንደ ምግብ ተመግቤው እንደ መጠጥ ጠጥቼው እንደ ልብስ ለብሼው እያለ ይመኝ ነበር። ቅዳሴ ገብቶ ሥርዓቱን ጨርሶ ከፍሬ ቅዳሴው ሲደርስ ከሊቃውንት ቅዳሴ የሚያስቸግር የማንን እናውጣለት እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ የለመኗትን የማትነሣ የነገሯትን የማትረሳ እመቤት ገልጻለት ጐሥዓ ልብየ ቃለ ሠናየ ብሎ ወይእዜኒ ንሰብሐ እስኪል ድረስ ሰተት አድርጎ ተናግሮታል። የሚንቁት የሚጠሉት ይህ የነገሩትን ቀለም እንኳን አከናውኖ መናገር የማይችል ዛሬስ እንግዳ ድርሰት እደርሳለው ብሎ አገኝ አጣውን የቆጥ የባጡን ይቀባጥራል ብለው አደነቁበት የሚወዱት የሚያከብሩት ከመንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እንዲህ ያለ ምሥጢር ከእሩቅ ብዕሲ ይገኛልን ብለው አደነቁለት። ወዲያው የሚወዱት የሚያከብሩት ጽፈን ደጉሰን አንይዘውምን አሉ። የሚንቁት የሚጠሉት ደግሞ ማን ተናገረው ብለን እንይዘዋለን አሉ። እንደ ልማዱ አድርገን አንይዘውም አሉ። ለሀገራቸው እንግዳ ድርሰት የተደረሰ እንደሆነ ጽፈው ደጉሰው ከእሳት ይጥሉታል ከእሳት ደህና የወጣ እንደሆነ ከውሃ ይጥሉታል ከውሃ የወጣ እንደሆነ ከህሙም ላይ ይጥሉታል ድውይ የፈወሰ እንደሆነ ደገኛ ድርሰት ነው ብለው ይይዙታል።

ይህንንም ቅዳሴ ማርያም ጽፈው ደጉሰው ከእሳት ላይ ጣሉት ከእሳት ደህና ወጣ ከውሃ ጣሉት ከውሃ ደህና ወጣ ከህሙም ላይ ጣሉት ድውይ ፈወሰ ይልቁንም ሙት አስነሥቷል። ደገኛ ድርሰት ነው ብለው ጽፈው ደጉሰው ይዘውታል በጥራዝም ፲፬ኛ አድርገው ጠርዘውታል። ከ፲፬ቱ ቅዳሴም ተአምራት ያልተደረገበት የለም።

የቀደሰበት ምን ቀን ነው ቢሉ ከእመቤታችን ከ፴፫ቱ በዓላት ባንዱ ቀን ነው። አንድ ባህታዊ ከባለሟልነት የተነሣ ከ፴፫ቱ በዓላት ማንን ትወጃለሽ ብሎ እመቤታችንን ጠየቃት ኪዳነምሕረትን ልደታን አስተርእዮን ፍልሰታን አለችው። ከሊህ ከ፬ቱስ ማንን ትወጃለሽ ቢላት ከጸባብ ወደ ሰፊ ከጨለማ ወደ ብርሃን የወጣውበት ነውና ልደቴን እወዳለው አለችው። ቀድሞ እኔ ሳልወለድ እናትና አባቴን መባችሁን አንቀበልም ብለው አዝነው ተክዘው ነበር የእነሱ ሃዘን ሃዘኔ ነውና እኔን ከወለዱ በኋላ መባቸውን ተቀብለዋቸው ደስ ብሏቸዋል የእነሱ ደስታ ደስታዬ ነውና እንዳለችው የልደታ እለት ነው የቀደሰው።

እሱስ ማንን ሊቀድስ ኖሯል ቢሉ ከቅዳሴ ሐዋርያት ሌላ አያውቅም ነበርና ቅዳሴ ሐዋርያትን። ይህስ አይደለም ለእመቤታችን ቅዳሴ ሐዋርያት ምኗ ነው ምን ቢቸግር ተበድሮ ጋሬዳ እንዲሉ ቅዳሴ እግዚእን ሊቀድስ ነበር ስሟን ባያነሣ እምድንግል ተወሊዶ ከመ ፈቃድከ ይፈጽም ብሎ በምሥጢር ያነሣታልና።

ከባሕር ወዲህስ ማን አምጥቶልናል ቢሉ ቅዱስ ያሬድ ማይ ኪራህ መደባይ ታብር በሚባል ቦታ ይኖር ነበር። እመቤታችን ቅዱስ ኤፍሬምን ከሶርያ አባ ሕርያቆስን ከብህንሳ በደመና ጠቅሳ ያረድ ካለበት አድርሳ አንተ ውዳሴየን አንተ ቅዳሴየን ነግራችሁት በዜማ ያድርስ ብላቸው እነሱም ነግረውት በዜማ አድርሶታል። ከዚሁ አያይዞ ፲፫ቱንም ቅዳሴ በዜማ ደርሷል። ይህም ሊታወቅ ሥረይ በቅዳሴ ማርያም ይበዛል። ከተከዜስ ወዲህ ማን አምጥቶልናል ቢሉ ሳሙኤል ትውልደ ጌዴዎን ዘገበዘ አክሱም ይለዋል እሱ አምጥቶልናል። እሱም ይሄን እየደገመ ሲሄድ ክንድ ከስንዝር ከመሬት መጥቆ ይሄድ ነበር። ከዕለታትም በአንዳቸው ውሃውን ቢባርከው ኅብስት ሆኖለት ተመግቦ ምዕመናንን መግቧቸዋል።

ሶበ አተቦ ለማይ በቅዳሴኪ እንዘ ይጼሊ ።
ረሰዮ ኅብስተ ጽጌ ሃይማኖት ሳሙኤል ዘሐቅለ ዋሊ ።
ምሕረተ ወፍትሐ ለተአምርኪ እኅሊ ።
ስረዪ ኃጢአትየ ወዕፀብየ አቅልሊ ።
እስመ ኵሎ ገቢረ ማርያም ትክሊ ።
እንዳለ ደራሲ። የፍቅር ምልክት ሁለት ንዋያት ሰጥታዋለች ነጭ ዕጣን እና እንቍ ነው። ሊቀ ካህናት ሳሙኤል እንዘ ይጼሊ በቅዳሴሃ። ማርያምኒ እኂዛ በእዴሃ አምጽአት ሎቱ ፪ተ አምኃ እንዲል። ከዚህ አያይዛ ውዳሴየን ከቅዳሴዬ ጋራ አንድ አድርጎ የሚደግመውን ሰው አንተ ከገባህበት ውሳጤ መንጦላዕት አገባዋለው ብላ ተስፋውን ነግራዋለች። ይኸውም ሊታወቅ ዛሬ በዋልድባ ያጠና በቃሉ ያላጠና በመጽሐፍ ቅዳሴ ማርያም ሳይደግም የሚውል የለም ይህም ተስፋ ውዳሴዋን ከቅዳሴዋ ጋር አንድ አድርጎ ለሚደግም ሰው ሁሉ ነው እንጂ ለእሱ ብቻ አይደለም። አንድ ባህታዊ ከምሥጋናሽ ሁሉ ማንን ትወጃለሽ ብሎ ቢጠይቃት ልጄ ዳዊትን አቡነ ዘበሰማያትን ቢደግሙለት እንዲወድ እኔም ውዳሴዬን ቅዳሴዬን ቢደግሙልኝ እወዳለው ብላዋለች።

አባ ሕርያቆስ ተሹሞ ሳለ ብዙ ድርሳንን ደርሷል ብዙ ተግሳጽ ጽፏል ከብዙውም አንዱ ይህ ቅዳሴ ነው ዕረፍቱ በጥቅምት ፪ ነው።

ልመናዋ ክብሯ በእኛ ይደርብንና ኅብስቱን በጻህል ወይኑን በጽዋዕ አድርጎ አክብሮ ለውጦ ሥጋ ወልደ እግዚአብሔር ደመ ወልደ እግዚአብሔር በሚያደርግበት ጊዜ በብህንሳ ኤጲስ ቆጶስ የተሾመ አባ ሕርያቆስ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት እመቤታችንን ያመሰገነበት ምሥጋና ይህ ነው። ቍርባን ቀሳውስት ሥጋውን በጻህል ወይኑን በጽዋዕ አድርገው ወደ መንበር የሚያቀርቡበት አኰቴት የሚለውጡት የሚያከብሩት።

አንድም በክብር በባለሟልነት ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡ።
አንድም ቍርባን የሚቀበሉት የሚያቀብሉት አኰተት የሚለውጡት የሚያከብሩት።

ልመናው ክብሩ በእኛ ይደርብንና በብህንሳ ኤጲስ ቆጶስ የተሾመ አባ ሕርያቆስ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት የተናገረው ቅዳሴ ይህ ነው ጸሎታ ወበረከታ ቢል ተመሥጋኝቱን ሲያይ ክብሯ ልመናዋ ይደርብንና ጸሎቱ ወበረከቱ ቢል አመሥጋኙን ሲያይ ነው።

፪. ይ.ካ፡ እግዚአብሔር ምስለ ኵ ልክሙ
ቄሱ እግዚአብሔር በሁላችሁም አድሮባችሁ ይኑር ይበል።

ይ.ሕ፡ ምስለ መንፈስከ
ሕዝቡም እንደ ቃልህ ይደረግልን ይበሉ።

ይ.ካ፡ አእኰትዎ ለአምላክነ
ቄሱ ፈጣሪያችንን አመስግኑት ይበል።

ይ.ሕ፡ ርቱዕ ይደሉ ።
ሕዝቡም እውነት ነው ይገባል ይበሉ።

ይ.ካ፡ ብነ ኀበ እግዚአብሔር አምላክነ ።
ሕዝቡም በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ አለን ይበሉ።

፫. ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ።

መጽሐፍ ከመጽሐፍ ማያያዝ ልማድ ነው። አባቷ ዳዊት ለንጉሠ ሰማይ ወምድር ምሥጋና ላቅርብ ባለ ጊዜ ጐሥዐ ብሎ ተናግሮ ነበርና እሱም ለንግሥተ ሰማይ ወምድር ምሥጋና ላቅርብ ባለ ጊዜ ጐሥዐ አለ።

አንድም ለአባቷ ለዳዊት የገለጸ መንፈስ ቅዱስ ምሥጢር ከምሥጢር አያይዞለት ጐሥዐ አለ። ወአየድዕ ይላል በልብ መደብ ቁሞ ወአነ አየድዕ ይላል። በቃል መደብ ቁሞ ልቡናዬ በጎ ነገርን አውጥቶ ተናገረ።
አንድም ልቡናየ ስንቡል መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ በጎ ነገርን ገሳ።

ሐተታ፦ በሀገራቸው የተመገቡት ምግብ ያልተስማማቸው እንደሆነ ዑድ ሰንደል የሚባል ሽቱ አለ ያንን ተመግበው በጎ በጎ ነገር ገሣው ይላሉና ያጎሥዓኒ እንዲል ትግሬ።

ሐተታ፦ ሦስት ጊዜ ጐሥዐ ጐሥዐ ጐሥዐ ብሎ መላልሶ ተናገረ ስለምን ቢሉ በንጽሐ ሥጋ በንጽሐ ነፍስ በንጽሐ ልቡና መዓርግ አምሳል።

አንድም ወጣንያን ማዕከላውያንን ፍጹማን የሚያመሰግኗት ስለሆነ።
አንድም በዚህ ዓለም በገነት በመንግሥተ ሰማያት ያሉ ጻድቃን የሚያመሰግኗት ስለሆነ ከዚህስ አስቀድሞ መንግሥተ ሰማያት የገባ የለም ብሎ ኋላ መንግሥተ ሰማያት የሚገቡ ጻድቃን የሚያመሰግኗት ሲለሆነ።
አንድም ሊቃውንት በምሥጢረ ሥላሴ መጀመር ልማዳቸው ነው። ሦስት ጊዜ ደጋግሞ መናገሩ የሦስትነት ቃሉ አለመለወጡ የአንድነት ምሳሌ ነው።
አንድም ወአነ አየድዕ ቅዳሴሃ ወአነ አየድዕ ውዳሴሃ ወአነ አየድዕ ዕበያቲሃ የሚል ነውና ሦስት አርዕስት ተናገረ ለሦስቱም ያመጣል።

፬. ወአነ አየድዕ ቅዳሴሃ ለማርያም

አባቷ ዳዊት ወአነ አየድዕ ግብርየ ለንጉሥ ብሎ ነበርና ለዚያ ዋዌ እኔም የእመቤታችንን ምሥጋና እናገራለሁ አለ።

ሐተታ፦ መጀመሪያ ጐሥዐ ብሎ ነበርና ለዚያ ኅዳግ። ይህስ ለራሱ አርእስት ነው ብሎ አ ላ በቅድስና ወበ ንጽሕ ስርጕ ት አንቲ የሚል ነውና ለዚያ አርዕስት ነው።

አኮ በአብዝኆ ― በማብዛት አይደለም
አላ በአውኅ ዶ ― በማሳነስ ነው እንጂ።

ሐተታ፦ የእመቤታችን ምሥጋና ከምሥጋና ቢበዛ እንጂ ያንሳልን መትህተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን አይደለችምን ቢሉ እውነት ነው የእመቤታችን ምሥጋና ሰማይና ምድር ብራና አብሕርት ቀለም ዕፀው ብርዕ አዕባን መድመጽ መላእክት ደቂቀ አዳም ጸሐፍት ቢሆኑ ባልተፈጸመም ነበር። እንደ ቅድስናዋ እንደ ንጽሕናዋ አይደለም ሲል እንዲህ አለ። ከዚያ ሁሉ ቅዱስ ቄርሎስ የቴዎዶስዮስን እህቶች የአርቃድያ የመሪናን ምሥጋናቸውን ተናግሮ ዝ ውዳሴ ዘተናገርነ ይውኅድ እምክብርክን እንዳለ።

አንድም ንባቡን በማብዛት ምሥጢሩን በማሳነስ አይደለም ንባቡን በማሳነስ ምሥጢሩን በማብዛት ነው እንጂ።

ወአነ አይድዕ ውዳሴሃ ለድንግል
እኔም የእመቤታችንን ምሥጋና እናገራለሁ።

ሐተታ፦ ሁለተኛ ጐሥዐ ብሎ ነበርና ለዚያ ኅዳግ። ይህስ ለራሱ አርእስት ነው ብሎ ኦ ድንግል አኮ ስፋጣን ዘናዘዙኪ አላ መላእክተ ሰማይ ሐወጹኪ በከመ ተብህለ ካህናት ወሊቃነ ካህናት ወደሱኪ የሚል ነውና።

አኮ በአንኆ በቃለ ዝንጋዔ

ዝንጋዔን የሚያመጣ ዝንጋዔን የሚያስከትል ነገርን በማብዛት አይደለም ብዙ ቢያወጉ ይዘነጉ ብዙ ቢተቹ ይሰለቹ እንዲሉ ነገር ከበዛ ዘንድ ከምን ተነሥቶ ከዚህ ደረሰ ይባላልና እስመ ኖኅ እምሥእርተ ርእስየ ጌጋይየ ። ወእምዝ ያነውኆ ለሰብእ። ግብር ዘአልቦ ምጣኔ ገዓር ውእቱ ወለገዓር ኒ ይተልዎ ዝንጋኤ አብዝኆ መጻሕፍት ያዘነግዕ ልበ እንዲል።

አላ በአሕፅሮ
በማሳጠር በመጠቅለል ነው እንጂ ሲሰበር ይሰንጠር ሲረዝም ይጠር እንዲሉ።

ወአነ አየድዕ ዕበያቲሃ ለድንግል
የድንግልን ገናንነቷን እናገራለሁ።

ሐተታ፦ ሦስተኛ ጐሥዐ ብሎ ነበርና ለዚያ ኅዳግ። ይህስ ለራሱ አርእስት ነው ብሎ ኦ ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ ብሎ የሚያመጣ ነውና ይህስ አይደለም አርዕስት ተቀዳደመ ለፊተኛው አርቆ ለኋለኛው አቅርቦ አይሰጥም ብሎ መጽአ ኀ ቤኪ ቃል ብሎ የሚያመጣ ነውና። ወአነ አየድዕ ውዳሴሃ ወአነ አይድዕ ቅዳሴሃ ወአነ አይድዕ ዕበያቲሃ ብሎ ሦስት ጊዜ መላልሶ ተናገረ። ኦ ማርያም በእንትዝ ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ ኦ ድንግል ምልዕተ ውዳሴ ። ኦ ድንግል አኮ ዘተአምሪ ርስሐት የሚል ነውና።

አንድም አባቷ ዳዊት ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን እስመ ኃረያ እግዚአብሔር ለጽዮን ብሎ ሦስት ጊዜ መላልሶ አመስግኗታል።

፭. ወእቀውም ዮም በ ትሕትና ወበ ፍቅር በዛቲ ዕለት ቅድመ ዝንቱ ምሥጢር ግሩም ።

ዮም እና በዛቲ ዕለት አንድ ወገን ቀድሶ ያቆረበባት ቀን ናት እንደጠሉኝ ልጥላቸው እንደናቁኝ ልናቃቸው ሳልል በፍቅር በትሕትና ጸንቼ ግሩም በሚሆን በሥጋው በደሙ ፊት እቆማለው።

ሐተታ፦ ሥጋው ደሙን ምሥጢር አለው ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢር አንዱ ምሥጢረ ቍርባን ነውና።

አንድም ከኃጢአት ነጽቶ ቢቀበሉት በልሳነ ነፍስ ያናግራልና።
አንድም ሲለወጥ አይታይምና ለበቁትም ሰዎች ስንኳ ከተለወጠ በኋላ ነው እንጂ ሲለወጥ አይታይምና።
አንድም የወዲያኛውን ምሥጢር ይገልጣልና ግሩም አለ። በሚገባ ቢቀበሉት ግሩም ጸጋ ያሰጣልና በሚገባ ባይቀበሉት ግሩም ፍዳ ያመጣልና።
አንድም ግሩማን መላእክት ከበውት ይቆማሉና።
አንድም ከኃጢአት ነጽቶ ቢቀበሉት ግሩም ምሥጢርን ይገልጻልና።
አንድም የአምላክ ሥጋ የአምላክ ደም አይገርም ማን ይግረም።
አንድም የሚወደድ ሲል ነው ኢትርዓይ ግርማ ርእየቱ ለኤልያብ እንዲል።
አንድም ልዩ ሲል ነው ግሩም ምክሩ እምእ ጓለ እመ ሕ ያው እንዲል።

ወቅድመ ዝንቱ ማዕድ ወቍርባን።
ማእድም ያለው ሥጋው ደሙ ነው።

ሐተታ፦ ማእድ አለው ማእድ ሥጋዊን ከበው እንዲመገቡት ይህንም አእሩግ ህጻናት ከበው ይቀበሉታልና።

አንድም ለማእድ ሥጋዊ ሰው እንዲመረጥለት ለዚህም የበቃና ያልበቃ ይመረጥለታልና።
አንድም ማዕደ ነፍስ ነውና ቍርባን እንዳለፈው።
አንድም ማእድ ጻህል ጽዋዕው ቍርባን ሥጋው ደሙ ነው።

፮. በአማን ቍርባን ውእቱ ዘኢ ይክሉ ይጥዐሙ እምኔሁ ግሙናነ መንፈስ ።

ልቡናቸውን ሰውነታቸውን በኃጢአት ያሳደፉ ሰዎች ሊቀበሉት የማይገባቸው መለኮት የተዋሐደው እውነተኛ ቍርባን ነው።

ሐተታ፦ ማን ይከለክላቸዋል ቢሉ ራሳቸው ፈርደው ይከለከላሉና።

አንድም ቄሱ ይከለክላቸዋልና።
አንድም እግዚአብሔር በምልዓት በልቡናቸው አድሮ ይከለክላቸዋልና።

ሕዝቡ ያልበቁ ልዑካኑ የበቁ የሆኑ እንደሆነ የሕዝቡን ለልዑካኑ ይደርብላቸዋል። ልዑካኑ ያልበቁ ሕዝቡ የበቁ ይሆኑ እንደሆነ የልዑካኑን ለሕዝቡ ይደርብላቸዋል። ሕዝቡም ልዑካኑም ያልበቁም የሆኑ እንደሆነ መልአክ ወስዶ በበረሃ ለወደቁ ባሕታውያን ያቀብላቸዋል ምግብ ሁኑአቸው የሚኖር ቅሉ ይህ ነው። ያም አያውቅም ይህም አያውቅም ያ እንዳይታበይ ይህ ከቀቢጸ ተስፋ እንዳይደርስ ነው።

አኮ ከመ መሥዋዕ ቶሙ ለቀደምት አበው ዘበደመ በግዕ ሐርጌ ወላህም ።
በደመ በግዕ በደመ ላህም የቀደሙ ሰዎች ይሰውት እንደነበረ መሥዋዕት አይደለም።

አንድም የቀደሙ ሰዎች በደመ ላህም በደመ በግዕ ይሰዉት እንደነበረ መስዋዕት አይደለም።

ሐተታ፦ ሀርጌን ለበግ የቀጸሉ እንደሆነ ሙክት ለላህም የቀጸሉ እንደሆነ ጊደር ማለት ነው።

፯. አላ እሳት ውእቱ ።
መለኮት የተዋሐደው ቍርባን ነው እንጂ።

እሳት ማኅየዊ ለርቱዓነ ልብ ለዕለ ይገብሩ ፈቃዶ ።

ለ እና ለ አንድ ወገን። እሳትም ብዬ ብላችሁ አንድነቱን ሦስትነቱን አውቀው ሕማሙን ሞቱን አምነው ኃጢአታቸውን ለመምህረ ንስሓ ነግረው መምህረ ንስሐ ያዘዘውን ሠርተው በሚገባ ለሚቀበሉ ሰዎች የሚያድን እሳት ነው።

ሐተታ፦ እሳት በመጠን የሞቁት እንደሆነ የበሉት የጠጡትን ያስማማል ደዌ ይከፍላል ይህም ከኃጢአት ነጽቶ ቢቀበሉት ሕይወተ ሥጋ ሕይወተ ነፍስ ይሆናል ደዌ ነፍስ ያርቃልና። እሳት በላዒ ለአማጽያን ለእለ ይክሕዱ ስሞ ።

ለ እና ለ አንድ ወገን ነው። እሳት ማኅየዊም ብላችሁ ስመ አምላክነቱን ለሚክዱ ሰዎች የሚያቃጥል እሳት ነው።

ሐተታ፦ ስመ አምላክነቱን ከካዱ የማን ሥጋ የማን ደም ብለው ይቀበሉታል ቢሉ ስመ ቍርባንነቱን ለሚክዱ ሰዎች።

ሐተታ፦ ስመ ቍርባንነቱንስ ከካዱ ምን ይረባናል ምን ይጠቅመናል ብለው ይቀበሉታል ቢሉ በግብሩ መካድ አለና። ከኃጢአት ሳይነጹ ቢቀበሉት በፍዳ ላይ ፍዳ የሚያመጣ ስለሆነ። እሳት ነበልባሉ ከወረደው ፍሕሙ ከመረተው ቀርበው ያለመጠን ቢሞቁት ያቃጥላል ይህም በማይገባ ቢቀበሉት ፍዳ ያመጣልና። ወይእዜኒ ዘበልዖ ለዝንቱ ኅብስ ት ወዘሰትዮ ለዝንቱ ጽዋዕ እንዘ ኢ ይደልዎ ደይኖ ወመቅሰፍቶ በልዓ ለርእሱ መንሱትኬ ነሢአ ሥጋሁ በድፍረት ወተመጥዎ ደሙ ዘእንበለ ኃ ፍረት እንዘ ቦ ላዕሌሁ ነውረ ኃጢአት እንዲል። ከዚህም ሥጋውን ከእሳተ ባቢሎን ደሙን ከማየ ግብጽ ምሳሌ አምጥተው ይናገራሉ። እሳተ ባቢሎን ሠለስቱ ደቂቅን ሳይነካ በአፍአ ያሉ የባቢሎንን ሰዎች አቃጥሎአቸዋል። ሥጋውም ከኃጢአት ነጽተው የሚቀበሉትን ያድናቸዋል ከኃጢአት ሳይነጹ የሚቀበሉትን ያጠፋቸዋልና። ማየ ግብጽ በግብጻውያን ሲለወጥባቸው በእሥራኤል አልተለወጠባቸውም። ደሙም ከኃጢአት ነጽተው የሚቀበሉትን ያድናቸዋል ከኃጢአት ሳይነጹ የሚቀበሉትን ያጠፋቸዋልና። ዛሬም ቀሳውስት ይህን ምሳሌ ይዘው የበደላችሁትን ሳትክሱ የቀማችሁትን ሳትመልሱ ከኃጢአት ሳትነጹ ሳትበቁ ብትቀበሉት ሥጋው ደሙ በነፍስ በሥጋ ያስፈርድባችኋል እያሉ አዋጅ ይነግሩበታል።

፰. በአማን እሳት ውእቱ ዘኢይክሉ ለኪፎቶ እሳታውያን እለ ነደ እሳት እሙንቱ ኪሩቤል ወሱራፌል ።

ከእሳት ከነፋስ የተፈጠሩ ኪሩቤል ሱራፌል ሊይዙት የማይቻላቸው መለኮት የተዋሐደው እውነተኛ ቍርባን ነው ተፈጥሮዋቸው ከእሳት ከነፋስ ነውና። ወሶበ ኢያእኮትኮ ለዘፈጠርከ እምነፋስ ወነድ ፈጠረ ህየንቴከ ሰብ አ ዘማሬ እማይ ወእመሬት እንዲል።

ሐተታ፦ ከዕለተ ሠሉስ አስቀድሞስ ግብር እም ግብር የተፈጠረ ፍጥረት የለም። የመላእክትም ተፈጥሮ እምኀበ አልቦ ነው ብሎ ግብራቸውን ሲያይ እሳት ነፋስ ኃያላን ረቂቃን ፈጣኖች ፈጻምያነ ፈቃድ ናቸው መላእክትም ኃያላን ረቂቃን ናቸውና ለተልዕኮ ይፋጠናሉና የፈጣሪያቸውን ፈቃድ ይፈጽማሉና።

ሐተታ፦ እሳት ሰብዓ ሰዶምን ደቂቀ ቆሬን አጥፍቷል ነፋስም ብእሲተ ዘማን ጥቅመ ሰናኦርን ሃራ ጰራግሞንን አጥፍቷልና።

አንድም የባለሟልነት ስማቸው ነው እገሌ ነደ እሳት ባለሟል ነው እንዲሉ።

ታሪክ ፦ ዘኢይክሉ ለኪፎቶ እለ ንጉሡ ዖዝያን ሊቀ ካህናቱ አዛርያስ ይባላል። በቀኙ ይቀመጣል ምነው በቀኜ ትቀመጥብኛለህ ይለዋል ወካህን ይነብር በየማነ ንጉሥ እንጂ ይለኛል ይለዋል። ከልብሰ መንግሥቱ ልብሰ ክህነቱ ይበልጣል ምነው ከእኔ የበለጠ ልብስ ትለብሳለህ ይለዋል ካህናቲከ ይለብሱ ጽድቀ እንጂ ይለኛል ይለዋል። ፍርዱን ይገስበታል ምነው ፍርዴን ትገስብኛል ይለዋል እምነ መንግሥ ት የዓቢ ክህነት እንጂ ይለኛል ይለዋል። እንዲህ አድርጎ ቤተ መንግሥትም እያረካከሰ ቤተ ክህነትን እያነጋገሠ እየጠቃቀሰ እያሞጋገሰ ቢያውከው በዚያም በዚያም ቢሉ ቀንቶበት ከቤተ መንግሥትማ ቤተ ክህነት ከበለጠ እኔስ በአባቴ ከቤተ መንግሥት ብወለድ በእናቴ ከቤተ ክህነት እወለድ የለምን ብሎ ማእጠንተ ወርቁን ይዞ ልብሰ ተክህኖውን ለብሶ ሊያጥን ገባ። ሲያጥን ጢሱ ቢያርፍበት ከግንባሩ ለምጽ ተቀረጸበት በሻሽ ሸፈነው ከሻሹ ላይ ወጣበት። ለምጻሙን እሥራኤል ስንኳንስ በቤተ መቅደስ በከተማ አያኖሩትምና እሱን አውጥተው ልጁን አንግሠዋል። በዘመኑ የነበረ ነቢይ ኢሣይያስ ነው ፈርቶ ሳይገስጸው ቢቀር ለምጽ ወጥቶበት ሃብተ ትንቢት ተነሥቶት ፫ ዓመት ከመንፈቅ ያህል ኖሯል። ወእምዝ በዓመተ ሞተ ዖዝያን ንጉሥ ርኢክዎ ለእግዚአብሔር እንዘ ይነብር ዲበ መንበሩ ብሩህ ወነዋህ እንዲል ዖዝያን በሞተበት ወራት ጌታ በመንበረ ጸባኦት እንዳለ ሆኖ ለኢሳይያስ ታየው። ያ ታፍረው ታከብረው የነበረው ንጉሥ ሞተ አለፈ እኔ ግን ኅልፈት ውላጤ የለብኝም ሲል። ሊያድነው ቢሻ መነ እፌኑ ኀ በ ሕዝ ብየ እ ሥራ ኤል ሁሉ ራሱን ጠበቀ አንገቱን ቀበረ ወደ ወገኖቼ ወደ እሥራኤል በመምህርነት ማንን ልስደድ አለ። እስመ ማዕከለ ሕዝ ብ ዘር ኵ ስ ከናፍሪሆሙ ሃሎኩ አነ እሥራኤል ለምጽ ይጸየፋሉ ደግሞም ትንቢት ተነሥቶብኛል እንጂ እኔ አልፈራም ነበር አለው። ወተፈነወ አሐ ዱ እምሱራፌል ወነስአ ፍህመ በጉጠት ወአልከፎ ከናፍሪሁ ወይቤ አእተትኩ ለከ ኃጢአ ተከ እንዲል። መልአኩን ከዓለመ መላእክት ፍህሙን በጉጠት ወስደህ አጉርሰው አለው። ኃጢአ ተከ ቢል ለምጹን አራቅሁልህ ኃጢአት ከ ቢል ትንቢቱን መለስኩልህ ሲል ነው።

ከዚህ በኋላ ለምጹ ድኖለት ትንቢቱ ተመልሶለት እንደገና አስተምሯልና ይህም ምሳሌ ነው። መልአኩ የቀሳውስት ጉጠት የሥልጣነ እግዚአብሔር ኢሳይያስ የምእመናን ለምጽ የፍዳ የመርገም ፍህም የሥጋ ወደሙ።

አንድም ከናፍረ ኢሳይያስ የምእመናን መልአኩ የዲያቆን ጉጠት የእርፈ መስቀል ፍህም የደሙ ምሳሌ። መላእክት ሥጋውን ደሙን የሚይዙበት ስልጣን የላቸውምና ዘኢይክሉ አለ ዘኢተገብረ ለመላእክት ተገብረ ለካህናት የሚያሰኘው ቅሉ ይሄ ነው። አባ መቃርዮስ እንዳየው ስለ ንጽሕናው መልአኩ የቄሱን እጅ ይዞ ለማርቆስ ዘዮናኒ ግብጻዊ ሲያቀብለው አይቷል።

ክፍል ፩።

፱. ኦ ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ ።

ኦ ቃለ አክብሮ ቃለ አህስሮ ቃለ አራኅርኆ ይሆናል። ቃል አክብሮ ኦ ድንግል ምልእተ ውዳሴ ብሎ የሚያመጣው ነው። ቃለ አራኅርኆ ኦ ዮሴፍ ወልደ ዳዊት ቃለ አህስሮ ኦ ሃናንያ ኦ አብዳን ሰብአ ገላትያ ነው። በእንተዝ ያለፈውን አጠፈ እንደገና ብሎ መጽሐፍ ያለፈውንም የሚመጣውንም ማጠፍ ልማድ ነውና የሚመጣውን አጠፈ እመቤታችን ሆይ እናከብርሻለን እናገንሻለን።

ሐተታ፦ እኛ እሷን የምናከብራት የምናገናት ሆነን አይደለም ክብርሽን ገናንነትሽን እንናገራለን ሲል ነው።

እስመ ወልድኪ ለነ መብልዓ ጽድቅ ዘበአማን ወስቴ ሕይወ ት ዘበአማን
እውነተኛውን ምግብ እውነተኛውን መጠጥ አስገኝተሽልናልና ስላስገኘሽልን።

ሐተታ፦ ዘበአማን አለ ከመስዋዕተ ኦሪት ሲለይ። ያ ሥጋዊ ይህ መንፈሳዊ ያ አፍአዊ ይህ ውሳጣዊ ያ ምድራዊ ይህ ሰማያዊ ነውና።

አንድም የዚህ ዓለም ምግብ ጠዋት በልቶ ለማታ ማታ በልቶ ለጠዋት ያሻል። ይህ ግን በሚገባ ከተቀበሉት በኃጢአት ካላሳደፉት ሕማሙን ሞቱን ለማዘከር ነው እንጂ አንድ ጊዜ ከተቀበሉት በሌላ ጊዜ አያሻምና።
አንድም የዚህ ዓለም ምግብ ኃሠር ይሆናል ይለወጥል። በእርሱ ግን ይህ ሁሉ የለበትምና።
አንድም የዚህ ዓለም ምግብ ሞትን ያስከትላል ይህ ግን የዘላለም ሕይወት ይሆናል።
አንድም ከአማናዊት እመቤታችን ስለተገኘ መብል ዐ ጽድቅ ዘበአማን ውስቴ ሕይወ ት ዘበአማን አለ።

፲. ኦ አበዊነ ንቡራነ እድ ስዩማን እለ መትልወ ሐዋርያት ።

አንቀጽ ተስማሚውን ያወርዳል። ናፈቅረክሙ ወነዓብየክሙ ሲል ነው። ተውህበ ጳውሎስ ሙቁሕ ብሎ ወካልዓንሂ መቁሐን ባለ ጊዜ ተወህቡ አገብዓ ለኤልዛቤል ወስተ ምስካባ ዘቀዳሚ ወእለሂ ዘመው ምሳሌሃ ባለ ጊዜ አገብዖሙ። ትኤምኃክሙ ቤተክርስቲያን እንተ ውስተ ባቢሎን ዘግብጽ ብሎ። ወማርቆስ ወልድየ ባለ ጊዜ ይኤምኃክሙ እንዳለበት። ከሐዋርያት ቀጥላችሁ ሐዋርያትን መስላችሁ በአንብሮተ እድ የምትሾሙ አባቶቻችን እናከብራቸዋለን እናገኛቸዋለን።

ሐተታ፦ ከሊቀ ጳጳስ ጀምሮ እስከ ቄስ ያሉት በአንብሮተ እድ ይሾማሉ። ቅብዓት ያለበት ነው ዲያቆን በአንብሮተ እድ ይሾማል ቅብዓት የለውም። ከዚያ በታች ያሉትን በቃል ይሾሟቸዋል።

እስመ ነሣእናክሙ አስተብቋዕያነ ለነ ለኀበ እግዚአብሔር ።

ወደ እግዚአብሔር ልታማልዱን። አስተበቊዓነ ከእግዚአብሔር አግኝተን ተቀብለናችኋልና እናከብራችኋለን እናገናችኋለን።

ሐተታ፦ ሊቀ ጳጳሱ በሞተ ጊዜ የበቁትን ደጋጎቹን መርጠው ስማቸውን በቅፋፍ ጽፈው ላለፈው ኦ እግዞኦ አዕርፍ ነፍሰ አቡነ እገሌ ለሚመጣው ኦ እግዚኦ አንብር ለነ ዲበ መንበሩ ኖላዌ ኄ ረ ኢንኩን ከመ መር ዔ ት ዘአልቦ ኖላዊ ወኢይምስጠነ ተኩላ መሳጢ እያሉ ይፀልዩበታል። ፀሎታቸውን ሲፈጽሙ አንድ ብላቴና አምጥተው እያነሣህ ስጠን ይሉታል እያነሣ ይሰጣቸዋል። ሳያይ መልሰው ይቀላቅሉታል አንዱን ፫ ጊዜ መላልሶ የሰጣቸው እንደሆነ ያሮስ ያሮስ አክዮስ አክዮስ ብለው ይሾሙታል ይደልዎ ይደልዎ ማለት ነው። አንዱን ፩ ጊዜ አንዱን ፩ ጊዜ የሰጣቸው እንደሆነ ግን ከጸሎቱ ይጨምሩበታል። ከሐዋርያት ሲያያዝ የመጣ እንደሆነ ይሁዳ በወጣ ጊዜ በይሁዳ እግር እኛ ባወቅን ማትያስ እና ባርናባስን መርጠናል አንተ እ ግዚኦ ማእምረ ኵሉ ልብ አርኢ ፩ ደ እምእ ሉ ዘኃረይከ ዘይነስአ ለመልእክተ ሢ መት ዘሐዋርያት። ኩላሊት ያመላለሰውን ልቡና ያሰበውን መርምረህ የምታውቅ አቤቱ ይህችን የሐዋርያትን ሹመት ገንዘብ የሚያደርጋትን ከእነዚህ ከሁለቱ የመረጥከው አንዱን ግለጥልን ብለው። በአስተ ዐ ጸውዎሙ ይላል። እጻ አጣጣላቸው ወወጽ አ ላእለ ማትያስ ይላል እጣ በማትያስ ወጣ መከራ የሚቀበልበት ነውና በ አለ።

አንድም ለማትያስ ዋጋ የሚያገኝበት ነውና ለ አለ ወተኈለቈ ምስለ ፲ ወ ፩ ሐዋርያት ከ፲፩ ሐዋርያት ፲፪ኛ ሁኖ ተቆጥሯልና እንዲህ አለ።

ወነሣዕናሆ ሙ በመዋእሊነ አስተብቋዕያነ ለነ በእግዚአብሔር እሎንተ ፪ተ ሊቀነ ጳጳሳት ። የእስክንድርያ ሊቃነ ጳጳሳት እለ እስክድሮስና አትናቴዎስን ወደ እግዚአብሔር ሊያማልዱን ተቀብለናቸዋልና አስተበቍዐነ ይላል። ከእግዚአብሔር አግኝተን ተቀብለናቸዋልና እናገናቸዋለን እናከብራቸዋለን።

ሐተታ፦ እለ እስክንድሮስ አርዮስን ተከራክሮ ረትቷልና አትናቴዎስም በእርሱ ሃዘን በእርሱ ፀሎት በዘመኑ አርዮስ ሙቷልና።

ብፁዕ ጳጳስ አባ እገሌ ዘሀገር ዓ ባይ እለ እስክንድርያ ።
በእስክንድርያ በመዲናዪቱ ሀገር የተሾመ አባ እገሌን።

ወዲበ ርእሰ ሀገረ አበዊነ ብፁዕ ጳጳስ
በመዲናዪቱ በአክሱም የተሾመ ንዑድ ክቡር የሚሆን አባ ሰላማን እንወደዋለን እናከብረዋለን እንዳለፈው ተርክ።

አንድም እሎንተ ክልዔተ ሊቃነ ጳጳሳት አባ እገሌ (ታዎድሮስ) ዘሀገር ዓባይ እለ እስክንድርያ ወዲበ ርእሰ ሀገረ አበዊነ ብፁዕ ወቅዱስ አባ እገሌ ( ማትያስ ) ።

የእስክንድርያውያን አባ እገሌን (ታዎድሮስን) የሀገራችን ጳጳስ አባ እገሌን (ማትያስን) እናከብራቸዋለን እንወዳቸዋለን። የእስክንድርያውንስ ሊቀ ጳጳስ ይሁን የሀገራችን ስለምን ሊቀ ጳጳስ አለው ቢሉ ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አስጠግቶ። ስምዖንን ከሌዊ አስጠግቶ ካህናት ኅሉፋነ ፍኖት ከበቱ ፍኖተ እግዚኦሙ እንዳለ።

አንድም ከሊቀ ጳጳስ ማዕርግ አድርሶ የሚሰደው ስለሆነ በመንበሩ አስቀምጦ ጭራውን መቋሚያውን መስቀሉን ሰጥቶ የሚሰደው ሰለሆነ።

አንድም ስም ሰጥተው ግብር ነስተውታልና ወያክብርዎ በስመ ሊቃናት ባሕቲቱ ዘእንበለ ይኩን ሎቱ ሥልጣነ ዝንቱ እንዲል። በእስክንድር እስክንድርያ ተብላለች።

ታሪክ ፦ እስክንድር የሚባል ገናና ንጉሥ ነበረ ሥነ በዓል ለማየት መንግሥት ለማዳረስም ቢሉ ለሌላም ነገር ቢሉ።

አንድም ያቁመን ለመጠጋት ኢየሩሳሌም ወጣ ከወጣ ዘንድ ሲመለስ ስም የሚያስጠራ ልጅ የለኝ ምን ሰርቼ ስሜን ላስጠራ አለ። ድልድይ ሰርተህ አስጠራ አሉት ይህች እስክንድርያ ማይ ጽንፋ ማይ ሃጹራ ይላታል ውሃውን በመዘውር መልሶ የብረት አምድ እያቆመ የብረት ድልድይ እየደለደለ በኖራ እየለበጠ በብረት እየጠረቀ የብረት ሰረገላ እያሸጋገረ የብረት መረባ ሰርቷል።
ልማደ ሰብእ ልማደ እንስሳ የሚወርድበት እንደ መሽረብ ያለ ሰርቶ አዞ ጉማሬ እየወጣ እንዳያውክ ገባሬ ተአምር አጽመ ኤልሳእን ቀብሮበታል። በዚያ ላይ ሦስት ድስት ምሉ ወርቅ ቀብሮበት ሂዷል ይህ የተደረገ በዘመነ ብሉይ ነው። ሲያያዝ ከዘመነ ሐዲስ ደርሷል ከዘመነ ሐዲስ እስከ ዘመነ ሊቃውንት ደረሰ። አትናቴዎስ በእስክንድርያ ተሹሞ ሳለ በዘመኑ ረሀብ ሆነ ወርቅ ተቀብሮ እያለ ነዳያን እየተራቡ እም ከመ ረከብኩ ሞገሰ በ ቅድመ አምላኪ የ ኢ የሀ ኀ ድጎ ለዝንቱ አድራማሌቅ ምኵ ራበ ሰገል እያለ ሲጸልይ ተምኔቱ ሳይፈጸምለት ሞተ። ከእርሱ ቀጥሎ ቴዎፍሎስ ተሾመ እሱም በዘመኑ ረሀብ ሆነ እምከመ ረከብኩ ሞገሰ በቅድመ አምላኪየ ኢየሀኀድጎ ለዝንቱ አድራማሌቅ ምኵ ራበ ሰገል እያለ ሲያዝን ይኖር ነበረ። ኋላ ግን አልአርታ የምትባል የሮም ንግሥት ብዙ ሠራዊት አስከትላ ሄደች። ስለምን ቢሉ ለምናኔ ብዙ ሰው አስከትሎስ ምናኔ የለም ብሎ ገዳማተ ግብጽን እጅ ለመንሳት። በገዳማተ ግብጽ ካሉ አበው ለመባረክ ከአበው አንዱ እሱ ነውና ወደ እሱ ሄደች። አዝኖ አየችው ምነው አዝናሀል አለችው እኔ አላዝን ማን ይዘን ወርቅ ተቀብሮ እያለ ነዳያን እየተራቡ አላት። አታስኮሰትረውምን አለችው። ባይቻለኝ አላት። ባንተ ጸሎት በእግዚአብሔር ረድኤት አስኮሰትርልሀለሁ ብላ ብታስኮሰትርለት ቴዳ ቴዳ ቴዳ የሚል ሦስት ድስት ምሉ ወርቅ ተገኝቷል። ቴዳ ማለት ታኦስ ማለት ነው ታኦስ የጌታ ስም ለነዳያን ይገባል ብሎ አንዱን ለነዳያን መጽውቶሎታል። አንዱን ቴዳ ማለት ቴዎዶስዮስ ማለት ነው ብሎ ለንጉሡ ሰዶለታል። ንጉሡም ለበረከት ያህል ከፍሎ አስቀርቶ መልሶ ሰዶለታል። በዚህ አብያተ ክርስቲያናትም ያንጽበት ለነዳያንም ይመጽውተው አልታወቀም። አንዱን ቴዳ ማለት ቴዎፍሎስ ማለት ነው ይሄ የእኔ ገንዘብ ነው ብሎ በዚህ ሰባት ያህል አብያተ ክርስቲያናት አንጾበታል። ታቦተ ኢየሱስ ታቦተ ማርያም ታቦተ ሚካኤል ታቦተ ሩፋኤል በዘባነ አንበሪ የታነጸ በዚያ ጊዜ ነው ታቦተ ኤልሳእ ታቦተ ዮሐንስ መጥምቅ ይህ አንድ ወገን ነው። ታቦተ ኤልሳቤጥ ታቦተ መርቆሬዎስ ነው። ወርቅ ስለተገኘባት ዓባይ አላት። ይኽስ አባ ሕርያቆስ የሚሻ መንፈሳዊ የሥጋው የደሙን ነገር ነው የመንፈሳዊ የሥጋው ደሙን ነገር ሲናገር መጥቶ ማሩን አምርሮ ወተቱን አጥቁሮ ወርቅ ተገኘባት ብሎ ዓባይ አይላትም ብሎ ወትከውን አሃቲ ሀገር ምስዋኦ ለእግዚአብሔር እንዲል በአራቱ ማዕዘን ሃይማኖት ሲጠፋ እሰከ ዕለተ ምፅአት ወልድ ዋሕድ ስትል ትኖራለችና ርእሰ አክሱም ሀገር መላ ኢትዮጵያ።

፲፩. ይ.ዲ፡ በእንተ ብፅእት ።

ወብጽእት አንቲ እንተ ተአምኒ ከመ ይከውን ቃል ዘነገሩኪ ተብላ በኤልሳቤጥ ቃል ስለተመሰገነች።

ወፍሥሕት ።
ተፈሥሒ ተፈሥሒ ተብላ በመልአኩ በገብርኤል ቃል ስለተመሰገነች።

ወስብሕት በኵሉ ።
ክቡር በውስተ ነቢያት ክቡር በውስተ ሊቃውንት እንዲል በሁሉ ዘንድ ስለተመሰገነች።

ወቡሩክት ።
ቡሩክት አ ንቲ እምአንስት ተብላ ስለተመሰገነች።

ወቅድስት ወንጽሕ ት እግዝእትነ ወላዲተ አምላክ ማርያም ድንግል ።
ንጽሕት ኵሎ ጊዜ ተብላ ስለ ተመሰገነች አምላክን ስለወለደች ስለ እመቤታችን ብለህ።

አንድም እሷን አማላጅ በማድረግ ዕጣን ቋጥረው ግብር ሰፍረው መባዕ ይዘው ወደ ቤተ እግዚአብሔር የሚሄዱት አስባቸው ይበል።

ሐተታ ፦ እግዝእትነ አለ ከግብርናተ ዲያብሎስ ነጻ አውጥቶ የሚገዛን ከእሷ በነሣው ሥጋ ስለሆነ ነው።

፲፪. ወበእንተ ቅዱሳን ክቡራን ።

ጽኑዓን ክቡራን መንፈሳውያን ረቂቃን ለሚሆኑ ሊቃነ መላእክት መዐርጋቸውን መናገር ነው።

ሰማያውያን ቦታቸውን መናገር ነው።
ወኃያላን ኃያላን ስለሚሆኑ ስለእነዚህ ብለህ።

አንድም በእነዚህ አማላጅነት።

ሐተታ ፦ በተፈጥሮ ኃይል ይሰጣቸዋልና።

አንድም በቅዳሴ በተራድኦ ምክንያት ይጨመርላቸዋልና።

ሰባኪ ።

ነሥሑ እስመ ቀርበት መንግሥተ ሰማያት እያለ።

ወጸያሄ ፍኖት ዮሐንስ መጥምቅ ።

ጺሁአ ፍኖቶ ለእግዚአብሔር እያለ ስለሚያስተምር መጥምቀ መለኮት ስለሚሆን ስለዮሐንስ ብለህ።

አንድም በእሱ አማላጅነት።

ወበእንተ ቅድሳን ስቡሐን ወላእካን ማቴዎስ ወማርቆስ ሉቃስ ወዮሐንስ ፬ ቱ ወንጌላውያን ።

ንጹሐን ክቡራን ላእካነ ቃል ስለሚሆኑ ስለ ፬ቱ ወንጌላውያን ስለ ማቴዎስ ስለ ማርቆስ ስለ ሉቃስ ስለ ዮሐንስ ብለህ።

አንድም በእነዚህ አማላጅነት ማቴዎስና ዮሐንስ ከየቦታቸው ይተረጐማሉ።

ማርቆስ ማለት አንበሳ ማለት ነው። አንበሳ ለላህም ጌታው ነው ይሰብረዋል። እሱም ከግብጽ አምላኮተ ላምህን አጥፍቷልና።

አንድም ንህብ ማለት ነው። ንህብ የማይቀስመው አበባ የለም እሱም አስቀድሞ ከጌታ ኋላ ከሐዋርያት ተምሯልና።
አንድም ካህን ማለት ነው ወአምጽኡ ማሬ ዘ ድዮስ እንዲል።

ሉቃስ ማለት መበሥር ማለት ነው። ብሥራተ መልአክን ይጽፋልና።
አንድም ተንሣኢ ማለት ነው። ለስብከተ ውንጌል ይጠናልና።
አንድም ዐቃቤ ሥራይ ማለት ነው። ቀድሞ ዐቃቤ ሥራይ ዘሥጋ ነበረ ኋላ ግን አቃቤ ሥራይ ዘነፍስ ሁኗልና።

፲፫. በእንተ ቅዱሳን አግብርቲከ ።

ክቡራን ባለሟሎችህ ስለሚሆኑ።

ሐተታ፦ የባለሟልነት ስማቸው ነው። ዳዊት ገብርየ ሙሴ ገብርየ እንዲል።

ጴጥሮስ ― ጴጥሮስ ማለት መሠረት ማለት ነው። መሠረትነቱ የሃይማኖት የልጅነት ነው።

ወያእቆብ
ስለያዕቆብ ብለህ።
ያዕቆብ ማለት አእቃጼ ሰኮና አኃዜ ሰኮና ማለት ነው። የቀደመው ያዕቆብ ሰኮና ኤሳውን ይዞ እንደተወለደ እሱም ወንጌልን ሲያስተምር በዚያው ይሞታልና። አእቃጼ ሰኮና ኤሳው እንደሆነ በትምህርቱ የመናፍቃንን ትምህርት ያሰናክላልና።

ወዮሐንስ ።
ስለ ዮሐንስ ብለህ።
ዮሐንስ ማለት ፍሥሐ ወሐሴት ርኅራኄ ወሣሕል ማለት ነው። ፍሥሐ ወሐሴት አለ ቅብዐ ትፍሥሕት መንፈስ ቅዱስ ያሰጣልና። ርኅራኄ ወሣሕል አለ በጸጋ ዘ ነሣ እክሙ በ ጸጋ ሀቡህ በከ ንቱ ዘ ነሣ እክሙ በከንቱ ሀቡ ባለው ጸንቶ ያስተምራልና።

ወእንድርያስ
ስለ እንድርያስ ብለህ።
እንድርያስ ማለት ተባዕ ለመስቀል በኵረ ሐዋርያት ማለት ነው። ተባዕ ለመስቀል አለ እስከ ሀገረ በላእተ ሰብእ ሄዶ አስተምሯልና።

ፊልጶስ ― ፊልጶስ ማለት መፍቀሬ አኀው ማለት ነው ፊልሳዳፎስ እንዲል፧
አንድም አኃዜ ኵናት ረያጼ አፍራስ ማለት ነው።
አንድም ሥውር ቦታ ማለት ነው ፌላሌምሌሞንም ንዑ ንኅድር ብሔረ ፊልሞን እንዲል።

ወበርተሎሜዎስ
ስለ በርተሎሜዎስ ብለህ።
በርተሎሜዎስ ማለት ተክል የማጠጣት ግብር ያለው ልጅ ማለት ነው። ኩን ወልደ ኃይል ኩን ወልደ የማን እንዲል።

አንድም ዕለቱን ወይን ተክሎ ለመሥዋዕት አድርሷልና።

ቶማስ
ስለ ቶማስ ብለህ።
ቶማስ ማለት ፀሀይ ማለት ነው። ፪ቱ አስማቲሁ ለፀሐይ ፩ዱ ኦርያሬስ ወካልኡ ቶማስስ እንዲል።

ወማቴዎስ
ስለ ማቴዎስ ብለህ።
ማቴዎስ ማለት ኅሩይ እመጸብሀን ማለት ነው ግብር ከሚያስገብርበት መርጦታልና።

ወያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ
ስለ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ ብለህ።
ወልደ እልፍዮስ በማለት ተለይቷል እንጂ ትርጓሜው እንዳለፈው ነው።

ታዴዎስ
ስለ ታዴዎስ ብለህ።
ታዴዎስ ማለት ዘርእ ወማእረር ማለት ነው ኦሪትን እንደዘር ወንጌልን እንደማእረር አድርጎ አስተምሯልና።
አንድም ዕለቱን ስንዴ ዘርቶ ዕለቱን ለመሥዋዕት አድርሷልና።

ወስምዖን ወማትያን
ሰለ ስምዖንና ሰለማትያን ብለህ።
ማትያን ማለት ምትክ ማለት ነው። ማትያስ ማለት ፀሐይ ማለት ነው።

፲ ቱ ወ ፪ ቱ ሐዋርያት ።
ስለ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ብለህ።
አንድም በእነዚህ አማላጅነት አስባቸው። ስማቸውን አስቀድሞ ቍጥራቸውን ወደኋላ አመጣ።

ወያዕቆብ ሐዋርያ እኁሁ ለእግዚእነ ኤጰስ ቆጰስ ዘኢየሩሳሌም ።
በኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስነት ስለተሾመ የጌታችን ወንድም ስለሚሆን። ወንጌልን ዙሮ ስላስተማሩ ስለያእቆብ ብለህ።

አንድም በእሱ አማላጅነት።

ሐተታ ፦ መገናኛው ጕንዱ አልዓዛር ነው። አልዓዛር ቅሥራንና ማትያንን ይወልዳል። ቅሥራ ኢያቄምን ኢያቄም እመቤታቸንን እመቤታቸን ጌታን። ማትያን ያዕቆብን ያዕቆብ ዮሴፍን ዮሴፍ ያዕቆብን ይወልዳል። በአንፃር ያለ ነውና እኁሁ አለ።

ለተዘምዶ እነ ያዕቆብ እነ ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ ይቀርቡታል ብሎ እናቱ በህጻንነቱ ሙታ ከአባቱ ቤት አግኝታው ከጌታ ጋር እያጠባች አሳድጋዋለችና። ኃሊብ ድንግልናዊንስ እሩቅ ብእሲ መጥባት አይቻለውም ብሎ እንደ እናት ሁና አሳድጋዋለችና። ኤጲስ ቆጰስ ዘኢየሩሳሌም አለ ያዕቆብ ወኮነ እግሩ ከመ እግረ ነጌ ይላል ከገድል ጽናት የተነሣ እግሩ እንደሙቀጫ ተድበልብሎ ነበርና ለስብከተ ወንጌል አይፋጠንም ብለው በኢየሩሳሌም ሹመውት ሄደዋል። ይኸማ ከሐዋርያት አንድ አንድ ደዌ የሌለበት አለ ቅዱስ ጴጥሮስንም ወኮነ ድውየ ወድግዱገ ሥጋ ይለዋል አልጸናበትም እንጂ። ቅዱስ ጳውሎስም ቀጭን ሰጥር ውጋት አዳጊት የምትባል ራስ ፍልጠት ደዌ ነበረበት። በዚያውስ ላይ ሐዋርያ ደመና ጠቅሶ ካሰበው ደርሶ ብዙ አስተምሮ አሳምኖ ብዙ አጥምቆ ይውል የለምን ቢሉ በኢየረሳሌም የነበሩ አይሁድ ምሁራነ መጻሕፍተ ነቢያት ናቸው ከእርሱ በቀር የሚያውቅባቸው የለም ብለው ሹመውታል። ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ እንዲሉ። ሐዋርያ አለው ወንጌል ዙሮ አስተምሯልና።

ወቅዱስ ወስቡሕ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት ።
ንጹሕ ክቡር ሊቀ ዲያቆናት የሰማዕታት ደገኛ።
አንድም የሰማዕታት ፊታውራሪያቸው ስለሚሆን ስለ እስጢፋኖስ ብለህ።
አንድም በእሱ አማላጅነት።
እስጢፋኖስ ማለት ወደብ መደብ ለሆቴ ደንጊያ ማኅቶተ ቁድ ማለት ነው። ነፋስ የማያስገባ ብርሃን የማይከለክል ፋና ነው። ቀዳሜ ሰማዕት አለ ከጌታ ቀጥሎ ከሐዋርያት አስቀድሞ መከራ የተቀበለ እሱ ነውና። ፮ቱን ዲያቆናት መርጠው ፯ኛ እርሱን መደበኛ አድርገው ሹመውታልና ሊቀ ዲያቆናት አለ።

፲፬. ወኵሎሙ ቅዱሳን ወሰማዕት እለ አዕረፉ በርትዕት ሃይማኖት ።

ውሎ ውሎ ከቤት ኑሮ ኑሮ ከመሬት እንዲሉ ሃይማኖታችንን አንክድም ብለው ስለሞቱ ሰማዕታት ብለህ።

አንድም በእነዚህ አማላጅነት።

ጳውሎስ
ስለ ጳውሎስ ብለህ።
አንድም በእሱ አማላጅነት
ጳውሎስ ማለት ንዋይ ኅሩይ ማለት ነው።

ጢሞቴ ዎስ
ስለ ጢሞቴዎስ ብለህ
ጢሞቴዎስ ማለት ዘአልቦቱ ጥሪት ማለት ነው።

ሲላስ
ስለ ሲላስ ብለህ።
ሲላስ መለት ፀሐይ ማለት ነው።

ወበርናባስ
ስለ በርናባስ ብለህ።
በርናባስ ማለት ወልደ ፍሥሐ ማለት ነው።

ቲቶ
ስለ ቲቶ ብለህ።
ቲቶ ማለት ሠርቅ ማለት ነው።

ወፊልሞና
ስለ ፊልሞና ብለህ።
ፊልሞና ማለት ሥውር ቦታ ማለት ነው።

ወቀሌምንጦስ
ስለ ቀሌምንጦስ ብለህ።
ቀሌምንጦስ ማለት ግንብ ማለት ነው።

፸ወ ፪ ቱ አርድዕት ።
ነሣሣለትና ስለ ሰባ ሁለቱ አርድዕት ብለህ።
አንድም በእነዚህ አማላጅነት አስባቸው።

፭ ቱ ፻ት ቢጽ ።
ስለ አምስት መቶ ቢጽ ብለህ።
አንድም እነዚህን አማላጅነት በማድረግ።

ሐተታ፦ እሊህ ከ፭፻ ብቅ ፮፻ ዝቅ የሚሉ በዕለተ ዓርብ እንደ አሸን ፈልተው ከእግረ መስቀል የተነሡ ናቸው። ቢጽ አላቸው በተፈጥሮ። ከእሊህ እስከ ዕርገት እስከ ጰራቅሊጦስ ያስተማረ አለ ወዲያው እስከ ትንሳኤ ቆይቶ ያረፈ አለ።

፫ ፻ ፩ ወ ፰ ርቱዓነ ሃይማኖት ።

ሃማኖታቸው ስለ ቀና ስለ ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ሊቃውንት ብለህ።
አንድም እነዚህን አማላጅ በማድረግ ዕጣን ቋጥረው ግብር ሰፍረው መብዓ ይዘው ቤተ ክርስቲያን የሚሄዱትን አስባቸው።
አንድም እነዚህን አማላጅ ስለአደረጉ።
አንድም በእነዚህ አማላጅነት አስባቸው።

፲፭፡ ለእሉኒ ወለ ኵሎ ሙ ተዘከሮሙ ለከ እግዚኦ ።
ያለፈውን የሚያመጣውን ላንተ ማደሪያ ወገን ሊሆኑ አቤቱ አስባቸው።

ለብፁዕ ወለቅዱስ ሊቀ ጳጳስነ አባ እገሌ
ንዑድ ክቡር የሚሆን አባ እገሌን።

ወብዑእ ወቅዱስ አባ እገሌ ።
ንዑድ ክቡር የሚሆን አባ እገሌን አስባቸው።

አንድም ለእነዚህ ብለው ዕጣን ቋጥረው ግብር ሰፍረው መብዐ ይዘው ወደ ቤተ እግዚአብሔር የሚሄዱትን አስባቸው።

፲፮. ከመ ትዕቀቦሙ በሕይወቶሙ ።
በሕይወተ ሥጋ ሳሉ ከመከራ ሥጋ ትጠብቃቸው ዘንድ።
አንድም ማሰብ ሌላን ዓለም ጠብቃቸው።

ወታድኅኖሙ ።
ታድናቸው ዘንድ።
አንድም ማዳን ሌላን አለ አድናቸው።

ወትሥረይ ሎሙ ኃ ጢአቶሙ ።
ኃጢአታቸውን ታስተሰርይላቸው ዘንድ።
አንድም ማዳን ሌላን አለ ኃጢአታቸውን አስተስርይላቸው።

ወትምሐ ረነ ኪያነሂ በጸሎተ ዚአ ሆሙ ለዓለ መ ዓለም ።
ትምሐረነ ካለ ለነሂ ኪያነ ካለ ትምሐር ባለ በቀና ነበር። ነገር ግን ልማደ መጽሐፍ ነው። እኛንም በእሳቸው ጸሎት ይቅር ትለን ዘንድ።
አንድም ማሰብ መጠበቅ ማዳን ኃጢአትን ማስተስረይ ሌላን አለ በእሳቸው ጸሎት ለዘለዓለሙ ይቅር በለን።

፲፯ . ይ . ካ ፡ ንፍቅ ጸሎተ ቡራኬ ።

ይ.ዲ፡ ንፍቅ መሐሮ ሙ እግዚኦ ።

(...........ይቀጥላል )

10/08/2025

🇪🇸 Zubimendi vs Athletic Bilbao:

1 assist
94% pass accuracy
2 key passes 🥇
100% accurate crosses
5/6 accurate long balls
1 interception
2 recoveries
5 duels won
4 tackles won 🥇
⭐️ 8.2 match rating

WHAT A PLAYER! 🪄

10/08/2025

የአትሌቲክ ቢልባኦው አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ስለ አርሰናል

"በዚህ የቅድመ ውድድር ዘመን የተጫወትነው በጣም ከባዱ ጨዋታ ነበር:: ከዚህ ቀደም ይህን ከፍተኛ ደረጃ እናያለን ብዬ አላሰብኩም ነበር ነገር ግን በቀላሉ ዛሬ ድንቅ ነበሩ:: ሊቨርፑልም ከባድ ነበር ነገር ግን ይህ ሌላ ደረጃ ነው።"

28/01/2025

#አጫጭር የዝውውር ጭምጭምታ ወሬዎች

ጄርሚ ዶኩ ከተለያዩ የአውሮፓ ክለቦች ጋር ስሙ ተያይዞ እየወጣ መሆኑ ተገለጸ።

ባርሴሎናን ጨምሮ በርካታ ክለቦች የማንችስትር ሲቲውን ኮከብ የዝውውር ራዳራቸው ውስጥ ማስገባታቸው ዲያሪዮ ስፖርት የተሰኘው የወሬ ምንጭ አስታውቋል።

የማንችስትር ዩናይትዱ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ ከባርሴሎና የሚቀረበውን ጥያቄ ለመስማት እየተጠባበቀ መሆኑ ተነግሯል።

የ27 አመቱ ተጫዋች ኤሲ ሚላንን ጨምሮ ከተለያዩ አውሮፓ እና ሜጀር ሊግ ሶከር ክለቦች ጥያቄ እንደቀረበለት ሲገለጽ መቆየቱ ይታወቃል።

አስቶን ቪላ ፖርቱጋላዊውን የቼልሲ አጥቂ ጆአኦ ፊሊክስ ፊርማ ለማግኘት ጥረት እያደረጉ ከሚገኙ ክለቦች መካከል አንዱ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።

የተጫዋቹ ወኪል ሆርጌ ሜንዴዝ በያዝነው የውድድር ዘመን በምዕራብ ለንደኑ ክለብ በሁሉም መድረክ ውድድሮች ዘጠኝ ጨዋታ ብቻ ያደረገውን ደንበኛው ወደ ሌላ ክለብ ለማሻገር እየሰራ መሆኑ ተነግሯል።

ባየር ሌቨርኩሰን የአስቶን ቪላውን የአጥቂ አማካይ ኢሊያኖ ቡዌንዴያ ለማስፈረም ሙሉ ለሙሉ ከስምምነት ላይ መድረሱ ታውቋል።

የ28 አመቱ ተጫዋች በመነሻ የውሰት ውል እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ በሚቆይ ውል እንደሚቀላቀልም ታውቋል።

03/01/2025

እርግጠኛ ሆኜ እናገራለው አርሰናል በዚህ ወር አንድ የፊት መሥመር ተጫዋች አልያም የክንፍ መሥመር አጥቂ ተጫዋች ያሥፈርማል ጥያቄው አሁን የትኛው ተጫዋች ነው በዚህ ወር የአርሰናል ተጫዋች የሚሆነው ነው ?

🇬🇭 Mohamed Kudus
🇨🇲 Bryan Mbuemo
🇪🇸 Nico Williams
🇧🇷 Matheus Cunha

የእኔ ምርጫ ቢገኝ ኒኮ ዊልያምስ የእናንተስ…👇🏼

15/10/2024
15/10/2024

saka ምርጥ ጎል

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Dubai?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Dubai