03/18/2026
ስንት እንጠብቅ?
Arsenal Ethiopia videos and news like.....
03/18/2026
ስንት እንጠብቅ?
03/18/2026
በኤክስፔክቴሽን ራይስ ለባላንዶር ቅድመ ግምት አግኝቷል
03/18/2026
ይሄ ልጅ ባላንዶር አይገባውም ነው የምትሉኝ?
03/17/2026
“ አርቴታ ሁነኛ ዘዴ መዘየድ ነበረበት “ ጄሚ ካራጋር
የቀድሞ የሊቨርፑል ተጨዋች ጄሚ ካራጋር አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ሊጉን ለማሸነፍ የሄደበትን መንገድ አድንቋል።
አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ እና የርገን ክሎፕ በከፍተኛ በጀት ለሊጉ ሲፎካከሩ እንደነበረ ጄሚ ካራጋር አስታውሷል።
“ ታዲያ አርቴታ በአነስተኛ በጀት እና የደሞዝ ስርዓት እንዴት ፔፕ ጋርዲዮላ እና የርገን ክሎፕን መብለጥ ይችላል ? “ ሲል ጄሚ ካራጋር ጠይቋል።
አክሎም “ በዚህ ምክንያት አርቴታ ሌላ መንገድ መፈለግ ነበረበት አድርጎታል “ ሲል አድናቆቱን ገልጿል።
“ አርሰናል ዋንጫውን ካሸነፈ ደጋፊዎች በቆመ ኳስ ነው ያሸነፈው ብለው ለአስር አመታት ያስታውሱታል ? “ ሲል ጄሚ ካራጋር ጠይቋል።
03/17/2026
“ ስለ አጨዋወቱ ዋንጫውን ካሸነፍን በኋላ ቁጭ ብለን እንነጋገራለን “ ቴሪ ሄንሪ
የፈረንሳዊው የቀድሞ ተጨዋች ቴሪ ሄንሪ የአርሰናል አጨዋወት ምንም ቢሆን ግድ እንደማይሰጠው ተናግሯል።
ስለ አርሰናል አጨዋወት ሀሳቡን የተጠየቀው ቴሪ ሄንሪ “ እኔ የምፈልገው ከ 22 አመታት በኋላ ሊጉን ማሸነፍ ብቻ ነው “ ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
ሄንሪ አያይዞም “ ሊጉን ካሸነፍን በኋላ ስለ አጨዋወቱ ቁጭ ብለን መነጋገር እንችላለን “ ሲል ጨምሮ ተናግሯል።
03/15/2026
እቺን የህክምና ማስረጃ ሰሞኑን ጠብቁ የመግደል ሙከራ በሚል😁😁 ልጁ መቼም አይፋታንም
03/15/2026
አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው አሉ😂😂😂😂
03/15/2026
ድንቄም የስፖርት ጋዜጠኛ😂 ይሄም አላዛርም መንሱርም ጋዜጠኛ በሚል ስም ነው አ የሚጠሩት
03/15/2026
“ ለዋንጫው 🏆 እስከመጨረሻ እንፋለማለን “ ጋርዲዮላ
የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ ፉክክር እስከመጨረሻው እንደሚፋለሙ ገልጸዋል።
“ አንድ ቀሪ ጨዋታ አለን “ ያሉት ፔፕ ጋርዲዮላ “ ከአርሰናል ጋርም በሜዳችን ጨዋታ አለን ስለዚህ እስከመጨረሻው መፋለም አለብን " ብለዋል።
ሆኖም ግን አርሰናል ላይ መድረስ የማንችል ከሆነ “ እንኳን ደስ አላችሁ እንላቸዋለን “ ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።
ጨዋታውን ስለተመለከቱበት ቦታ የተጠየቁት ጋርዲዮላ “ ጥሩ ነገር ነው ወድጄዋለሁ ፤ ወደዛ ቦታ ተመልሼ ለመሄድ ተጨማሪ ቢጫ ለማየት እሞክራለሁ "ብለዋል።
03/15/2026
“ ዶውማን ድንቅ ልጅ ነው ፍርሀት የለበትም “ ዮኬሬሽ
የመድፈኞቹን ቀዳሚ ግብ ያስቆጠረው ቪክቶር ዮኬሬሽ ማክስ ዶውማን ባሳየው እንቅስቃሴ መደነቁን ገልጿል።
“ ዶውማን አስደናቂ ተጨዋች ነው “ ያለው ዮኬሬሽ “ በተረጋጋ መልኩ ያለ ፍርሀት ነው የሚጫወተው “ ሲል አድናቆቱን ገልጿል።
አክሎም " እሱ ሁልጊዜም ኳስ ሲደርሰው ትክክለኛውን ውሳኔ ነው የሚወስነው ለእሱ በጣም ደስተኛ ነኝ “ ብሏል።
“ ዛሬ ማሸነፍ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እናውቃለን ፤ በቡድኑ ውስጥ ትክክለኛ አስተሳሰብ እና እምነት ይዘህ ከገባህ ማንኛውንም ነገር ማሳካት ትችላለህ።" ዮኬሬሽ
03/15/2026
“ ዶውማን የሚያደርገው ነገር ተፈጥሯዊ አይደለም “ አርቴታ
የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ማክስ ዶውማን ሜዳ ላይ ያሻውን እንዲያደርግ ፍቃድ ሰጥተው እንዳስገቡት ገልጸዋል።
“ ማክስ ዶውማን እያደረገ ያለው ነገር ተፈጥሯዊ አይደለም “ ያሉት አርቴታ አስቸጋሪ ጊዜ አያስፈራውም ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም “ ለዶውማን ገብተህ የፈለከውን ነገር አድርግ እና ድሉን አምጣ ብዬ ነግሬ ነው ያስገባሁት "ብለዋልቸ
“ ጨዋታው ማንም ባልጠበቀው መልኩ ተጠናቋል ፤ ኤምሬትስ ላይ ካሳለፍኳቸው አስደሳች ቅፅበቶች አንዱ ነው “ ሚኬል አርቴታ
03/11/2026
“ አርሰናል ሻምፒየንስ ሊግ ያሸንፋል ” ጄሚ ካራጋር
የቀድሞ የሊቨርፑል ተጨዋች ጄሚ ካራጋር አርሰናል በሻምፒዮንስ ሊጉ ጥሩ ጊዜ እንደሚያሳልፍ ገምቷል።
በተንታኝነት እያገለገሉ የሚገኙት የቀድሞ ተጨዋቾች ጄሚ ካራጋር እና ሚካ ሪቻርድስ ግምታቸውን ሲያስቀምጡ “ አርሰናል ለፍፃሜ ይደርሳል “ ብለዋል።
ጄሚ ካራጋር በፍፃሜው ጨዋታ አርሰናል አሸንፎ “ ሻምፒዮን ይሆናል “ ሲል ገምቷል።
በሌላ በኩል ጄሚ ካራጋር ሊቨርፑል ወደ ቀጣዩ ዙር ያልፋል የሚል ምንም ተስፋ የለኝም ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።