09/08/2022
ጎንቻሎ ጉዴስ በ30 ሚሊየን ዩሮ ዎልቭስን በቋሚ ኮንትራት ተቀላቅሏል ሲል የተጫዋቹ ክለብ ቫሌንሲያ በይፋዊ መግለጫው አረጋግጧል። 🚨🟠🇵🇹
ጉዴስ የሕክምና ምርመራውን አጠናቅቆ በቅርቡ ውሉን ይፈርማል።
ምንጭ ፦ Fabrizio Romano
አልካንትራ በጉዳት ምክንያት ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል።
የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የመሐል ሜዳ ተጫዋች ቲያጎ አልካንታራ ባጋጠመው ጉዳት ለሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ይፋ ተደርጓል ።
ሊቨርፑል የሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ ከፉልሀም ጋር ባደረጉበት መርሐ ግብር የጡንቻ መሸማቀቅ ያጋጠመው አልካንታራ ለስድስት ሳምንታት ከሜዳ የሚርቅ ይሆናል ።
ቲያጎ አልካንታራ እስከ መስከረም አጋማሽ ለክለቡ ግላጋሎት የማይሰጥ ሲሆን ከ ክሪስታል ፓላስ ፣ ማንችስተር ዩናይትድ ፣ በርንማውዝ ፣ ኒውካስትል ፣ ኤቨርተን እና ዎልቭስ ጋር የሚደረጉ ጨዋታዎች ያመልጡታል ።
ዴስትኒ ኡዶጊ ወደ ቶተንሃም 𝙝𝙚𝙧𝙚 𝙬𝙚 𝙜𝙤 !
ቶተንሃም ኡዶጊን ለማስፈረም ከዩዲኔዝ ጋር ሙሉ ስምምነት ተደርሷል።
የለንደኑ ክለብ ለተጫዋቹ ዝውውር 20 ሚሊየን ዩሮ ይከፍላል። ከተጫዋቹ ጋር ከግል ስምምነቶች በኋላ ባለተሰጥኦው ጣሊያናዊ የግራ ተመላላሽ በ2023 የስፐርስ ተጫዋች ይሆናል።
እስከዛ ድረስ በአንድ አመት የውሰት ውል እዛው ዩዲኒዜ ይቆያል።
ምንጭ ፦ Fabrizio Romano
OFFICIAL ፦ የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትዱ ግብ ጠባቂ ሰርጅዮ ሮሜሮ በነፃ ዝውውር የአርጀንቲናውን ክለብ ቦካ ጁንየርስ በአንድ ዓመት ኮንትራት መቀላቀሉ ይፋ ሆኗል።
ምንጭ ፦ Fabrizio Romano
ማንቸስተር ዩናይትዶች ከአድሪያን ራቢዮት እና ከእናቱ ቬሮኒኬ ጋር በቀጥታ ተገናኝተዋል!
በግል ውል ላይ ለመደራደር ከጁቬንቱስ ጋር ምንም ችግር የለም በዚህ ክረምት ራቢዮትን መሸጥ ይፈልጋሉ።
ኤሪክ ቴን ሃግ ከፈረንሳዩ ተጫዋች ጋር በተደረገው ቀጥተኛ ውይይትም ተሳትፏል።
ቼልሲዎች ለዌስሊ ፎፋና አዲስ ፕሮፖዛል በማዘጋጀት ላይ ናቸው!
እና ባለፈው ሳምንት የ£70m ጥያቄ ውድቅ ከተደረገባቸው በኋላ እንደገና ሙከራ ያደርጋሉ።
➪ FabrizioRomano
ኤሪክ ቴን ሃግ ማርኮ አርናውቶቪችን ይፈልጋል እና ከእሱ አንድ ነገር ማግኘት እንደሚችል ያስባል።
ቴን ሃግ በማንቸስተር ዩናይትድ የሚፈልገውን ሁሉ እያገኘ ነው - አድሪያን ራቢኦትንም ይፈልጋል።
🚨| በርናርዶ ሲልቫ ባርሴሎናን ለመቀላቀል ደመወዙን በብዙ ዝቅ ለማድረግ ፈቃደኛ ነው።
🚨| ባርሴሎና ፍሬንኪ ዲዮንግ ቢቆይም እንኳ ለበርናርዶ ሲልቫ እንደሚፈርም ነግረውታል።
ኮስቲች ወደ ጁቬንቱስ፣ Here We Go!
ሙሉ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ክፍያ ወደ €16m ተጨማሪ ክፍያ ተካትቷል - ኮስቲች የህክምና ምርመራዎችን ለማድረግ በቅርቡ ወደ ቱሪን ይበራል።
ምንጭ፦ Fabrizio Romano
ጁቬንቱሶች ለሜምፊስ ዴፓይ የ 2 ዓመት ኮንትራት ሊያቀርቡለት ተዘጋጀተዋል ።
ምንጭ፦ Dimarzio
የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል ከታች ያለዉን ሊንክ ይጫኑ
👇
https://t.me/hulusporthighlight
08/08/2022
አቡበከር ናስር በይፋ ዝውውሩን ማጠናቀቁን ፌዴሬሽኑ አስታወቀ !
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ አቡበከር ናስር ወደ ደቡብ አፍሪካው ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የሚያደርገውን ዝውውር ማጠናቀቁን የሚገልፅ የፊፋ ITC ማረጋገጫ በዛሬው ዕለት አግኝቷል። ከዛሬ ጀምሮም በቋሚ ውል የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ተጫዋች መሆኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ይፋ አድርጓል።
[ Via Ethio Kickoff ]
DEAL DONE
ሆፈንሄም አንጄሊኖን በአንድ ዓመት የውሰት ውል እና በ €20 ሚልየን ዩሮ የመግዛት አማራጭ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።
በክረምቱ ከሜምፊስ ዴፓይ ወይም ኤባሚያንግ አንዱ ብቻ ባርሴሎናን ይለቃል።
ዴፓይ በነፃ ክለቡን መልቀቅ እንደሚችል ተነግሮታል ነገር ግን ዴፓይ ይህንን የሚቀበለው ከትልቅ ክለብ ጥያቄ ከቀረበለት ነው፣ ጁቬንቱስ የተጫዋቹ ፋላጊ ከሆኑ ቡድኖች መካከል አንዱ ናቸው።
[ Fabrizio Romano ]
ሞናኮ የቼልሲውን የመሀል ተከላካይ ማላንግ ሳር በአንድ ዓመት የውሰት ውል ለማስፈረም በቃል ደረጃ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
በቀጣዩ ዓመት ሞናኮዎች ተጫዋቹን በ 15 ሚልየን ዩሮ በቋሚ የሚገዙት ይሆናል።
[ David Ornstein ]
በማንችስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ ሲፈለግ የነበረው ስሎቬንያዊ የሳልዝበርግ አጥቂ ቤንጃሚን ሴስኮ የጀርመኑን ክለብ RB ሌፕዚሽ በአንድ ዓመት ኮንትራት ለመቀላቀል ተስማምቷል።
[ Fabrizio Romano ]
ማንችስተር ዩናይትድ ለማርኮ አርናቶቪች ዝውውር ያቀረቡትን ገንዘብ ለመጨመር ተዘግጅተዋል።
ኤሪክ ቴን ሀግ 100% ተጫዋቹን ይፈልጉታል፣ ተጫዋቹም ወደ ዩናይትድ መምጣት ይፈልጋል።
[ Plettigoal ]
የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል ሁሉ ስፖርት
የእግር ኳስ ሀይላይቶች የምያገኙበት ቻናል
https://t.me/hulusporthighlight
26/07/2022
▪️ !
እግርኳስን በ ላቀ ደረጃ ከሚጫወቱ ተጫዋቾች መካከል ተቀዳሚው ነው ፤ የ ሰውነት አቅምን በሚፈልግበት ደረጃ ኳስን በ ጭንቅላት እና በ አይን ከ ጥበበኛ እግሮች ጋር መጫወት እንደሚቻል ያስመሰከረ ድንቅ ተጫዋች ነው ። 10 ቁጥር ማልያንም ቦታውንም ነግሶበታል ፣ በ አንድ ደረጃ ከፍ ያደረገ ተጫዋች ነው ። ገና ኳሷ እግሩ ስር ስትገባ ትስቃለች ። ከእሱ ውጪ ማንም እንደዚህ አይወራለትም አመለ ሸጋው እና መልከመልካሙ ሜሱት ኦዚል ።
ስለ እሱ ለማውራት የክለቡ ደጋፊ ሳይሆን የ እግርኳስ ተመልካች መሆን በቂ ነው ምትሀተኛ ነው ተቃራኒ ደጋፊም ሆነህ እጅህን በ አፍህ አስጭኖ ከዛም ያስጨበጭብሀል ። መቼም ወደ ክለባችን ሲመጣ ብዙዎች አላመኑም ፤ ሁላችንም የጠበቅነው አጠባበቅ የማይረሳ ነው ። እንደጠበቅነው አላሳፈረንም ለብዙ ዓመታት በ እንከን የለሽ እግሮቹ ፣ በሚያስደምሙ አይኖቹ ፣ በላቀ ጭንቅላቱ በ እግርኳስ እንድንዝናና አድርጎናል ።
እሱን መግለፅ ከባድ ቢሆንም ምትሀተኛ ፣ የ አሲስት ንጉስ ፣ ተወዳጅ ፣ መልከመልካም ፣ አይናማ ፣ የክለብ ፍቅር ያለው ፣ ደግ ፣ የ እግርኳስ ውበት ፣ ሌጀንድ..🥵 ብቻ ስለ እሱ ማውራት ትርፉ ቃላት ማባከን ነው ። ብቻ ምርጡ 10 ቁጥር ለባሽ እና ምርጡ 10 ቁጥር ተጫዋች ሜሱት ኦዚል!
* Maestro !
- ተወዳጁ እና ተናፋቂው የ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሊጀምር 10 ቀናት ብቻ ቀርተውታል !
26/07/2022
እንደ አንድ የጣልያን ሚድያ ዘገባ ከሆነ የዲዮንግ ጉዳይ አልሆን ያላቸው ማንችስተር ዩናይትዶች የላዚዮውን አማካይ ሰርጄ ሚሊንኮቪች ሳቪች ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረዋል ።
ሮማ እና ማንችስተር ዩናይትድ በኤሪክ ባይ ዙሪያ ንግግር ማድረግ ጀምረዋል።
(Dimarzio)!
አትሌቲክ ቢልባኦ ለኢኒጎ ማርቲኔዝ 60 ሚሊየን ዩሮ እየጠየቁ ነው ! ባርሴሎና ፍላጐት ያላቸው ሲሆን ለተከላካዩ በቅርቡ ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ ሊያቀርቡ ይችላሉ !
🎙 EL MARzio
ቲሞ ወርነር ቼልሲን ሊለቅ ይችላል !
ጀርመናዊው የቼልሲ አጥቂ ቲሞ ወርነር በዚህ ክረምት ቼልሲን ሊለቁ ከሚችሉ ተጫዋቾች አንዱ እንደሆነ ተዘግቧል። የጁቬንቱሱ አሰልጣኝ ማሲሚልያኖ አሌግሪ የተጫዋቹ ፈላጊ ናቸው።
ቼልሲ ከዚህ ቀደሞ ኖርዲ ሙኬሌን ከሌፕዚሽ ለማስፈረም ወርነርን በውሰት የዝውውሩ አካል ለማድረግ ንግግር አድርገው ነበር።
[ Fabrizio Romano ]
🚨 ማንቸስተር ሲቲዎች አጥቂውን ሊያም ዴላፕን ለማስፈረም ከሳውዝአምፕተን የቀረበላቸውን የ16 ሚሊየን ዩሮ ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል !
🎙FABRIZIO ROMANO
ስካማካ ነገ ሜዲካሉን የሚያደርግ ይሆናል ! 🏥 የዌስትሀም ተጫዋቾ መሆኑም ይፋ ይደርጋል !
📰 AS
እንደ በርካታ የእንግሊዝ ሚድያዎች ዘገባ የአርሰናሉ ግብ ጠባቂ በርንድ ሌኖ ለ ሌላኛው የለንደን ክለብ ፉልሀም ፊርማውን ለማኖር ተቃርቧል ✍
ክሪስትያኖ ሮናልዶ በዛሬው ዕለት ወደ ማንችስተር ዩናይትድ እየተመለሰ ነው እናም ስለ ዩናይትድ የወደፊት ቆይታው ንግግር የሚያደርግ ይሆናል።
በዚህ ሰዓት የልምምዱ አካል ይሆናል አይሆንም የሚለው ጉዳይ ግልፅ አይደለም።
[ David Ornstein ]
የስፔኑ ቫሌንሽያ አርቱር ሜሎን ለማስፈረም ከጁቬንቱስ ጋር ንግግር አድርገዋል ።
[ David Ornstein ]
20/07/2022
አዲስ አዳጊዎቹ ኖቲንግሀም ፎረስቶች ጄሴ ሊንጋርድን ለማስፈረም ጥሩ ንግግር ላይ ናቸው ✍
𝐎𝐅𝐅𝐈𝐂𝐀𝐋:-
የጣልያኑ ክለብ ሮማ ፓውሎ ዲባላን በሶስት አመት ኮንትራት ማስፈረሙን ይፋ አድርጎል ::
ቼልሲ የሴቪያውን ጁለስ ኩንዴ በ €50 ሚልየን ዩሮ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ለመድረስ ከጫፍ ደርሰዋል።
[ Di Marzio ]
🗣 የሊሉ ፕሬዝዳንት ኦሊቨር ሌታንግ
"ሬናቶ ሳንቼስ በዚህ ክረምት ሊልን የሚለቅ ይሆናል። መዳረሻውም ፓሪስ ወይ ሚላን ይሆናል፣ ሁለት ትላልቅ ዕድሎች ለሬናቶ።"
እንደ ፋብሪዝዮ ሮማኖ ዘገባ የ 24 ዓመቱ የሌፕዚሽ የቀኝ መስመር ተከላካይ ኖርዲ ሙኬሌ ፓሪሴንዠርመን ለመቀላቀል ተስማምቷል።
አርማንዶ ብሮጃ ወደ ዌስትሃም
አሁንም ቼልሲ እና ዌስትሃም አርማንዶ ብሮጃን ለማስፈረም በቀጥታ ድርድር ላይ ናቸው። ቼልሲ አሁን አርማንዶን ለማቆየት እየጣሩ ነው ቱሄል ለሱ ትልቅ አድናቆት አለው - እንዲቆይ ይፈልጋል።
ዌስትሃም አሁንም እየጣሩ ነው። በቋሚ ዝውውር ላይ ብቻ እየተነጋገሩ ነው።
🎖 (ምንጭ : Fabrizio Romano)
🚨 BREAKING:
ኦሌክሳንደር ዚንቼንኮ በአርሰናል ቤት የሚያቆየውን የአራት አመት ኮንትራት ፈርሟል።
🎖 (ምንጭ : Fabrizio Romano)
𝐎𝐅𝐅𝐈𝐂𝐀𝐋:- የሃደርስፊልዱ የግራ ተከላካይ ሃሪ ታፎሎ ኖቲንግሃም ፎረስትን በረጅም ጊዜ ውል ተቀላቅሏል።
አትሌቲኮ ማድሪድ ሁለት ስምምነቶችን ለመፈፀም ተዘጋጅቷል። ⚪️🔴
▫️🇦🇷 ናሁኤል ሞሊና ባለፈው ሳምንት እንደዘገበው ቀጣዩ ፈራሚ ይሆናል። የግል ውሎችም ተስማምተዋል።
▫️🇸🇰 ያን ኦብላክ ከአትሌቲ ጋር አዲስ ኮንትራት ይፈራረማል።
በኩኩሬላ ዝውውር ለይ መስማማት አልተቻለም!
ማን ሲቲ እና ብራይተን በማርክ ኩኩሬላ ዋጋ 20 ሚሊየን ፓውንድ ተለያይተዋል። ማን ሲቲ የብራይተንን የ50ሚ.ፓ ዋጋ የመክፈል ፍላጎት የላቸውም እና የተጫዋቹ ዋጋ ወደ £30M አካባቢ እንደሆነ ያምናሉ።
ብራይተን ዝቅተኛ ክፍያ ለመቀበል ካልተዘጋጀ በስተቀር ማን ሲቲ ከዚህ በኃላ ለማርክ ኩኩሬላ ዝውውር እንቅስቃሴ አያደርግም።
19/07/2022
ባርሴሎና ከጁለስ ኩንዴ ጋር በአራት ዓመት ኮንትራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ✍
ኤዲሰን ካቫኒ የስፔኑን ቪላርያል ለመቀላቀል ተስማምቷል ✍
[ Marca ]
📝 𝐃𝐄𝐀𝐋 𝐃𝐎𝐍𝐄:
ባየር ሙኒክ ማቲያስ ዲላይትን በ €70 ሚልየን ዩሮ + €10 ሚልየን ዩሮ ተጨማሪ ገንዘብ ከጁቬንቱስ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።
ዲላይት በባየርን ቤት የ 5 ዓመት ኮንትራት ተፈራርሟል።
OFFICIAL
ጆዋኦ ካንሴሎ አዲሱ የማንችስተር ሲቲ '7' ቁጥር ማልያ ለባሽ ሆኗል።
7 ቁጥር ለመስመር ተከላካይ 🤔
18/07/2022
ማንቸስተር ዩናይትዶች የክሪስትያኖ ሮናልዶን ኮንትራት ለማራዘም እያሰቡ ይገኛል።
ምንጭ ፦ Telegraph
ዩሪ ቲልማንስ በዚህ ሳምንት ከብሬንዳን ሮጀርስ ጋር በሌስተር ሲቲ ስላለው የወደፊት ቆይታው ይወያያል።
🚨 ዚንቼንኮ ወደ አርሰናል
👉 ከ አርብ ጀምሮ በአርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ መካከል የ £30 ሚልየን ፓውንድ ስምምነት ላይ ተደርሷል። በግል ጉዳዮች ንግግሮች ቀጥለዋል፣ ክለቡ በዚህ ሳምንት መጨረሻ የፋይናንሻል ውሳኔ ላይ መድረስ ይፈልጋል።
👉 ዚንቼንኮ፣ አርሰናልን መቀላቀል ይፈልጋል፣ ነገር ግን የኮንትራት ጉዳዮች በንግግር ላይ ቀጥለዋል።
🎖 (ምንጭ : Fabrizio Romano)
ፓውሎ ዲባላ ወደ ሮማ - Here We Go !
አርጀንቲናዊው አማካይ ፓውሎ ዲባላ በ 3 ዓመት ኮንትራት የጣልያኑን ኤስ ሮማን በነፃ ለመቀላቀል ተስማምቷል።
ሞሪኖ ለስምምነቱ ወሳኝ ሰው ነበር - ለዲባላ በስልክ ደውሎ ስለ ፕሮጀክቶ አብራርቶለታል። ሁሉም ፋይሎች እየተዘጋጁ ሲሆን ስምምነቱ ተጠናቋል።
[ Fabrizio Romano ]
📝 𝐃𝐄𝐀𝐋 𝐃𝐎𝐍𝐄:
ኤሲ ሚላን የዝላታን ኢብራሂሞቪችን ኮንትራት ለተጨማሪ አንድ ዓመት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።
17/07/2022
ዝላታን ኢብራሂሞቪች በሚቀጥሉት ቀናት ውሰጥ ከኤሲ ሚላን ጋር ያለውን ኮንትራት ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንደሚያራዝም ታዋቋል።
አዲስ ውል እስከ ሰኔ 2023 ድረስ ፀንቶ ይቆያል፣ ደሞዝ ወደ €1/1.5m የተጣራ ከተጨማሪ ክፍያ ጋር በአፈፃፀሙ ላይ በመመስረት።
በጥቅምት ወር 41ኛ አመት ይሆነዋል - ዝላታን አያቆምም ይቀጥላል።
🎖 (ምንጭ : Fabrizio Romano)
አያክስ ካልቪን ባሴን ከሬንጀርስ በ €22m የዝውውር ዋጋ ለማስፈረም ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ካልቪን ባሴን በቅርቡ የህክምና ምርመራውን ሊያደርግ ይችላል።
🎖 (ምንጭ : Fabrizio Romano)
🗣 የባየርኑ ኦሊቨር ካህን ሀሪ ኬንን በ 2023 ክረምት ስለማስፈረም
"በቶተንሀም ቤት ኮንትራት አለው። በእርግጥም ምርጥ አጥቂ ነው፣ ነገር ግን ይሄ ለወደፊቱ ህልም ነው። ስለዚህ ሚፈጠረውን አብረን እንይ።"
በቶተንሀም ቦርድ ሀሪ ኬንን የማይነካ ወይም ለሽያጭ የማይቀርብ ተጫዋች ነው።
🎖 (ምንጭ : Fabrizio Romano)
ቼልሲ እና ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን ለፕሬስኔል ኪምፔምቤ ስምምነት በቀጥታ እየተነጋገሩ ነው ።
ፒኤስጂ ከተጫዋቾቹ ከ 60/65 ሚሊየን ዩሮ ይፈልጋል ። ቼልሲዎች ደግሞ 45/50 ሚሊየን ዩሮ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል። ገና በሂደት ላይ ያለ ዝውውር ነው ።
ፒኤስጂ ኪምፔምቤን የቡድኑ አካል አድርጎ ይቆጥረዋል ነገር ግን ጥሩ ወጋ ከቀረበለት ለመሸጥ ዝግጁ ነው።
🎖 (ምንጭ : Fabrizio Romano)
BREAKING
🚨ቼልሲዎች ጁሌስ ኩንዴን ለማስፈረም ተቃርበዋል ::
SKY SPORT
ሶኒ ፐርኪንስ የሊድስ ዩናይትድ ተጫዋች ሆኖ ኮንትራቱን ፈርሟል!
{FABRZIO ROMANO}
BREAKING:
ማንቸስተር ዩናይትድ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝን በ 5 አመት ኮንትራት ማስፈረማቸውን አረጋግጠዋል ::
📝 DEAL DONE: ፒኤስቪ ጃራድን ብራንትዋይትን በውሰት ውል ከኤቨርተን ማስፈረማቸውን አረጋግጠዋል ::
{PSV}
16/07/2022
አርሰናል ጀርመናዊውን የክንፍ መስመር ተጫዋች ሌሮይ ሳኔን የማስፈረም ፍላጎት አላቸው።
ባየር ሙኒክ የ26 አመቱ ኮከብ ለይ $70m ለጥፎበታል። [BILD_Sport በTDDL]
OFFICIAL: ሰርጅ ግናብሪ በባየር ሙኒክ ቤት እስከ ሰኔ 2026 የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ተፈራርሟል ። ✍🏻🔴🧑🍳
🚨 ዚንቼንኮ ወደ አርሰናል
👉 አርሰናል እና ማንቸስተር ሲቲ በአሌክሳንደር ዚንቼንኮ ዝውውር ጉዳይ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
👉 የለንደኑ ክለብ ለዩክሬናዊው ተጫዋች ዝውውር £30m ይከፍላል።
👉 አሁን በግላዊ ውሎች እና የደመወዝ ዝርዝሮች ላይ በተጫዋቹ በኩል ድርድር እየተካሄደ ነው ከዚያም ይጠናቀቃል።
🎖 (ምንጭ : Fabrizio Romano)
16/07/2022
Here We Go ! ሮበርት ሌዋንዶውስኪ ወደ ባርሴሎና
ባርሴሎና ፖላንዳዊውን የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በ €50 ሚልየን ዩሮ ከ ባየር ሙኒክ ለማስፈረም ተስማምተዋል።
ተጫዋቹ በቅድመ ውድድር ዝግጅት ዛሬ ወይም ነገ ባርሴሎናን የሚቀላቀል ይሆናል ።
🎖 (ምንጭ : Fabrizio Romano)
ዌስትሃም አርማንዶ ብሮጃን ለማስፈረም 25 ሚሊየን ፓውንድ እና 5 ሚሊየን ፓውንድ ቦነስ ለቼልሲ አቅርበዋል።
𝐎𝐅𝐅𝐈𝐂𝐈𝐀𝐋: ፌዴሪኮ በርናርዲስኪ ከጁቬንቱስ ጋር ያለው ኮንትራት ካለቀ በኋላ በነፃ ዝውውር ቶሮንቶ FC ተቀላቅሏል።
የኢንጊሊዙ ክለብ ዌስትሃም የሊሉን አማካኝ አማዱ ኦናናን ለማስፈረም ሶስተኛ ጥያቄ አቅርበዋል።
የ ኢንጊሊዙ ክለብ ለሊል ያቀረቡት ጥያቄ 38 ሚሊየን ዩሮ + ቦነስ ነው።
➩sky sport
ባየርን ሙኒክ ሮበርት ሌዋንዶቭስኪ ከሸጠ በኋላ ቀጣይ እንቅስቃሴዎችን ጀምሯል
▫️ የጀርመኑ ክለብ ለማቲያስ ዲላይት አዲስ ይፋዊ ጥያቄ በቅርቡ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል። ጁቬዎች ከተከላካዩ ሽያጭጠ €90/100m አካባቢ ይፈልጋሉ።
▫️ ባየርን ሙኒክ ኮንራድ ላይመርን ለማስፈረም አርቢ ላይፕዚግን አጥብቆ እየጠየቀ ይገኛል።
▫️ ግናብሪ ኮንትራቱን እስከ 2026 አራዝሟል።
🎖 (ምንጭ : Fabrizio Romano)
የቼልሲው አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል፡ " አርማንዶ ቦርጃ የእኛ ተጫዋች ነው፣ እና እስካሁን እሱን የመሸጥ ፍላጎት የለንም"
ዌስትሃም ለብሮጃ የ35 ሚሊየን ዩሮ ጥያቄ አቅርቧል የቼልሲን መልስ እየጠበቁ ነው።
🎖 (ምንጭ : Fabrizio Romano)
🚨አርሰናል እና ማንቺስተር ሲቲ በቃል ደረጃ ከስምምነት ደረሱ!
👉 አርሰናል እና ማንቺስተር ሲቲ በቃል ደረጃ በዚቼንኮ ዝውውር ጉዳይ በ30 ሚሊዮን ፓውንድ አካባቢ ከስምምነት ደርሰዋል።
👉 ስለ ግል ጉዳዮች አሁንም ንግግሮች ቀጥለዋል።
ፋብሪዚዮ ሮማኖ🌕
16/07/2022
አሁን ደሞ ስለ ሀገራች ዝዉዉሮች እናያለን ከናንተ ሚጠበቀዉ ፔጁን ማረግ ብቻ ነዉ
🚨 ይፋዊ !
መከላከያ ከነዓን ማርክነህን በ 2 ዓመት ኮንትራት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።
Via Soccer Ethiopia
🚨 ፋሲል ከነማ እና ሁለቱ አጥቂዎች
👉 ፋሲል ከነማ ጌታነህ ከበደን ለማስፈረም ንግግሮች እያደረገ ይገኛል። ጌታነህ ከመከላከያ ጋር ስምምነት ላይ አልደረሰም። በአሁኑ ሰአት ከፋሲል ጋር ያለው ንግግርም በጥሩ ሁኔታ ቀጥሏል።ንግግሮች ከተጠናቀቁ ምናልባትም ነገ ዝውውሩ ይፋ ይደረጋል።
👉 ሌላው ፋሲል ከነማ ማስፈረም ሚፈልገው ተጫዋች አማኑኤል ገብረሚካኤል ነው ሆኖም በዚህ ዝውውር ላይ ብዙም ገፍተው ባይሄዱም አመራሮቹ ወደ ክለባችን እናመጣዋለን እያሉ ይገኛሉ።
ዳንኤል መምሩ( ብስራት ኤፍኤም)🌕
🚨 በሀምሌ 7 እና 8 የፀደቁ ዝውውሮች እና ወሎች
👉ከተጀመረ 8ኛ ቀኑን ባስቆጠረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች የዝውውር መስኮት ከሐምሌ 7 እና 8 ከቀኑ 11 ድረስ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመገኘት ውል የፀደቀላቸው አዲስ ፈራሚዎች እንዲሁም ውል ያደሱ ነባር ተጫዋቾች ዝርዝር ከታች አንደኛ ምስሉ ላይ የምትመለከቱትን ይመስላል።
አርባምንጭ ከተማ ከመስመር ተከላካዩ ጋር በስምምነት ተለያይቷል
የአዞዎቹ የግራ መስመር ተከላካይ ከክለቡ ጋር ቀሪ አንድ ዓመት እያለው በስምምነት ተለያይቷል።
ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ከከፍተኛ ሊጉ በመነሳት ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲገባ ካስቻሉ ተጫዋች መካከል የግራ መስመር ተከላካዩ ተካልኝ ደጀኔ ይጠቀሳል፡፡ ላለፉት አምስት ዓመታት በክለቡ ቆይታ የነበረው የቀድሞው የደደቢት እና የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች በአዞዎቹ ቤት ቀሪ የአንድ ዓመት ውል የነበረው ቢሆንም ለክለቡ ባስገባው የልቀቁኝ ደብዳቤ መነሻነት በጋራ ስምምነት ከክለቡ ጋር መለያየቱ ታውቋል፡፡
ተጫዋቹም ቀጣይ ማረፊያውን ለማግኘት ስለመቃረቡ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Via Soccer Ethiopia
ሲዳማ ቡና አማካይ ክፍሉን በማጠናከሩ ገፍቶበታል
ከአቤል እንዳለ በመቀጠል በኢትዮጵያ ቡና የምናውቀው ሌላኛው አማካይ ወደ ሲዳማ ቡና አምርቷል።
ዘንድሮ ሊጉን በደረጃ ሰንጠረዡ ሦስተኛ ላይ ተቀምጦ ያጠናቀቀው ሲዳማ ቡና እንዳለ ከበደ እና ሙሉቀን አዲሱን እንዲሁም ደግሞ ከሰዓታት በፊት አቤል እንዳለን አዳዲስ ተጫዋቾች አድርጎ ማስፈረሙ ይታወሳል፡፡ አመሻሹን ደግሞ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹን ዊሊያም ሰለሞንን አራተኛ ፈራሚው አድርጎታል፡፡
በኢትዮጵያ ወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ መነሻውን ያደረገው እና በመከላከያ እንዲሁም ያለፉትን ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ ቡና በመጫወት ያሳለፈው አማካዩ በኢትዮጵያ ቡና ቤት የሚያቆይ ውል ቢኖረውም ከሰሞኑ በስምምነት ከተለያየ በኋላ ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ማረፊያውን ሲዳማ ቡና አድርጓል።
Via Soccer Ethiopia
15/07/2022
🚨 𝐇𝐄𝐑𝐄 𝐖𝐄 𝐆𝐎! ዲጄድ ስፔንስ ወደ ቶተንሃም!
ቶተንሃም የዲጄድ ስፔንስን ስምምነት ሊያጠናቅቅ ነው። የአምስት አመት ውል ይፈራረማል፣ የህክምና ምርመራዎች ተዘጋጅተዋል - አሁን የተወያዩበት የመጨረሻ ዝርዝሮች እና ኮንትራቶች እየተዘጋጁ ነው።
ክፍያ £12.5m እና ተጨማሪ ይሆናል፣ አጠቃላይ ክፍያ ከ £20m በታች ይሆናል።
🎖 (ምንጭ : Fabrizio Romano)
ካሊዱ ኩሊባሊ የቼልሲ ተጫዋች ተብሎ ሊቆጠር ይችላል። ሁሉም ነገር ተጠናቅቋል።🔵
▫️ ውል ተፈራርሟል፣ የአራት አመት ውል + ለቀጣይ የውድድር ዘመን ከማራዘሚያ አማራጭ ጋር።
▫️ በናፖሊ እና በቼልሲ መካከል የሚፈረሙ ሰነዶች በሙሉ ተጠናቀዋል ለዝውውሩም €40m ተከፍሏል።
▫️ ሜዲካል በተሳካ ሁኔታ በለንደን ተጠናቀቀ አሁን ቡድኑን ለመቀላቀል ወደ ሎስ አንጀለስ ይሄዳል።🛩
🎖 (ምንጭ : Fabrizio Romano)
ማንቸስተር ሲቲ አሁንም ማርክ ኩኩሬላን ይፈልጋል። ፣ ምንም ለውጦች የሉም -
ኦሌክሳንደር ዚንቼንኮ አርሰናልን ከተቀላቀለ ሲቲዎች ኩኩሬላን ለማስፈረም ንግግሮቹን ወደ አስፈላጊ ደረጃዎች ይወስዳሉ።
ሲቲ ዚንቼንኮን በዚህ ክረምት ለመልቀቅ ክፍት ነው።
መድፈኞቹ በዚንቼንኮ ስምምነት ላይ እየሰሩ ነው። ይህ ካልተሳካላቸው የአንደርሌክቱን ተጫዋች ሰርጂዮ ጎሜዝ የመጠባበቂያ አማራጭ አድርገዋል ።
🎖 (ምንጭ : Fabrizio Romano)
ናታን አኬ አይሸጥም !
ማንችስተር ሲቲዎች በቼልሲ ሲፈለግ የቆየውን የመሐል ተከላካያቸው ናታን አኬን እንደማይሸጡት ተገልጿል ።
ሲቲዎች የ 27 ዓመቱን ተከላካያቸውን ናታን አኬ ትክክለኛ የዝውውር ሂሳብ ከቀረበላቸውን ለመሸጥ ፍላጎቱ እንደነበራቸው ሲገለፅ ቢቆይም አሁን ላይ በክለቡ እንደሚቆይ ይፋ ሆኗል ።
ናታን አኬ እና ማንችስተር ሲቲዎች ካደረጉት ንግግር በኋላ በኢቲሀድ እንዲቆይ ከስምምነት መደረሱ ታውቋል ።
ባየር ሙኒክ ተጫዋቹን ለማቆየት ተስማማ !
በአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች በጥብቅ ሲፈለግ የነበረው የባየር ሙኒኩ የፊት መስመር ተጫዋች ሰርጂ ናብሪ ኮንትራቱን ለማራዘም መስማማቱ ተገልጿል ።
ናብሪ አዲሱ ኮንትራቱን በይፋ በመጪው ቀናት እንደሚፈራረም ሲጠበቅ ለረጅም ጊዜ በክለቡ እንደሚቆይ ይጠበቃል ።
ናብሪ ከአምስት አመታት በፊት ሙኒኮችን ሲቀላቀል 63 ጎሎችን አስቆጥሮ አራት የቡንደስሊጋ ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችሏል ።
ጄሲ ሊንጋርድ በሚቀጥለው ሳምንት ውሳኔውን ያሳውቃል።
እንግሊዛዊው አማካይ ወደ MLS አይሄድም ነገር ግን ከሳዑዲ ሊግ በዓመት 10 ሚሊዮን ፓውንድ ደሞዝ የሚያስገኝለትን የኮንትራት ጥያቄ እያሰበ ነው።
የ29 አመቱ ተጫዋች ቅድሚያ የሚሰጠው በፕሪምየር ሊግ መቆየት ነው፣ ከፕሪምየር ሊግ ሶስት ክለቦች ጥያቄ አቅርበውታል ነገርግን የሳዑዲ ጥያቄ ለሊንጋርድ እንደ ከባድ አማራጭ ይቆጠራል።
ምንጭ ፦ David Orenstein
የሳካ አዲስ ኮንትራት
የሳካን ኮንትራት ማራዘም አርሰናል ሁልጊዜም ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ ሲሆን ሙሉ ስምምነት ላይ ለመድረስ ከወኪሉ ጋር የሚደረገው ድርድር አሁንም ቀጥሏል።
ሳካ በአርሰናል ፕሮጀክት ደስተኛ ነው እናም አሁን የደመወዝ ዝርዝሮች ላይ እየተወያዩ ነው።
🎖 (ምንጭ : Fabrizio Romano)