25/05/2026
✅የስፔን ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻው የአለም ዋንጫ ሙሉ ስብስብ!!!
ባርሳ 8 ተጫዋቾችን አስመርጧል!!
➖ነጭ የለበሰ አለ ከመሃላቸው? ፈልጉልኝ እስቲ አልታይ አለኝ!
የስፔን እግርኳስ የጀርባ አጥንት ማን እንደሆነ ቀድመን እናውቃለን!!!
አፍሮ የሚለውን ቃል ከአፍሪካዊ ቅፅል የተዋስን ሲሆን ፔጁ በስፔን የባርሴሎና ክለብ ደጋፊዎች ማህበር (ፔንያ) እውቅና ያለው የአፍሮ ባርሳ ደጋፊዎች ልሳን ነው
25/05/2026
✅የስፔን ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻው የአለም ዋንጫ ሙሉ ስብስብ!!!
ባርሳ 8 ተጫዋቾችን አስመርጧል!!
➖ነጭ የለበሰ አለ ከመሃላቸው? ፈልጉልኝ እስቲ አልታይ አለኝ!
የስፔን እግርኳስ የጀርባ አጥንት ማን እንደሆነ ቀድመን እናውቃለን!!!
21/05/2026
የማጥቃቱን ክፍል ማን ይሸፍነው!!?
-ውድ የአፍሮ ቤተሰቦች ከዚህ ቀደም ባርሳ በዚህኛው የዝውውር መስኮት ምን ለመስራት እንዳቀደ በሁለት ተከታታይ ክፍል አቅርበንላችሁ ነበር።
እነሆ አሁን ደግሞ የመጨረሻውን ክፍል እንደሚከተለው አሰናድተንላችኋል።
-በባለፈው ፅሁፋችን አጠቃላይ ተሰናባች ተጫዋቾቻችንንን ስናነሳ ከአጥቂ ክፍል ሩኒ፣ራሽፎርድ እንዲሁም እርግጥ የሆነውን የሌቫን መውጣት አንስተንላችሁ ነበር።
-አሁን በዚህኛው ሳምንት እንደሚሰሙ ዜናዎች ከሆነ ደግሞ ራሽፎርድ በባርሳ ከፍተኛ የሆነውን የደሞዝ ቅነሳ በማድረግ ለመቆየት እንደተስማማ እና ባርሳም ዝውውሩን ቋሚ ለማድረግ ከማንችስተር ጋር ንግግር መጀመሩን እየተጠቆመ ይገኛል።
እኔ በግል የዚህ ዝውውር በከፍተኛ ደረጃ ከሚቃወሙት ውስጥ ነኝ።
➖i know ቁጥሮች ለሱ እንደሚያደሉ ነገር ግን እመኑኝ ራሽፎርድ ልክ ጥሩ ቁጥር እንዳለው ሁሉ በተቃራኒውም ደግሞ በሱ ምክንያት የጎደሉን ነገራቶች ይበዛሉ።ያው አሁንም ደግሜ ስለዚህ ትንተና መናገር አልፈልግም።በቀደመ ፅሁፎቼ ላይ ስላብራራሁት
-የሩኒን ጉዳይ እንዲሁ ለመወሰን ይከብዳል።
ምክንያቱም ላሚን ስላለ ይሸጥ አሊያም በውሰት ይሰጥ ቢባል እንኳን ላሚን በማይኖርበት ግዜስ የሚለው ጥያቄን ያጭራል!!ለዚህም ነው ባርሳ በቶሎ ልጁን በውሰት ለመስጠት እና የመጫወቻ እድል እንዲሁም እራሱን የሚያጎለብትበት አማራጭን እንዲያይ ያላደረገው።
-የልጁ ፀባይም ትንሽ ለአሰልጣኝ አባላቶች ሳይከብድ የቀረ አይመስልም።በቅርቡ ሩኒ ከ አለም ዋንጫው ስብስብ ውጭ ሲሆን ዋና አሰልጣኙ ግራሃም ፖተር ያቀረቡት ምክንያት ምናልባት በባርሳም መልበሻ ክፍል ውስጥም ይህ ሳይኖር እንዳልቀረ እየተነገረ ይገኛል።
----- አሁን ጥያቄው" በነሱ ምትክ ማን ይምጣ" ?የሚለው ወይም ደግሞ ባርሳ በእርግጥ የሚፈልገው ተጫዋች ምን አይነት እና ማን ነው? የሚለውን አብረን ለማየት እንሞክር!!!
✅"9"ቁጥር
-ከሌቫ መውጣት በኋላ ባርሳ ወደ ገበያው እንደሚወጣ ጥርጥር የለውም።ግን ገበያ ላይ እውን እንደ ሌቫ አይነት classic 9 ቁጥር አለ??
1.ሃሪ ኬን
-እኔ የእድሜው ጉዳይ ባይሆን ኖሮ ባርሳ ቀጥታ ሃሪ ኬንን ቢያመጣ ምሬጫዬ ነው።ነገር ግን እድሜውን ስመለከት ይህ ፈፅሞ እንዳይሆን የምመርጠው ነው።
2.ቪክቶር ኦሲሜን
-literally speaking ፍሊክ ለሚፈልገው pressing የሚመች ትክክለኛ ምርጫ ይመስላል።
ጎል ማግባት ላይም አይታማም።
በቱርክ ሊግ እና በጋላታሳራይ እንዲሁም ቀድሞ በናፖሊ ይህንን በሚገባ አሳይቷል።
ነገር ግን ኦሲሜንን አንድ የማይለቀው ችግር አለበት።እሱም ፀባዩ ነው። " egoistic " ነው።
በቡድን አጋሮቹ ላይ ቃላቶችን ከመሰንዘር ወደ ኋላ አይልም።
-ብዙ የግል ነገሮችን ማሳካት የሚመኝ ተጫዋች መሆኑ እኔ አልወደድኩለትም።ምክንያቱም ለላሚን ከፍቸኛ የሆነ ቀውስ ስለሚፈጥርበት።እንደ ኦሲሜን አይነት ተጫዋች መጥቶ የቡድኑ ቁጥር 1 ለመሆን ከሚታትር ተጫዋች ጋር ላሚንን አሰልፎ ማጫወት ቡድኑን መግ-ደ-ል ነው።
3.ዩሊያን አልቫሬዝ
-የባርሳ የክረምት ሙሉ ወሬው የሆነ ተጫዋች።
personally እኔ አደንቀዋለው።
ነገር ግን እመኑኝ አስረግጬ የምነግራችሁ ነገር ቢኖር ባርሳ የሚፈልገው አይነት ተጫዋች አይደለም።
-ምናልባት ተሳስቼ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ባርሳ የሚፈልገው አይነት ተጫዋች መሆኑን እጠራጠራለው።
-ምናልባት በአትሌቲ አጨዋወት ምክንያት ሚናው ጎልቶ አልወጣብኝም ይሆናል።
ነገር ግን ወጥነቱን እጠራጠራለው።ብልጭ ድርግም አይነት performance ይበዛዋል።
+ ለተጫዋቹ የሚጠየቀው ፍፁም የተጋነነ ሂሳብ ልጁ ወደ ባርሳ ከመምጣቱ ይልቅ ጎንካሎ ራሞስ አንዱ የዝውውሩ operation በመሆን ወደ psg የማምራት ከፍተኛ እድል እንዳለው እየተዘገበ ይገኛል።
-➖➖ምናልባት ፍሊክ የአጥቂ መስመር fluidityን መተግበርን አዲሱ እቅዳቸው ካደረጉ ልጁ ሁነኛ መፍትሄና የprojectኡ መሳካት ዋነኛ ቁልፍ ሊሆን ይችላል።
4.ካርሎስ ኤስፒ
-ግዙፉና የሌቫንቴ የዘንድሮ የላሊጋ ክስተት ካርሎስ ኤስፒ ሌላኛው radar ውስጥ የገባ ልጅ ነው።
-አጨራረስ ፣ቦታ አያያዝ፣የግንባር ኳስ አጠቃቀም ላይ በብዙ መንገድ ጥሩ የሆነ ልጅ ነው።
ምናልባት ተክለ ሰውነቱን አይተን ቅልጥፍና ይጎድለዋል ልንል እንችላለን ።ነገር ተጫዋቹ ሊጉ ላይ በሚታይ መልኩ መድመቁ ይህንን ስጋት ፉርሽ ያደርግብናል።
ያውም ላለመውረድ እየተጫወተ በሚገኘው ሌቫንቴ 10 ግብ ማስቆጠር መቻል ትልቅ ነው።
i know ሌቫንቴዎች ከሚፈጥሩት የግብ እድል አንፃር ምንም ላይመስለን ይችል ይሆናል ነገር ግን ልጁ የሆነ እይታን ይፈልጋል።
የኔም ምርጫ እሱ ነው!!!!!
✅ የግራ መስመር ተጫዋች
➖በዚህ መስመር ላይ ከራፊንሃ ውጭ ብዙዎቻችሁ ማሰብ እንደማትፈልጉ አውቃለሁኝ።ነገር ግን ከየትኛው ስፍራ በላይ በዚህ ስፍራ ላይ ተጫዋች ያስፈልናል።
በምንም ተኣምር በራሽፎርድና በራፊንሃ ላይ ብቻ ተመርኩዘን ድልን መጠበቅ አይታሰብም።
-እኔ በግል ብዙ በዚህ መስመር ላይ ተጫዋቾቹን እንዲሁ ለማጥናት ሞክሪያለሁኝ።
ነገር ግን አሁን ላይ በዚህ መስመር የሚጫወቱ ተጫዋቾቹን በብዛት እና በጥራት ማግኘት አይታሰብም።
ጥቂት የሚገኙትም ትልልቅ ክለቦቹ የሚለቋቸው ተጫዋቾች አይደሉም።
✔️ሆኖሞ ግን ባርሳ በዚህ መስመር ተጫዋች ካስፈረመ መሆን ያለበት ሚካ ሆት'ስ ነው።
ይህ ቤልጄማዊ እያሳየ ያለው አቋም እጅግ የሚገርም እና ባርሳ ለሚጠይቀው አጫዋወት ሁነኛ መፍትሄ ነው።
አያክስ ላይ ሳይሆን ኤሬዲቪሲው ላይ ገኖ ወጥቷል።
ፍጥነት ፣ቅልጥፍና ፣ብልሃት፣አጨራረስ ሁሉንም ያሟላ ድንቅ ወጣት ነው።
i hope የባርሳ scoutኧች አይናቸውን እንደሚጥሉበት።
ከዚህ ተጫዋች ውጭ አሁን ላይ ለባርሳ ይሆናል የምለው የለም።
ስለዚህ አጠቃላይ ባርሳ ቢያስፈርማቸው ትልቅ ለውጥ ይመጣል የምልባቸው በእስካሁኑ ፅሁፎቼ ሲጠቃለል፦
1. አሌክስ ሬሚሮ
2.ቩስኮቪች
3.አንድሬ ራትዩ
4.ካርሎስ ኤስፒ
5.ሚካ ሆት'ስ
ከላይ የዘረዘርኳቸው ተጫዋቾች በሙሉ በየሊጎቻቸው ብቃታቸውን ያስመሰከሩ ተጫዋቾች ናቸው።
ከዛ የበለጠ ጥቅሙ ደግሞ ወጣት መሆናቸው እና ብዙ ለመማሪያ ግዜ እንዲኖራቸው መሆኑ ጥቅኑ ሰፍ ነው።
የውል ማፍረሻቸውም እጅግ ሲበዛ አነስተኛ ነው።
-አጠቃላይ ሁሉም ተደምረው ከ80-100m€ ብቻ ቢያስወጡ ነው።
i don't think ከነዚህ ውጭ ለባርሳ fit ይሆናሉ የምላቸው ተጫዋቾች መኖራቸው።
so ባርሳ እነዚህን ተጫዋች የግሉ ቢያደርግ ትርፋማ ይሆናል።
እናንተስ ምን ትላላችሁ??
20/05/2026
✅ባርሳ ከኢማራቱ ኢስላሚክ ባንክ ጋር የስፖንሰርሺፕ ውል ተፈራርሟል።
✔️ በተያያዘ ዜናም ባርሳ ወደ የ1:1 ደንብ መመለሱን ብዙ የስፔን መገናኛ ብዙሃን በመናገር ላይ ይገኛሉ
17/05/2026
እሱ ሌቫ ነው።
በሁሉም የተወደደ !!!
ለክለቡ ያለውን በሙሉ የሰጠ!!!
ስለሱ እንመለስበታለን
ነገር ግን በመጨረሻ ላይ ባደረገው ንግግር ፅሁፌን ልቋጭ" ለስቴድየሙ ብሰናበትም፣ ልቤ እዚህ ለዘላለሙ ይኖራል"!!!!!!!!
17/05/2026
ሌቫቫቫቫ
ይከብዳል ከምር
17/05/2026
ጨዋታው በባርሳ 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
17/05/2026
ተመልከቱልኝማ የባርሳን ደጋፊ ለሌቫ ያለውን ውዴታ በየደቂቃው ሲያወሳ👏👏👏
17/05/2026
WOW CANCELO👏👏🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
አጥቂ እንበልህ ወይስ የመስመር ተከላካይ??
what a goal
3-1
17/05/2026
ሩኒ እና አራውኾ ኸደ ሜዳ ገብተዋል
ራፋ እና ኤ.ጋርሲያ ተቀይረው ወጥተዋል
17/05/2026
ራፋፋፋፋፋፋ ደገመው
2-0
17/05/2026
የመጀመሪያ አጋማሹን እንዴት ተመለካታችሁት??