Selman Arsenal-አርሰናል

Selman Arsenal-አርሰናል

Share

አርሰናልን የተመለከተ መረጃ በስፋትና በፍጥነት እናደርሳለን

Photos from Selman Arsenal-አርሰናል's post 10/03/2026

ነገ በሻንፒየንስ ሊጉ ከሜዳ ውጪ ከባየርሊቨርኩሰን ጋር ለምናደርገው ጨዋታ ዛሬ የአርሰናል ተጨዋቾች ልምምዳቸውን በሚያምር መልኩ ጥርስ በጥርስ ሆነው አከናውነዋል።

ትሮሳርድ እና ካላፊዮር በኤፍኤካፑ በጉዳት ተቀይረው የወጡ የነበረ ቢሆንም ዛሬ ከቡድኑ ጋር ልምምዳቸውን በሚገባ አከናውነዋል፣ ዊልያም ሳሊባም ገጥሞት ከነበረው የቁርጭምጭሚት ህመም ሙሉ በሙሉ አገግሞ ትሬኒንጉን በሚገባ ሰርቷል፣ ወጣቶቹ ዶውማን እና ሳልሞን ዛሬም ከቡድኑ ጋር ልምምድ አድርገዋል።

በዛሬው ልምምድ ኦዴጋርድና ቤን ዋይት አልታዩም ከእነሱ ውጪ ያሉት በሙሉ ዝግጁ ናቸው።

09/03/2026

የኤፍኤ ካፕ የሩብ ፍፃሜ እጣ ድልድል ይፋ ተደርጓል። ከሜዳ ውጪ ቢሆንም የምንገጥመው ክለብ ሳውዝሃምፕተን ሆኗል።

በቃ ዘንድሮ የሚቀረን ዋንጫ አይኖርም

09/03/2026

የቀድሞው የአስቶንቪላው ተጨዋች ጋቢ አግቦንላሆር የአርሰናል ተጫዋቾች በሴት-ፒስ (set-pieces) አጠቃቀማቸው ላይ የሚሰነዘርባቸውን ትችት እንዴት ለተነሳሽነት እንደሚጠቀሙበትና ተቺዎቻቸውን ደግሞ እንዴት ማበሳጨት እንዳለባቸው እንዲህ በማለት ይገልፃል፦

​እኔ በአርሰናል ተጫዋቾች ቦታ ብሆን ኖሮ ሰዎችን ለማናደድ በማንኛውም በሚያገኙት ግብ ተጫዋቾች በሙሉ ወደ ተጠባባቂ ወንበር (bench) እየሮጡ መፈንጠዝ አለባቸው።

​በተለይ ከሴት-ፒስ ጎል ስታገቡ አከባበራችሁን አድምቁት። አታድርጉ ለሚሏችሁ ሰዎች ደግሞ ይባስ ብላችሁ ሰዓት በማባከን አናድዷቸው።

07/03/2026

እንደምንም አሸንፈን 8ት ውስጥ ገብተናል፣ በትንሽ ክለብ ልንዋረድ ነበር። የሜዳው ነገር አይወራም ምንም ኳስ ሊያጫውታቸው አልቻለም።

ኤዜ ተቀይሮ ገብቶ ጥሩ እንቅስቃሴ አድርጎ ቆንጆ ጎል አስቆጥሮ ገላገለን እንጂ ጨዋታው በጣም አስቸጋሪ ነበር።

ጋብርኤል ጄሱስ ግን ይህ ዓመት እንዳለቀ ቻውውው የእሱ ግዜ አብቅቷል

አሁን አሳሳቢው ነገር የትሮሳርድና የካላፊዮሪ በጉዳት ተቀይሮ መውጣት ነው፣ ጉዳታቸው ምን ያህል እንደሆነ ገና አልታወቀም

07/03/2026

ማንስፊልድን የሚገጥመው አሰላለፍ

ዶውማን እና ማርሊ ሳልማን አሰላለፍ ውስጥ ገብተዋል

07/03/2026

ዛሬ 9:15 ላይ በ5ኛው ዙር የኤፍኤካፕ ዋንጫ ጨዋታ ከሜዳ ውጪ ተጉዘን በሊግ 1 ከሚጫወተው ማንስፊልድ ታውን ጋር እንጫወታለን። ይህ ክለብ 24 ክለቦች በሚፋለሙበት ሊግ 1 ላይ 41 ነጥብ ሰብስቦ 16ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ባለፈው ዙር ከሜዳቸው ውጪ ተጉዘው በፕሪሜርሊጉ የሚጫወተውን በርንሌይን 2:1 አሸንፈው ወደ ቀጣይ ዙር ያለፉ ቢሆንም ከዛ በኋላ በሊጉ ካደረጓቸው 4 ጨዋታዎች አንዱንም አላሸነፉም 2ቱን ተሸንፈው 2ቱን አቻ ተለያይተዋል።

አርሰናል ዛሬ ብዙ ተቀያሪ ተጨዋቾችን እንደሚጠቀም ይጠበቃል፣ ሆኖም ይህን ጨዋታ በቀላሉ ብዙ ጎል አስቆጥሮ በማሸነፍ ወደ ቀጣይ ዙር እንደሚያልፍ ይጠበቃል።

06/03/2026

አርሰናል ላለፉት 22ዓመታት የፕሪሜርሊጉን ዋንጫ ማሳካት አልቻለም፣ ባለፉት 3 ዓመታት ደግሞ የዋንጫውን አንድ ጆሮ ከያዘ በኋላ በሚያሳዝን ሁኔታ ከዋንጫው ጋር መገናኘት አልቻለም። አርሰናል በእንግሊዝ ምድር የነበረውን አሰልቺ የሆነውን የአጨዋወት ባህል በአርሰን ዌንገር አማካኝነት በመቀየር እስካሁን የአርሰናል ደጋፊዎች ብቻ ሳይሆን የተቃራኒ ክለብ ደጋፊዎች ጭምር በአጨዋወቱ የሚዝናኑበት ክለብ ነው።

እሄን ሁሉ ዓመት በቶታል ፉትቦል ሲያዝናና የቆየውን ክለብ አሁን ላይ አርሰናል አሰልቺ የሆነ አጨዋወት ነው የሚጫወተው እያሉ ብዙ ኳስ አላዋቂዎች ሲዘላብዱ ይታያል፣ በተለይ የማንቺስተር የቀድሞ ተጨዋቾች ቀንድ ማብቀል ነው የቀራቸው።

አሁን ላይ ለአርሰናል የሚያስፈልገው ዋንጫ እንጂ በጨዋታ ሰውን ማዝናናት አይደለም እሱንማ ስንት ዓመት አሳየን ግን ዋንጫ አላመጣልንም፣ አሁንም ቢሆን አርሰናል ከፈለገ ኳስ መጫወት በጣም ቀላል ነገር ነው፣ ስለዚህ አርሰናል አላማው አንድና አንድ ነው እሱም በየትኛውም መንገድ ውጤት ይዞ መውጣትና ከዋንጫ ጋር መታረቅ።

የቀሩትን 8 ጨዋታዎች አሸንፈን ዋንጫውን የግላችን ማድረጋችን የግድ ነው፣ እኔ ስለ አጨዋወታችን አይጨንቀኝም ውጤት እስካስጠበቅን ድረስ ለምን ምትትር ከበረኛ እስከ በረኛ ኳስ እየጠለዙ 90 ደቂቃው አያልቅም ብቻ ጎል አስቆጥረው 3 ነጥብ ያምጡልኝ።

በመጨረሻም እኛን ለምትተቹ ከፈለጋችሁ ገመድ እናቀብላቹሃለን መታነቅ ትችላላችሁ ለናንተ ወሬ ቦታ የለንም እሄን ያልኩት በጣም ስላበዛችሁት ነው

እኛ መድፈኞች ነን(We Are Arsenal)

04/03/2026

ሲጀመር እንቅልፍ ምን ያደርጋል እንደዚህ አይነት ደስታ እያለ

ዊልያም ኦሱላ ምንድነው ያደረግከው ፣ በጎዶሎ የተጫወተው ኒውካስትል አቻ እራሱ እኮ ትልቅ ውጤት ነበር፣ ነገር ግን ተቀይሮ የገባው ኦሱላ በረኛውን አቁሞ ባናና ሹት ድንቅ ጎል በ90ኛው ደቂቃ አስቆጥሮ አፋቸውን አዘጋቸው። የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች ማለት አሁን ነው፣ እነሱ እዚህ ለብራይተን እየቋጠሩ ኒውካስትሎች ስጥት ••••••••

በቅርቡ ወደቦታችሁ ትመለሳላችሁ ቼልሲም እየመጣ ነው ሊቨርፑልም ይመለሳል እናንተ ግን 6ተኛን ማንም አይነካባችሁም

04/03/2026

ምን አይነት ጣፋጭ ምሽት ናት ዋው ዋው ዋው ፣ አርሰናል እንደ ዛሬ ugly(አስቀያሚ) ጨዋታ ሲጫወት በዚህ ዓመት አይቼው አላውቅም፣ ነገር ግን ውጤት አስጠብቆ መውጣቱ እውነትም የዋንጫ ቲም መሆኑን አስመስክሯል።
ውድ የሆነች 3 ነጥብ ይዘን ተመልሰናል

በአንፃሩ ሲቲ ውድ የሆኑ 2 ነጥቦችን በሜዳውና በደጋፊው ፊት ላለመውረድ በሚታገለው ኖቲንግሃም ጥሏል፣ አሁን ነጥቡ በ 7 ልዩነት ሆኗል ምንም እንኳን ሲቲ 1 ጨዋታ ያነሰ ቢጫወትም

ዛሬ የብዙዎችን ጨጓራ አቃጥለናል፣ አሁንስ ዋንጫውን እንደምንበላ አላመናችሁም ወይ?

04/03/2026

አርቴታ ስለ ዊሊያም ሳሊባ ከቡድኑ ውጭ መሆን ሲናገር እንዲህ ብሏል፦

​ከቼልሲ ጋር በነበረን ጨዋታ ቁርጭምጭሚቱ ታጥፎ (ተመትቶ) ነበር። እንደምንም ጨዋታውን መጨረስ ችሎ ነበር፣ ነገር ግን ዛሬ ለመሰለፍ በጣም ህመም ስለነበረው ሊጫወት አልቻለም።

04/03/2026

ብራይተንን የሚገጥመው አሰላለፍ

ማክስ ዶውማን ቤንች ላይ አለ

01/03/2026

የአፍሪካውያን ቀልድ ይመቸኛል፣ ይሄ ከዛሬው ጨዋታ በኋላ ከተፃፈ ፖስት ስር አንዱ የአርሰናል ደጋፊ ፅፎት ያገኘሁት ኮሜንት ነው
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

የአርሰናል ተልዕኮ ግልጽና ቀጥተኛ ነበር ይላል። ወይ አርሰናል ቼልሲን ያሸንፋል፣ ወይም ቼልሲ በአርሰናል ይሸነፋል። ያም ሆነ ይህ ቼልሲ ያለቅሳል፣ ለንደንም በአርሰናል ቀይ ትደምቃለች!

​አማራጩ ሁለት ብቻ ነው፤ አርሰናል ማሸነፍ ወይም ቼልሲ መሸነፍ። ውጤቱ ግን አንድ ነው ቼልሲ ማልቀሱ አይቀርም

በነገራችን ላይ ሚኬል አርቴታ እንደ ቼልሲ ብዙ ግዜ ያሸነፈው ክለብ የለም፣ 11 ግዜ ቼላውን ሃንግ ማድረግ ችሏል።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

00
Addis Ababa