ሊቨርፑል አርማውን ዝቅ አድርጓል !
የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የዲያጎ ጆታን ህልፈት ተከትሎ በክለቡ ውስጥ የሚገኘው አርማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አድርጓል።
ደጋፊዎቹ በበኩላቸው ከአንፊል ስታዲየም አቅራቢያ አበባ በማስቀመጥ በተጫዋቹ ህልፈት ሀዘናቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።
የሊቨርፑል ተጨዋቾች እንዲሁ ሀዘናቸውን ሲገገልፁ ዳርዊን ኑኔዝ “ የተሰማኝን ህመም የምገልፅበት ቃል የለኝም “ ብሏል።
ዳርዊን ኑኔዝ አክሎም " ሁልጊዜም ከፈገግታህ ጋር አስታውስሀለሁ ምርጥ የቡድን አጋር ነበርክ።“ ብሏል።
የፖርቹጋሉ ክለብ ፖርቶ በተመሳሳይ በክለቡ አርማው ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ በማድረግ ሀዘናቸውን እየገለፁ ነው።
Askuala sport
እንኳን ወደ አስኳላ ስፖርት ደህና መጡ ይህ ቻናል የእግር ኳስ እና ተዛማጅ የስፖርት እንዲሁም የተጫዋች ታሪክ የዝውውር እና ተዛማጅ ዜናዎች ወደናንተ ያደርሳል
28/10/2024
አንቶኒዮ ሩዲገር ጉዳት አላጋጠመውም !
ጀርመናዊው የሪያል ማድሪድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አንቶኒዮ ሩዲገር በተደረገለት ምርመራ ጉዳት እንዳላጋጠመው መረጋገጡ ተገልጿል።
አንቶኒዮ ሩዲገር ሪያል ማድሪድ ከባርሴሎና ባደረጉት ጨዋታ የጉዳት ስሜት እንዳለው ተገልጾ ነበር።
ተጨዋቹ በቀጣይ ሎስ ብላንኮዎቹ ከቫሌንሽያ ጋር በሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታ መሰለፉ በሚሮረው ስሜት ላይ የተመረኮዘ እንደሚሆን ተገልጿል።
"SHARE"
28/10/2024
“ ለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ “ ብሩኖ ፈርናንዴዝ
የማንችስተር ዩናይትዱ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የስንብት መልዕክቱን አስተላልፏል።
“ ለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ “ ሲል መልዕክቱን ያስተላለፈው ፈርናንዴዝ የተጋራናቸውን ጊዜያት አደንቃለሁ መልካሙን እመኝልሃለሁ ሲል ተናግሯል።
ብሩኖ ፈርናንዴዝ አክሎም ቡድኑ በጥሩ ሁኔታ ላይ ባይገኝም የክለቡ ደጋፊዎች ኤሪክ ቴንሀግ ለክለቡ የሰሯቸውን ጥሩ ነገሮች እንዲያቆዩ ጠይቋል።
የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን ስንብት ያወቁት ክለቡ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ ሲያደርገው መሆኑ ተገልጿል።
"SHARE"
28/10/2024
ቴንሀግ የመጀመሪያ ተሰናባች አሰልጣኝ ሆነዋል !
አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ከማንችስተር ዩናይትድ ሀላፊነት መሰናበታቸውን በክለቡ ዛሬ ጠዋት እንደተነገራቸው ተገልጿል።
ኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በዘንድሮው የውድድር አመቱ የፕርሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ተሰናባች አሰልጣኝ ሆነዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ አዲስ አሰልጣኝ በቋሚነት እስከሚቀጥር ሩድ ቫን ኔስትሮይ ከሌሎች አባላት ጋር ቡድኑን እንዲመራ እንደተጠየቀ ተገልጿል።
አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ማንችስተር ዩናይትድን ከተረከቡ ወዲህ ለዝውውር 650 ሚልዮን ዩሮ ማውጣታቸው ተነግሯል።
አሰልጣኙ በክለቡ ቆይታቸው የኤፌ ካፕ እና ሊግ ካፕ ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችለዋል።
አሰልጣኙ ቡድኑን በመሩባቸው አመታት
- በ 2022/23 #ሶስተኛ
- በ 2023/24 #ስምንተኛ ( በክለቡ ታሪክ አስከፊ ደረጃ ) ደረጃዎችን ይዘው አጠናቀዋል።
በዘንድሮው የውድድር ዘመን ከዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች በኋላ አስራ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው ይገኛሉ።
"SHARE"
28/10/2024
ኤሪክ ቴንሀግ ከማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝነት በይፋ ተሰናብቷል
[FABRIZIO ROMANO]
"SHARE"
27/10/2024
አርሰናል ከሊቨርፑል ነጥብ ተጋርተዋል !
በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ከሊቨርፑል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።
የአርሰናልን ግብ ቡካዩ ሳካ እና ሚኬል ሜሪኖ ሲያስቆጥሩ ለሊቨርፑል ቨርጅል ቫን ዳይክ እና መሐመድ ሳላህ ከመረብ አሳርፈዋል።
ግብፃዊው የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ ከአርሰናል ጋር ባደረጋቸው አስራ አምስት የሊግ ጨዋታዎች አስራ አንድ ግቦችን አስቆጥሯል።
በሊጉ ስንተኛ ደረጃ ላይ ናቸው ?
2️⃣ ሊቨርፑል :- 22 ነጥብ
3️⃣ አርሰናል :- 18 ነጥብ
ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?
ቅዳሜ - ሊቨርፑል ከ ብራይተን
ቅዳሜ - ኒውካስል ዩናይትድ ከ አርሰናል
"SHARE"
26/10/2024
ሀሪ ክላርክ በታሪክ ሁለተኛው ተጨዋች ሆኗል !
ኢፕስዊች ታውን በብራንትፎርድ 4ለ3 በተሸነፈበት ጨዋታ የቀኝ መስመር ተከላካዩ ሀሪ ክላርክ በታሪክ ሁለተኛው ተጨዋች ሆኗል።
ተጨዋቹ በጨዋታው ላይ በራሱ ላይ ግብ ሲያስቆጥር እንዲሁም በቡድኑ ላይ ፍፁም ቅጣት ምት እንዲሰጥ ምክንያት ሆኖ በቀይ ካርድ ከሜዳም ወጥቷል።
ይህንንም ተከትሎ ሀሪ ክላርክ በአንድ ጨዋታ በራሱ ላይ አስቆጥሮ ፣ ፍፁም ቅጣት ምት አሰጥቶ ቀይ ካርድ የተመለከተ በታሪክ ሁለተኛው ተጨዋች ሆኗል።
"SHARE"
26/10/2024
የሽኝት መርሐግብር!...
የታላቁ የእግር ኳስ ሰው አሥራት ኃይሌ የሽኝት መርሐ ግብር ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል።
በትናንትናው ዕለት ህልፈተ ህይወታቸው የተሰማው የቀድሞ ተጫዋች እና አሰልጣኝ አሥራት ኃይሌ ሥርዓተ ቀብር ነገ ይካሄዳል።
ቦሌ ከሚገኘው መኖርያ ቤት 5:00 ላይ በመነሳት ከ6:00-7:00 ታሪክ በሰሩበት አዲስ አበባ ስታዲየም የሽኝት መርሐ ግብር የሚከናወን ሲሆን በመቀጠል 7:00 ላይ ለገሀር በሚገኘው መድሀኔዓለም የካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን የፀሎት መርሐ ግብር ተከናውኖ ሥርዓተ ቀብራቸው ከቀኑ 9:00 በጴጥሮስ ጳውሎስ መካነ መቃብር ይካሄዳል።
መላው የስፖርት አፍቃሪም የሀገር ባለውለታው አሥራት ኃይሌ የሽኝት መርሐ ግብር እና ሥርዓተ ቀብር ላይ እንዲገኝ ጥሪ ቀርቧል።
አስተባባሪ ኮሚቴው
Via ድሬ ቲዩብ
"SHARE"
26/10/2024
ማንችስተር ሲቲ የሊጉን መሪነት ተረከበ !
በዘጠነኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ሳውዝሀምፕተንን 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉ መሪ ሆነዋል።
የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግብ ኤርሊንግ ሀላንድ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጨዋች ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር ዘመኑ አስራ አንደኛ የሊግ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።
አስቶን ቪላ በበኩሉ ከበርንማውዝ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በመጨረሻ ደቂቃ ግብ አስተናግዶ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።
በሌሎች ጨዋታዎች
- ብሬንትፎርድ ኢፕስዊች ታውንን 4ለ2 ሲያሸንፍ
- ብራይተን ከዎልቭስ 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
የብራይተኑ የፊት መስመር ተጨዋች ዳኒ ዌልቤክ በውድድር ዘመኑ ባደረጋቸው ዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች ስድስት ግቦችን አስቆጥሯል።
ብርያን ምቤሞ በብሬንትፎርድ ታሪክ በሊጉ ከሀምሳ በላይ ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ የቻለ የመጀመሪያው ተጨዋች ሆኗል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
1️⃣ ማንችስተር ሲቲ :- 23 ነጥብ
3️⃣ አስቶን ቪላ :- 18 ነጥብ
5️⃣ ብራይተን :- 16 ነጥብ
ቀጣይ መርሐ ግብር ?
ቅዳሜ - በርንማውዝ ከ ማንችስተር ሲቲ
እሁድ - ቶተንሀም ከ አስቶን ቪላ
ቅዳሜ - ሊቨርፑል ከ ብራይተን
"SHARE"
26/10/2024
ናፖሊ መሪነቱን አጠናክሯል !
በዘጠነኛ ሳምንት የጣሊያን ሴርያ መርሐ ግብር ናፖሊ ከ ሊቼ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነታቸውን አጠናክረዋል።
የናፖሊን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ዲ ሎሬንዞ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
ናፖሊ በሊጉ የሰበሰባቸውን ነጥቦች ወደ ሀያ ሁለት ከፍ በማድረግ ሊጉን በአምስት ነጥቦች ልዩነት መምራት ጀምሯል።
የደረጃ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?
1⃣ ናፖሊ - 22 ነጥብ
1⃣9⃣ ሊቼ - 5 ነጥብ
ቀጣይ ጨዋታ ?
ማክሰኞ - ኤሲ ሚላን ከ ናፖሊ
ማክሰኞ - ሊቼ ከ ቬሮና
"SHARE"
26/10/2024
ማንቸስተር ዩናይትድ በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው ያለፉት 7 ጨዋታዎች ያስመዘገበው ውጤት፡-
🤝 ከክሪስታል ፓላስ 0-0 አቻ ተለያይተዋል
🤝 ከ FC Twente ጋር 1-1 አቻ ተለያይተዋል
❌ በቶተንሃም 0-3 ተሸንፏል
🤝 ከ FC ፖርቶ ጋር 3-3 አቻ ተለያይተዋል
🤝 ከአስቶን ቪላ 0-0 አቻ ተለያይተዋል
✅ ብሬንትፎርድን 2-1 አሸንፏል
🤝 ፌነርባቼን 1-1 አቻ ተለያይተዋል
1 ሽንፈት ፣ 1 ድል ፣ 5 አቻ!
"SHARE"
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
NO