Tarikua Sisay - ታሪኳ ሲሳይ

Tarikua Sisay - ታሪኳ ሲሳይ

Share

Journalist

14/06/2026

ታሪክ ሲሰራ እንዲህ ነው! 🥹❤️⚽

ትናንት ምሽት በሳን ፍራንሲስኮ ቤይ ኤሪያ ሳንታ ክላራ ስታዲዬም በተደረገ የምድብ B ሁለተኛ ጨዋታ: የ2022ቱ የአለም ዋንጫ አዘጋጇ የመካከለኛዉ ምስራቋ ሀገር ኳታር በእግር ኳስ ደረጃ እጅግ ከምትበልጣት አዉሮፓዊታ ሀገር ስዊዘርላንድ ጋር አቻ በመዉጣት ነጥብ ተጋርታ መዉጣት ችላለች። ይሄም ለኳታር በአለም ዋንጫ ታሪክ የመጀመሪያ ነጥቧ ነዉ።

​የኳታር ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ማህሙድ አቡናዳ ጨዋታው እንደተጠናቀቀ ባለበት ቁልቁል ተዘረረ! ይህ ፍጹም ስሜታዊ የነበረ ቅጽበት፣ ለአንድ ሀገር ምን ማለት እንደሆነ በትክክል ያሳያል።
​ሀገሩ ኳታር በዓለም ዋንጫ ታሪኳ የመጀመሪያውን ነጥብ ስታስመዘግብ፣ ከጀርባው የነበረው ልፋት፣ ጫና እና የህልም እውን መሆን ስሜት አሸንፎት መሬት ላይ እንዲወድቅ አድርጎታል።
​ይህ እኮ ዝም ብሎ 1 ነጥብ አይደለም፤ ይህ፦
​የማይቻል የሚመስለውን የመስበር ታሪክ ነው!
​የዓመታት ድካም ፍሬ ያፈራበት ቅጽበት ነው!
​ለአንድ ሀገር አዲስ ታሪክ የተጻፈበት ምዕራፍ ነው!

​ኳስ ከጨዋታነት በላይ የሆነው ለዚህ ነው! ለኳታር እና ለማህሙድ አቡናዳ ይሄን ታሪክ ለሰሩት የብሄራዊ ቡድኑ አባላት ፍፁም የማይረሳ የደስታ ምሽት ሆኖ አልፏል።! 🇶🇦🔥

Photos from Tarikua Sisay - ታሪኳ ሲሳይ's post 29/10/2025

“ማንበብና መጻፍ ነዉ ሱሴ፤ ሌትም ቀንም አልመርጥም፡፡ የምተኛዉ ረጅም እንቅልፍ ከአራት ሰዓት አይበልጥም፡፡ ከፍተኛ የገንዘብ አቅም ቢኖረኝ ብዬ ተመኝቼ አላዉቅም፣ ቢኖረኝ ግን በሁሉም ክልሎች ዘመናዊ ቤተ መጻሕፍት አስገነባለሁ፡፡ ‹አንብብ-አንብቢ-አንብቡ-እናንብብ› በሚል መርህ ትዉልዱን ማነጽ ተግባሬ ይሆን ነበር” #ደራሲና #ጋዜጠኛ ዘነበ ወላ🙏🏼🙏🏼🙏🏼

28/10/2025

When they ask me what’s home I said it’s “እናት”

26/10/2025

እኔምለው?

የሄደ ተወቃሽ
የጠበቀ ታጋሽ
የሄደማ አጥፊ
በዳይ ፍቅርን ገፊ
ያስኬደስ ምንድን ነው?
ትእግስት የሚያሳጣው
መቆየት እንዳይችል
እንዲሄድ ያረገው አሱስ ግን ምንድን ነው?

@ሕሊና ሽፈራው

26/10/2025

#መልሕቅ
መልሕቅ ማለት መርከብን ከማዕበልና ከወጀብ የሚታደግ የመርከቧ አለኝታ ማለት ነው። በዕብራውያን መልእክት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምእመናን መልሕቅ ተብሏል።
“ይህም ተስፋ እንደ ነፍስ መልሕቅ አለን፤ እርሱም እርግጥና ጽኑ የሆነ ወደ መጋረጃውም ውስጥ የገባ ነው፤ በዚያም ኢየሱስ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት የሆነው ስለ እኛ ቀዳሚ ሆኖ ገባ” (ዕብ. 6፡19)።

26/10/2025

“በትልቁ አስብ በትንሹ ጀምር!”
ጋሽ ዘነበ ወላ🙏🏼

25/10/2025

መፅሐፍ ላይ ያለ አንድ የሞት ፍርድ የሚጠባበቅ ፍርደኛ ገፀ ባህርይ ነበር።
ከስቅላቱ አንድ ቀን በፊት ስፖርት ይሰራል! ምን እያደረግክ ነው ቢሉት “ጤናዬን እየጠበቅሁ ነው አለ አሉ! ማምሻም እድሜ ነው!

25/10/2025

“ሆድ ድንጋይ እበላለሁ ቢል ጉሮሮ ማን ቢያሳልፍህ”😏

23/10/2025

ገንዘብን ለማግኘት ጠንካራ ሰራተኛ እና ሃቀኛ መሆን አለብህ is a complete scam.
ተብላችኋል!

22/10/2025

God uses your lowest times to create the highest version of you. Hang in there 🩷

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Addis Ababa