23/06/2025
በ6ኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታ አንዱ የስፖርት አይነት የነበረው የዊልቼር ቅርጫት ኳስ ውድድር በዛሬው እለት ፍጻሜውን አግኝቷል።
በውድድሩም በወንድም በሴትም የአዲስአበባ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ቡድን ሻምፒዩን (አሸናፊ) መሆን ችሏል። እንዲሁም አማራ ክልል በወንድ 2ኛ በሴት 3ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል። በተመሳሳይ ኦሮሚያ በሴት 2ኛ በወንድ 3ኛ ሆኖ ውድድሩን ሲያጠናቅቅ ድሬዳዋ በወንድ በሴት እንዲሁም ትግራይ በወንዶች ተሳታፊ ሆነዋል።
በወንዶች የፍጻሜ ጨዋታውን የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ክቡር አቶ አንበሳው እንየው እና የዊልቼር ቅርጫት ኳስ የስራ አስፈጻሚ አባላት ተገኝተው ውድድሩን ተመልክተዋል በመልዕክታቸውም የስራ አስፈጻሚ አባላትን አመስግነዋል ስፖርተኞቹንም አበረታተዋል።
ሰኔ 16/2017 ዓ.ም
ጅማ
21/06/2025
የዛሬ የጨዋታዎች ውጤት እና የነገ የጨዋታዎች ፕሬግራም
ከጅማ
20/06/2025
የኢትዮጵያ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ አሶሴሽን 6ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ
ሰኔ 13/ 2017 ዓ. ም ጅማ
አሶሴሽኑ 6ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በጅማ ከተማ አካሂዷል በጉባኤውም 7 ክልሎች እና 2 ከተማ መስተዳደሮች በተወካዮቻቸው ተሳታፊ ሁነዋል::
በጉባኤውም በሚከተሉተ አጀንዳዎቸ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ከተደረገ በኋላ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል
1. የፋይናንስ መመሪያ ማሻሻያ
2. የ4 አመት ስትራቴጂክ ዕቅድ
3. የሁለት አመት የፋይናንስ ሪፖርት
4. የ2017 ዓ.ም ሪፖርት
5. የ2018ዓ.ም ዕቅድ
በተጨማሪም አዳዲስ ክልሎች የአባልነት ጥያቄ አቅርበው ተቀባይነተ አግኝተዋል::
20/06/2025
Today's Game Result and Tomorrow Program!!
19/06/2025
6ኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታ የዊልቼር ቅርጫት ኳስ ውድድር የዛሬ ውጤት እና ቀጣይ ፕሮግራም
19/06/2025
በ6ኛው የኢትዮጵያ መላ ጨዋታዎች ላይ የዊልቼር ቅርጫትኳስ ውድድር አንዱ ሆኖ እየተካሄደ ይገኛል።
6ኛው የኢትዮጵያ መላ ጨዋታ በጅማ ከተማ በርካታ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣የስፖርት ቤተሰቦች እና ስፖርተኞች በተገኙበት ሰኔ 10/2017 ዓ.ም በደመቀ ሁኔታ የመክፈቻ ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን በዛሬው ዕለት ውድድሮች በተለያዩ የስፖርት ማዝውተሪያ ስፍራዎች ብዙ ተመልካች በተገኘበት መካሄድ ጀምሯል።
የዊልቼር ቅርጫትኳስ ስፖርትም በወንዶች 5 በሴቶች 4 ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች ተሳታፊ ሆነው ዛሬ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ጅምናዚየም ውስጥ የመጀመሪያ ቀን 4 ጨዋታዎች ተካሂደዋል። በዕለቱ የአሶሴሽኑ ስራ አስፈጻሚዎች በቦታው በመገኘት ውድድሩን ታድመዋል ተሳታፊ ክልሎችንም አበረታተዋል።
12/10/2017 ዓ.ም ውጤት
በወንድ
ኦሮሚያ 10-5 ድሬዳዋ
ትግራይ 10-38 አዲስአበባ
በሴት
ኦሮሚያ 5-16 አዲስአበባ
አማራ 24-0 ድሬዳዋ
የ13/10/2017 ፕሮግራም
በወንድ
ድሬዳዋ ከ አማራ
ኦሮሚያ ከ ትግራይ
በሴት
አዲስአበባ ከ አማራ
ድሬዳዋ ከ ኦሮሚያ
#ስፖርተኞችን በቦታው በመገኘት እንድታበረታቱ እና በውድድሩ እንድትዝናኑ ተጋብዛችኋል።
#ጅማ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ባለው ጅምናዚየም።
22/09/2024
አስቸኳይ አስቸኳይ አስቸኳይ
==================
እንዴት ከረማችሁ? እንዴት ሰነበታችሁ? የዊልቼር ቅርጫት ኳስ ቤተሰቦች!
ሊቢያ ከ23 አመት በታች በወንዶች የዊልቼር ቅርጫት ኳስ ሻምፒዮና ጥር ወር ላይ ታዘጋጃለች። ከተሳካልን (በጀት ከተፈቀደ) ልንሳተፍ ፈልገናል እና
#ፓስፖርት ያላችሁ እድሜያችሁ (የፓስፖርት) ከ23 አመት በታች የሆናችሁ በውስጥ መስመር
#የፓስፖርታችሁን ፎቶ ላኩልኝ።
#መልካም ቀን
22/06/2024
With Wheelchair Basketball Federation of India - WBFI – I just got recognized as one of their top fans!
22/06/2024
With IWBF Africa – I just got recognized as one of their top fans!