በመለያ ምት
1⃣ 2⃣ 3⃣ 4⃣ 5⃣
🟡 ❌ ✅ ✅ ❌ ✅
🔴 ✅ ✅ ❌ ✅ ✅
⌚️የሙሉ ሰዓት ውጤት'
ጋሞ ጨንቻ 0-0 ሀላባ ከተማ
ሀላባ ከተማ በመለያ ምት 4ለ3 ጋሞ ጨንቻን በማሸነፍ የ2018 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር አሸናፊ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ እና የዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።
Bereket Dereje Football Agent, በረከት ደረጀ የእግርኳስ ወኪል
በኢትዮጵያ እግርኳስ ችሎታ እያላቸው
እድል ማግኘት ላልቻሉ ተጫዋቾች
ቅድሚያ እንሰጣለን።
Ethiopian Premier League
Sheger Derby
27/03/2026
Congratulations to all Ethiopians 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
18/03/2026
አወይ አፍሪካ
ሴኔጋል አሸንፋው የነበረው የአፍሪካ ዋንጫ ለሞሮኮ ተሰጠ።
06/10/2025
በቅርብ ቀን ከካብ ኢንተርቴይመንት
13/08/2025
#ክፍል1
ከፊፋ የክለቦች የጥራት ደረጃ መለኪያ ጋር የተጣጣመው እና ከ2022/23 እና 2024/25 እ.ኤ.አ ጀምሮ በየውድድር ዓመቶቹ እየተሻሻለ የሚወጣውና በአሁን ወቅትም አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው አሰጣጥ መመሪያ ደንቦች (CAF Club Licensing Regulations) ላይ በመለኪያነት እና በመገምገሚያነት በተቀመጡት መመዘኛ መስፈርቶች መሰረት የክለብ ብቁነት ፈቃድ ለማግኘት እንዲሁም በአህጉራዊ እና በአገር አቀፍ ሊግ ውድድሮች ላይ ለመሳተፍና ለመወዳደር የሚያስፈልጉትን መመዘኛ መስፈርቶችና በክለቦቹ መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ከዚህ በታች በዝርዝር እናያቸዋለን።
✅ ⚽️ ( )
ካፍ ያወጣው የክለብ ፈቃድ መመዘኛ መስፈርቶች በአምስት (5) ዋና ዋና ቁልፍ ምድቦች የተከፋፈሉ ሲሆን፤
እያንዳንዱ ምድብ ውስጥ በአስገዳጅነት መሟላት ያለባቸው "የኤ (A) መስፈርቶች" እና አስገዳጅ ያልሆኑ እንደ አማራጭ ሊሟሉ የሚችሉ "የቢ/የሲ (B/C) መስፈርቶች" አሉ።
የካፍ የክለብ ፈቃድን ለማግኘት በጣም አስፈላጊ የሆኑት ሁሉም የ"ኤ(A)" መስፈርቶችን ማሟላት ግዴታ ነው፤
ሁሉም የ"ኤ(A)" መስፈርቶች ካልተሟሉ ፈቃድ አይሰጥም።
___________________________________
)
⚽️ ሁሉንም "የኤ (A) መስፈርቶችን ማሟላት ግዴታ ነው፤
🏆 🏆
➣ :- ክለቡ ቢያንስ አንድ የታዳጊዎች ወይም ወጣቶች ቡድን (ከ15–21 ዓመት በታች ቡድን (U15-U21)) ሊኖረው ይገባል ፣ በተጨማሪ ቡድኑ በውድድር ላይ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፤
➤ ፡- ቡድኖቹ በፌዴሬሽኑ አስተዳደር ውስጥ በትክክል መመዝገብ አለባቸው፤
➤ :- አሰልጣኞች ህጋዊ የካፍ ወይም ተመጣጣኝ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል፤
➤ :- ታዳጊና ወጣት ተጫዋቾች ብቁ በሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች ህክምና ማግኘት እና ክትትል ሊደረግላቸው ይገባል፤ ክለቦች ይህ መሟላቱንና የሕክምና ባለሙያዎችን መቅጠራቸውን ወይም ከህክምና ተቋም ጋር ውል መፈፀማቸውን ማረጋገጥ አለባቸው፤
➤ :- የታዳጊና ወጣት ቡድኖች ለሥልጠና የተዘጋጁ ምቹ ቦታዎች ሊኖራቸውና ሊያገኙ ይገባል ፤
➢ :- በአግባቡ የተሰናዳ በግልፅ የተቀመጠና በሰነድ የተደገፈ የታዳጊዎችና የወጣቶች ስልጠና መርኃ ግብር (Youth Development Program)እና የስልጠና ሥርዓት መዋቅር ሊኖረውና ሊያቀርብ ይገባል።
___________________________________
⚽️ ሁሉንም "የኤ (A) መስፈርቶችን ማሟላት ግዴታ ነው፤
🏆 🏆
➣ #ስታዲየም 🏟️ :- በካፍ ተቀባይነት ያለው እና ለደህንነት ፣ ለመቀመጫዎች ፣ ለመብራት ፣ ለመገናኛ ብዙሃን ዞኖች እና ለመልበሻ ክፍሎች ካፍ ያወጣውን ዝቅተኛ መስፈርቶችን ያሟላ ስቴዲየም ክለቦች ሊኖራቸው ይገባል ፤
➤ ፡- ክለቦች የሚጠቀሙበትን ስታዲየም ለማስመዝገብ የስታዲየም ባለቤት ሊሆኑ ይገባል ወይም ከስታዲየም ባለቤት ጋር ስታዲየሙን ለረጅም ጊዜ ለመጠቀም የሊዝ ኪራይ ውል ወይም ስምምነት ሊኖራቸው ይገባል፤ ክለቦች የባለቤትነት ማስረጃ ወይም የኪራይ ውል ወይም ስምምነት ማስረጃ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፤
➤ ፡- ክለቦች ቢያንስ ለዋናው ቡድን ተስማሚ የሆነ የሥልጠናና የልምምድ ቦታ ሊኖራቸው ይገባል፤
➢ #ፍተሻ:- ካፍ ወይም ፌዴሬሽኑ ሁሉንም ተቋማትና መገልገያዎች የመመርመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
___________________________________
⚽️ ሁሉንም "የኤ (A) መስፈርቶችን ማሟላት ግዴታ ነው፤
🏆 🏆
| ኃላፊነት | አስፈላጊነት | የሚፈለገው ፈቃድ/ ብቃት |
➣ | ዋና አሰልጣኝ (ለዋናው ቡድን) | ✔️ አስገዳጅ | ዝቅተኛ CAF A ፈቃድ ወይም ተመጣጣኝ ፈቃድ |
➤ | የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ | ✔️ አስገዳጅ | የካፍ የግብ ጠባቂ ዲፕሎማ |
➤ | የአካል ብቃት አሰልጣኝ | ✔️ የሚመከር | በስፖርት ሳይንስ የተመረቀ ወይም በአካል ብቃት አሰልጣኝነት የሰለጠነ |
➤ | የቡድን ሐኪም | ✔️ አስገዳጅ | ፈቃድ ያለው የሕክምና ሐኪም ወይም የሕክምና ተቋም |
➤ | የፊዚዮቴራፒ ባለሙያ | ✔️ አስገዳጅ | ፈቃድ ያለው የፊዚዮቴራፒ ባለሙያ |
➤ | ዋና ሥራ አስኪያጅ | ✔️ አስገዳጅ | የሙሉ ጊዜ ሠራተኛ ለኦፕሬሽኖች ኃላፊነት ያለው |
➤ | የፋይናንስ ኃላፊ| ✔️ አስገዳጅ | የተረጋገጠ የሂሳብ አዋቂ ባለሙያ ወይም ተዛማጅ የሙያ ብቃት |
➤ | የመገናኛ ብዙሃን/የኮሚኒኬሽን ኃላፊ | ✔️ አስገዳጅ | የፕሬስ/የመገናኛ ብዙሃን እና የዜና/የሪፖርት አፃፃፍና አቀራረብ እውቀትና ያለው |
➤ | የደህንነት ኃላፊ | ✔️ አስገዳጅ | የህዝቡን እና የቦታውን ደህንነት የሚጠብቅና የሚያረጋግጥ |
➤ | የክለብ ፈቃድ ሰጪ ባለሙያ | ✔️ አስገዳጅ | የክለብ ፈቃድ አሰጣጥ ማመልከቻዎችን የሚያዘጋጅ፣ የሚልክና ምላሽ የሚሰጥ |
➢ | የቅንነትና የታማኝነት ኃላፊ (ካፍ 2024) | ✔️ አስገዳጅ | ግዴታዎችን እና የፀረ-ሙስና ጥረቶችን የሚያስተዳድር |
___________________________________
⚽️ ሁሉንም "የኤ (A) መመዘኛ መስፈርቶችን ማሟላት ግዴታ ነው፤
🏆 🏆
➣ ፡- ክለቦች በሀገሪቱ ህግ መሰረት ህጋዊ ሰውነት አግኝተው የተመዘገቡና የተቋቋሙ መሆን አለባቸው (ለምሳሌ PLC፣ ማህበር፣ አክሲዮን ኩባንያ)፤
➤ :- ክለቦች የክለባቸውን መዋቅር አወቃቀር ፣ ባለቤትነት፣ የቦርድና የአስተዳደር ስልጣን የሚገልፅ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው ፤
➤ #አባልነት:- ክለቦች ከብሔራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር እና ከፌዴሬሽን ጋር ተያይዞ የተመዘገበ መሆን አለበት፤
➢ :- ክለቦች የክለባቸውን የባለቤትነት አወቃቀር እና የቁጥጥር መዋቅር ሙሉ መረጃና መግለጫ ማቅረብ አለበት ።
___________________________________
⚽️ ሁሉንም "የኤ (A) መስፈርቶችን ማሟላት ግዴታ ነው፤
🏆 🏆
➣ ፡- ክለቦች በIFRS ወይም በአገር አቀፍ ደረጃዎች መስፈርት መሰረት ኦዲት ተደርጎ የተዘጋጀ ያለፈው በጀት ዓመት ዓመታዊ የሂሳብ መግለጫዎች ሪፖርት የግዴታ ማቅረብ አለባቸው፤
➤ :- ክለቦች ካለፈው የበጀት ዓመት ሪፖርቱ እስከሚቀርብበት ቀን ድረስ ምንም አይነት ዘግይተው ለተጫዋቾች፣ ለአሰልጣኞች፣ ለክለቦች፣ ለታክስ ባለስልጣናት፣ ወዘተ የሚከፈሉ ክፍያዎች እና ምንም ዓይነት ውዝፍ የእዳ ክፍዎች ሊኖርባቸው አይገባም፤ ክለቦች ውዝፍ እዳ ካለባቸው እዳቸውን ከፍለው እስከሚያጠናቀቁ ድረስ እና ከእዳ ነፃ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ እስከሚያቀርቡ ድረስ ፈቃድ አይሰጣቸውም ፤
➤ ፡- ክለቦች ለቀጣዩ የውድድር ዘመን የበጀት እና የገንዘብ ፍሰት ትንበያን የሚገልፅና የሚያሳይ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው ፤
➢ :- ክለቦች ኪሳራ ላይ እንዳልሆኑ ፣ በመክሰር ሂደት ላይ አለመሆናቸውን እና በኪሳራ ወይም በህገ ወጥ አሠራር ውስጥ አለመሆናቸውን የሚገልፅና የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው ።
___________________________________
📌 🏆 🏆
◆ ካፍ ሁሉም የክለብ ፈቃድ ማመልከቻዎች በካፍ የክለብ ፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት (CAF Club Licensing Online Platform (CLOP)) በኩል እንዲቀርቡ ይፈልጋል።
◈ ደጋፊ ሰነዶች (ኮንትራቶች፣ ፋይናንሺያል፣ ሲቪዎች፣ ወዘተ) መጫንና መላክ አለባቸው።
◇ ዘግይተው ወይም ያልተሟሉ ማቅረቢያዎች ወደ አውቶማቲክ ውድቅነት ሊያመሩ ይችላሉ።
___________________________________
©️ Bereket Dereje Mekonnen
(FIFA Licenced Football Agent, Authorized FIFA Legal Portal Representative, CAS Legal Representative)
10/08/2025
✅የካፍ የአሰልጣኝነት ፈቃድ ደረጃዎች እና መስፈርቶች
#የአሰልጣኞችን ብቃት ለመለካት፣ ጥራት ለመጨመር፣ ደረጃ ለማረጋገጥ ሲል #ካፍ የተለያዩ የአሰልጣኝነት ሙያ ፈቃድ የባለሙያዎች ደረጃዎችን እና ሊሟሉ የሚገቡ መስፈርቶችን በማውጣት ከ2018 እ.ኤ.አ ጀምሮ አባል ፌደሬሽኖች በአስገዳጅነት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ ሰጥቷል፤
በዚህ ፅሁፍ እስከ ድረስ ያሉትን የተለያዩ በጥልቀት የምንመረምር እና የምናብራራ ሲሆን በተጨማሪም እያንዳንዱን የፈቃድ ደረጃዎች ላይ የተቀመጡ ብቃቶችን፣ ኃላፊነቶችን፣ ለማሰልጠን የተፈቀደላቸው የክለብ ቡድኖች ደረጃና የሊግ ደረጃ እንዲሁም ተያያዥ ነገሮችን በሰፊው የምናይ፣ የምንዳስስና የምናብራራ ይሆናል።
5. የካፍ ዲ ፈቃድ፡- የመነሻ/የመጀመሪያ ደረጃ (CAF D License: Foundation Level)
ወደፊት በአሰልጣኝነት ሙያ ለመዝለቅና እስከ ፕሮፌሽናልነት ደረጃ ድረስ ለመድረስ ለሚፈልጉ ሁሉ ይህ የካፍ ዲ ፈቃድ እንደ መነሻ፣ መሰረታዊና መጀመሪያ ደረጃ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን፤
ይህ የምስክር ወረቀት አሰልጣኞች ከታዳጊዎች፣ ከወጣቶች እና ከአማተር ተጫዋቾች ጋር ለመስራት የሚያስችላቸውን መሠረታዊ እውቀቶችን የሚያስጨብጥ ፣ ለአሰልጣኝነት ሙያ የሚያስፈልጉ ግንዛቤዎችን የሚፈጥሩ እና ያላቸውን ክህሎቶች ለማዳበር የሚያዘጋጅ ነው።
ይህ የዲ ፈቃድ መሰረታዊ የአሰልጣኝነት መርሆዎችን ፣ የስልጠና ክፍለ ጊዜን እቅድ ማውጣት እና የጨዋታ ህግጋት የመጀመሪያ ምዕራፍን (an introduction to the laws of the game) በስልጠና ወቅት የሚሸፍናቸውና የሚዳሣቸው ይሆናል፡፡
የካፍ ዲ ፈቃድ ያላቸው አሰልጣኞች መሠረታዊ የታዳጊዎች ልማት ፕሮግራሞችን ለመምራት (grassroots development programs) ፣ በእድሜ እርከን የተከፋፈሉ የታዳጊና የወጣት ቡድኖችን ለማሰልጠን (U20, U17, U15) እና የመጀመሪያ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና ክፍለ ጊዜዎችን ለመከታተልና ለመውሰድ ብቁ ናቸው ።
4. የካፍ ሲ ፈቃድ፡ የልማትና የእድገት ደረጃ (CAF C License: Development Level)
በካፍ የአሰልጣኝነት የፈቃድ ደረጃዎች ቅደም-ተከተል ተዋረድን በመከተል ወደ ላይ ከፍ ለማድረግ ስንፈልግ ከካፍ ዲ ፈቃድ ቀጥሎ የምናገኘው የካፍ ሲ ፈቃድን ሲሆን፤
ይህ የካፍ ሲ ፈቃድ ከታዳጊዎች ከፍ ባሉ የዕድሜ ቡድኖች እና በውድድር ቦታዎቻቸው ላይ ያለውን የተጫዋቾች እድገት ላይ በዋናነት ትኩረት ይሰጣል።
ይህ የምስክር ወረቀት ጥልቀት ያለው የአሰልጣኝነት ዘዴዎችን ፣ የስልት ትንተናዎችን (ታክቲካዊ ትንታኔዎችን) እና የስፖርት ስነ-ልቦናን ያካተተ ስልጠናን ማጠናቀቅ የሚገልፅ የእውቅና ማረጋገጫ ነው።
የካፍ ሲ ፈቃድ ያላቸው አሰልጣኞች በአካዳሚ፣ በታዳጊ፣ በወጣት እና በአማተር ሊግ (ብሔራዊ ሊግ) ደረጃ የሚገኙ ቡድኖችን በዋና አሰልጣኝነት ማሰልጠንና መስራት ይችላሉ፤
የካፍ ሲ ፈቃድ ያላቸው አሰልጣኞች ተጫዋቾችን ከመሰረታዊ ክህሎቶቻቸው ወደ ላቁና ከፍ ወዳሉ ቴክኒኮች እንዲያሳድጉ እና በሊግ ደረጃ እንዲጫወቱ ለማድረግ ይሰራሉ፡፡
3. የካፍ ቢ ፈቃድ፡ የላቀ ደረጃ (CAF B License: Advanced Level)
የካፍ ቢ ፈቃድ ታቅዶ የተነደፈውና የተዘጋጀው የአሰልጣኝነት ፈቃድ ደረጃቸውን ለማሳደግና ወደ ከፍተኛ የሙያ ደረጃ መሸጋገር ለሚፈልጉ አሰልጣኞች የተዘጋጀ ሲሆን፤
ብዙ ጊዜ ፕሮፌሽናል እና ከፊል ፕሮፌሽናል ተጫዋቾችን ለማሰልጠን፣ ለማስተዳደርና ብቁ ለማድረግ ያለመ የፈቃድ ደረጃ ነው ።
ይህ የምስክር ወረቀት የተራቀቁና የላቁ ታክቲካል ስልቶችን፣ የተጫዋቾች አስተዳደርን እና ጥልቀት ያለው የጨዋታ ትንተናን ያካተተ ስልጠናን ማጠናቀቅ የሚገልፅ የእውቅና ማረጋገጫ ነው።
የካፍ ቢ ፈቃድ ያላቸው አሰልጣኞች ፕሮፌሽናል የወጣት አካዳሚዎችን ፣ የተጠባባቂ ቡድኖችን፣ በሁለተኛ ደረጃ ሊጎች (ከፍተኛ ሊግ) ላይ የሚወዳደሩ ቡድኖችን ወይም ከፊል ፕሮፌሽናል ክለቦችን ለመምራትና ለማሰልጠን ብቁ ናቸው፤ እንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የእግር ኳስ ውድድሮች ላይ በረዳትነት ሊሳተፉ ይችላሉ ።
2. የካፍ ኤ ፈቃድ : የከፍተኛ ደረጃ ( CAF A License: Elite Level)
የካፍ ኤ ፈቃድ ከፍተኛ የአሰልጣኝነት ደረጃ ሲሆን የላቀና ከፍተኛ የሆነ የቴክኒክ እና የታክቲክ ዕውቀትን መለኪያ በማድረግ የሚሰጥ የፈቃድ ደረጃ ነው።
የካፍ ኤ ፈቃድ ያላቸው አሰልጣኞች የፕሮፌሽናል ክለብ ዋና ቡድኖችን ማሰልጠን የሚችሉ ሲሆን ውስብስብ የሆኑ ስልቶችንና ስትራቴጂዎችን ነድፈው በከፍተኛ የውድድር ደረጃዎች ላይ የመምራት እና መመሪያ የመስጠት ብቃት፣ አቅምና እውቀት ያላቸው አሰልጣኞች ናቸው ።
ይህ የምስክር ወረቀት ብሔራዊ ቡድኖችን ለማሰልጠን እና በአፍሪካና በዓለም ከ23ና ከ20 ዓመት በታች የቻን ዋንጫ መድረኮች ላይ ለመምራት ወይም ፕሮፌሽናል ክለቦችን በአህጉራዊና በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ለመምራት፣ ይዞ ለመቅረብና ለማሰልጠን በቅድመ ሁኔታ ለአሰልጣኞች የሚቀመጥ መስፈርት ነው ።
1. የካፍ ፕሮ ፈቃድ: የበቃ ፕሮፌሽናል/ባለሙያ ደረጃ (CAF Pro-License: Expert Level)
የአሰልጣኝነት ብቃቶች ቁንጮና ከፍተኛ ደረጃ የሆነው የካፍ ፕሮ ፈቃድ በጣም ልምድ ላላቸው እና በሙያቸው ውጤታማ ለሆኑ (ለተሳካላቸው) አሰልጣኞች የሚሰጥ የአሰልጣኝነት ፈቃድ ደረጃ ነው ።
የዚህ ፈቃድ ደረጃ ምስክር ወረቀት አሰልጣኞችን በእግር ኳስ ውስጥ በጣም አስፈላጊና በጣም አስቸጋሪ ለሆኑ ሚናዎች የሚያዘጋጅ እና እንደ አፍሪካ ዋንጫ (AFCON) ወይም የፊፋ የዓለም ዋንጫ ወይም የኦሎምፒክ ውድድሮች ባሉ ታላላቅ ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ብሔራዊ ቡድኖችን ማሰልጠን እንደሚችሉ የሚገልፅ የእውቅና ማረጋገጫ።
የፕሮ ፈቃድ መርሃ ግብርና ስርአተ ትምህርት የላቀ ከፍተኛ የአሰልጣኝነት አሰለጣጠን ዘዴዎችን ፣ የአመራር ክህሎቶችን እና ከፍተኛ ልምድና ፕሮፋይል ያላቸው ተጫዋቾችን የማስተዳደር ችሎታን ያካተተ ስልጠና የሚሰጥበት የአሰልጣኝነት የፈቃድ ደረጃ የመጨረሻው ደረጃ ነው።
በ የካፍ የአሰልጣኝነት ፈቃድ የተለያዩ ደረጃዎችን ( እስከ ድረስ) እና መስፈርቶችን እንዲሁም ለእያንዳንዳንዱ ደረጃዎች የሚያስፈልጉና ሊሟሉ የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎችን ፣ ብቃቶችንና ኃላፊነቶችን በጥልቀት የምናይ የምንመረምር እና የምናብራራ ሲሆን፤
በተጨማሪ የካፍ አሰልጣኝነት ፈቃድ መስፈርቶችን በክለቦች የደረጃ ዓይነት፣ በውድድር ደረጃ እና በሚያስፈልገው የአሰልጣኝነት ፈቃድ ደረጃ ላይ በመመርኮዝና መሰረት አድርገን በመከፋፈል በዝርዝር የምናያቸውና የምንዳስሳቸው ይሆናል፡፡
ይቀጥላል .................
©️ Bereket Dereje Mekonnen
(FIFA Licenced Football Agent, Authorized FIFA Legal Portal Representative, CAS Legal Representative)
04/08/2025
#ተጫዋቾች ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ፣ ችሎታቸውን እንዲያሳድጉ፣ የፕሮፌሽናልነት ደረጃ እንዲደርሱ፣ ሙያቸውን በታማኝነት እንዲያገለግሉ፣ በስነ-ስርዓት ተቀርፀው እና በስነ-ምግባር ታንፀው እንዲያድጉ እንዲሁም በወጥ አቋም ለረጅም ጊዜ በሙያው እንዲቆዩ በማድረግ ረገድ #አሰልጣኝ ወሳኝ ሚናን የሚጫወት በመሆኑ ካፍ በአህጉሪቱ የእግር ኳስ ልማትና እድገት ላይ ብቁ #አሰልጣኞች የሚሰጡትን ጥቅም፣ የሚያበረክቱትን ፋይዳና ያላቸውን አስፈላጊነት በመገንዘብ እውቅና በመስጠት ብቁ የሆኑ አሰልጣኞችን ለመለየት በማውጣት ስልጠናውን አጠናቀው የምዘና ፈተናውን ላለፉና ብቁ ለሆኑ አሰልጣኞች ስልጠናቸውን ማጠናቀቃቸውን፣ የምዘና ፈተናቸውን በብቃት ማለፋቸውን እና የአሰልጣኝነት ፈቃድ ደረጃውን የሚገልፅ የእውቅና ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል።
የአፍሪካ እግርኳስ አስተዳዳሪና የበላይ አካል የሆነው (ካፍ/CAF) የዓለም እግርኳስ አስተዳዳሪና የበላይ አካል ከሆነው ከ (ፊፋ/FIFA) ጋር የሚጣጣም ዓለም አቀፍ የሆነ የአሰልጣኝነት ማዕቀፍ እና በመላው አህጉሪቱ ወጥነት ያለው የአሰልጣኝነት ስልጠና ትምህርትና ብቃትን የሚያረጋግጥ የተዋቀረ የአሰልጣኝነት ፈቃድ ስርዓት (Coaching Licensing System) በመዘርጋት እየሰራ ይገኛል።
ካፍ በአገር አቀፍ ሊጎች እና በአህጉራዊ ውድድሮች (ካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ እና ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ) ላይ የሚሳተፉትን ክለቦች ጨምሮ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ በሚገኙ አገራት የውስጥ ሊግ እርከን ውድድሮች ላይ በሚሳተፉ የተለያዩ ፕሮፌሽናል ክለቦችን እንዲሁም ብሔራዊ ቡድኖችን ለማሰልጠን ለሚፈልጉ ግለሰቦች (አሰልጣኞች) ዝቅተኛውን የአሰልጣኝነት ፈቃድ መስፈርቶችን (Minimum Coaching License Requirements) ያወጣና ያስቀመጠ ሲሆን፤
እነኚህ የአሰልጣኝነት ፈቃድ መስፈርቶች መሟላት አለማሟላታቸውን ካፍ በየአመቱ ለክለቦች ፈቃድ በሚሰጥበት ወቅት በካፍ የክለብ ፈቃድ መዋቅር (CAF Club Licensing Online Platform (CLOP)) አማካኝነት ይቆጣጠራል እንዲሁም በካፍ የክለብ ፈቃድ መመሪያ ደንቦች መሠረት ደንቦቹን ያስፈፅማል።
በ የካፍ የአሰልጣኝነት ፈቃድ የተለያዩ ደረጃዎችን ( እስከ ድረስ) እና መስፈርቶችን እንዲሁም ለእያንዳንዳንዱ ደረጃዎች የሚያስፈልጉና ሊሟሉ የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎችን ፣ ብቃቶችንና ኃላፊነቶችን በጥልቀት የምናይ የምንመረምር እና የምናብራራ ሲሆን፤
በተጨማሪ በ የካፍ አሰልጣኝነት ፈቃድ መስፈርቶችን በክለቦች የደረጃ ዓይነት፣ በውድድር ደረጃ እና በሚያስፈልገው የአሰልጣኝነት ፈቃድ ደረጃ ላይ በመመርኮዝና መሰረት አድርገን በመከፋፈል በዝርዝር የምናያቸውና የምንዳስሳቸው ይሆናል፡፡
ይቀጥላል .................
©️ Bereket Dereje Mekonnen
(FIFA Licenced Football Agent, Authorized FIFA Legal Portal Representative, CAS Legal Representative)
15/07/2025
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ የፊፋ የእግር ኳስ ኤጀንቶች ማኅበር እየታዩ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት እና በቀጣይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አደረጉ፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን፣ የቲኤም ኤስ ባለሙያ ወ/ሮ ዘውድነሽ ይርዳው፣ የኢትዮጵያ የፊፋ የእግር ኳስ ኤጀንቶች ማህበር ፐሬዝደንት አቶ ኤዶሚያስ በቀለ፣ የማህበሩ ም/ፐሬዝደንት አቶ በረከት ደረጀ፣ የማህበሩ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኢዩኤል ደባሽ፣ የማህበሩ የሒሳብ ሹም አቶ ገሮ ገረመው እና የማህበሩ ህዝብ ግንኙነት አቶ ኤርሚያስ በቀለ በተደረገው ውይይት ህገወጥነትን ስለመከላከል፣ ሰለ ሀገራዊ የእግር ኳስ ኤጀንቶች መተዳደሪያ ደንብ፣ ታዳጊዎችን ስለማብቃት፣ ስለ ፕሮፌሽናልነት፣ የሀገራችንን ተጫዋቾች በማብቃት ወደ ውጭ ሀገራት ስለመላክ፣ ክለቦችን ስለማብቃትና ማሳደግ ዙርያ ሀሳቦች ተነስተው የተወያዩ ሲሆን በቅርበት ለመሥራትና የደረሱበትን ለመገምገም ቀጣይ ቀጠሮ በመያዝ ተጠናቋል።
15/07/2025
በሀገራችን እግርኳስ በየቀኑ የሚሰማው ነገር ተስፋ አስቆራጭ ሁኖ ቀጥሏል።ዘንድሮም ለፊፋ ኤጀንትነት/ለተጫዋቾች ወኪልነት/ ከተፈተነኑ ተፈታኞች አንድም ሰው አላለፈም።
15/07/2025
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Address
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 09:00 - 17:00 |
| Tuesday | 09:00 - 17:00 |
| Wednesday | 09:00 - 17:00 |
| Thursday | 09:00 - 17:00 |
| Friday | 09:00 - 17:00 |
| Saturday | 09:00 - 17:00 |