03/05/2026
በዩናይትድ ቤት ስኬታማ መሆን ከየትኛውም ክለብ ስኬት በላይ ነው - ብሩኖ
ካፒቴን ብሩኖ ፈርናንዴሽ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ስኬታማ መሆን በየትኛውም ሌላ ክለብ የማይገኝ ደስታ ይፈጥርልኛል ብሏል።
ብሩኖ 19 ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል በሊጉ አዲስ ክብረወሰን (21) ለማስመዝገብ በቀሪ አራት ጨዋታዎች ሁለት ተጨማሪ አሲስት ይጠበቅበታል።
ደጋፊዎቻችን ዩናይትድን ወደቀደመ ከፍታው እንዲመለስ ምን ያህል ጉጉት እንዳላቸው አውቃለሁ፥ እኔም ከደጋፊዎቻችን ጋር ለክለቡ ስኬት አብሬ መጓዝና የሚቻለንን ማድረግ ነው የምፈልገው ብሏል።
ከክለቡ ጋር የካራባኦ እና ኤፍ ኤ ዋንጫዎችን ቢያሸንፍም ይህ በቂ አለመሆኑን ለስካይ ስፖርት ተናግሯል።
እነዚህን ዋንጫዎች ብናሸነፍም ክለቡም እኔም የምመኘው ስኬት ገና ስለሆን በዩናይትድ ያለኝ ውል እስከሚያበቃ ጥረታችን ይቀጥላል ሲል ተደምጧል።
02/05/2026
ዩናይትድ ወደ ቻምፒየንስ ሊግ ተመለሰ
ማንቸስተር ዩናይትድ በይፋ ወደ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ መመለሱን አረጋግጧል
በሊጉ 6ኛ ደረጃ የነበረው ብራይተን በኒውካስል ዩናይትድ ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ ዩናይትድ ከወዲሁ የ2026/27 የቻምፒየንስ ሊግ ትኬቱን ቆርጧል
ዩናይትድ ነገ ከሊቨርፑል ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ጨምሮ በቀሪ አራት ጨዋታዎች 3ኛ ደረጃውን ለማስጠበቅ የሚፋለም ይሆናል።
23/08/2025
ሆይሉንድ ወደ ናፖሊ...
ራስሙስ ሆይሉንድ በዩናይትድ የመቆየት ፍላጎት ቢኖረውም ከክለቡ እንደሚለቅ የተረጋገጠ ይመስላል
ዴንማርካዊው አጥቂ ወደ ኤሲ ሚላን እንደሚያቀና በስፋት ሲነገር ቢቆይም መዳረሻው ናፖሊ እንደሚሆን ተዘግቧል
የሴሪ አው ሻምፒዮን ተጫዋቹን በቋሚነት የመግዛት ውል በተካተተበት የውሰት ውል ለማስፈረም መቃረቡ ተነግሯል
ሆይሉንድ ወደ ኔፕልሱ ክለብ የሚዘዋወር ከሆነ ከቀድሞ የዩናይትድ አጋሩ ስኮት ማክቶሚናይ ጋር ዳግም የሚገናኝ ይሆናል...
Manchester United - Gech
12/08/2025
ብራይተን፥ ዩናይትድ ለባሌባ ያቀረበውን አማራጭ ውድቅ ማድረጉ ተነግሯል
ስካይ ስፖርት እንደዘገበው ማንቸስተር ዩናይትድ ካርሎስ ባሌባን ለማስፈረም የዝውውር ገንዘብና ተጫዋች አቅርቧል
ነገር ግን ብራይተኖች ዩናይትድ ያቀረበውን የዝውውር አማራጭ ሳይቀበሉት መቅረታቸውን ስካይ ዛሬ ማለዳ አስነብቧል
ዩናይትድ ለዝውውሩ ምን ያህል መነሻ ሂሳብ እና ማንን በተለዋጭነት እንዳቀረበ የተገለጸ ነገር የለም
በተያያዘ የዛሬ ጠዋት መረጃ፥ ብራይተን ለመሸጥ ፍቃደኛ ካልሆነ በስተቀር ተጫዋቹ ወደ ኦልድትራፎርድ የመምጣት ፍላጎት እንዳለው ዩናይትዶች እርግጠኛ መሆናቸውን ዴይሊ ሚረር ዘግቧል
11/08/2025
ዶናሩማ ከፒኤስጂ እንደሚለቅ ተረጋግጧል...
ፓሪ ሰን ዠርማዎች ግብ ጠባቂውን ከአውሮፓ ሱፐር ካፕ ስብስባቸው ውጭ ማድረጋቸው ተዘግቧል
ማንቸስተር ዩናይትድ የግብ ጠባቂው ፈላጊ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፥ ተጫዋቹ ከፒኤስጂ ጋር እንደሚለያይ እርግጥ ሆኗል
ዶናሩማ ከዩናይትድ በተጨማሪ በቼልሲም የሚፈለግ ሲሆን መዳረሻው እንግሊዝ እንደሚሆን ፋብሪዚዮ ዘግቧል
09/08/2025
ባይንዲር
ማጓየር
ዮሮ
ሄቨን
ዶርጉ
ካሴሚሮ
ብሩኖ
ምቡሞ
ኩንሃ
አማድ
ማውንት
09/08/2025
"የማንቸስተር ገናና ታሪክ ፍጹም የተለየ መሆኑ እርግጥ ነው! ከዚያም በላይ እኔ የተሳብኩት ግን በመጪው የዩናይትድ ስኬታማ ጊዜ ነው" - ቤንጃሚን ሼሽኮ
09/08/2025
ሼሽኮ ለዩናይትድ ፊርማውን አኑሯል
ለአምስት ዓመት የሚያቆየውን ውል ፈርሟል
በዛሬው ጨዋታ በኦልድትራፎርድ በይፋ ከደጋፊዎች ጋር ይተዋወቃል