አርሰናል daily fans page በኢትዮጵያ

አርሰናል daily fans page በኢትዮጵያ ስለ አርሰናል፦
☞የዝውውር ዜናዎች
☞የጫወታ ቅድመ ትንታኔዎ?

🔴⚪ አርሰናል በአሜክስ ስታድየም ከብራይተን ጋር በምናደርገው ጫወታ ግምታዊ የአርሰናል XI አሰላለፍ ፦🇪🇸 ራያ🇳🇱 ቲምበር🇬🇬ኮንሳ🇧🇷 ጋብርኤል🇮🇹 ካላፊዮሪ🇧🇷 ብሩኖ ጉማሬሽ🇬🇬 ራይስ🇳🇴 ኦዴ...
17/09/2026

🔴⚪ አርሰናል በአሜክስ ስታድየም ከብራይተን ጋር በምናደርገው ጫወታ ግምታዊ የአርሰናል XI አሰላለፍ ፦

🇪🇸 ራያ
🇳🇱 ቲምበር
🇬🇬ኮንሳ
🇧🇷 ጋብርኤል
🇮🇹 ካላፊዮሪ
🇧🇷 ብሩኖ ጉማሬሽ
🇬🇬 ራይስ
🇳🇴 ኦዴጋርድ
🇬🇬ሳካ
🇩🇪 ሃቨርትዝ
🇬🇷 ቶሊስ

🔥 የዚህ የውድድር ዘመን እስካሁን ካጋጠሙን በጣም ከባድ ፈተናዎች አንዱ! አርሰናል ወደ Amex ስታድየም በመጓዝ በፋቢያን ሁርዘለር የሚመራውን ጥሩ አቋም ላይ የሚገኘውን ብራይተንን ይገጥማል።

👀 ማይክል አርቴታ ሰንደርላንድን ካሸነፈው ቋሚ XI አሰላለፍ ውሥጥ ሁለት ለውጦች ሊደረግ ይችላል ቤን ዋይት ጉዳት ምክንያት ቀኝ ፉልባክ ቦታ ላይ ቲምበርን ሊተካ ይችላል፤ እንዲሁም በሰንደርላንድ ጨዋታ የጫወታው ቀያሪ ምርጥ ብቃቱን ያሳየን ብሩኖ ጉማሬሽ ስኬሊን ተክቶ ወደ ቋሚ አሰላለፉ ሊመለስ ይችላል ቀሪው XI ግን እንደተጠበቀው ሊቀጥል ይችላል። 💯

⚽ እናንተ በዚህ ግምታዊ XI ላይ እነማንን ለውጥ ታደርጋላችሁ? ወይስ ይህ አሰላለፍ ፍጹም የሆነውን የውድድር ዘመን የድል ጉዟችንን ለማስቀጠል በቂ ነው? 👇🔴⚪

🗣ክርስቶስ ዞሊስ ስለ አርሰናል የቡድን መንፈስ፦🎙“በልምምድም ሆነ በሜዳ ላይ ሁላችንም እርስ በርሳችን እንረዳለን እኛ ሁልግዜም ራሳችንን ለማሻሻል የምንፈልግ አንድ ቡድን ነን፣ ግባችንም እያ...
17/09/2026

🗣ክርስቶስ ዞሊስ ስለ አርሰናል የቡድን መንፈስ፦

🎙“በልምምድም ሆነ በሜዳ ላይ ሁላችንም እርስ በርሳችን እንረዳለን እኛ ሁልግዜም ራሳችንን ለማሻሻል የምንፈልግ አንድ ቡድን ነን፣ ግባችንም እያንዳንዱን ጨዋታ ማሸነፍ ነው።"

🎙"ስለዚህ በልምምድ ላይም የምንጠይቀው ደረጃ ከፍ ያለ ነው
በተለይ ስብስባችን ውሥጥ በርካታ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች ብዙ ትምህርት እና ልምድ ይሰጡናል ከእኛ ጋር ያወራሉሚኬል ሜሪኖ፣ ጋብርኤል ማጋሌሽ፣ ዴክላን ራይስ… ብዙ ነገር ከእነሱ እሰማለሁ፤ ማይልስም እንዲሁ።"

🎙"እንደነዚህ ያሉ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች ከጎንህ መኖራቸው በጣም ጥሩ ነው፤ ከእነሱም ብዙ መማር ትችላለህ።”

🗣ክርስቶስ ዞሊስ ስለ ካይ ሀቨርትዝ እና ዮኬሬሽ ፦

🎙"ሁለቱም በጣም ጥሩ ሰዎች ናቸው እንዲሁም ማንም ከሚያስበው በላይ በጣም ምርጥ ጓደኛሞች ናቸው በጣም ይቀራረባሉ አብረው ልምምድ ይሰራሉ አንዱ ከአንዱ ይማራል ቅርርባቸው እጅግ የተለየ ነው በአንድ ቦታ የሚጫወቱ ተጫዋቾች በዚህ ልክ መዋደዳቸው እና መቀራረባቸው በጣም አስደሳች ነገር ነው እኔ ለአርሰናል ከመፈረሜ በፊት በዚህ ልክ ቅርብ ጓደኞች ናቸው ብዬ አልጠበኩም ነበር።"

🥹…የአርሰናል ደጋፊዎች ይህን ቀን ለማየት ስንት ትችትና  መሳለቂያ የሆኑ አስተያየቶች ተሰጥተውብን ነበር ....?“አርሰናሎች አሰልቺ እግር ኳስ ይጫወታሉ... በቆመ ኳስ ብቻ የሚተማመን ቡድ...
17/09/2026

🥹…የአርሰናል ደጋፊዎች ይህን ቀን ለማየት ስንት ትችትና መሳለቂያ የሆኑ አስተያየቶች ተሰጥተውብን ነበር ....?

“አርሰናሎች አሰልቺ እግር ኳስ ይጫወታሉ... በቆመ ኳስ ብቻ የሚተማመን ቡድን ነው ... ” ተብለን፣ ተተችተን፣ ተሳልቀውብን ነበር.... ዛሬ ግን ከቀድሞ ተቺዎቻችን አንዱ አርሰናልን ብቻ ለመተቸት ሚዲያ ላይ የሚወጣው የቀድሞ የቸልሲ ተጫዋች ጆን ኦቢ ሚኬል ... ሳይወድ በግዱ ስለ ጀግናው ክለባችን ምስክርነቱን ሰጥቷል ...

“አርሰናል አሁን ሊሸነፍ የማይችል ቡድን ይመስላል” እያለ ነው! 😳🔥

🗣የቀድሞ የቼልሲ ኮከብ ጆን ኦቢ ሚኬል በObi One Podcast ላይ ስለ ሚኬል አርቴታ አርሰናል ከፍተኛ አድናቆትን ሰጥቶታል በአድናቆቱም እንዲህ ገልጾታል አርሰናል በአሁኑ ሰዓት በፕሪሚየር ሊጉ ያለው ምርጥ ቡድን እና ምርጥ ስኳድ ብሎታል፦

🗣️ ጆን ኦቢ ሚኬል በObi One Podcast ላይ ስለ አርሰናል የተናገረው፦

🎙“ይህ ቡድን አሁን በሊጉ ምርጡ ቡድን ነው በዚህ ላይ ምንም ጥያቄ የለም ከባለፈው የውድድር ዘመን የተሻለው ነገር አርሰናል አሁን የሻምፒዮንነት እውቀትና ልምድ ማግኘቱ ነው።"

🎙“አሁን እያሳዩ ያሉት ብቃት ጨዋታውን ሲመሩ እንዴት ጫወታውን መቆጣጣር እንዳለባቸው፣ ቀድሞ ሲገባባቸው እንዴት ውጤት መቅልበስ እንደሚችሉ፣ እና ጨዋታውን እንዴት መቆጣጠር እና የጨዋታውን ግፊት ማሳነስ እና ውጤቱን ማስጠበቅ ምን ማረግ እንዳለባቸው በሚገባ አውቀዋል ከዚያም በላይ ይህን ቁጥጥር ከጥሩ እግር ኳስ ጋር እያጣመሩት ነው።”

🎙“እራሳቸውን በሜዳ ላይ በነፃነት እየገለጹ ነው ጥሩ እግር ኳስ እየተጫወቱ፣ ጎሎችን እያስቆጠሩ እና በመከላከልም ሆነ በማጥቃቱ ጠንካራ ናቸው።”

🎙“ለእኔ አሁን እሥከ አሁን ካየዋቸው ቡድኖች ሊሸነፉ ቡድን ይመስላሉ።"

🗣ጆን ኦቢ ሚኬል በፖድካስቱ በተለየ ሁኔታ ማርቲን ኦዴጋርድን አድንቋል፦

🎙"ካፒቴኑ እንደ “አዲስ ፈራሚ” እንደተመለሰ ገልጾ፣ አሁን በጣም ንቁ፣ በጣም የተሳለ ቢላ ፣ እድሎችን የሚፈጥር እና ጎሎችንም የሚያስቆጥር የአርሰናልን ማጥቃት የሚያቀጣጥል እና ተጋጣሚ ቡድንን የሚያፈራርስ የማይታመን ብቃት እያሳየ ይገኛል በማለት አሞካሽቶታል ...

🎙እንዲሁም ቡካዮ ሳካን ደሞ ..."ሳካ ወደ ምርጥ አቋሙ እየተመለሰ እንዳለ እና እራሱን ለማሳየት የተራበ ተጫዋች እንደሚመስል ገልጿል።..

🗣ኦቢ ሚኬል አክሎም ስለ አርሰናል እና ሎሎች ተፎካካሪ ቡድኖች ከአርሰናል ጋር ስላላቸው ልዩነት እንዲህ ይናገራል፦

🎙"አርሰናልን ከሌሎቹ ቡድኖች የሚለየው ነገር አጠቃላይ ቡድኑ የተረጋጋ ሜዳ ላይ መረጋጋትና ወጥነት ያለው ቡድን ነው የእነሱ ተፎካካሪ ክለቦች ቼልሲ፣ ማንችስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል ትልቅ ለውጦችን ሲያሳልፉ፣ አርሰናል ግን አሰልጣኙን፣ የቡድኑን ዋና አካል እና የጨዋታ ስርዓቱን እንደያዘ ቀጥሏል።"

🗣 ጆን ኦቢ ሚኬል የመጨረሻ አስተያየቱን እንዲህ አርቴታን አመስግኖ ንግግሩን ጨርሷል፦

🎙"ምናልባት ከሁሉም የሚበልጠው ምስጋና ነው.... እንዲህ አይነት ቡድን ላስመለከተን አርቴታ ምስጋና ይገባዋል..."
..🤖🏆 “ሚኬል አርቴታ ቡድን ብቻ ሳይሆን ማሽን ነው የገነባው ያውን የገነባው ማሽን የሚያሸንፍ ማሽን ገንብቷል።”

😂 ከ“አሰልቺ አርሰናል” እስከ “ሊሸነፍ የማይችል የሚያሸንፍ ማሽን”... ጊዜ ምን ያህል ሰዎችን እንደሚቀይር!

‼የቀድሞ ተቺዎቻችን አሁን የአርቴታን ስራ ማድነቅ ጀምረዋል!እኛ ግን አዲስ ተቺዎች መፈለግ አለብን… የቀድሞዎቹ ሁሉም ተቺዎቻችን የአርሰናል እና የአርቴታ ደጋፊዎቻችን እየሆኑ ነው! 😂🔴⚪

‼የመድፉ ቤተሰቦች ይህን ለመስማት ጆሮአችሁን በደንብ ክፈቱ! 😮‍💨🔥"አርሰናል አሁን በሜዳ ላይ የሚያሳየው ነገር ተፎካካሪ ቡድኖችን ማስፈራት ጀምሯል! .... ይህን የሚለው ማን ነው? የማን...
17/09/2026

‼የመድፉ ቤተሰቦች ይህን ለመስማት ጆሮአችሁን በደንብ ክፈቱ! 😮‍💨🔥

"አርሰናል አሁን በሜዳ ላይ የሚያሳየው ነገር ተፎካካሪ ቡድኖችን ማስፈራት ጀምሯል! .... ይህን የሚለው ማን ነው? የማንችስተር ዩናይትድ ሌጀንድ ሪዮ ፈርዲናንድ! 👀

🗣️ ሪዮ ፈርዲናንድ ስለ አርሰናል፦

🎙“በዚህ የውድድር ዘመን አርሰናልን ሊፎካከር የሚችል አንድም ቡድን አላየሁም አርሰናል ብቻ ነው የተረጋጋ አቋም ያለው፤ ሌሎቹ ቡድኖች ትልቅ ለውጦችን አድርገዋል።"

🎙"ከአርሰናል በዚህ ሲዝን የምጠብቀውም የሜዳ ላይ ብቃይ ይሄንኑ ነበር እንደጠበኩትም ሜዳ ላይ ጠንካራ፣ ለተጋጣሚ ቡድን ከባድ፣ ተጋጣሚውን በየትኛውም መንገድ የሚያስቆም እና ከተጋጣሚው ስህተት ተጠቅሞ የሚቀጣ ቡድን።"

🎙አሁን እንደ ሻምፒዮን እየተጫወቱ ነው።

🎙አሁን በራስ መተማመን የተሞላ እና በጣም ጥሩ፣ ውብ እግር ኳስ እየተጫወቱ ነው በተጨማሪም በመከላከሉ ረገደም በኩል በጣም ጠንካራ ናቸው።” 🔥

🏆 አርሰናል እንደ ሻምፒዮን እየተጫወተ ነው! በዚህ አመትም የሊጉን ቻምፒዮንነት ክብር ያስጠብቃል።"

🗣ፖል ስኮልስ አዲሱ ሲዝን መጀመሪያ ላይ ስለ ሊጉ የዋንጫ ፉክክር ይህን ተናግሮ ነበር ፦🎙🎙ማን ዩናይትድ እና ካሪክ ሊጉን ለማሸነፍ እድል ይኖራቸዋል ብዬ አስባለሁ አርሰናልን ደግሞ ብዙዎች ...
17/09/2026

🗣ፖል ስኮልስ አዲሱ ሲዝን መጀመሪያ ላይ ስለ ሊጉ የዋንጫ ፉክክር ይህን ተናግሮ ነበር ፦🎙

🎙ማን ዩናይትድ እና ካሪክ ሊጉን ለማሸነፍ እድል ይኖራቸዋል ብዬ አስባለሁ አርሰናልን ደግሞ ብዙዎች ከዚህ ግዜ ጀምሮ ከሌሎች የበላይ እንደሚሆኑ ይጠብቋቸዋል ነገር ግን እኔ በዛ መንገድ አልመለከተውም አርሰናል በሶስተኛ ወይም በአራተኛ ደረጃ ላይ ሊያጠናቀቅ ይችላል ብዬ አምናለው አርሰናል 3ኛ ወይም 4ኛ ደረጃን ይዞ ቢያጠናቅቅ እኔ አልገረምም።"

😁😁የማን ዩናይትድ አብዛኞቹ ሌጀንዶቻቸው ግን ስለ እግር ኳስ ትንታኔ ምንም ዓይነት ግንዛቤ የላቸውም ልበል።😁

⚠እግር ኳስን ሲያሳዩ ውሥጣቸው ጥላቻ፣ ቁጭት እና ስሜታዊ ሆነው እያዩ እራሳቸው ግራ ገብቷቸው ደጋፊዎቻቸውን ግራ ያጋባሉ ፣ እግር ኳስን አለመረዳታቸውን የምናውቀው ደግሞ ከእነሱ ውስጥ ማንም አንድ እንኳን የረባ አሰልጣኝ መውጣት ያልቻለበት አንዱ ምክንያት ነው። 🤣🤣🤣🤣🤣🤣

🎙አይ ፖል ስኮልስ 😁😁

💫የማክስ ዶውማን የለውጥ ሂደት በአርሰናል ቤት🤍♥️The Evolution of Arsenal's Wonderkid Max Dowman 💫🤍♥️
17/09/2026

💫የማክስ ዶውማን የለውጥ ሂደት በአርሰናል ቤት🤍

♥️The Evolution of Arsenal's Wonderkid Max Dowman 💫🤍♥️

🚨የFleetwood Town ደጋፊዎች ከአርሰናል ጋር በመመደባቸው ታላቅ ደስታ ላይ ናቸው🔴⚪ ✅ የፍሊትዉድ ታውን ክለብ ደጋፊዎች በዘንድሮው የካራባዎ ካፕ (Carabao Cup) የእጣ ድልድል ...
17/09/2026

🚨የFleetwood Town ደጋፊዎች ከአርሰናል ጋር በመመደባቸው ታላቅ ደስታ ላይ ናቸው🔴⚪

✅ የፍሊትዉድ ታውን ክለብ ደጋፊዎች በዘንድሮው የካራባዎ ካፕ (Carabao Cup) የእጣ ድልድል መርሃግብር ላይ ከታላቁ አርሰናል ጋር መድረሳቸው ሲረጋገጥ፣ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ በጩኸትና በሆታ ሲገልፁ ታይተዋል።

✅ ይህ ክስተት የእንግሊዝ የጥሎ ማለፍ ውድድሮች (እንደ ካራባዎ ካፕ ያሉ) ልዩ ውበት ሲሆን፣ በታችኛው ዲቪዚዮን ለሚገኙ ክለቦች እና ደጋፊዎች ከትላልቆቹ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ጋር መጫወት ምን ያህል ታሪካዊ እና አስደሳች አጋጣሚ እንደሆነ በግልፅ የሚያሳይ ነው።

✅ ለክለቡ ተጫዋቾችም ሆነ ደጋፊዎች ይህን መሰሉ ጨዋታ ከውድድርነቱ ባለፈ ትልቅ የልምድ ልውውጥ እና በክለባቸው ታሪክ ውስጥ የማይረሳ የእግር ኳስ ትዝታን ጥሎ የሚያልፍ ይሆናል።

💬እንደምትሸነፍ እያወክ እንኳን ከአርሰናል ጋር መጫወት ያስደስታል🔴⚪

🗣️ የሲውዲን ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ግራሃም ፖተር ስለ ቪክቶር ዮኬሬሽ፦ 🇸🇪❤️🎙“ቪክቶር ላይ የተወሰነ የአቋም መውረድ አለ ይህ ደሞ እንዲህ ያሉ ጊዜያት በማንኛውም እግር ኳስ ተጫዋች ላይ...
17/09/2026

🗣️ የሲውዲን ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ግራሃም ፖተር ስለ ቪክቶር ዮኬሬሽ፦ 🇸🇪❤️

🎙“ቪክቶር ላይ የተወሰነ የአቋም መውረድ አለ ይህ ደሞ እንዲህ ያሉ ጊዜያት በማንኛውም እግር ኳስ ተጫዋች ላይ ይከሰታሉ አንዳንድ ጊዜ አቋምህ ይወርዳል፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ይመለሳል።"

🎙ቪክቶር የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ነው አርሰናልን ከ22 አመታት የሊጉ ሻምፒዮን እንዲሆን ካስቻሉ ተጫዋቾች አንዱ ነው ባለፈው ሲዝን ለአርሰናል 9 ቁጥር ቦታ ላይ ተጫውቶ ብዙ ጎሎችን አስቆጥሯል።"

🎙"ለብሄራዊ ቡድናችንም በማጣሪያ ጨዋታዎቹ ላይ እጅግ የሚያስደንቅ አቋም አሳይቷል፣ በዓለም ዋንጫውም ጥሩ ጨዋታ አድርጓል።”

❤️🇸🇪 “ቪክቶርን እንወደዋለን አሁንም የቡድናችን ቁልፍ ተጫዋች ነው የቀድሞ ፎርሙን መልሶ ማግኘት እንደሚችል ሙሉ ለሙሉ እርግጠኛ ነኝ ስዊዲንም በሜዳ ላይ ዳግም ደስታውን እንዲያገኝ የሚያግዙትን ሁኔታዎች ለመፍጠር ትሰራለች። 💪⚽

🔴⚪️ ውድ የአርሰናል ቤተሰቦች ቪክቶር ዮኬሬሽ በቅርቡ ወደ ምርጥ አቋሙ ይመለሳል ብላችሁ ታምናላችሁ? 👀❤️

🚨🔴⚪️ 𝐎𝐅𝐅𝐈𝐂𝐈𝐀𝐋: አርሰናል ቪንሰንት ጆሴፍን አስፈረመ!አርሰናል የእንግሊዝ U16 ቡድን ተስፈኛ አጥቂ ቪንሰንት ጆሴፍን ለ2026/27 የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ዓመት ስኮላርሺፕ ቡድኑ ...
17/09/2026

🚨🔴⚪️ 𝐎𝐅𝐅𝐈𝐂𝐈𝐀𝐋: አርሰናል ቪንሰንት ጆሴፍን አስፈረመ!

አርሰናል የእንግሊዝ U16 ቡድን ተስፈኛ አጥቂ ቪንሰንት ጆሴፍን ለ2026/27 የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ዓመት ስኮላርሺፕ ቡድኑ አባል አድርጎ አስፈርሟል። ❤️

ጆሴፍ ከሊቨርፑል የመጣ ሲሆን፣ ባለፈው የውድድር ዘመን በU18 ደረጃ በጥሩ አጀማመር ጀምሮ 3 ጎሎችን በመጀመሪያዎቹ 2 ጨዋታዎቹ አስቆጥሯል። 🔥

ነገር ግን የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ሪከርዱ የበለጠ ያስደንቃል፦

🏴 9 ጨዋታዎች
⚽ 8 ጎሎች
🅰️ 1 አሲስት

በአርሰናልም የብሔራዊ ቡድን አጋሮቹ ኤመርሰን ንዋኔሪ እና ቻርሊ ፊሊፕስን ያገኛል። በተለይም ከንዋኔሪ ጋር ለእንግሊዝ ወጣት ቡድን ሲጫወቱ ያላቸውን ጥምረት በአርሰናል ለማሳደግ እድሉን ያገኛሉ። 🤝🔴⚪️

🌟 አርሰናል በአካዳሚው ውስጥ ወጣትና ተስፈኛ ተጫዋቾችን ማሰባሰቡን ቀጥሏል።

እስካሁን ገና ብዙ የሚቀረው ቢሆንም፣ በ9 የእንግሊዝ U16 ጨዋታዎች 8 ጎሎች ማስቆጠር መቻሉ በእርግጥ ትኩረትን ይስባል! 👀🔥

❤️🤍 እንኳን ደህና መጣህ፣ ቪንሰንት ጆሴፍ!

𝐖𝐄𝐋𝐂𝐎𝐌𝐄 𝐓𝐎 𝐀𝐑𝐒𝐄𝐍𝐀𝐋! 🔴⚪️

🚨🏆 𝗕𝗥𝗘𝗔𝗞𝗜𝗡𝗚 𝗡𝗘𝗪𝗦!🇫🇷 William Saliba 🌟🔥🚨🔴⚪️ 𝐁𝐈𝐆 𝐖𝐈𝐋𝐋𝐘 𝐈𝐒 𝐁𝐀𝐂𝐊! 😍📈ዊሊያም ሳሊባ ዛሬ ጠዋት ወደ ሶብሃ ሪያልቲ የልምምድ ማዕከል በፈገግታ ተመልሷል። 💪❤️❇️...
17/09/2026

🚨🏆 𝗕𝗥𝗘𝗔𝗞𝗜𝗡𝗚 𝗡𝗘𝗪𝗦!🇫🇷 William Saliba 🌟🔥

🚨🔴⚪️ 𝐁𝐈𝐆 𝐖𝐈𝐋𝐋𝐘 𝐈𝐒 𝐁𝐀𝐂𝐊! 😍

📈ዊሊያም ሳሊባ ዛሬ ጠዋት ወደ ሶብሃ ሪያልቲ የልምምድ ማዕከል በፈገግታ ተመልሷል። 💪❤️

❇️ከጀርባ ጉዳቱ ማገገሚያ ሂደቱን እያሳደገ በጂም ውስጥ የጥንካሬና የአካል ብቃት ልምምዱን ጀምሯል።

▫️ግድግዳው ዊሎ በጥሩ መንፈስ መመለሱ ትልቅ ዜና ነው። ❤️

⏳ እስካሁን የዊሎ የመመለሻ ቀን አልተወሰነም አርቴታም የማገገም ሂደቱን መጠበቅና ትክክለኛውን ጊዜ ማክበር እንደሚገባ ተናግሯል።

🔥 ነገር ግን ይህ ለሳሊባ መመለስ ትልቅ እርምጃ ነው!

❤️🤍 እንኳን ደህና መጣህ፣ ቢግ ዊሊ!

𝐖𝐄 𝐌𝐈𝐒𝐒𝐄𝐃 𝐘𝐎𝐔! 🔴⚪️

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አርሰናል daily fans page በኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category