Ethio Live Events

Ethio Live Events

Share

Mule

09/12/2024

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል የተደረሰው የሠላም ስምምነት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የጎላ ሚና ያለው ነው ሲሉ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህራን ተናገሩ።

ሌሎች ታጣቂ ሀይሎችም ከጠመንጃ ይልቅ የሰለጠነ አማራጭን ሊከተሉ እንደሚገባ ምሁራኑ ጠቁመዋል።

ሆሳዕና፦ 30/03/2017 ዓ.ም (ሀድያ ቴሌቪዥን)

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አመራር የነበሩት ሰኚ ነጋሳ ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ጋር በቅርቡ የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል።

የስምምነቱን ፋይዳ በተመለከተ ለሀድያ ቴሌቪዥን አስተያየታቸውን የሰጡት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህራን የሆኑት መምህር ጌታሁን አበራ እና መምህር ሙሉጌታ አስፋው፤ የሰለም ስምምነቱ ለሀገሪቱ ሰላም እና ልማት መረጋገጥ ያለው አስተዋጽኦ ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸዋል።

በትምህርት ክፍሉ የሰላምና ግጭት አፈታት መምህር ጌታሁን አበራ የሰላም ስምምነቱ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲረጋጋ፣ ሰዎች ከቦታ ወደ ቦታ ያለ ስጋት እንዲንቀሳቀሱ እንዲሁም የቀድሞ ታጠቂ ሀይሎች ለሀገራቸው ልማት የበኩላቸውን እንዲወጡ በር የሚከፍት ነው ብለዋል።

ስምምነቱ ሌሎች ታጠቂ ሀይሎችም የሰላም አማራጭን እንዲከተሉ በር የሚከፍት መሆኑንም መምህር ጌታሁን ጠቁመዋል።

ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው ያሉት መምህር ጌታሁን የክልሉ መንግስትና ታጣቂ ቡድኑ ለሰላም ቅድሚያ በመስጠታቸው ሊመሰገኑ ይገባልም ብለዋል።

ሰላም በአንድ ጀንበር አይገነባም ያሉት መምህር ጌታሁን ሁሉም አካል ሰላምን ሊንከባከብ እና ለሰላም ዘብ መቆም እንደሚገባም አንስተዋል።

በዩኒቨርሲቲው በተመሳሳይ የትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት መምህር ሙሉጌታ አስፋው፤ የሰላም ስምምነቱ ለሀገር ሰላም እና ልማት ያለውን አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ነው የሚለውን የባልደረባቸውን ሀሳብ አጠናክረዋል።

ኦሮሚያ ክልል የሀገሪቱ እምብርት ላይ የሚገኝ ክልል እንደመሆኑ በክልሉ ውስጥ የሚፈጠሩ የሰላም ችግሮች የሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ላይ አሉታዊ ጫና የሚያሳድር መሆኑን ጠቁመዋል።

በመሆኑም በክልሉ መንግስትና በሰኚ ነጋሳ በሚመራ ታጣቂ ሀይል መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ለኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያዊያን እፎይታን የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሰላም የሁሉም ነገር ቁልፍ መሆኑን የጠቆሙት መምህር ሙሉጌታ፤ ሁለቱም ሀይሎች ችግሮችን በሰላም ለመፍታት የወሰኑት ውሳኔ ኢትዮጵያ የምታተርፍበት መሆኑን ጠቁመዋል።

በወንድማማቾች መካከል በሚደረግ ውጊያ የሚመለስ የፖለቲካ ጥያቄ የለም ያሉት መምህር ሙሉጌታ፤ ሁለቱ ሀይሎች አለመግባባትን በሰላም ለመፍታት መወሰናቸው ይበል የሚያሰኝ ነው ብለዋል።

ምሁራኑ እንደተናገሩት ሁለቱ አካላት ስምምነት ከመፈራረማቸው ባሻገር በስምምነቱ የተነሱ ሀሳቦችን ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆን አለባቸው።

በመሳሪያ ጥያቄያቸውን ለማስመለስ ጥረት የሚያደርጉ ሌሎች ታጣቂ ሀይሎችም፤ የሰላም አማራጭን ሊከተሉ እንደሚገባ ምሁራኑ ጠቁመዋል።
live events

Photos from Ethio Live Events's post 17/09/2024

በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) በአደረባቸው ህመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

የፕሮፌሰር በየነን ሕልፈተ-ሕወት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡

በአስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልዕክትም÷ በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) በኢትዮዽያ ገንቢ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምልክት ነበሩ ብለዋል።

ረዘም ላለ ጊዜ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስሰማ ከልብ አዝኛለሁ ሲሉም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ያቆዩት ውርስ እና ቅርስ ፀንቶ እንዲቀጥል ነፍሳቸውም በሰላም እንድታርፍ እመኛለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)።

Photos from Ethio Live Events's post 22/01/2024

የቀብር ሥነ-ስርዓቱ ተፈፀመ

* ebs - በሰበአዊነት ለአደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እጅ እንነሳለን

| የአንጋፋው ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ የቀብር ስነ-ስርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ተፈፀመ፡፡

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ባደረበት ህመም በአሜሪካ ሕክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ባለፈው ሳምንት ሕይወቱ ማለፉ ይታወቃል፡፡

በአሜሪካ የተለያዩ መርሃ ግብሮች ከተከናወኑ በኋላ ዛሬ ማለዳ የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ አስከሬን አዲስ አበባ የገባ ሲሆን÷ የሙያ አድናቂዎቹ፣ የስራ ባልደረቦቹ እና የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።

በሚሊኒየም አዳራሽም የስንብት መርሐግብር ከተካሄደ በኋላ በመንበረ ጸባኦት ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ቤተሰቦቹ፣ የሙያ አድናቂዎቹ፣ የስራ ባልደረቦቹ በተገኙበት የፍትሃት እና የቀብር ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡

Photos from Ethio Live Events's post 22/01/2024

የአስፋዉ መሸሻ አስክሬን አዲስአበባ ገባ።

19/01/2024

ዛሬ ጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም ካዲስኮ አደባባይ አለፍ ብሎ ያጋጠመ የትራፊክ አደጋ ነዉ። በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱን ከአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመክታል።

አሽክርክር ረጋ ብለህ አትቸኩል ትደርሳለህ ዘና ብለህ

Photos from Ethio Live Events's post 19/01/2024

የአስፋው መሸሻ ስንብትና ጸሎተ ፍታት

| የአስፋው መሸሻ የጸሎተ ፍትሃት ስነስርዓት ሜሪላንድ በሚገኘው የደብረ ገነት መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን ተካሂዷል። በዚህ ስነስርዓት ላይ ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል፡ የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን ጨምሮ በዲሲ፣ ቨርጂኒያና ሜሪላንድ የሚገኙ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት የሃይማኖት አባቶች ተገኝተው ጸሎት ፍትሃቱን መርተዋል።

ትላንትና እና ዛሬ በቨርጂኒያ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አዳራሽ የስንብት፣ የማስተዛዘንና የጸበል ጸዲቅ ዝግጅቶችም ተካሂደዋል።

በሁለቱም ቀናት በተካሄዱት ስንስርዓቶች ተገኝታችሁ በአስፊቲ ዕልፈት ሃዘናችሁን የገለጻችሁ፣ ለቤተሰቦቹ መጽናናትን የተመኛችሁና፣ ለዝግጅቶቹ መሳካት መልካም ትብብራችሁን ለቸራችሁ ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።

Photos from Ethio Live Events's post 17/01/2024

አርባምንጭ በጥምቀት ዋዜማ

Photos from Ethio Live Events's post 14/01/2024

ነብስህ በሰላም ትረፍ አስፊቲ !!!!

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Christ Army International Church
Addis Ababa
MULE