Dynamic Fitness/ዳይናሚክ ፊትነስ

Dynamic Fitness/ዳይናሚክ ፊትነስ

Share

FEEL åŵëšőmé. LIVE HEALTHY.BE WELL!

03/10/2023

ውድ የዳይናሚክ ፊትነስ ቤተሰቦች የወንድማችንን የ አብዮት አበበን ህልፈተ ህይወት አስመልክቶ ነገማታ 12:00ማለትም በ23/1/16 የሻማ መብራት ስነሰርአት ስለምናደር እምትችሉ መታቹ የሀዘናችን ተካፋይ እንድትሆኑን በአክብሮት እንጠይቃለን ።

Photos from Dynamic Fitness/ዳይናሚክ ፊትነስ's post 30/09/2023

📌የሀዘን መግለጫ
የቀድሞ የዳይናሚክ ፊትነስ ቤተሰብ የሆነው ወንድማችን አብዮት አበበ ከዚህ አለም በሞት ተለይቶናል። ለማመን ይከብዳል የ አቢን ሞት መስማት። ፈጣሪ የወንድማችንን ነብስ ይማርልን።🙏🙏🙏

Photos from Dynamic Fitness/ዳይናሚክ ፊትነስ's post 14/08/2023

ሰላም ለናንተ ውድ የዳይናሚክ ቤተሰቦች በ7/12/15 በ ሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር የነበረን ጉብኝት በግሩም ሁኔታ የተካሄደ ሲሆን የነበራቹና የበኩላችሁን አስተዋፆ ያደረጋቹ በሙሉ ቀና ልብ ቸር እጅ ነውና ያላቹ አምላክ ጨምሮ ጨምሮ ይስጣቹ፣ ። ከታሰበው በላይ በጥሩ ሁኔታ የተሰበሰበ ሲሆን የአመቱን መጨረሻ በጥሩ የበጎ አድራጎት ተግባር ፈፅመናል። ይህም እንዲሳካ በተለያየ ነገር ያገዛቹና ሳስቱ የበኩላቹን አስተዋፅዖ ያደረጋችሁ በሙሉ ቀጣዮም አመት ያሰባችሁት የሚሳከበት ያርግላቹ።🙏🙏🙏

Photos from Dynamic Fitness/ዳይናሚክ ፊትነስ's post 14/08/2023

በ 9/11/15 የነበረን የ outdoor exercise በጥሩ ሁኔታ ተካሄዶ ነበር የሚቀጥልም ይሆናል።

Photos from Dynamic Fitness/ዳይናሚክ ፊትነስ's post 14/08/2023

ሰላም ለናንተ ውድ የዳይናሚክ ቤተሰቦች። በ 24/10/15 በ ወዳጅነት ፓርክ የነበረን የ outdoor exercise በግሩም እና በደማቅ ሁኔታ የተካሄደ ሲሆን የ ሻመፒዮን ፣ዲአፍሪክስ እና የአዶቲና ጂም ስፓርተኞች ተገኝተው በህብረት ጥሩ እንቅስቃሴ ተሰርቷል።

Photos from Dynamic Fitness/ዳይናሚክ ፊትነስ's post 14/08/2023

በ 20/9/15 የነበረን የ outdoor እንቅስቃሴ በ ግሩም ሁኔታ የተካሄደ ሲሆን በሁሉም ጥያቄ መሰረት በቀጣይ ወርም የሚደገም ይሆናል።

Photos from Dynamic Fitness/ዳይናሚክ ፊትነስ's post 20/04/2023

በ 24/7/15 በ እንጦጦ ፓርክ የነበረን የ እግር ጉዞ/Hiking /በ ግሩም ሁኔታ ተካሄዷል። በ እግር ጉዟችን የ እንጦጦን ውብ ተፈጥሮን እየተመለከትን፤ እንደ እርጎ የወፈረ ንፁህ አየራችንን እየማግን ፤የተለያዮ አዝናኝ ጨዋታዎችን እየተጫወትን ጥሩ ትውስታን ለመያዝ ችለናል። በ እግር ጉዞ/Hiking / በመሳተፍ የ እግር ጉዞው ድምቀት የሆናቹ በሙሉ ሰላማቹ ይብዛ።😊🙏

Photos from Dynamic Fitness/ዳይናሚክ ፊትነስ's post 08/03/2023

ሰላም ለናንተ ውድ የዳይናሚክ ፊትነስ ቤተሰቦች የምንግዜም ኩራት የሆኑት የ ዳይናሚክ ፊትነስ ስፖርተኞች የአዲስ አበባ ከተማ ክብደት ማንሳትና ሰውነት መገንባት ፌዴሬሽን በካቲት 22/2015 ዓ.ምያዘጋጀው የክብደት ማንሳት ሻምፒዮና ውድድር በጃን ሜዳ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል የተካሄደ ሲሆን ከ55 ካታጎሪ በወንድ በቀለ ጋንች ከቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ከለብ 1ኛ አልአዛር ሃብታሙ እና ሰኢድ አብዱልፈታ 2ኛ እና 3ኛ ሲወጡ በ64 ካታጎሪ ሴት ሕይወት ገለቱ ከላም ስፖርት ክለብ 1ኛ ስትሆን ክርስቲና ቀነኒሳ ከዳይነሚክስ ፊትነስ 2ኛ መሆን ችላለች።

ውድድሩ በ61 ካታጎሪ በወንድ በአምላክ ንጉሴ ኃይለማርያም ሐይሉ እና ዮሴፍ ያሻ ከዳይናሚክ ፊትነስ በቅደም ተከተል ከ1ኛ እስከ 3ኛ ሲወጡ በ67 ካታጎሪ ወንድ ብሩክ አለማየሁ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ሚኪያስ ሃብታሙ እና ልዑል ደረጀ 2ኛ እና ሦስተኛ በመሆን አጥናቀዋል።

በ81 ኪሎ ካታጎሪ ወንድ የቅዱስ ጊዮርጊሱ ተመስገን ዜና 1ኛ የአብስራ ጌታቸው ከዳይነሚክስ ፊትነስ 2ኛ በመሆን አጠናቋል።

በ89 የኪሎ ካታጎሪ ወንድ የትምጌታ ክንፉ ከቅዱስ ጊዮርጊስ 1ኛ ቸርነት ባሕሩ ከሰም 2ኛ ሲሆኑ የዳይነሚክሱ ሚኪያስ ጥላሁን 3ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል።

Photos from Dynamic Fitness/ዳይናሚክ ፊትነስ's post 27/01/2023

ሰላምን ለናንተ ውድ የዳይናሚክ ፊትነስ ቤተሰቦች ዮሴፍ ያሻን የዓመቱ ምርጥ ለውጥ/Dynamic Change/ ያመጣ ሰው ላስተዋውቃቹ። ከ 74ኪሎ ወደ 61.5 ኪሎ የተደረገ ጉዞ🏃‍♂🏃‍♂።
ይሄ ነው (ዲሲፕሊን ) ማለት💪💪። የካቲት ወርን የነፃ የወር ክፍያ አግኝተሀል። Keep it up👍
አስታውሱ!!
በአካል ብቃት እንቅስቃሴዎ ውስጥ ምንም ያህል ጊዜ አጭር ቢወጡም ወይም እድገትዎ የቱንም ያህል ቀርፋፋ ቢሆንም፣ እናንተ ካልጀመሩት ሁሉ በጣም የተሻላቹ ናችሁ ።
ዛሬ ሊጎዳቹ ይችላል ወይም ህመም ሊኖረው ይችላል, ነገር ግን ነገ ጠንካራ ትሆናላችሁ ።.
እራሳቸሁን ወደ ገደቡ ለመግፋት ፍቃደኛ ካልሆናቹ በስተቀር ሰውነታችሁ ምን ማድረግ እንደሚችል በፍፁም አታውቁም።
በህይወታችሁ ላይ ቀናት ለመጨመር አትሰለጥኑም። በምትኩ፣ በቀናትዎ ላይ ህይወት ለመጨመር እንጂ።

Photos from Dynamic Fitness/ዳይናሚክ ፊትነስ's post 17/01/2023

ሰላም ለናንተ ውድ የ ዳይናሚክ ቤተሰቦች ለ ሆስፒታል ማስገምቢያ የሚውል በ7/5/15 በሬስ 4 ኤቨር (Race 4 ever) የ5 ኪሎ ሜትር የተዘጋጀው ሩጫ ላይ በመሳተፍ አጋርነታችንን አሳይተናል። በዚህ የ መልካም ተግባር ላይ የተሳተፋቹ የምንግዜም ኩራት የሆናቹ የዳይናሚክ ፊትነስ ቤተሰቦች ክብረት ይስጥልን ምስጋና ይገባችኋል። አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ የሚያሰራው ሆስፒታል በሰላም አልቆ ለማየት ያብቃን።መልካሙን አስቧልና መልካሙን ነገር ያብዛለት🙏።

17/01/2023

ፓርኩ የሚገኝበት አካባቢ (ማለትም በአቅራቢያው ያሉት ሞገሌ፣ አደሬና ዳሞቻ የተባሉ ተራራዎችንም የያዘው) አካባቢ ወጨጫ ይባላል፡፡ በሆለታ አልያም በሰበታ መስመር ወደ ፓርኩ መሔድ የሚቻል ሲሆን፡ ፤ ፓርኩ ከጥቂት ዓመታት በፊት በፌደራል አስተዳደር ሥር መናገሻ ሱባ ፓርክ በሚል ይተዳደር ነበር፡፡ አሁን ሱባ ሰበታ ዲስትሪክት ፓርክ የሚል በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሥር ይገኛል፡፡

ከባህር ወለል በላይ ከ2,200 እስከ 3,385 ሜትር ከፍታ ላይ በሚገኘው ፓርኩ 186 የአዕዋፋት ዝርያዎች ይኖራሉ፡፡ ግንደ ቆርቁር (አቢሲኒያን ዉድ ፓከር)፣ አቢሲኒያን ካት በርድ፣ ብላክ ሔርድ ሲስኪንና የሎ ፍሮንትድ ፓሮት የተባሉት ዝርያዎች አገር በቀል ናቸው፡፡ ፓርኩ ከ32 በላይ የሚሆኑ አጥቢዎች መኖሪያም ነው፡፡ 12 ከሚደርሱት ትናንሽ አጥቢ እንስሳቶች፣ ኋይት ሩትድ ራት (እግረ ነጭ ፍልፍል) እና 20 ከሆኑት ትልልቅ አጥቢዎች ደግሞ የምኒልክ ድኩላ አገር በቀል ናቸው፡፡

በፓርኩ ከ70 ዓይነት በላይ ዕፅዋት ያሉ ሲሆን፣ ጽድ፣ ወይራ፣ ጥቁር እንጨትና ዝግባ ይጠቀሳሉ፡፡ በፓርኩ ያሉ ዕፅዋት እርስ በእርስ ተሳስረው ስለሚታዩ ‹‹ጁኒፐር ኦልያ ቤልት›› የሚል ቅፅል ስም ተሰጥቷቸዋል፡፡ በፅዶቹ ሥር የበቀሉ ወይራዎች በፅዶቹ ላይ መጠምጠማቸው ይጠቀሳል፡፡

በፓርኩ አራት ካምፕ ሳይቶች (ጐብኚዎች እንደማረፊያ የሚጠቀሙባቸው) ቦታዎች አሉ፡፡ የመጀመርያው በፓርኩ መግቢያ የሚገኘው ሳይት ሲሆን፣ ኤግዚቢሽን ሴንተር ሌላው ነው፡፡ ገበር ካምፕ ሳይት፣ መልካ ኢትዮጵያ ሰኚ ለተሠኘው ፕሮጀክቱ የሚጠቀምበት ነው፡፡ ሞሩ ካምፕ ሳይት የተባለው የሎ ፍሮንትድ ፓሮትን የመሰሉ አዕዋፋት እንዲሁም ጅብ፣ ነብርና የዱር ድመትን የመሰሉ እንስሳትን ለመመልከት የተመቸ ነው፡፡ ጃንሆይ ካምፕ ሳይት በሚል የሚታወቀው ሳይት፣ ቀድሞ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለማረፊያ ይጠቀሙበት የነበረ ነው፡፡

ፓርኩ አራት ዋና ዋና መንገዶች አሉት፤ በመኪና በእግር ወይም በሳይክል የሚኬድባቸውም ናቸው፡፡ ጦና መንገድ በአንድ ወቅት የፓርኩ ጥበቃ ሠራተኛ በነበሩና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ባበረከቱ ግለሰብ ስም የተሰየመ መንገድ ነው፡፡ አራት መንታ የባቡር ሐዲድ መስመርና የእንጨት መሰንጠቂያው የሚገኝበት እንዲሁም የምኒልክ ድኩላ በብዛት የሚታይበት ነው፡፡ ኦልድ ትሪ መንገድ ረዥም ዕድሜ ያለው ዛፍ መገኛ ሲሆን፣ ዋናው መንገድ ወደ አደሬ፣ ሞግሌና ዳሞቻ ተራራዎች ይወስዳል፡፡ በጉዞ ዘለግ ያለ ጊዜ (ወደ 4፡30 የሚወስደው) ደግሞ ፏፏቴው መንገድ ነው፡፡

ባጭሩ በዚህ ታሪካዊና ውብ ስፍራ የማይረሳ ድንቅ ጊዜ እንደሚኖረን ሙሉ እምነት አለኝ!!

17/01/2023

ወዳጆች እሁድ ስለምትጎበኙት ስፍራ ያለችኝን ጥቂት ግንዛቤ ካነበብኩት ተነስቼ ላካፍላችሁ።

ሱባ መናገሻ ጥብቅ ደን በአፍሪካ ቀዳሚው ፓርክ።
Suba Forest the oldest park in Africa.

ከ9,000 ሔክታር በላይ በሆነ መሬት የተንጣለለው ሱባ ፓርክ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ታሪካዊ ፓርኮች አንዱ ሲሆን፣ በብዝሀ ሕይወት ከበለፀጉ ስፍራዎች መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡ በአፍሪካ ካሉ ፓርኮች ዕድሜ ጠገቡ እንደሆነም ይነገርለታል፡፡ ፓርኩ የተመሠረተው በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፣ በአጼ ዘርዐ ያዕቆብ
ንግሥና ወቅት ነበር፡፡ ንጉሡ በወቅቱ ባዶ የነበረውን አካባቢ በዕፅዋት የሞሉት ወፍ ዋሻ ከተባለ ስፍራ ባስመጧቸው የዕፅዋት ዝርያዎች ነበር፡፡

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ1900 ዓ.ም. የጥብቅ ደን አዋጅ ባስነገሩበት ጊዜ በአዋጁ ከተካተቱ ውስጥ ይኸው ፓርክ አንዱ ነው፡፡ በአገሪቱ ግንባር ቀደም የሚባለው የችግኝ ጣቢያ የተቋቋመው በፓርኩ እንደሆነ ይነገራል፡፡
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የስልጣን ዘመን የተተከለው ሱክያ (አይረን ውድ) የተሰኘ ዛፍ ሱባን ከሌሎች ፓርኮች ልዩ ያደርገዋል፡፡
ዛፉ ፍሬ የሚሰጠው በ70 ዓመቱ ሲሆን፣ ለንጉሡ 70ኛ ዓመት የልደት በዓል ከተበረከቱ ስጦታዎች አንዱ ነበር፡፡

በፓርኩ 500 ዓመት የሆነው (በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተተከለ) የፅድ ዛፍ ይገኛል፡፡ በፓርኩ ታሪክ አይረሴ ከሆኑት በ1892 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ የገባው የእንጨት መሰነጠቂያ ይነሳል፡፡ በእንፋሎት ኃይል የሚሠራው ማሽኑ የተተከለው፣ ለመኳንንት የሚሆኑ ቤቶችን ለማዘጋጀት የሚውሉ እንጨቶች እንዲሰነጠቁበት ታልሞ ነበር፡፡ ማሽኑ ከተተከለ በኋላ ለ30 ዓመታት ያህል ወደ 1,600 ሔክታር የሸፈኑ ዕፅዋት ተቆርጠዋል፡፡ ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ደግሞ ሁለት ዓመት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ 3,500 ሔክታር የሚሆን ደን እንደተጨፈጨፈ ይናገራል፡፡ እንጨቱን ከቦታ ቦታ ለማጓጓዝም የባቡር ሐዲድ ተተክሏል፡፡

በወቅቱ ደኑ የደረሰበት ጭፍጨፋ በፓርኩ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ እንጨት መሰንጠቂያው በፓርኩ ታሪክ ላይ ጥቁር ጠባሳ ቢጥልም፣ በታሪካዊነቱ ለጐብኚዎች ዕይታ ይቀርባል፡፡

ፓርኩ የሚገኝበት አካባቢ (ማለትም በአቅራቢያው ያሉት ሞገሌ፣ አደሬና ዳሞቻ የተባሉ ተራራዎችንም የያዘው) አካባቢ ወጨጫ ይባላል፡፡ በሆለታ አልያም በሰበታ መስመር ወደ ፓርኩ መሔድ የሚቻል ሲሆን፡ ፤ ፓርኩ ከጥቂት ዓመታት በፊት በፌደራል አስተዳደር ሥር መናገሻ ሱባ ፓርክ በሚል ይተዳደር ነበር፡፡ አሁን ሱባ ሰበታ ዲስትሪክት ፓርክ የሚል በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሥር ይገኛል፡፡

ከባህር ወለል በላይ ከ2,200 እስከ 3,385 ሜትር ከፍታ ላይ በሚገኘው ፓርኩ 186 የአዕዋፋት ዝርያዎች ይኖራሉ፡፡ ግንደ ቆርቁር (አቢሲኒያን ዉድ ፓከር)፣ አቢሲኒያን ካት በርድ፣ ብላክ ሔርድ ሲስኪንና የሎ ፍሮንትድ ፓሮት የተባሉት ዝርያዎች አገር በቀል ናቸው፡፡ ፓርኩ ከ32 በላይ የሚሆኑ አጥቢዎች መኖሪያም ነው፡፡ 12 ከሚደርሱት ትናንሽ አጥቢ እንስሳቶች፣ ኋይት ሩትድ ራት (እግረ ነጭ ፍልፍል) እና 20 ከሆኑት ትልልቅ አጥቢዎች ደግሞ የምኒልክ ድኩላ አገር በቀል ናቸው፡፡

በፓርኩ ከ70 ዓይነት በላይ ዕፅዋት ያሉ ሲሆን፣ ጽድ፣ ወይራ፣ ጥቁር እንጨትና ዝግባ ይጠቀሳሉ፡፡ በፓርኩ ያሉ ዕፅዋት እርስ በእርስ ተሳስረው ስለሚታዩ ‹‹ጁኒፐር ኦልያ ቤልት›› የሚል ቅፅል ስም ተሰጥቷቸዋል፡፡ በፅዶቹ ሥር የበቀሉ ወይራዎች በፅዶቹ ላይ መጠምጠማቸው ይጠቀሳል፡፡

በፓርኩ አራት ካምፕ ሳይቶች (ጐብኚዎች እንደማረፊያ የሚጠቀሙባቸው) ቦታዎች አሉ፡፡

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Addis Ababa
11396254

Opening Hours

Monday 05:00 - 21:00
Tuesday 05:00 - 21:00
Wednesday 05:00 - 21:00
Thursday 05:00 - 21:00
Friday 05:00 - 21:00
Saturday 05:00 - 21:00
Sunday 05:00 - 21:00