Ethiopian Table Tennis Federation

Ethiopian Table Tennis Federation

Share

This is Official Face book page of Ethiopian Table Tennis Federation!! Follow and Like for updated information.

23/04/2026

"Happy World Table Tennis Day! 🏓🌍

Celebrating the sport we love today and every day. Let’s play!

የአለም ጠረጴዛ ቴኒስ ቀን ለሁላችሁም እንኳን አደረሳችሁ! 🇪🇹

"

Photos from Ethiopian Table Tennis Federation's post 31/03/2026

19 ኛው ሃገር አቀፍ የፌደራል መንግስት ሰራተኞች የጠረጴዛ ቴኒስ ስፖርት ውድድር በአዲስ ከተማ ወወክማ እየተካሄደ ይገኛል።
10 የፌደራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሁለቱም ፆታ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ስፖርቱ ሰራተኞችን ከስራቸው ጐን ለጐን ጤናቸውን የሚጠብቁበት ፣ ትውውቅን እና ወዳጅነትን የሚፈጥሩበት ነው።
ፌዴሬሽኑ ለነዚህ መስሪያ ቤቶች ክለብ እንዲያቋቁሙ እና ስፖርቱን ወደተሻለ ደረጃ እንዲደርሶ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ ያስተላልፋል ።

ውድድሩ አርብ 25 07 2018 ዓ.ም ፍፃሜውን ያገኛል ።

Photos from Ethiopian Table Tennis Federation's post 12/02/2026

የወደፊቶቹ የጠረጴዛ ቴኒስ ኮከቦች በአዳማ! 🏓

በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ባለው የመጀመሪያው ሀገር አቀፍ ከ15 ዓመት በታች የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር ላይ የጠረጴዛ ቴኒስ ውድድሮች በቡድን እና በነጠላ በሁለቱም ፆታዎች መከናወን ጀምረዋል። በውድድሩ ላይ 6 የወንድ እና 5 የሴት ቡድኖች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ይህ ተሳትፎ በየክልሉ በሚገኙ ታዳጊ ስፖርተኞች ላይ በትኩረት መስራት አስፈላጊ መሆኑን በግልጽ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን ከዚህ ቀደም ከነበረው ሁኔታ አንፃር በዚህ ውድድር ላይ የተሻለ የእድሜ ተገቢነት ተከብሮ በመገኘቱ የተሰማውን ደስታ ገልጾ ለክልል አሰልጣኞች እና ለባለድርሻ አካላት ምስጋናውን አቅርቧል። ፌዴሬሽኑ ለሁሉም ተሳታፊ ስፖርተኞች መልካም የውድድር ጊዜን እየተመኘ ስፖርታዊ ጨዋነት የሰፈነበት ቆይታ እንዲሆንላቸው ይመኛል።

📅 የካቲት 2018 📍 አዳማ፣ ኢትዮጵያ



Future Table Tennis Stars Shine in Adama! 🏓

The first-ever National Under-15 Youth Sports Training Assessment Competition is currently taking place in Adama, where table tennis matches have officially commenced in both team and individual event for both genders. With 6 boys' teams and 5 girls' teams participating, this event highlights the vital importance of consistently investing in youth talent across all region.

The Ethiopian Table Tennis Federation has expressed its appreciation to regional coaches and stakeholders, noting that age eligibility standards have significantly improved in this competition compared to previous years. As the games continue, the Federation extends its best wishes to all young athletes for a successful and fair competitive season .

📅 February 2026 📍 Adama, Ethiopia

Photos from Ethiopian Table Tennis Federation's post 06/02/2026

በኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ላለፉት አምስት ቀናት ሲካሄዱ የቆዩ ውድድሮች ዛሬ ፍፃሜቸውን አገኙ።

ጥር 20፣ 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን የ2018ዓ.ም 1ኛ ዙር የክለቦች ሻምፒዮና ውድድርን በአራት የእድሜ ካታጎሪ በሁለቱም ፆታ እና ለመጀመሪያ ጊዜ 1ኛ ዙር የምርጥ 16 ውድድርን በሁለቱም ፆታ ከጥር 15-19/2018ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሲያካሂድ ቆይቶ ዛሬ በተካሄዱ የፍፃሜ ውድድሮች አጠቃላይ መርሀ-ግብሩን አጠናቋል።

11 ክለቦች የተሳተፉበት ውድድር በነጠላ ከ15 ዓመት በታች በወንድ ትንሳኤ ሞገስ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሴት እየሩሳሌም አያሌው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ ከ15 ዓመት በታች በቡድን በወንድ የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ፣ ከ19 ዓመት በታች በነጠላ በወንድ ለይኩን ኤፍሬም ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ እና በሴት ጅንካለም ጎሹ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እንዲሁም ከ19 ዓመት በታች በቡድን በወንድ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና በሴት ኦሜድላ ስፖርት ክለብ አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡

ከ40 ዓመት በታች በተደረጉ ውድድሮች በወንድ ነጠላ ደራራ መኮንን እና በሴት ፌቨን ታምሩ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊዎች ሆነዋል። በተመሳሳይ ከ40 ዓመት በታች በወንድ ቡድን በተደረገ ውድድር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በሴት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አሸናፊ ሆነዋል።

ከ40 ዓመት በታች በድብልቅ ወንድ እና ከ40 ዓመት በታች በጥንድ በወንድ እና በሴት በተደረጉ ውድድሮችም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊ ሆኗል፡፡ ።

በ2018ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው የምርጥ 16 ውድድርም በኢትዮጵያ የጠረጴዛ ቴኒስ ስፖርት በተጫዋችነት፣ በአሰልጣኝነትና በመሪነት ጉልህ አሻራ አሳርፈው ላለፉት ኢንስትራክተር ሀይለየሱስ አስፋው መታሰቢያነት እንደተካሄደ ፌዴሬሸኑ አስታውቋል።

በተያያዘም በዚህ የምርጥ 16 ውድድር የሚሳተፉት ተወዳዳሪዎች በ1ኛው ዙር የክለቦች ሻምፒዮና ተሳትፈው ባስመዘገቡት ውጤትና ከዚህ በፊት በተደረጉ ውድድሮች በነበራቸው ደረጃ የተመረጡ ስፖርተኞች በሁለቱም ፆታ ያለ እድሜ ልዩነት በውጤት እንዲወዳደሩ የተደረገበት መሆኑን ፌዴሬሸኑ በማሳወቅ ስፖርተኞች እርስ በርስ ልምድ የሚቀስሙበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እና በዓለም አቀፍ የጠረጴዛ ቴኒስ የውድድር ስታንዳርድ መሰረት ተተኪ የብሔራዊ ቡድን ስፖርተኞችን ለማፍራት ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በመጨረሻም በተለያየ የእድሜ እርከን በግልና በቡድን በተካሄዱ ውድድሮች አሸናፊ ለሆኑ ስፖርተኞቸ በየደረጃው የዋንጫ የሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶ በ2018ዓ.ም የክለቦች ሻምፒዮና ለተሳተፉ ክለቦችና ጨዋታውን ለመሩ ዳኞች የመስክር ወረቀት ተሰጥቶ አጠቃላይ አሸናፊ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ አንስቷል።

Photos from Ethiopian Table Tennis Federation's post 03/02/2026

የቶፕ 16 አሸናፊዎች (Top 16 Winners)
ታሪክ ተጻፈ! የመጀመሪያው የቶፕ 16 ውድድር ንጉሥና ንግሥት ታወቁ! 👑

በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደውና እጅግ አስደሳች የነበረው የ"ቶፕ 16" ውድድር በታላቅ ድምቀት ተጠናቋል። በኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ዓለም አዲስ ምዕራፍ የከፈቱት አሸናፊዎቻችን፦🏓

🏅 በወንዶች፡ እዮብ ሲሳይ – የጥንካሬ እና የክህሎት ተምሳሌት በመሆን አሸናፊነቱን አረጋግጧል!
🏅 በሴቶች፡ ፌቨን ታምሩ – ድንቅ ብቃቷን በማሳየት የንግሥትነቱን ዘውድ ደፍታለች!🇪🇹

ለአሸናፊዎቻችን ያለዎትን አድናቆት በኮሜንት ይግለጹላቸው! 👏🎊🏓🇪🇹

03/02/2026

የዩቲዩብ ቻናል ጥሪ (YouTube Launch)
የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ አሁን በእጅዎ ስልክ ላይ! 📱🇪🇹

የጠረጴዛ ቴኒስ ትዕይንቶች፣ አስደሳች ነጥቦች እና ታሪካዊ ውድድሮች እንዳያመልጥዎ! የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን በይፋ የዩቲዩብ ቻናሉን ከፍቷል።

ከዚህ በኋላ የሚደረጉ ታላላቅ ውድድሮችን በቀጥታም ሆነ በድጋሚ በቻናላችን ማግኘት ይችላሉ። አሁኑኑ ሰብስክራይብ በማድረግ የቤተሰባችን አባል ይሁኑ፤ ለወዳጅዎም ያጋሩ!🏓🇪🇹

🔗 ሰብስክራይብ ለማድረግ ሊንኩን ይጫኑ፦ https://youtube.com/?si=H--tbaGxY4lR_Vp_

RANK 2026 JANUARY 03/02/2026

🏓 የጥር 2018 የተጫዋቾች ደረጃ ወጥቷል! (Ranking Update) 🏓

🏆 የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ኮከቦች እነማን ናቸው?
የጥር ወርን በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ያጠናቀቁት ተጫዋቾች እነማን እንደሆኑ ያውቃሉ? 🇪🇹

📊 የተጫዋቾች የቅርብ ጊዜ የብቃት መለኪያ የሆነው
የጃንዋሪ 2026 የደረጃ ዝርዝር (Ranking) አሁን ይፋ ሆኗል 🇪🇹

⭐️ የእርስዎ ተወዳጅ ተጫዋች ስንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ይሆን?

👇 ሙሉውን ዝርዝር ለማየት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ

RANK 2026 JANUARY

27/01/2026

🏓 Big News! The Ethiopian Table Tennis Federation is launching the first Top 16 Tournament. 🇪🇹

The first ever Top 16 highest-ranked players in the nation. One stage. No room for error. Who will be the first-ever Top 16 Champion in both Gender? 🏆

🏓 ታላቅ ዜና! የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የምርጥ (Top 16) ውድድር እየተካሄደ ነው። 🇪🇹

በሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው 16 ተጫዋቾች።
አንድ መድረክ።
ለስህተት ቦታ የለም።
የመጀመሪያው የቶፕ 16 ሻምፒዮን ማን ይሆን? 🏆

22/01/2026

የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን የ20018 ዓ.ም የውድድር አመቱ ሁለተኛውን ውድድር ከጥር 15 - 19 የመጀመሪያ ዙር የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ሊያካሂድ ዝግጅቱን አጠናቋል ።

ውድድሩም በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ይካሄዳል።

15/01/2026

🏓 የ2ተኛ ደረጃ የብሔራዊ ዳኝነት ስልጠና ጥሪ (Level 2 National Umpire Training)
የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን የዳኞችን አቅም ለማሳደግ እና የዓለም አቀፍ ዳኝነት (ITTF Level 3/International Umpire) ዕጩዎችን ለማፍራት ያዘጋጀውን የደረጃ 2 ብሔራዊ ዳኝነት ስልጠና በቅርቡ ይጀምራል።

ፌዴሬሽኑ ለሁሉም የክልል ፌዴሬሽኖች በደብዳቤ ጥሪ ያስተላለፈ ሲሆን፣ በተጨማሪም ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸውን እና መስፈርቱን የሚያሟሉ ዳኞችን አወዳድሮ ማሰልጠን ይፈልጋል።

📅 የስልጠናው መርሃ-ግብር
የኦንላይን ስልጠና (በቴሌግራም)፦ ከጥር 8( አርብ) ጀምሮ።
የስልጠናው ሰዓት ከምሽቱ 1፡30 - 3፡30

የአካል ስልጠና (አዲስ አበባ)፦ ጥር 13 እና 14 (በአካል ተገኝቶ የሚሰጥ ተግባራዊ ስልጠና)።

📋 ሰልጣኞች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መሠረታዊ መስፈርቶች
ስማርት ስልክ፦ የቴሌግራም መተግበሪያን እና የቪዲዮ ኮንፈረንስ ሶፍትዌሮችን መጠቀም የሚችል ስልክ ወይም ላፕቶፕ ሊኖራቸው ይገባል።

የኢንተርኔት ግንኙነት፦ ለሁሉም የስልጠና ቀናት የሚሆን አስተማማኝ የኢንተርኔት አገልግሎት ማመቻቸት።

ተገኝቶ መከታተል፦ ሙሉ ስልጠናውን መከታተል ግዴታ ሲሆን፣ የስልጠና ሰዓት ያላከበረ ወይም የመጨረሻውን የብቃት መመዘኛ ፈተና ያላለፈ ሰልጣኝ የዕውቅና ሰርተፍኬት እንደማይሰጠው እናሳስባለን።

📑 የአመዘጋገብ ሂደት
ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች የትምህርት እና የዳኝነት ሠርተፍኬታችሁን በ +251946656428 ቴሌግራም ላይ እንዲትልኩ እንጠይቃለን።

ማሳሰቢያ፦ መመዝገብ ብቻውን ለስልጠናው መመረጥን አያረጋግጥም። ፌዴሬሽኑ ሰነዶችን መርምሮ መስፈርቱን የሚያሟሉትን ብቻ ለስልጠናው የሚጋብዝ ይሆናል።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address

Stifanos
Addis Ababa