11/06/2025
ሙሉጌታ ከበደ (ወሎየው) ህይወቱ አልፏል
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ደማቅ ታሪክ መጻፍ የቻለው ከምንጊዜም ኢትዮጵያውያን አጥቂዎች ቀዳሚው ሙሉጌታ ከበደ ባገጠመው ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ህይወቱ አልፏል።
ቅኝት በኳስ ሜዳ በሙሉጌታ ከበደ ህልፈተ-ህይወት የተሰማትን ሐዘን እየገለጸች ለመላው የስፖርት ቤተሰቦች መጽናናትን ትመኛለች።
08/01/2025
Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Ayenew Brilie Yigzaw, Helem Adem Suleymen, Muluken Bitew, Wegne Teshome Biruk Best
01/09/2024
ከወደ ሰከላ ሌላ ልዑል🙏🙏🙏
ከጌትነት ዋለ በሃላ ሌላ የመሰናክል አሸናፊ አግንተናል በርታልን!!!
ሃይሉ አያሌው!!!
አያሌው ፋሚሊ እንኳንደስ አላችሁ !!!!
16/06/2024
ቤተልሄም ሌላ ሀገር ብትሆን. ....
....
ሩቅ አይደለም ፡ ከሁለት ወራት በፊት
በጋና አክራ ውስጥ በተካሄደው የመላው አፍሪካ ውድድር ላይ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የወርቅ ሜዳሊያ በማምጣት ታሪክ ያስመዘገበች ወጣት ፡ ዛሬ ላይ. ..የሚያሳክማት ጠፍቶ የሰው ያለህ እያለች ነው ቢባል ማን ያምናል ?
ግን የሆነው ይኸው ነው ። ወጣቷ ቦክሰኛ ቤተልሄም ገዛኸኝ የጋናውን ውድድር አሸንፋ ከመጣች በኋላ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የማንዴላ ካፕ ውድድር ላይ የሀገሯን ....የኢትዮጵያን ስም ለማስጠራት ሄዳ ፡ በውድድሩ ላይ ባጋጠማት የትከሻ ውልቃት ምክንያት የሚያሳክማት አጥታ እነዛ የቦክስ ሪንግ ላይ የሚዘሉ እግሮቿ ታስረው አልጋ ላይ ከወደቀች ሰነባብቷል ።
( እዚህ ላይ ሌላው አስገራሚው ነገር በዚህ ጉዳት ባጋጠማት ውድድር ላይ እንኳን. . ቤተልሄም እንደዛ ሆና ለሀገሯ የብር ሜዳልያ አስገኝታለች )
....
ከደቂቃዎች በፊት ለዚህች ወጣት ደውዬ እንደተረዳሁት ፌዴሬሽኑ እሷን ለማሳከም የሚበቃ 500 ሺህ ብር የለኝም እንዳላት ፡ ሌላው ቀርቶ ስልኳን እንኳን ለማንሳት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ነግራኛለች ።
...
ይህ እንደ ሀገር አሳፋሪ ነገር ነው ። ይህች ልጅ የተጎዳችው ሀገሯን ለማስጠራት ታስቦ በተወዳደረችበት መድረክ ላይ ሆኖ ሳለ የፌዴሬሽኑ አያገባኝም ብሎ ፊቱን ማዞር ለቀጣይ ይህችን መሳይ ወጣት ስፖርተኞች ለማፍራት ያስቸግራል ።
....
ይህች ወጣት ስፖርተኛ በሌላ ሀገር ብትሆን ብለን ስናስብ ደግሞ ነገሩ ይበልጥ የሚያበሳጭ ነገር ነውና ፡ አቅምና መልካም ልብ ያላችሁ ደጋግ ሰወች ይህችን ወጣት በመደገፍ ፡ ጤናዋ ተመልሶ ዳግም ወደምትወደው ስፖርት እንድትመለስ እናግዛት ።
.......
ለሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን የወርቅ ሜዳልያ በማምጣት ታሪክ የሰራችውን ፡ ይህችን ተስፋ ያላት ወጣት ማውራትና መደገፍ ለምትፈልጉ ስልኳና የባንክ አካውንቷ ከስር ይገኛል ። ( ፖስቱን ሼር ባደርገው ሊጠቅማት ይችላል ካላችሁም ሼር በማድረግ ተደራሽ እናርገው )
ደውለን እናበረታታት ፡ በቻልነው መጠን በገንዘብ እንርዳት
0956354158 ምክትል ሳጅን ቤተልሔም ገዛኸኝ
1000193673426 CBE Betelhem Gezahegn
Via tesfaya !
20/05/2024
አሌሀንድሮ ጋርናቾ ኤቨርተን ላይ ያስቆጠራት ጎል የ BBC SPORT የአመቱ ምርጥ በመባል ተመርጣለች
20/05/2024
✍️ "የታላቅ ሰዉ ስንብት ' ስንብት ብቻ አይደለም ምክንያቱም ከሀዘኑ እኩል ኧረ እንዲያዉም በሚበልጥም ልክ በደስታ ልባችንን የሚያሞቁ ትዝታዎችንም ትቶልን ያልፋል። ነጮቹ ሲተርቱ "ስለተጠናቀቀ ማዘን ሳይሆን ስለተመለከትነዉ መደሰት አለብን!" እንደሚተሉት ነዉ።
.......ሊቨርፑል ብቻ ሳይሆን ፕሪሚየር ሊጉ እኚህን ሰዉ አጥቷል። ላለፉት 9የሚጠጉ የዉድድር አመታት ተወዳጁን የክለቦች ዉድድር ያደመቁት ሰዉ ከደመቁበት ፣ ከፈነጠዙበት ፣ ሀዘንን ብሎም በፅንፉ ታላቅ ደስታን ካዩበት ፤ ጎልምሰዉ እርጅናን ከጀማመሩበት ቤት እና ቦታ ዳግም እንደማይመለሱ ቃላቸዉን ሰጥተዉ ተሰናብተዉናል።
አሰልጣኙ ስለ ስኬታቸዉም ሆነ ስለ እግርኳስ አዋቂነታቸዉ ብዙ ተብሎላቸዋል ሊቨርፑልን ከተቀላቀሉበት ጊዜ ጀምሮ ቡድኑን በሜዳ ላይ የቀየሩበት መንገዳቸዉ ሊቅ አስብሎ አስሞኳሽቷቸዋል። በተለይም ከአቻቸዉ ከፔፕ ጋር የፈጠሩት “የአዋቂዎቹ ባላንጣነት” ሁሌም በየአመቱ ለመመልከት ከሚያጓጉን ጨዋታዎች መካከል ነዉ ፥ አሁን ግን ዳግም በቀደመ ልክ ላናጣጥመዉ ታሪኩን ብቻ ትቶልን አልፏል። ይናፍቀናል!!!
ከሁሉም በላይ ግን ሁሌም የሚደንቀኝን ነገራቸዉ ላካፍላችሁ ይህም “ካራክተራቸዉ” ወይንም ሰብዕና እና ማንነታቸው ነዉ። በሌሎች ኤሊት አሰልጣኞች ላይ ብዙም የምንመለከተው ፀባይ እንመልከትባቸዋለን። ከተጫዋቾች ጋር ያላቸዉ “የአባትነት እና የልጅ ግንኙነት” -መከባበር- ፣ ደጋፊዉን የራሳቸዉ ሰራዊት የሚያደርጉበት ጥበብ ፣ ከከተማዉ ጋር ያላቸዉ መስተጋብር - የተወለዱበት ይመስል ከተማዉን ያወቁበት ፥ ምን እንደሚፈልግ የተረዱበት ነገሩ - የሚያስደንቅ ነዉ። በዚህም ሊቨርፑል ብቻ ሳይሆን ከተማዉ መርሲሳይድ ሁሌም ይናፍቃቸዋል።
ክሉፕ እስካሁን ባሰለጠኑባቸዉ ክለቦች “የህዝቡ ሰዉ” ሲሆኑ ተመልክተናል። ከዚህ ቀደም ስለ ሰዉዬዉ አንድ ጋዜጠኛ ሲናገር “ክሉፕ ከሙኒክ ይልቅ የዶርትሙንድ ፣ ከዩቬ ይልቅ የሮማ ፣ ከሲቲ በይበልጥ የሊቨርፑል አሰልጣኝ ናቸዉ።” ሲል አድምጬዋለሁ ይህንን መነሻ አድርጌ እኔም ሳክልበት የጊዮርጊስ አሰልጣኝ ከሚሆኑ ይልቅ የቡና አሰልጣኝ ናቸዉ እለዋለሁ ወደ ራሳችን ሳቀርበዉ። ነገሩ ምንን ለማሳየት የርገን ከተሳካላቸዉ ቡድኖች ይልቅ “በአንድ የታሪክ ወቅት ስኬታማ የነበሩ አሁን ላይ ግን በረዥመ እንቅልፍ ዉስጥ ያሉ አሊያ ደግሞ ታሪካቸዉ በዋንጫዎች ያልደመቁ ግን ሁሌም ለዋንጫ በመፎካከር የሚጠቀሱ ቡድኖችን” ማሰልጠን እና ማጀገን ይችሉበታል የሚለዉን በጥሩ ሁኔታ ገልፆልናል።
ይህ ነገራቸዉ ታዲያ ከደጋፊዉ ፣ ከተጫዋቾቻቸዉ እንዲሁም ከከተማው ጋር የተለየ ትስስርን ይፈጥርላቸዋል። በተለይም ደግሞ ለማሰልጠን የሚመርጧቸዉ ቡድኖች ከፍተኛ የሆነ የደጋፊ መሰረት ያላቸዉ ናቸዉና ከእነርሱ ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት ላይ አተኩረው ይሰሩበታል ፣ ራሳቸዉን በእየሳምንቱ በስታዲየም ከሚታደሙት ፤ ለክለባቸዉ 90ደቂቃ ከሚዘምሩ እንደ አንዱ ያደርጋሉ በዚህም ልዩ አንድነትን ይፈጥራሉ። ተጫዋቾች ከደጋፊው ፣ ራሳቸዉ ከደጋፊዉ ፣ ብሎም አመራሮች ከቀዩ አቀንቃኞች የሚኖራቸዉ ይህ ልዩ ግንኙነት ለስኬታቸዉ እንደ አንድ ቁልፍ ምክንያት ይጠቀሳል።
በዚህም ባህሪያቸዉ አማካኝነት ክሉፕ ‘ ክሉፕ በመሆናቸዉ ብቻ ያለፏቸዉ ችግሮች ፣ የተሻገሯቸዉ መሰናክሎች አሉ። አንዱን ብቻ እንኳ ለመጥቀስ የደጋፊዉን በባለቤቶቹ ላይ ያነሳዉን ጥያቄ በራሳቸዉ መንገድ - በሜዳ ላይ ዉጤታማነታቸዉ - ምላሽ እየሰጡ ትኩረቶች ወደ ዋንጫ ፉክክር እና ወደ እያንዳንዱ ፍልሚያዎች እንዲሆን በማድረግ ባለቤቶቹን እኳ ማስረሳት ችለዋል በዚህ ሁሌም በሊቨርፑል ሲናፈቁ ይኖራሉ።
ለማጠናቀ
06/05/2024
አትሌት ጠና ነገሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ ፡፡
**********************************
ሚያዝያ 28/2016 ዓ.ም
ኢትዮጵያን በባርሴሎና ኦሎምፒክ በማራቶን በመሳተፍ የወከለው እና በሌሎች አለም አቀፍ ውድድሮች ሀገሩን የወከለ አትሌት ጠና ነገሬ
ህልፈተ ህይወት ምክንያት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለቤተሰቦቹ ፣ ለባልደረቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለመላው አትሌቲክስ ቤተሰብ መጽናናትን ይመኛል።
👉 የቀብር ስነ ስርዓቱም :- በዛሬው እለት ከቀኑ 9:00 ሰዓት በሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።
22/04/2024
ሚያዝያ 14፤2016 -አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ ለአምስት ዓመታት ከአትሌቲክስ ታገደች
የ21 ዓመቷ የመካከለኛ ርቀት አትሌት ለአምስት ዓመታት መታገዷን የገለጠው አትሌቲክስ ኢንቴግሪቲ ዩኒት የተባለው ተቋም ነው።
ተቋሙ በቀድሞው ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ሰሌዳው ላይ በለጠፈው መግለጫ አትሌቷ ምርመራ ከተደረገላት በኋላ ቅጣት ማስተላለፉን አሳውቋል።
የዓለም አትሌቲክስ አካል የሆነው ይህ ተቋም ባወጣው መግለጫ፣ አትሌቷ ሁለት የተከለከሉ ንጥረ-ነገሮችን መውሰዷን አምናለች ብሏል።
ዘርፌ፤ ቴስቶስቴሮን የተባለውን እና ኢፒኦ የተሰኘውን አትሌቶች በደማቸው ውስጥ የበለጠ ኦክሲጅን እንዲኖር የሚያደርግ ንጥረ ነገር መውሰዷን አምናለች።
ዘርፌ በቶኪዮ ኦሊምፒክስ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ስምንተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል።
የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…
Facebook: https://bit.ly/3Hng6Qt
Website: https://www.bisrattv.com/
Telegram: https://t.me/Bisrat101fm
YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB
Twitter: https://twitter.com/Bisrat101fm
TikTok: https://bit.ly/4
04/04/2024
አድሮ ቃሪያ የሆነ ከትላንቱ የማይማር፣ ዉሃ ቢወቅጡት እንቦጭ! ትናንት ያነቀፈው ድንጋይ ዛሬም የሚደግመው፣ በዓለቀ ሰአት ትኩረቱን የሚያጣ፣ ሲያርስ ከርሞ ምርቱን ለዝንጀሮ የሚለቅ፣ በትናንት መገለጫው ዛሬ የሚረታ፣ የጻፈውን ታሪክ ራሱ የሚደልዝ፣ በወርቅ ብዕሩ ላይ ማጥንት የሚጨምር፣ ወዝ አልባ ዩናይትድ።
27/03/2024
🎙 የብስራቱ ጋዜጠኛ ዳንኤል መምሩን ቃል በመዋስ ልጀምር "በአለማችን ላይ ከባዱ ስራ አሰልጣኝነት ነዉ" ሲል ይናገራል።
✅ እዉነት ነዉ ይህ ስራ በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉ ስራዎች መካከል ቢመደብ ማጋነን አይሆንም። አንድን ቡድንን ማሰልጠን ማለት 11 ተጫዋቾችን እንዴት መጫወት እንዳለባቸው ከመናገርም ያለፈ ትልቅ ሀላፊነት ነዉ።
✅ በአንድ ቡድን ዉስጥ ያሉ ተጫዋቾች ላይ አንድ አይነት አስተሳሰብ ማስረፅ ፣ የሚባሉትን ተረድተዉ ለአንድ አላማ እንዲሰለፉ ማድረግ ፣ ከማህበራዊ ሆነ ከቤተሰብ ህይወት ተነጥሎ በታክቲክ ቦርድ ላይ ለሰዓታት አፍጥጦ ማዉጣት እና ማዉረድን ይጠይቃል ፤ እነዚህ ከብዙ ከሚሰሩ ስራዎች ዉስጥ ጥቂቶቹ ናቸዉ።
✅ በቅርብ አመታት ከተመለከትናቸዉ 'ወጣት' አሰልጣኞች መካከል በዚህ ስራ ላይ ተዋጥቶላቸዋል ብለን ካነሳን የሚኬል አርቴታ ስምን በዝርዝር ውስጥ ማካተታችን አይቀርም ፤ ለአመታት የተቸገረዉን በቀዉስ ዉስጥ የነበረዉን አርሰናልን በለጋ የአሰልጣኝነት ልምዱ የቀየረበት መንገድ አስደናቂ ነዉ።
❓ ይኸዉ የመድፈኞቹ አለቃ ዛሬ 42ኛ አመቱን እያከበረ ይገኛል። የሚኬል የአርሰናል ቆይታ ስኬታማ ነዉ ትሉታላችሁ ?
✍️ Abel Yilma