Hussein Zinaab

Hussein Zinaab

Share

Yes we can!!!!! +~+ ~~~~~~~+++++++

01/09/2026

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሽን አገራዊ ለውጡን መነሻ አድርጎ ባካሄደው ተቋማዊ ሪፎርም ገቢውን ከ 41 እጥፍ በላይ አሳድጓል።

በ2018 በጀት አመት ከፍተኛ የገቢ እድገትና ታሪካዊ ስኬት እንዲመዘገብ መላው የተቋማችን ሰራተኞች ላበረከታችሁት የላቀ አስተዋጽኦ ምስጋናችንን እያቀረብን የ እንኳን ደስ አላችሁ መልእክታችንን እናስተላልፋለን !

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
በአዲስ ምእራፍ ለተሻለ ነገ !

01/09/2026

የ2019 ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቂ የበዓል ፍጆታ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ መጪውን የአዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ በአገር ውስጥ ለሚገኙ ሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ወ/ሮ ሀቢባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ መጪውን የአዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ የምርት እጥረት እንዳይፈጠር ከክልሎች እና ከአጎራባች ከተሞች ጋር በቅርበት ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው ለዚህም በቂ የበዓል ፍጆታ ምርቶች መዘጋጀታቸውን አሳውቀዋል።

ወ/ሮ ሀቢባ አክለውም ከ28/12/18 ዓ ም ጀምሮ በዓሉን በማስመልከት በ11ዱም ክ/ከተሞች የበዓል ባዛሮች በይፋ ስራ የሚጀምሩ መሆኑን ገልፀው የእሁድ ገበያዎችም ሳምንቱን ሙሉ ክፍት እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

በባዛሮቹ ከበዓል ፍጆታዎች በተጨማሪ የኢንዱስትሪ ምርቶች፣ ለትምህርት የሚሆኑ ግብዓቶች እና የተለያዩ አልባሳቶች የሚቀርቡ መሆናቸውን ወ/ሮ ሀቢባ አሳውቀዋል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ አርቴፊሻል የሆነ የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያሳወቁት ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በየደረጃው የሚገኙ የህገ-ወጥ ንግድ መከላከልና የገበያ ማረጋጋት ግብረ-ኃይል አባላት ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በመግለጫቸው የበዓል ፍጆታ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ በቂ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀው፣ ህገ-ወጥ የሆነ ማንኛውም የንግድ እንቅስቃሴ ሲያጋጥም የከተማችን ነዋሪ በ8588 ነፃ የስልክ ጥሪ በመደወል ጥቆማ መስጠት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

01/09/2026
Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ Addis Ababa City Communication's post 01/09/2026
Photos from Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ's post 31/08/2026
Photos from Hussein Zinaab's post 27/08/2026

ዛሬ ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማችን በመካሄድ ላይ ያለውን “የሜክሰድ ማርሻል አርት እና የንኪኪ ስፖርት በአንድ መድረክ የሚይዘው ዓድዋ ፋይት ናይት" ውድድር፣ በታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በመገኘት ወጣቶችን አበረታተዋል።

ክብርት ከንቲባ በመልእክታቸው፥ ውድድሩ በአደጉና በበለፀጉ ሀገራት እጅግ ተወዳጅ ስፓርት ሲሆን፤ ደረጃቸውን የጠበቁ የስፓር መሰረተ ልመቶችን የሚፈልግ በመሆኑ እስከአሁን በአገራችን ሲካሄድ አይስተዋልም፥ ዛሬ ግን በከተማችን በተሰሩ ዘርፈ ብዙ ምቹ የስፓርት መሰረተ-ልማቶች እውን በመሆናቸዉ አዳዲስ የፓርት አይነቶች እየተካሄዱ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።

በመቀጠልም፥ ውድድሩ ወጣቶች ልዩ ተሰጥኦና ችሎታቸዉን የሚዳብሩበት ፣ለስፖርት ቱሪዝም፥ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መስተጋብር የሚጠናከርበት፣ የከተማችንን ገፅታ የሚቀይር እና ተወዳዳሪነታችን የሚጨምር ነው ብለዋል።

በመጨረሻም እንዲህ አይነት ውድድሮች፥ ወጣቱን ታሳቢ ያደረጉ መሠረተ-ልማቶችን ይበልጥ አጠናክረን እንድንሰራ ያደርገናል፤ ወጣቱም አለማቀፍ የተወዳዳሪነት መንፈስ እንዲያሳድግ ዕድል ይሰጣል ሲሉ ገልፀዋል።

ክብርት ከንቲባ በመልእክታቸው አዘጋጆችን “በርቱ” ያሉ ሲሆን፤ ለተወዳዳሪዎችም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

25/08/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ፤ እንኳን ለ1 ሺህ 501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በዓሉን ስናከብር እንደከዚህ ቀደሙ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፤ ለሌላቸው በማካፈል፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የታመሙትን በመጠየቅ እንዲሆን እመኛለሁ።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ - ኢድ ሙባረክ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

Hordoftoota amantaa Islaamaa hundaaf Baga Ayyaana Mawliidaa Nabiyyii Mahaammad (S.A.W) 1, 501ffaaf nagaan geessan!

Ayyaanicha wayita kabajnu akkuma kanaan duraa lammiilee keenya rakkatan gargaaraa, warra hin qabneef qoodaa, warra daaran uffisuun, warra dhukkubsatan gaafachuun akka ta'un hawwa.

Irra deebiin baga geessan - Iid Mubaarak!

Waaqni Itoophiyaa fi uummata ishee haa eebbisu!

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Addis Ababa