ኢትዮ አርሰናል / Ethio Arsenal

ኢትዮ አርሰናል / Ethio Arsenal

Share

–Welcome to the official page Ethio Arsenal

ሁሌም ስለ አርሰናል በትኩሱ እንዘግባለን ፔጁን ፎሎ ፣ ሼር ያድርጉ።

– Join on telegram : https://t.me/Ethio_Arsenal

22/03/2026

ድል ለአርሴ ! 🔥😍

22/03/2026

ድል ለመድፈኞቹ ! 🔥

22/03/2026

•|| Wembley dayyyyyy ! 😍🏆

አርሰናል 🆚 ማንችስተር ሲቲ

🧤 ቀኑ ደርሰ ። ለታላቁ ኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ እየተፎካከርን ያለነው አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ በሊግ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ እንገናኛለን። ክለባችን አርሰናል ለ 4 ዋንጫዎች እየተፎካከረ ይገኛል። ምናልባት ዛሬ ከአራቱ አንዱን ሀ ብሎ የሚጀምርበት ቀን ሊሆን ይችላል ። ለማንኛውም...አርሰናል ከ ማንችስተር ሲቲ ቅድመ ዳሰሳ👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

📅 የ ጨዋታ ቀን --> ዛሬ ዕሁድ
🕰 የ ጨዋታ ሰዓት --> ማታ 1:30
😎 የመሀል ዳኛ--> ፒተር ባርንስ
🏟 የ ጨዋታ ሜዳ --> ዌምብሌይ ስቴድየም

▪️|| [ ቅድመ ጨዋታ ትንተና ]

✓ የቡድን ዜናዎች
✓ እውነታዎች
✓ የጨዋታ ግምቶች
✓ ግምታዊ አሰላለፍ
✓ ወሳኝ ነጥቦች

▪️|| የ ቡድን ዜና !

• የአርሰናል

- በክለባችን አርሰናል በኩል ጁርያን ቲምበር እና ማርቲን ኦዴጋርድ ለዛሬው ጨዋታ መድረሳቸው አጠራጣሪ መሆኑን እና ስብስቡ ውስጥ እንደሚገኙ ተስፋ በማድረግ ከመጨረሻው ልምምድ በውሃላ ውሳኔ እንደሚወስን አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አሳውቋል ። ሌላ አዲስ የጉዳት ዜና የሌለ ሲሆን እንደሚታወቀው ሚኬል ሜሪኖ ከጨዋታው ውጪ ነው ።

በግብ ጠባቂ ቦታ ላይ ኬፓ እንደሚጀምር የተለያዩ ዘገባዎች እየወጡ ነው ።

• ማንችስተር ሲቲ

- በማንችስተር ሲቲ በኩል ጆስኮ ግቫርዲዮል ለጨዋታው እንደማይደርስ የተረጋገጠው ተጫዋች ሲሆን ከ ክሪስታል ፓላስ ያስፈረሙት እና ፓላስ እያለ አርሰናልን የገጠመው ማርክ ጉኤሂ በካራባኦ ህግ መሰረት የዛሬው ጨዋታ ያመልጠዋል ።

▪️|| እውነታዎች [ ቢቢሲ እና ኦፕታ ]

✓ ክለባችን አርሰናል ከማንችስተር ሲቲ ጋር ባደርገው ያለፉት 6 ጨዋታዎች ምንም ጨዋታ አልተሸነፈም ።

✓ ማንችስተር ሲቲዎች 8 ጊዜ የካራባኦ ካፕ ዋንጫን ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን የሚበለጡት በ 10 ጊዜ ሻምፒዮኖቹ ሊቨርፑሎች ብቻ ነው።

✓ አርሰናል በኦፕታ ዋንጫውን የማሸነፍ 51.9 % ዕድል ተሰቶታል ።

▪️|| ግምታዊ አሰላለፍ

- አርሰናል

• ኬፓ ፣ ዋይት ፣ ሳሊባ ፣ ጋብሪኤል ፣ ሂንካፔ ፣ ዙቢሜንዲ ፣ ራይስ ፣ ኤዜ ፣ ሳካ ፣ ዮኬሬሽ ፣ ትሮሳርድ

- ማንችስተር ሲቲ

• ትራፎርድ ፣ ኑኔስ ፣ ዲያዝ ፣ ስቶንስ ፣ ኤት-ኑሪ ፣ በርናርዶ ፣ ሮድሪ ፣ ኦራይሊ ፣ ቼርኪ ፣ ሀላንድ ፣ ሴሜንዮ

▪️|| የውጤት ግምቶች

✓ [ Sport illustrated ] - አርሰናል 2-1 ማን ሲት

✓ [ Sky Sports] - አርሰናል 1-1 ማን ሲቲ ( ሲቲ በፔናሊቲ ያሸንፋል )

✓ [ ✍🏽 Hafiz ] - አርሰናል 2-1 ማን ሲቲ

• ወሳኝ ነጥቦች 👌🏽

- ይህ ጨዋታ ክለባችን አርሰናል በዚህ አመት ከሚያደርጋቸው እጅግ ትልቅ ጨዋታዎች ውስጥ አንዱ ነው ። አንደኛ ነገሩ የዋንጫ ነው ! ለረጅም ጊዜያት ክለቡ ፣ ተጫዋቾቹ እና አሰልጣኙ ወደናፈቁት ወደናፈቅነው የዋንጫ አሸናፊነት የሚመልስ ታላቅ ጨዋታ ነው።

ሲቀጥል ተጋጣሚው ማንችስተር ሲቲ መሆኑ ጨዋታውን ይበልጥ ያገዝፈዋል ። እንደሚታወቀው ማንችስተር ሲቲ ለአመታት ዋንጫ ከአፋችን ላይ የቀማን ፣ አሁን ደሞ ለፕሪሚየርሊጉ ፉክክር ከኋሏ ከኋላ አለው እያለን ያለ ክለብ ነው ። ታድያ በፍፃሜው ጨዋታ ይህን ተፎካካሪያችንን ማሸነፍ ለቀሪ የ ፕሪሚየርሊግ ሻምፒዮንነት ማረጋገጫ ጨዋታዎች እና እንዲሁም ሌሎች ዋንጫዎች ትልቅ ሞራል እና መነሳሳት ይፈጥራል

- በዛሬው ጨዋታ የቀኝ መስመር ተከላካያችን ቤን ዋይት የሚጀምርበት በጣም ሰፊ ዕድል አለ ። ምንም እንኳን በመከላከሉ ትልሽ ስጋት ሊያሳድርብን ቢችልም በማጥቃቱ በኩል የ ቤን ዋይትን ኳሊቲ በሚገባ መጠቀም ያስፈልጋል። Overlap እያደረገ በመግባት ወደ ቦክስ የሚጥላቸው ኳሶች በአጥቂ ቦታ ላይ ለሚሰለፈው ዮኬሬሽ ወይም ሃቨርትዝ ትልቅ ስንቅ ይሆናሉ ።

• የዛሬውን ጨዋታ ቅድመ ትንተና አዘጋጅቼ ያቀረብኩላችሁ [ ✍🏽 ሀፊዝ ] ነበርኩ ድል ለ ውዱ ክለባችን ተመኘሁ ! 🙏🏽

- እናንተም የ ጨዋታ ግምታችሁን ፣ ጨዋታው ላይ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ፣ ምን ሊመስል እንደሚችል ግምታችሁን አስቀምጡ ! 👇🏽

COME ON YOU GUNNERSSS 🏆🔥🔥🔥

"

21/03/2026

ዌምብሌይ 🏟️

አርሰናል በዌምብሌይ ስታዲየም ያለው ብቃት ዝም ብሎ ድል ሳይሆን ፍጹም የበላይነት ነው። ካደረጋቸው የመጨረሻዎቹ 14 ጨዋታዎች 13ቱን ማሸነፉ ስታዲየሙ ለክለቡ "ሁለተኛው ኢምሬትስ" እንደሆነ ማረጋገጫ ነው።

ይህ ውጤት የሚያሳየው መድፈኞቹ በታላላቅ መድረኮችና በግፊት ውስጥ የመጫወት ልዩ ብቃት እንዳላቸው ነው። ዌምብሌይ ለአርሰናል ደጋፊዎች የደስታ፣ ለተቃራኒ ቡድኖች ግን የጭንቀት ሜዳ እንደሆነ ያመላክታል።

"ድል ለአርሰናል፣ የነገ ሰው ይበለን፣ መልካም አዳር!

21/03/2026

የብሔራዊ ቡድን ጥሪ ወይስ የችኮላ ውሳኔ? የትሮይ ዲኒ ጠንከር ያለ ትችት

ትሮይ ዲኒ ገና የ16 ዓመት ታዳጊዎችን ወደ ብሔራዊ ቡድን የመጥራት አባዜን ክፉኛ የተቸ ሲሆን፣ ዳውማንም ላይ
ከሚፈጥረው አላስፈላጊ ጫና ባለፈ በቡድኑ ውስጥ ላለው ሚዛን መዛባት ምክንያት እንደሚሆን አስገንዝቧል።

"በፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ እንኳ ያልጀመረን ልጅ ለአገር ምርጥ ቡድን መጥራት ጥቅሙ ምንድን ነው?" ሲል የጠየቀው ዲኒ፣ እንደ እነ ጁድ ቤሊንግሃም፣ ፊል ፎደን፣ ኮል ፓልመር እና ኤቤሪቺ ኢዜ ያሉ በከፍተኛ ብቃት ላይ የሚገኙ ኮከቦች ባሉበት ስብስብ ውስጥ፣ አንድን ታዳጊ ለመያዝ ሲባል ማን ሊቀነስ እንደሚችል በጥያቄ ምልክት አቅርቦታል። እንደ እሱ እይታ፣ ብሔራዊ ቡድን በችሎታ የታገዘ ልምድ የሚጠይቅ መድረክ በመሆኑ፣ ሁሉንም ተስፋ ሰጪ ወጣቶች በአንድ አውሮፕላን ጭኖ ወደ ትልቅ ውድድር መሄድ የማይታሰብና የሊጉን አንጋፋ ተጫዋቾች የሚጋፋ ውሳኔ ነው።

Photos from ኢትዮ አርሰናል / Ethio Arsenal's post 21/03/2026

"የካራባኦ ዋንጫ ተጠባቂ ፍጥጫ፡ አርሰናል ከ ማንቸስተር ሲቲ"

ነገ እሁድ (መጋቢት 13/2018 ዓ.ም) በዌምብሌይ ስታዲየም የሚካሄደው የአርሰናል እና የማንቸስተር ሲቲ የካራባኦ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ለሁለቱም ክለቦች የውድድር ዓመቱን ዕጣ ፈንታ የሚወስን ታሪካዊ ፍልሚያ ነው ።

በተለይም አርሰናል ከ34 ዓመታት በኋላ ይህንን ዋንጫ በማንሳት ለፕሪምየር ሊግ እና ለሻምፒዮንስ ሊግ ጉዞው ስንቅ ለመያዝ ሲያልም፣ በዌምብሌይ 12 ጨዋታዎችን ያሸነፈው የሚኬል አርቴታ ስኬታማ ታሪክም ትልቅ ተስፋ ሆኖለታል።

በአንጻሩ ከሻምፒዮንስ ሊግ የወጣው ማንቸስተር ሲቲ የውድድር ዘመኑን ያለ ዋንጫ ላለማጠናቀቅና የአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላን ቆይታ ለማረጋገጥ ማሸነፍ ግዴታው ሲሆን፣ በ2018 አርሰናልን አሸንፈው የጀመሩት የገናናነት ዘመን ዘንድሮ በዚሁ ክለብ እጅ እንዳያበቃ ከፍተኛ ሥነ-ልቦናዊ ጫና ይኖርባቸዋል።

1. ሚኬል አርቴታ፡ በዌምብሌይ ስታዲየም ያደረጋቸውን 12ቱንም ጨዋታዎች (በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት) በማሸነፍ አስደናቂ ታሪክ አለው።

2. ፔፕ ጋርዲዮላ፡ በ2018 የመጀመሪያ የእንግሊዝ ዋንጫቸውን ያነሱት አርሰናልን 3-0 አሸንፈው ነበር። ዘንድሮ ግን ካልተሳካላቸው የጋርዲዮላ የሲቲ ቆይታ ሊያበቃ እንደሚችል ይገመታል።

ይሄ ዋንጫ ለምን ወሳኝ ሆነ?

ታዋቂው ተጫዋች አለን ሺረር እንዳለው፣ ይህ ጨዋታ ለአርሰናል ለሌሎች ሦስት ዋንጫዎች (ሊግና ሻምፒዮንስ ሊግ) ተጨማሪ ስንቅ የሚሆን ሲሆን፣ ለሲቲ ደግሞ የክለቡንና የአሰልጣኙን ቀጣይ እጣ ፈንታ የሚወስን ነው።
ነገ ምሽት 1፡30 ላይ የሚካሄደው ይህ ጨዋታ የቬንገር ዘመን በ2018 እንዳበቃ ሁሉ፣ የጋርዲዮላም ዘመን ማብቂያ ይሆን ? የሚለው በጉጉት ይጠበቃል።

Photos from ኢትዮ አርሰናል / Ethio Arsenal's post 20/03/2026

📸ለካራባኦ ካፕ ፋይናል ብርቱ ልምምድ እየተደረገ ይገኛል።"

19/03/2026

"ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።

ለኢትዮ አርሰናል ቤተሰቦች፡ በዓሉ የድል እና የደስታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። ልክ እንደ መድፈኞቹ ሜዳ ላይ እንደሚፈነጥዙት፣ በቤታችሁም ደስታ ይፍሰስ!

ለመላው ኢትዮጵያውያን አንድነታችን የጠነከረበት፣ ፍቅራችን የጎላበት በዓል ይሁንልን።

"ኢድ ሙባረክ! መልካም በዓል!"

19/03/2026

የ2025/26 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ድልድል እጅግ አስደሳች የሆኑ ፍልሚያዎችን ይዞ የቀረበ ሲሆን፤ በግራ በኩል ካለው መስመር ፒኤስጂ ከሊቨርፑል እንዲሁም ሪያል ማድሪድ ከባየር ሙኒክ የሚያደርጉት ታላቅ ጨዋታ ነው ።

በቀኝ በኩል ደግሞ የስፔን ላሊጋ ተቀናቃኞቹ ባርሴሎና እና አትሌቲኮ ማድሪድ እርስ በእርስ ሲገናኙ፣ የለንደኑ አርሰናል ደግሞ ከፖርቹጋሉ ስፖርቲንግ ሊዝበን ጋር ወደ የፍፃሜ ጨዋታ ለመድረስ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ።

18/03/2026

የአርሰናል ደጋፊ ነህ? የአርሰናል ደጋፊ ነሽ? 🔴⚪

እንግዲያውስ ምን ትጠብቃላችሁ? የለንደን ኩራት የሆነውን የአርሰናልን ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት ምርጡን ገጻችንን አሁኑኑ Follow አድርጉ።

• 📌 ትኩስ ዜናዎች
• 📌 የጨዋታ ትንታኔዎች
• 📌 ምርጥ የመድፈኞቹ ድባብ

ይህንን ፖስት Share በማድረግ ሌሎች መድፈኞች እንዲቀላቀሉን እና ቤተሰባችንን እንዲሆኑ ሰበብ እንሆን ።

🔗ይቀላቀሉ : ኢትዮ አርሰናል / Ethio Arsenal

አርሰናል ለዘላለም!

18/03/2026

ፒተር ባንክስ ተመርጧል !

በመጪው የሳምንቱ መጨረሻ በአርሰናል እና በማንችስተር ሲቲ መካከል የሚደረገውን ተጠባቂ የካራባኦ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ፒተር ባንክስ (Peter Bankes) በመሀል ዳኝነት እንዲመሩት መመደባቸው ታውቋል።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address

Addis Ababa