Sirak Sport Page

Sirak Sport Page

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sirak Sport Page, Sports, Addis Ababa.

Sirak official sport page– የእግር ኳስና ሌሎች ስፖርቶች በቅርብ የሚከታተሉበት የትክክለኛ እና የፈጣን ዜና ምንጭ።
የቀኑን ጨዋታዎች ትንታኔዎች ውጤቶች እና አስደናቂ እይታዎችን በፍጥነት ያገኛሉ።
👉 ማሳሰቢያ :- ሁልጊዜም ተግቼ የምፅፈው ለእናንተ አዳዲስ መረጃ ለመስጠት ስለሆነ እናንተ ደግሞ like comment share በማድረግ ትተባበሩኝ ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ 👏👏

Photos from Sirak Sport Page's post 07/07/2026

🇦🇷 አርጀንቲና 0 - 1 ግብፅ 🇪🇬(የመጀመሪያው አጋማሽ እረፍት)

ግብፅ ጠንካራዋን አርጀንቲናን 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት እየመራች ወደ መልበሻ ክፍል አምርታለች።

ያሰር ኢብራሂም በ15ኛው ደቂቃ ላይ ኤም. አተያ ባመቻቸለት ኳስ ለፈርኦኖቹ ቀዳሚዋን ጎል አስቆጥሯል። በአንጻሩ አርጀንቲናዎች በ21ኛው ደቂቃ ላይ አቻ ለመሆን ወርቃማ ዕድል አግኝተው የነበረ ቢሆንም፥ ሊዮኔል ሜሲ የመታውን የፍፁም ቅጣት ምት (Penalty) የግብፅ ግብ ጠባቂ ኡፋ ሹቤር (Oufa Shobeir) በብቃት አድኖበታል።

⚽ የጎል አግቢ (በሀገር)፦

ያሰር ኢብራሂም 15' (ግብፅ 🇪🇬)

Photos from Sirak Sport Page's post 30/06/2026

ሞሮኮ ኔዘርላንድስን በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም ዋንጫ የ32ቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሞሮኮ ኔዘርላንድስን በመለያ ምት በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቅላለች።

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በመደበኛው 90 ደቂቃ እንዲሁም በተጨማሪ 30 ደቂቃ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል።

አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠ የመለያ ምት ሞሮኮ 3 ለ 2 በማሸነፍ 16ቱን መቀላቀል ችላለች፡፡

ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ሩብ ፍጻሜውን ለመቀላቀል አዘጋጇን ሀገር ካናዳ ትገጥማለች።

23/06/2026

አልቫሬዝ - "ልቀቁኝ ህልሜን ልኑርበት"

አትሌቲኮ ማድሪድ - "ውላችን ላይ የተቀመጠው የውል ማፍረሻ 500 ሚሊየን ዩሮ ካልተከፈለን አንለቅህም"

Photos from Sirak Sport Page's post 17/06/2026

ሜሲ ሀትሪክ ሰርቶ በአለም ዋንጫው ብዙ ጎል የማስቆጠር ሪከርዱን ከሚሎስላቭ ክሎሰ ጋር ተጋርቷል!🔥

ይሄ ሰው 2022 ላይ እግርኳስ የጨረሰ መስሎን ነበር በጣም ተሳስተናል እያደረ እንደወጣት እየጎመራ የሚሄድ የእግርኳስ ታላቁ ሰው...

29/05/2026

‎🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 𝗢𝗙𝗙𝗜𝗖𝗜𝗔𝗟: ባርሴሎና አንቶኒ ጎርደንን ከኒዉካስትል በ€80 ሚሊዮን ዩሮ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።

20/05/2026

ሰበር

ታዋቂዉ ሬጌ አቀንቃኝ ሳሚ ዳን አርሰናል ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ ዛሬ ምሸት 12 ሰዐት አርሰናልን የተመለከተ አዲስ ዘፈን እንደሚለቅ ይፋ አድርጓል።😯

20/05/2026

ማክስ ዶውማን የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግን ያነሳ በታሪክ በእድሜ ትንሹ ተጫዋች ሆኗል።16 አመት ከ140 ቀን ላይ ይገኛል።🌟🏆️

19/05/2026

ፔፕ ጋርዲዮላ፡- "በማንችስተር ሲቲ እና በቡድኔ ስም፣ ለዚህ ​​የፕሪሚየር ሊግ ድል አርሰናልን፣ ሚኬል [አርቴታን]፣ ሰራተኞቹን፣ የክፍል ውስጥ ሰራተኞች፣ ሁሉም ተጫዋቾች፣ ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ - ይገባቸዋል!" [SkySportsPL]

19/05/2026

አርሰናል የ 2025/2026 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሆነ።

አርሰናል ከ22 አመት ጥበቃ በኋላ ሻምፒዮን ሆኗል።

ለመላዉ የአርሰናል ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ!

19/05/2026

ሰበር

ሳዉዝሀምፕተን ከፕሌይ ኦፍ ፍፃሜ ዉጪ ተደረገ

ሳዉዝሀምፕተን ከፍፃሜ ጨዋታ ዉጪ የተደረገበት ምክንያት የሚድልስብሮውን ልምምድ ሲሰልሉ በመገኝታቸዉ እንደሆነ ተረጋግጧል፤እንደ አወዳዳሪዉ አካል ገለፃ ከሆነ ቡድኑ የሌሎች ክለቦች ልምምድ ማዕከል ሰላይ በመላክ ልምምዳቸዉን ያሰልል እንደነበር ታዉቋል።

ቡድኑ በቀጣይ አመትም 4 ነጥብ ተቀንሶበት ዉድድሩን የሚጀምር ይሆናል፤ሳዉዝሀምፕተን በዚህ የዉድድር ዘመን 80 ነጥቦችን የሰበሰበ ሲሆን ለፕሌይ ኦፍ ፍፃሜም ደርሶ ነበር፤በፍፃሜዉ ጨዋታ ሳዉዝሀምፕተንን በመተካት ሀል ሲቲ እንደሚጫወት ታዉቋል።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Address

Addis Ababa