21/07/2026
የአዲስ አበባ ለውጥ ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲና የኮንፍረንስ ማዕከልነቷን ያደሰችበት ጉዞ ነው
ኢትዮጵያ ታሪካዊ የአፍሪካ መዲናነቷንና ዲፕሎማሲያዊ ገጽታዋን በአዲስ መልክ በመገንባት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ የኮንፍረንስና የኤግዚቢሽን ማዕከል ለመሆን በቃች። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መሪነት ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተከናወኑት ግዙፍ ፕሮጀክቶች አዲስ አበባን ለአለም አቀፍ ጉባኤዎች ይበልጥ ማራኪና ዝግጁ አድርገዋታል።
አድዋ ድል መታሰቢያ ግዙፍ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ሁነቶችን ለማስተናገድ የሚያስችል ዘመናዊ የአዳራሽና ኤግዚቢሽን ማዕከል፣ የአፍሪካ ህብረት አዲስ አዳራሽና አቪዬሽን ከተማ፣ ግዙፍ አየር ማረፊያዎችንና መስተንግዶዎችን ጨምሮ የተከናወኑ የትራንስፖርትና የሎጅስቲክስ ማሻሻያዎች ይበልጥ ተመራጭ አድርጓታል። በተጨማሪም ወዳጅነት ፓርክ፣ የእንጦጦ ፓርክና የዓመታት የሸገር ውበት ፕሮጀክቶች ለአለም አቀፍ እንግዶች ምቹ፣ ጽዱ እና አረንጓዴ አካባቢን በመፍጠር የመዲናዋን ገጽታ ሙሉ በሙሉ ቀይረዋል።
18/07/2026
10/07/2026
09/07/2026
30/06/2026
25/03/2026
02/03/2026
15/02/2026