Ethio handball for ever

Ethio handball for ever

Share

handball family

Photos from Ethio handball for ever's post 03/08/2026

The official draw for the African Men's Junior & Youth Handball Championships will take place on Tuesday, 4 August 2026, in Abidjan, Côte d'Ivoire.

🇷🇼 East Africa Rwanda is in both categories.

🤾 Junior Category

Pot 1: Egypt, Tunisia, Algeria, Guinea
Pot 2: Angola, Côte d'Ivoire, Libya, Cameroon
Pot 3: DR Congo, Nigeria, Benin, Rwanda
Pot 4: Congo, Madagascar, Zimbabwe

🤾 Youth Category

Pot 1: Egypt, Tunisia, Guinea, Morocco
Pot 2: Algeria, Côte d'Ivoire, Libya, Cameroon
Pot 3: Rwanda, Nigeria, Congo, Zambia
Pot 4: Burundi, Madagascar

📅 Championship Dates

• Junior: 5–12 September 2026
• Youth: 15–22 September 2026

Photos from Ethio handball for ever's post 18/05/2026

10ኛው የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ በመቀሌ 70 እንደርታ ለሁለት ተከታታይ አመት አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

ያለፉት 10 ዓመታት በደማቅ ሁኔታ ሲካሄድ የነበረው የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ አመት ውድድር በዓመቱ በ3 ከተሞች እየተዘዋወር ሲካሄድ ቆይቶ በሀዋሳ ከተማ በትላንትናው እለት በመቀሌ 70 እንደርታ አሸናፊነት ሲጠናቀቅ በዓመቱ ፕሪሚየር ሊግ የመቻል ክለብ እና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ሁለተኛና ሶስተኛ በመውጣ ደረጃቸውን አግኝተዋል።

በማጠቃለያ ፕሮግራሙም

1. መቀሌ 70 እንደርታ የእጅ ኳስ ክለብ - የወርቅ ሜዳሊያና ዋንጫ
2. መቻል የእጅ ኳስ ክለብ - የብር ሜዳሊያ
3. ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የእጅ ኳስ ክለብ - የነሀስ ሜዳሊያ
4. ኦሜድላ - የፀባይ ዋንጫ

ያገኙ ሲሆን
የዓመቱ
1. ኮከብ ተጫዋች - የእጅ ኳስ ተጫዋች አብርሀም ካሳሁን ከመቀሌ 70 እንደርታ
2. ኮከብ ዳኛ - የእጅ ኳስ ዳኛ በድሉ አበበ
3. ኮከብ አሰልጣኝ - የእጅ ኳስ አሰልጣኝ አማኑኤል ስዩም ከመቀሌ 70 እንደርታ

11/05/2026

What a Rwandan player said about Ethiopia

10/05/2026

Kenyan player

09/05/2026

All East African players and coaches on tour in Adwa Museum

Photos from Ethio handball for ever's post 09/05/2026

Rwanda wins in U-18 U-20 both categories

Photos from Ethio handball for ever's post 07/05/2026

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የእጅ ኳስ ቡድን ዩጋንዳን በማሸነፍ ለፍጻሜ ደረሰ
ሚያዚያ 29 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የዞን 5 (IHF) ትሮፊ ውድድር የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የወንዶች ብሔራዊ ቡድን ዩጋንዳን 41 ለ 39 በማሸነፍ ለፍጻሜ ማለፉን አረጋግጧል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ስምንት ሀገራት የተሳተፉበት ይህ ውድድር በሁለቱም ጾታዎች በ17 እና በ20 ዓመት በታች የዕድሜ እርከኖች እየተካሄደ ይገኛል።
በሁለቱም ዘርፎች አንደኛ ሆነው የሚያጠናቅቁ ብሔራዊ ቡድኖች ለአህጉራዊው የአፍሪካ የእጅ ኳስ ውድድር በቀጥታ የማለፍ ታላቅ ስፖርታዊ ዕድል እንደሚያገኙም ታውቋል።
ውድድር ነገ ሚያዝያ 30 በሚደረጉ የዋንጫ ጨዋታዎች ፍጻሜውን ያገኛል በሁለቱም ካታጎሪ በ4 ኪሎ ከ 7 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል

Photos from Ethio handball for ever's post 06/05/2026

ዓለም አቀፍ እጅ ኳስ ትሮፊ 2026 የዞን 5 የምስራቅ አፍሪካ ውድድር የመክፈቻ መርሃ ግብር ተካሄደ።

ሚያዚያ 28፣ 2018ዓ.ም አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ዓለም አቀፍ እጅ ኳስ ትሮፊ 2026 የዞን 5 የምስራቅ አፍሪካ ውድድር ለ4ኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን ዛሬ የመክፈቻ መርሃ ግብር ተካሄዷል።

ክቡር ፀጋዬ ማሞ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በውድድሩ መክፈቻ ላይ እንደተገለፁት ይህ መድረክ ቀጠናዊ ትስስርን ለማጠናከር እና የእጅ ኳስ ስፖርትን ለማሳደግ ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ስፖርትን እንደ ዓለም አቀፍ የአንድነት መገለጫ በመመልከት የስፖርት መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት እና የወጣቶችን ተሳትፎ በማበረታታት ለዘርፉ እድገት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

​ይህ የዞን 5 ማጣሪያ ውድድር መንግስት ለስፖርት ልማት የሰጠውን ትኩረት አንዱ ማሳያ መሆኑንም ተናግረዋል።

በምስራቅ አፍሪካ በማደግ ላይ ያለውን የስፖርት መንፈስ በማድነቅ፣ ስፖርተኞች በታማኝነት እና በስፖርታዊ ጨዋነት መወዳደር እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበት የኢትዮጵያ እና የምስራቅ አፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚደንት ውድድሩ ለተተኪ አትሌቶች እድል የሚፈጥር እንደሆነ አመላክተዋል።

አክለውም የባህል ልውውጥ የሚካሄድበት፣ የአፍሪካዊ አንድነት የሚጠናከርበት ከመሆኑም ባሻገር የቀጠናው የእጅ ኳስ የጥንካሬ የሚለካበት እንደሆነም ገልፀዋል።

ውድድሩ ለአፍሪካ ሻምፒዮና ለማለፍ የሚደረግ የመጀመሪያው የጉዞ ምዕራፍ ነው።

በዞን 5 የምስራቅ አፍሪካ የእጅ ኳስ ውድድር 8 ሀገራት በሁለት የዕድሜ ዕርከን ከ17 እና ከ19 ዓመት በታች ይፎካከራሉ።

በውድድሩ ኬኒያ፣ ቡሩንድ፣ ሯዋንዳ፣ ጅቡቲ፣ ታንዛኒያ ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ተሳታፊ ናቸው።

05/05/2026
Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Addis Ababa