16/10/2025
👉መሃመድ አላባር ና ቱርኪ አል ሼክ ማናቸው?|👉ራፊኒሃ ወደ ዩናይትድ ?? 👉ዩናይትድ ለ UAE consortium ሊሸጥ ነው። ስለ ሽያጩ ምን ተባለ ዝርዝር ጉዳዮቹ👉መሃመድ አላባር ና ቱርኪ አል ሼክ ማናቸው?👉ባሌባ ና አንደርሰን ወደ ዩናይትድ 👉ካስሚሮ ና ቡርኖ ሊለቁ ነው።....
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bizu Sport/ቢዙ ስፖርት, Sports League, Addis Ababa/Ethiopia, Addis Ababa.
16/10/2025
👉መሃመድ አላባር ና ቱርኪ አል ሼክ ማናቸው?|👉ራፊኒሃ ወደ ዩናይትድ ?? 👉ዩናይትድ ለ UAE consortium ሊሸጥ ነው። ስለ ሽያጩ ምን ተባለ ዝርዝር ጉዳዮቹ👉መሃመድ አላባር ና ቱርኪ አል ሼክ ማናቸው?👉ባሌባ ና አንደርሰን ወደ ዩናይትድ 👉ካስሚሮ ና ቡርኖ ሊለቁ ነው።....
28/09/2025
የዩናይትድ አዲሱ ስቴድየም ግንባታ ተቋርጧል። ምን ችግር ገጠመው? ዝርዝሩ ጉዳዮቹ Join this channel to get access to perks:https://www.youtube.com/channel/UCuQrXqI9nb93bBmrKvNRwhQ/join
27/09/2025
27/09/2025
👉በሩብን አሞሪም ና በዣቢ አሎንሶ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው??
ሁለቱም አሰልጣኞች በፊት በነበሩት ክለብ አሎንሶ በባየርን ሌቨርኩሰን አሞሪም በስፖርቲንግ ሊዝበን ቤት በ 3-4-3 formation በጣም ስኬታማና ውጤታማ ቡድን ገንብተው አሁን ላይ ሁለት የአለማችን ሃያላን ክለቦችን እያሰለጠኑ ይገኛሉ።አሎንሶ ሪያልማድሪድን ሲያሰለጥን አሞሪም ማንቸስተር ዩናይትድን እያሰለጠነ ይገኛል።
በሁለቱ አሰልጣኞች መካከል ያለው መሰረታዊ ልዩነት adaptability ነው።አሎንሶ club world cup ውድድር ላይ 3-4-3 አሰላለፍ ሞክሮ በሪያልማድሪድ ቤት ያሉት ተጨዋቾች ይሄን አሰላለፍ ለመተግበር ብቁ ስላልሆኑ በቀጥታ ራሱን adapted በማድረግ የተለያዩ ውጤታማ ሊያደርጉት የሚችሉትን አሰላለፎች እየተገበረ ይገኛል።በሪያልማድሪድ ቤት በአሁን ሰአት 4-3-3 , 4-4-2 , 4-2-3-1 እና ሌሎችንም አሰላለፎች በመጠቀም ውጤታማ ጉዞ እያደረገ ይገኛል።በአዲሱ የውድድር አመትም ከ 7 ጨዋታዎች 7 ቱንም በማሸነፍ እየገሰገሰ ይገኛል።
በአንፃሩ አሰልጣኝ ሩብን አሞሪም በሊዝበን ውጤታማ የሆነበትን የአጨዋወት መንገድ ዩናይትድ ቤት በተደጋጋሚ ሞክሮት ላለፉት 9 ወራት ሊሰራለት አልቻለም።በዚህ የአጨዋወት መንገድ በዩናይትድ ቤት 32 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አድርጎ 9 አሸንፎ 17 ተሸንፎ 7 አቻ ወጥቷል።በዩናይትድ ታሪክ በ36.26% ዝቅተኛ የማሸነፍ ንፃሬ ያለው አሰልጣኝ ሲሆን በፕሪሚየር ሊጉም 25.5% የማሸነፍ ንፃሬ ያስመዘገበ አሰልጣኝ በመሆን አስከፊ ሪከርድ ማስመዝገቡን ቀጥሎበታል።በተደጋጋሚ ለሚዲያዎች እንደተናገረውም በፍፁም የአጨዋወት መንገዱን በመቀየር ፍላጎት እንደሌለው አስታውቋል።በምንም ተአምር adapt ማድረግ አይፈልግም በዚህም ምክንያት ዩናይትድንም ራሱንም አደጋ ላይ እየጣለ ይገኛል።ብዙ የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ ሌጀንዶች ከዚህ በዋላ አሞሪም በፍፁም መቀጠል የለበትም እያሉ ይገኛሉ።በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚንቀሳቀሱ የዩናይትድ ደጋፊዎችም አሞሪም ከክለቡ መሰናበት እንዳለበት ሃሳባቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።
የዩናይትድ ደጋፊዎች ስለ አሞሪም ምን ሃሳብ አላቹ? ይባረር ወይስ ይቀጥል???
27/09/2025
👉It's A Time to change the manager
አሞሪም ለቆ የጣሊያኑ ታክቲሺያን አሸናፊው አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ዩናይትድን መረከብ አለበት የሚሉ ድምፆች ተበራክተዋል።
የዩናይትድ ደጋፊዎች ምን አስተያየት አላቹ??
27/09/2025
👉ማንቸስተር ዩናይትድ የአዲሱን ስቴድየም ግንባታ ስራ አቋርጠውታል!!!! ለምን??
አዲሱ ስቴዲየም ዲዛይኑ በታዋቂው አርክቴክት Lord Normal Foster ኩባንያ በ Foster + partner የተሰራ ሲሆን።አርክቴክቱ እንደገለፁትም One of the most exciting project in the world today በማለት ስለ ፕሮጀክቱ ያላቸውን አድናቆት ገልፀው ነበር።
ስታዲየሙ ሶስት ከርቀት የሚታዩ Trident ያሉት ሲሆን በዩናይትድ ባጅ devil ሉ ከያዘው ጦር ጋር እንዲመሳሰል ተደርጎ የተሰራ ሲሆን በ 200 mile ወይም 40 Km ድረስ የሚታይ 200 metre ወደላይ የሚረዝም trident ነው።ከሊቨርፑል ከተማ ድረስ የሚታይ ነው ተብሎ ተነግሮለታል።
ስታዲየሙን የሸፈነው umbrella ደግሞ የማንቸስተር ከተማ በጣም ዝናባማ ከተማ ስለሆነች የከተማው ህዝብ ብዙ ግዜ በጃንጥላ ስለሚንቀሳቀስ ይሄንን የማህበረሰቡን አኗኗር የሚያሳይ ነው ተብሎለታል።umbrella ው ስቴድየሙን ብቻ ሳይሆን ከስታዲየሙ ውጪ ያሉትን ለደጋፊዎች ተብሎ የተሰራውን public recreational area ጨምሮ እንዲሸፍን ተብሎ የሚሰራ ሲሆን solar energy ና የዝናብ ውሃን በመቀየር አካባቢውን በማብራት ና በመስኖ እፅዋቶችን ጭምር የሚያለማ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት ከ £300m-£400m የሚፈጅ የጣራ ቴክኖሎጂ ልባስ እንደሆነ ተነግሮለታል።
ስታድየሙ 100ሺ የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን በእንግሊዝ ታላቁ ዌምብሌይ ስቴድየምን በመብለጥ ቁጥር አንድ የመያዝ ሲኖረው በአውሮፓ ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ላዬ ተቀምጧል በአዲሱ የባርሳ ስቴድየም በ Spotify camp nou 106ሺ የመያዝ አቅም ባለው ስቴድየም ብቻ ነው የሚበለጠው።
ስታድየሙን ለመገንባት £2B የሚፈጅ ሲሆን የትራፎርድ አካባቢም አብሮት የሚለማ ይሆናል።17ሺ አዳዲስ ቤቶች በስታድየሙ ዙሪያ የሚገነቡ ሲሆን 92ሺ አዳዲስ የስራ እድሎችም ይፈጠራሉ።በአመት 1.8 ሚሊየን ህዝብ ስቴድየሙን ና አካባቢውን ይጎበኛሉ ተብሎ የተገመተ ሲሆን ለ UK ኢኮኖሚም በአመት £7.3B ያስገኛል ተብሎ በኢኮኖሚስቶች ግምት ተሰጥቶታል።
👉ታዲያ ስቴድየሙን ለመገንባት ምን ችግር ገጠመው???
እንደ ምክንያትነትም የተነሳው ስታድየሙ ሊገነባበት የነበረው ቦታ ላይ የመሬት ባለቤቶቹ(Freightliners) አሳልፈው መስጠት ስላልፈለጉ ነው።
ባለቤቶቹ ቦታውን ለመስጠት እስከ 400 ሚልየን ፓውንድ የጠየቁ ሲሆን የክለባችን ሰዎችም ይህ ከልክ ያለፈ ዋጋ ነው በማለት ፕሮጀክቱን አቁመውታል።ዩናይትዶች መሬቱን በ £50m እንገዛዋለን የሚል ግምት ነበራቸው።በመካከላቸው ያለው gap £350m በጣም ሰፊ gap ና አንድ መለስተኛ ስቴድየም ሊገነባ የሚችል እንደሆነ ይገመታል።
እናም በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የቀረበው የታዋቂው አርክቴክ ንድፍ አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ እንደማይሰራ እርግጥ ሁኗል።
የክለባችን ሰዎችም አዳዲስ ፅንሰ-ሀሳቦችን እየገመገሙ ሲሆን አርክቴክቶቹም ሌላ ስታድየም ለመገንባት ቦታ መፈለግ ወይንም ደግሞ ያንኑ ኦልድትራፎር ያለበት ቦታ ላይ መገንባት በሚለው ላይ ውይይት እያደረጉ ነው።
ሆኖም ግን አንዳንድ ምንጮች እንደዘገቡት ከሆነ በዚህ ሰአት አብላጫው ድምፅ ኦልድትራፎርድን አፍርሶ ይገንባ የሚለው እንደሆነ ተናግረዋል።
(The Athletic , Laurie Whitwell )
24/09/2025
በታሪክ ከፍተኛ የባሎን ዶር አሸናፊዎች
🇦🇷 ሊዮኔል ሜሲ (8 ጊዜ)
🇵🇹 ክርስቲያኖ ሮናልዶ (5 ጊዜ)
🇫🇷 ሚሼል ፕላቲኒ (3 ጊዜ)
🇳🇱 ዮሃን ክሩፍ (3 ጊዜ)
🇳🇱 ቫን ባስተን (3 ጊዜ)
ከፍተኛ የባሎን ዶር አሸናፊ ሀገራት
🇦🇷 አርጀንቲና፡ 8 ጊዜ በአንድ ተጫዋች
🇵🇹 ፖርቱጋል፡ 7 ጊዜ በ3 ተጫዋቾች
🇳🇱 ኔዘርላንድስ፡ 7 ጊዜ በ3 ተጫዋቾች
🇩🇪 ጀርመን፡ 7 ጊዜ በ5 ተጫዋቾች
🇫🇷 ፈረንሳይ፡ 7 ጊዜ በ5 ተጫዋቾች
ከፍተኛ የባሎን ዶር እጩ ተወዳዳሪዎች
🥇- ክርስቲያኖ ሮናልዶ 🇵🇹 (18 ጊዜ)
🥈- ሊዮኔል ሜሲ 🇦🇷 (16 ጊዜ)
🥉- ፓኦሎ ማልዲኒ 🇮🇹 (13 ጊዜ)
ከፍተኛ የባሎን ዶር አሸናፊ ሊጎች
🇪🇸 ላሊጋ፡ 24 ጊዜ በ14 ተጫዋቾች
🇮🇹 ሴሪአ፡ 18 ጊዜ በ14 ተጫዋቾች
🇱🇷 ጆርጅ ዌአ በታሪክ የመጀመሪያው አውሮፓዊ ያልሆነ የባሎን ዶር አሸናፊ ነው።
🇱🇷 ጆርጅ ዌአ በታሪክ ብቸኛው አፍሪካዊ የባሎን ዶር አሸናፊ ነው።
ሌቭ ያሺን በ1963 ባሸነፈበት ወቅት በታሪክ የባሎን ዶርን ያሸነፈ ብቸኛው ግብ ጠባቂ ነው።
ፍራንዝ ቤከንባወር በታሪክ ባሎን ዶርን ሁለት ጊዜ ያሸነፈ ብቸኛው ተከላካይ ነው።
✅ በ1972 አሸንፏል።
✅ በ1976 አሸንፏል።
የፈረንሳይ እግር ኳስ የአመቱ ምርጥ የክለብ ሽልማት (ከ2021 ጀምሮ)
✅ 2021 - ቼልሲ
✅ 2022 - ማንቸስተር ሲቲ
✅ 2023 - ማንቸስተር ሲቲ
✅ 2024 - ሪያል ማድሪድ
22/09/2025
King Of World football 2025
ኦስማን ዴምቤሌ በወንዶቹ የ 2025 የባሎንዶር አሸናፊ መሆኑ ተረጋግጧል።
well deserved ousman😍🤙
17/09/2025
Breaking
ኒውካስል ዩናይትድ ኮቢ ማይኑን ከማንቸስተር ዩናይትድ በጃንዋሪ የዝውውር መስኮት ለማስፈረም እንቅስቃሴ ለማድረግ እያሰቡ ይገኛሉ።
አሰልጣኝ ኤዲ ሃው የተጫዋቹ የረጅም ግዜ አድናቂ ሲሆን በጃንዋሪ የዝውውር መስኮት ማይኑን ለማስፈረም ሙከራ ማድረግ ይፈልጋል ተብሏል።
(talksport)