Ethio Electric SC ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ

Ethio Electric SC ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ይህ የመብራት ሃይል ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ፔጅ ነዉ።

🇦🇹🇦🇹🇦🇹 ደስ የሚል ዜና 🇦🇹  ኢትዮ. ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ሁለት ዘመናዊ ባሶችን ተረክቦዋል ::ይህንን ላደረጋችሁ የክለባችን የበላይ ጠባቂዎችና የቦርድ አባላት ከፍ ያለ ምስጋና ይገባ...
01/09/2026

🇦🇹🇦🇹🇦🇹 ደስ የሚል ዜና

🇦🇹 ኢትዮ. ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ሁለት ዘመናዊ ባሶችን ተረክቦዋል ::

ይህንን ላደረጋችሁ የክለባችን የበላይ ጠባቂዎችና የቦርድ አባላት ከፍ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል ::

👉The New Generation👉ወርቃማው ትዉልድ 👉ከ1993ቱ ቲም 👉የማትረሱት  ተጫዋች :ጎል :ዉጤት እና ተጫዋች ግልፁ
18/08/2026

👉The New Generation

👉ወርቃማው ትዉልድ

👉ከ1993ቱ ቲም

👉የማትረሱት ተጫዋች :ጎል :ዉጤት እና ተጫዋች ግልፁ

🇦🇹 ኢትዮ. ኤሌክትሪክ በዚህ አመት ይጠቀምባቸው ከነበሩ የመጀመሪያ ተሰላፊ ተጫዋቾች መካከል እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት ሰባቱ (7) ለሌሎች ክለቦች ፈርመዋል ::እነሱም :-  1.ያሬድ የ...
16/08/2026

🇦🇹 ኢትዮ. ኤሌክትሪክ በዚህ አመት ይጠቀምባቸው ከነበሩ የመጀመሪያ ተሰላፊ ተጫዋቾች መካከል እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት ሰባቱ (7) ለሌሎች ክለቦች ፈርመዋል ::
እነሱም :-
1.ያሬድ የማነ ከ38 ጨዋታ 37 ጨዋታ የተሰለፈ
2.ሀሰን ሁሴን ከ38 ጨዋታ 35 ጨዋታ የተሰለፈ
3.ኢዮብ ገ/ማርያም ከ38 ጨዋታ 35 ጨዋታ የተሰለፈ

4.በፍቃዱ አስረሳሀኝ ከ38 ጨዋታ 35 ጨዋታ የተሰለፈ
5.በረከት ወልደዩሐንስ ከ38 ጨዋታ 34 ጨዋታ የተሰለፈ
6.ቢኒያም በቀለ ከ38 ጨዋታ 34 ጨዋታ የተሰለፈ
7. የሱፍ ሞሩ ከ38 ጨዋታ 30 ጨዋታ የተሰለፈ

ዮርዳኖስ አባይ (ቡሎ)
15/08/2026

ዮርዳኖስ አባይ (ቡሎ)

ኢትዮ. ኤሌክትሪክ ሌላኛዉን ወሳኝ ተጫዋች አጣ:: ወሳኙን የግብ ዘብ  የሱፍ ሞሩ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ  በተሰለፈባቸው 30 ጨዋታዎችን በሙሉ በመሰለፍ 2700 ደቂቃዎች በመሰለ...
15/08/2026

ኢትዮ. ኤሌክትሪክ ሌላኛዉን ወሳኝ ተጫዋች አጣ::

ወሳኙን የግብ ዘብ የሱፍ ሞሩ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በተሰለፈባቸው 30 ጨዋታዎችን በሙሉ በመሰለፍ 2700 ደቂቃዎች በመሰለፍ በጥሩ ብቅትና አስደናቂ እንቅስቃሴ ከደረጉ ተጫዋቾች አንዱ ነበር ::

የሱፍ ሞሩ ወሳኝና ለጎል የቀረቡ ኳሶችን በማዳን ኢትዮ. ኤሌክትሪክ 5ኛ ደረጃ ይዞ እንድያጠናቅቅ ከደረጉ ወሳኝ ተጫዋች ነበር ::

🇦🇹 ከኢትዮ. ኤሌክትሪክ ወጣት ቡድን በማደግ ላለፉት ሁለት አመታት በዋናው ቡድን በመሃል ተከላካይነት በመጫወት አስደናቂ አቋሙን  በማሳየት ያሳለፈው ቢኒያም በቀለ ኢትዮ.ኤሌክትሪክን ከለቀቁ...
14/08/2026

🇦🇹 ከኢትዮ. ኤሌክትሪክ ወጣት ቡድን በማደግ ላለፉት ሁለት አመታት በዋናው ቡድን በመሃል ተከላካይነት በመጫወት አስደናቂ አቋሙን በማሳየት ያሳለፈው ቢኒያም በቀለ ኢትዮ.ኤሌክትሪክን ከለቀቁ ወሳኝ ተጫዋቾች አንዱ ነው ::

🇦🇹 ቢኒያም በቀለ በተደጋጋሚ ከኤልፓ አመራሮች ተገናኝቶ ድርድር ሲያካሄድ ነበር ነገር ግን በአመራሮቹ በኩል ፌዴሬሽኑን ከክለቦች ጋር የሚያደርገዉን ዉይይት ዉሳኔ እንጠብቃለን በማለታቸው በዚህ መሃል ይህን ወሳኝ ተጫዋች ቅ/ጊዮርጊሶች በሁለት አመት ዉል የግላቸው አድርገዉታል ::

በሀዋሳ ኮረም ሜዳ መነሻዉን ያደረገው ቢኒያም በቀለ በዘንድሮው አመት ለኢትዮ. ኤሌክትሪክ በ34 ጨዋታዎች 2889 ደቂቃዎችን ተሰልፎዋል ::

🇦🇹 ከቢ ቡድን እያሳደጉ መጥቀም በሚችሉበት ሰአት ማቆየት እየተቻለ ለሌሎች ክለቦች አሳልፎ መስጠት በጣም ያስቆጫል ::

🇦🇹 👉 በኢትዮ. ኤሌክትሪክ አመራሮች ቸልተኝነት ክለቡን ብዙ አመታት ማገልገል  እየፈለገና እየቻለ እንዲለቅ የተደረገው                ያሬድ የማነ 🇦🇹👉ያሬድ የማነ የግራ መስመር ተ...
13/08/2026

🇦🇹 👉 በኢትዮ. ኤሌክትሪክ አመራሮች ቸልተኝነት ክለቡን ብዙ አመታት ማገልገል እየፈለገና እየቻለ እንዲለቅ የተደረገው ያሬድ የማነ

🇦🇹👉ያሬድ የማነ የግራ መስመር ተከላካይ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከሚገኙ ተስፋ ሰጪ እና ጥራት ያላቸው የግራ ተከላካዮች መካከል አንዱ ነው።

🇦🇹👉 ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ታዳጊ ቡድን ያደገው ያሬድ፣ በዋናው ቡድን ውስጥ በቋሚነት እየተጫወተና ለክለቡ ጉልህ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኝ ነበር ።

🇦🇹👉በመከላከልም ሆነ በማጥቃት ውስጥ ያለው ተሳትፎ ከፍተኛ ሲሆን፣ ጥሩ የኳስ ቁጥጥር፣ ፍጥነት እና የግራ እግር ጥራት ያለው ተጨዋች ነው።

👉 ትኩረት የሚሻው ኢትዮ. ኤሌክትሪክ💔 በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከሚወዳደሩ ክለቦች ዉስጥ አንዱ የሆነው ኢትዮ. ኤሌክትሪክ 👍 በሊጉ  ካሉት 18 ክለቦች ዉስጥ አንዱ ነው ሁሉም ክለቦች ለሚቀ...
02/08/2026

👉 ትኩረት የሚሻው ኢትዮ. ኤሌክትሪክ💔

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከሚወዳደሩ ክለቦች ዉስጥ አንዱ የሆነው ኢትዮ. ኤሌክትሪክ

👍 በሊጉ ካሉት 18 ክለቦች ዉስጥ አንዱ ነው ሁሉም ክለቦች ለሚቀጥለው አመት የዋንጫ ተፎካካሪ ሆነው ለመቅረብ ዉል የጨረሱን ዉላቸዉን በማደስ ክፍተት ባለባቸው ቦታ ላይ ቦታዉን ይሸፍኑልኛል በማለት እያስፈረሙ ቡድናቸዉን በማጠናከር ላይ ይገኛሉ ::

👉 ኢትዮ. ኤሌክትሪክ ወሳኝ የሆኑ ተጫዋቾቹን በተፎካካሪ ክለቦች እየተነጠቀ ነው ::

👉 የሊጉ ክለቦች ሁሉም ራሳቸዉን እየጠናከሩ ባሉበት ሰአት ኢትዮ. ኤሌክትሪክ ግን ምንም እንቅስቃሴ እያደረገ አይደለም በዝውውር ሆነ ሁል በማደስ ደረጃ ምንም እንቅስቃሴ እያደረገ አይደለም ::

👉 እባካችሁ የኢትዮ. ኤሌክትሪክ ደጋፊዎች የባለ ድርሻ አካላት ሁላ ለዚህ ክለብ ድምፅ ሁኑለት::

ሳሙኤል አለባቸው (ሳሚ ጊቻው )
01/08/2026

ሳሙኤል አለባቸው (ሳሚ ጊቻው )

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ላለፉት አስራ ምናምን አመታት ከሊጉ መውረድ ፣ መውጣት እና ላለመውረድ ሰቀቀን ውስጥ ሆኖ አሳልፎ አምና ቡድኑ በኮች ዘሪሁን ሸንገታ እየተመራ አምስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀ...
30/07/2026

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ላለፉት አስራ ምናምን አመታት ከሊጉ መውረድ ፣ መውጣት እና ላለመውረድ ሰቀቀን ውስጥ ሆኖ አሳልፎ አምና ቡድኑ በኮች ዘሪሁን ሸንገታ እየተመራ አምስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቁ ለዘንድሮ በጥሩ ዝግጅት ለዋንጫ ተፎካካሪ ቡድን ይዘው ይመጣሉ ስንል ጭራሽ አሰልጣኙን ለማባረር ታስቦ ከብዙ ንግግሮች በኋላ እንዲቀጥል ተደርጓል።

ቡድኑ ላይ ጥሩ የሚባሉ ተጫዋቾችን ማስቀጠል እና ሌላ ቲሙን ሊያጠነክሩ የሚችሉ ተጫዋቾችን ይጨምራሉ ብለን ስንጠብቅ ያሉንን ወደ ሌላ ቲም እየለቀቁ ነው በሚቀጥለው አመት ላለመውረድ ሳይሆን መውረድ ፍላጎቱ የሚመስለው የኢትዮ ኤሌክትሪክ አመራሮች በተጫዋች ፊርማ ላይ እስካሁን ዝምታቸውን መርጠዋል እባካችሁ ይህ ክለብ ዋጋ የተከፈለበት ክለብ ነው አቶ አርአያ የተቀመጡበት ወንበር ላይ ተቀምጣችሁ ክለቡ የዋንጫ ተፎካካሪ ብቻ ሳይሆን ዋንጫ የሚያነሳ ቲም ለመገንባት ሞክሩ።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Electric SC ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category