Are you ready for our next unforgettable journey? Join an existing group to explore the stunning landscapes of the Afar Danakil Depression, one of the hottest places on Earth!
Danakil Depression 3-Day Tour Package
Dates: 02 - 04 May 2025 / ሚያዝያ 24 - 26 2017 ዓ.ም Experience the dramatic landscapes of the Danakil Depression with a 3-day adventure exploring active volcanoes, salt lakes, and otherworldly scenery.
The tour covers Erta Ale, Dallol, and Afdera, offering an unforgettable journey through one of the world's most extreme environments.- Breathtaking Scenery: Unique geological formations, colorful sulfur springs, and vast salt flats.-Adventure Activities:Trekking, photography, and more!
Booking now! +251942545470
Guzo Adwa Hiking Events
Its all about Nature,History,culture , hiking , trekking and camping adventures in ethiopia ��?
18/04/2025
Wishing everyone a fun, relaxing, and safe weekend!
📌🏔️ Kundudo mountain
📷 Abel Gashaw
የወርሃ ሚያዝያ ትልቁ ጉዟችን " ጉዞ ወደ አፋር ደናኪል ዲፕሬሽን" ከሚያዝያ 24-26 (ከአርብ-እሁድ)
በፍፁም እንዳያመልጣችሁ!
ለተጨማሪ መረጃዎች ይደውሉልን!
📞 +251942545470,+251964423971
አስቀድሞ ቦታ በማስያዝ የክፍያ ቅናሽ ዕድሉን ይጠቀሙ!
Thank you, Harar, for the unforgettable memories during the shewaleid festival . The warmth, culture, and hospitality made it truly special .we had an amazing time!
13/04/2025
ፈረንጆቹ "porters” ይሏቸዋል ፤ እኛ ደሞ "አጋዦቻችን"
ተራራን ያለነሱ ድጋፍ እና ዕርዳታ መውጣት የማይታሰብ ነው::
ስራቸው ቀላል አይደለም:: እንግዶች ለተራራ ላይ አዳር የሚያስፈልጓቸውን ንብረቶች በሙሉ እነርሱ በጀርባቸው ተሸክመው ወደ ተራራ ላይ ይወጣሉ ::
የካምፒንግ ጉዟችን የልብ ምት ናቸው ብንል ማጋነን አይሆንም:: እነሱ ከሌሉ የማደሪያ ድንኳኖቻችን ፣ የመተኛ ብርድልብሶቻችን ፣ የማብሰያ እቃዎቻችን እንዲሁም ሌሎች ለጉዞ አስፈላጊ ንብረቶቻችንን በሙሉ ይዞ በነፍስወከፍ መውጣት እጅግ ከባድ ነው::
በምስሉ ላይ የሚታዩት ወጣቶች የቁንድዶ ተራራ የአንድ ምሽት አዳራችን ስኬታማ እንዲሆን የረዱን ናቸው::
ወደ ቁንዱዶ ተራራ እንግዳ እየመጣ መሆኑን በስልክ መረጃ ሲደርሳቸው እራሳቸውን በሚገባ አዘጋጅተው ይጠብቃሉ:: እንግዳ በአግብቡ ያስተናግዳሉ ፤ በአደራ የተሰጣቸውን ንብረት በተራራው ጫፍ ላይ በታማኝነት ያስረክባሉ::
ለዚህ ሁሉ አገልግሎታቸው ደግሞ ያለምንም ጭቅጭቅ ተመጣጣኝ ክፍያ ይጠይቃሉ::
ከፍተኛ ክብር እና ምስጋና ለተራራው ላይ አጋዦቻችን በሙሉ::
መልካም ሰንበት!
11/04/2025
ተጨማሪ ውብ ምስሎች !
📷 በ Abel Gashaw
Visit Harar
11/04/2025
የባቢሌ ማስታወሻ
10/04/2025
በኢትዮዽያ ብቸኞቹ የዱር ፈረሶች እዚህ ይገኛሉ::
ቁንድዶ ወይንም በተለምዶ አጠራር "W"ተራራ ላይ🏔️ (ከባህር ጠለል በላይ 2,950 ሜ)
ከአዲስ አበባ 565 ኪሎ ሜትር ወይንም ከሀረር ከተማ 80 ኪሎ ሜትር ርቅት ላይ የሚገኘው ይህ ተራራ በምስራቅ ሃረርጌ ጉርሱም እና ጃርሶ ወረዳዎች መሃል ይገኛል::
የቁንድዶን ተራራ ለመጎብኘት ቀላሉ እና ተመራጩ መንገድ በጠዋቱ በረራ ከአዲስ አበባ -ድሬድዋ በማቅናት በመቀጠልም በሀረር ከተማ በኩል ወደ ጉርሱም ከተማ በመኪና በመ ጓ ዝ ቁንዱዶ ተራራ ላይ የውሎ ገብ ወይንም በተራራው ላይ የአንድ ቀን የድንኳን ውስጥ አዳር አድርጎ መመለስ ይቻላል:: (ከአዲስ አበባ ወይንም ከሀረር ከተማ ራቅ ካለ ቦታ ወደ ቁንድዶ ተራራ ለሚሄዱ ተጓዦች በተራራው ላይ ቢያንስ አንድ ምሽት ቢያሳልፉ ተመራጭ ይሆናል)
ቁንዱዶ እጅግ ውብ ተራራ ነው:: ባለግርማ ሞገሶቹ የዱር ፈረሶችን በቅርብ ርቀት ማየት ደግሞ ሌላኛው የጉዞው አስደሳች ክፍል ነው::
Visit Harar
09/04/2025
እኛ በአስታራቂው የጀጎል መንገድ ታርቀናል:: እናንተም ሞክሩት🤗
📷 Abel Gashaw
Good Morning from Mount Kundudo 🏔️🌞
2,950 M ASL.
08/04/2025
"እኔስ በሀገሬ እንኳን ሰው ወፍ አለምዳለው"
ሀረር ላይ ቀን ከንስር አሞራ ጋር ውለን : ማታ ከጅቦች ጋር አመሸን:: ጉብኝታችን አሁንም ይቀጥላል::
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Contact the business
Telephone
Website
Address
16054