የስፖርቱ አለም ዝነኞች ሚስጥር -

የስፖርቱ አለም ዝነኞች ሚስጥር - የስፖርቱ ዓለም ዝነኞች አስገራሚና ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኙበታል

ሉዊስ ሀል ኮንትራቱን አራዝሟል !ኒውካስል ዩናይትድ የመስመር ተጨዋቹ ሉዊስ ሀልን ውል እስከ 2031 ማራዘሙን በይፋ አስታውቋል።ማንችስተር ዩናይትድ በዚህ ክረምት ሉዊስ ሀልን ለማስፈረም ጥረ...
11/09/2026

ሉዊስ ሀል ኮንትራቱን አራዝሟል !

ኒውካስል ዩናይትድ የመስመር ተጨዋቹ ሉዊስ ሀልን ውል እስከ 2031 ማራዘሙን በይፋ አስታውቋል።

ማንችስተር ዩናይትድ በዚህ ክረምት ሉዊስ ሀልን ለማስፈረም ጥረት ቢያደርግም ኒውካስል ውድቅ ማድረጉ አይዘነጋም።

እንግሊዛዊው የግራ መስመር ተሰላፊ ሀል በክለቡ የሁለት አመት ውል ቢቀረውም አዲስ የተሻሻል ውል ተሰጥቶታል።

ኒውካስል ዩናይትድ በተጨዋቹ ኮንትራት ውስጥ የውል ማፍረሻ አንቀጽ እንዳላካተተ ተገልጿል።

ይህም ማለት ማንችስተር ዩናይትድ ዳግም ለማስፈረም ከጠየቀ ኒውካስል ውድቅ የማድረግ ወይም ከፍተኛ ክፍያ የመጠየቅ እድል ይሰጠዋል።
https://t.me/+w8RCswOtQzs4ZmY8
https://www.facebook.com/wawlovtad

አሊሰን የገንዘብ ቅጣት ተጣለበት ! የሊቨርፑሉ ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር ከኖቲንግሀም ጨዋታ በኋላ የተጨዋች መቀየሪያ ቦርድ በእግሩ ሰብሮ ነበር። አሁን ላይ አሊሰን ቤከር ቦርዱን በመስበሩ የ...
10/09/2026

አሊሰን የገንዘብ ቅጣት ተጣለበት !

የሊቨርፑሉ ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር ከኖቲንግሀም ጨዋታ በኋላ የተጨዋች መቀየሪያ ቦርድ በእግሩ ሰብሮ ነበር።

አሁን ላይ አሊሰን ቤከር ቦርዱን በመስበሩ የ 8,000 ፓውንድ የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለበት ተገልጿል።

አሊሰን ቦርዱን የሰበረው ፍፁም ቅጣት ምት እንዲሰጥባቸው ምክንያት ሆኗል በሚል ነበር።

በጨዋታው ወቅት የተጨዋች መቀየሪያ ኤሌክትሮኒክ ቦርዱ ተበላሽቶ ተቀይረው ሊገቡ የነበሩ የሊቨርፑል ተጨዋቾች ዘግይተው ነበር።.
https://t.me/+w8RCswOtQzs4ZmY8
https://www.facebook.com/wawlovtad

“ በርናርዶ ሲልቫ አስፈርሙኝ ብሎ ጠይቆናል ” ዴኮ የባርሴሎናው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ዴኮ ባርሴሎና በርናርዶ ሲልቫን ለምን እንዳላስፈረመ አስረድተዋል። “ በርናርዶ ሲልቫ አስፈርሙኝ ብሎ ለ...
10/09/2026

“ በርናርዶ ሲልቫ አስፈርሙኝ ብሎ ጠይቆናል ” ዴኮ

የባርሴሎናው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ዴኮ ባርሴሎና በርናርዶ ሲልቫን ለምን እንዳላስፈረመ አስረድተዋል።

“ በርናርዶ ሲልቫ አስፈርሙኝ ብሎ ለባርሴሎና ጥያቄ አቅርቦ ነበር ” ሲሉ ዴኮ ተናግረዋል።

አክለውም “ ነገርግን ባርሴሎና ውስጥ ቋሚ እንደማይሆን እና አነስተኛ ክፍያ እንደሚያገኝ ሲረዳ ሪያል ማድሪድን ለመቀላቀል ወስኗል “ ብለዋል።
https://t.me/+w8RCswOtQzs4ZmY8
https://www.facebook.com/wawlovtad

“ የቼልሲ ዋንጫ ለቶተንሀም ሊሰጥ ይገባል ” ፖቼቲኖአርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ቼልሲ 2017 ያሳካው የሊግ ዋንጫ ለቶተንሀም እንዲሰጥ ጠይቀዋል። “ ቼልሲ የፋይናንስ ደንብ መጣ...
10/09/2026

“ የቼልሲ ዋንጫ ለቶተንሀም ሊሰጥ ይገባል ” ፖቼቲኖ

አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ቼልሲ 2017 ያሳካው የሊግ ዋንጫ ለቶተንሀም እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

“ ቼልሲ የፋይናንስ ደንብ መጣሱን አምኖ ቅጣቱንም ተቀብሏል “ ያሉት ፖቼቲኖ “ ስለዚህ ዋንጫው ለቶተንሀም መሰጠት አለበት “ ብለዋል።

“ ምክንያቱም ውድድሩ የተደረገው በተመሳሳይ ህግ አይደለም እነሱ ጥሰዋል “ ሲሉ አስረድተዋል።

አክለውም “ የቼልሲ ደጋፊዎች እንደሚበሳጩብኝ አውቃለሁ ነገርግን የጣሰው ቶተንሀም ቢሆንም ዋንጫው አይገባንም ብዬ እናገር ነበር " ብለዋል።

ቼልሲ በ 2016/17 የውድድር ዘመን ሊጉን ሲያሳካ ቶተንሀም ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ነበር ያጠናቀቀው።
https://t.me/+w8RCswOtQzs4ZmY8
https://www.facebook.com/wawlovtad

🚨 የ2026 የወንዶች ባሎንዶር 30 እጩዎች፦🏴 ጁድ ቤሊንግሃም🇪🇸 ፓው ኩባርሲ🇪🇸 ማርክ ኩኩሬያ🇫🇷 ኦስማን ዴምቤሌ🇨🇴 ሉዊስ ዲያዝ🇵🇹 ብሩኖ ፈርናንዴስ🇧🇷 ጋብሪኤል🇳🇴 ኤርሊንግ ሃላንድ🇲🇦 አ...
08/09/2026

🚨 የ2026 የወንዶች ባሎንዶር 30 እጩዎች፦

🏴 ጁድ ቤሊንግሃም
🇪🇸 ፓው ኩባርሲ
🇪🇸 ማርክ ኩኩሬያ
🇫🇷 ኦስማን ዴምቤሌ
🇨🇴 ሉዊስ ዲያዝ
🇵🇹 ብሩኖ ፈርናንዴስ
🇧🇷 ጋብሪኤል
🇳🇴 ኤርሊንግ ሃላንድ
🇲🇦 አሽራፍ ሀኪሚ
🏴 ሃሪ ኬን
🇬🇪 ክቪቻ ክቫራትስኬሊያ
🇪🇸 ላሚን ያማል
🇸🇳 ሳዲዮ ማኔ
🇧🇷 ማርኪንዮስ
🇦🇷 ላውታሮ ማርቲኔዝ
🇫🇷 ኪሊያን ምባፔ
🇵🇹 ኑኖ ሜንዴስ
🇦🇷 ሊዮኔል ሜሲ
🇵🇹 ጆአዎ ኔቬስ
🇫🇷 ማይክል ኦሊሴ
🇪🇨 ዊሊያን ፓቾ
🇲🇽 ጁሊያን ኪኞኔስ
🏴 ዴክላን ራይስ
🇪🇸 ሮድሪ
🇪🇸 ፋቢያን ሩይዝ
🇫🇷 ዊሊያም ሳሊባ
🇪🇸 ፌራን ቶሬስ
🇫🇷 ዳዮት ኡፓሜካኖ
🇧🇷 ቪኒሲየስ ጁኒየር
🇵🇹 ቪቲንያ
https://t.me/+w8RCswOtQzs4ZmY8
https://www.facebook.com/wawlovtad

ማክ አሊስተር ኮንትራቱን አያራዝምም ! አርጀንቲናዊው የሊቨርፑል አማካይ ማክ አሊስተር በክለቡ ያለውን ውል እንደማያራዝም አረጋግጧል። ማክ አሊስተር በሊቨርፑል ያለው ውል በ 2028 የሚያበቃ...
08/09/2026

ማክ አሊስተር ኮንትራቱን አያራዝምም !

አርጀንቲናዊው የሊቨርፑል አማካይ ማክ አሊስተር በክለቡ ያለውን ውል እንደማያራዝም አረጋግጧል።

ማክ አሊስተር በሊቨርፑል ያለው ውል በ 2028 የሚያበቃ ሲሆን አዲስ ውል እንዳልተሰጠው ተናግሯል።

“ እድል ነበር “ ያለው ማክ አሊስተር “ ነገርግን ክለቡ አዲስ ውል ለማቅረብ ቁመናው ላይ እንዳልሆነ ሰምቻለሁ “ ብሏል።

አክሎም “ የሰማሁት ዜና በጣም አሳዝኖኛል “ ሲል ገልጿል።

" ስቦዝላይ እና ግራቨንበርች ውላቸው ተራዝሟል ይገባቸዋል እኔንም አስደስቶኛል ነገርግን እኔ ያንን ባለማግኘቴ አዝኛለሁ “ ማክ አሊስተር
https://t.me/+w8RCswOtQzs4ZmY8
https://www.facebook.com/wawlovtad

አሰልጣኝ ሰርዲዮቪች ሚሎቲን ሚቾ በቅ.ጊዮርጊስ ቤት ሚከፈላቸው ወርሃዊ ደሞዝ 5000 USD ወይም 815,000 የኢትዮጵያ ብር ነው! በዚህም በሊጉ ከሚገኙና ከፍተኛ ወርሃዊ ደሞዝ ከሚያገኙ አ...
08/09/2026

አሰልጣኝ ሰርዲዮቪች ሚሎቲን ሚቾ በቅ.ጊዮርጊስ ቤት ሚከፈላቸው ወርሃዊ ደሞዝ 5000 USD ወይም 815,000 የኢትዮጵያ ብር ነው!
በዚህም በሊጉ ከሚገኙና ከፍተኛ ወርሃዊ ደሞዝ ከሚያገኙ አሰልጣኞች መካከል ሰርቢያዊው 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
https://t.me/+w8RCswOtQzs4ZmY8
https://www.facebook.com/wawlovtad

Address

Addis Ababa
1982

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የስፖርቱ አለም ዝነኞች ሚስጥር - posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category