Haset Sport ሀሴት ስፖርት

Haset Sport ሀሴት ስፖርት

Share

ይህ ቻናል 24 ሰዐት ስፖርታዊ መረጃዎችን በፍጥነት ወደ እናንተ ያደርሳል።

Photos from Haset Sport ሀሴት ስፖርት's post 19/07/2026

የመጀመሪያ አጋማሽ : የጨዋታ እንቅስቃሴ

- ስፔን በመጀመሪያው አጋማሽ ሙሉ የጨዋታ ብልጫ ወስዳ የመጀመሪያ አጋማሽ ተጠናቋል።

- ስፔኖች በጨዋታ እንቅስቃሴ ፣ የኳስ ፍሰት እና ፍጥነት ከአርጀንቲና ተሽለው ታይተዋል።

- አርጀንቲና በሁለተኛው አጋማሽ እንዳለፉት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች የሚያገኟቸውን የግብ እድል ይጠቀማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

- ስፔን የግራ መስመር ክፍል ተጫዋቿ ኩኩሬላ ወደ ፊት መስመር ተጠግቶ መጫወቱ አርጀንቲና በአምስት ተከላካይ እንድትጫወት አስገድዷታል።

- በዚህም የአርጀንቲና ተጫዋች በስፔን የመሐል ሜዳ ክፍሉ ላይ ጫና እንዳያደርግ አድርጎታል።

- ስፔን በመጀመሪያው አጋማሽ በነበራቸው እንቅስቃሴ ከኳስ ጋር እና ከኳስ ውጪ ተጋጣሚያቸውን ተጭነው ሲጫወቱ ተመልክተናል።

Photos from Haset Sport ሀሴት ስፖርት's post 15/06/2026

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው የተለያዩ ባህላዊ እና ሌሎች ይዘቶቸ ያሏቸው የሙዚቃ ሥራዎችን ለአድማጭ ተመልካች ያበረከተ ሲሆን ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ነበር።

Photos from Haset Sport ሀሴት ስፖርት's post 12/06/2026

ከሞት አፋፍ እስከ ሀገርን ወክሎ ጎል ማስቆጠር...
ከዛሬ ስድስት አመታት በፊት ራውል ሂሚኔዝ በህይወት እና በሞት መካከል ነበር። ዛሬ ላይ ግን በአለም ዋንጫው ሀገሩን ሜክሲኮ ወክሎ ጎል አስቆጥሯል።
ሂሚኔዝ ከ6 አመታት በፊት ክለቡ ወልቭስ ከ አርሰናል ጋር ሲጫወት አሰቃቂ የጭንቅላት ጉዳት አጋጥሞት ከሜዳ ወጣ። በሀኪሞች በመትረፉ እድለኛ እንደሆመ ተነገረው። ለ9 ወራት ያህልም ከሜዳ ርቆ ህክምና ሲከታተል ቆየ። ተመልሶ ወደሜዳ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮም ታዲያ ጭንቅላቱ ላይ መከላከያ ' head guard' ማሰር ነበረበት። አሁን ድረስም' head guard' አስሮ ይጫወታል።
ትላንት ምሽት በ2026ቱ አለም ዋንጫ ሀገሩ ሜክሲኮ ደቡብ አፍሪካን ባሸነፈችበት ጨዋታም ሁለተኛዋን ጎል አስቆጠረ፤ ለራሱ ደግሞ በአለም ዋንጫ ያስቆጠረው የመጀመሪያው ጎል ሆኖ ተመዘገበለት። ከጎሏ በኋላም ደስታው እምባውን መቆጣጠር እስኪያቅተው ድረስ እንደነበር በቴሌቭዥን ስክሪኖቻችንን ተመለከትን።

Photos from Haset Sport ሀሴት ስፖርት's post 30/05/2026

አርሰናል ከፒኤስጂ እያደረጉ የሚገኙትን የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ 1ለ0 እየመሩ ወደ እረፍት አምርተዋል።

ካይ ሀቨርትዝ አርሰናልን ቀዳሚ ያደረገች ግብ በጨዋታው መጀመሪያ ደቂቃ አስቆጥሯል።

⚽️ የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ ፒኤስጂ 77% - 23% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

- ፒኤስጂ በመጀመሪያው አጋማሽ ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ ማድረግ የቻለው 1️⃣ ጊዜ ነው።

- አርሰናል በመጀመሪያው አጋማሽ በፒኤስጂ የፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ውስጥ መግባት የቻለው 4️⃣ ጊዜ ነው።

18/05/2026

ይገምቱ ይሸለሙ
20,000 birr
ለመሸለም
1 FOLLOW ያድረጉ
2 SHARE ያድርጉ
መልካም ዕድል
#ይገምቱይሸለሙ

17/05/2026

👏🇵🇹💥ብሩኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖ 20ኛው አሲስት ደፈነውውውውውው ሪከርዱን መጋራት ቻለ ምቤሞ በመጨረሻም ካሰውው አሁን ፖርቹጋላዊዉ ነበልባል የምንጊዜም ብቸኛው ባለሪከርድ ለመሆን እነሆ 1 አሲስት ብቻ በቂው ነው።

17/05/2026

ይህንን ፎቶ ዕውነተኛ የማን.ዩናይትድ ደጋፊዎች ዝም ብለው አያልፉትም።

16/05/2026

ማንችስተር ሲቲ ሻምፒዮን ሆኗል !

በእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ፍፃሜ ማንችስተር ሲቲ ቼልሲን 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆኗል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ጎል አንቶይን ሴሜኒዮ አስቆጥሯል።

የአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን በውድድር ዘመኑ ሁለተኛ የሀገር ውስጥ ዋንጫውን አሳክቷል።

ማንችስተር ሲቲ 8️ኛ የኤፌ ካፕ ዋንጫውን ሲያሸንፍ ቼልሲ በበኩሉ በተከታታይ ለአራተኛ ጊዜ የኤፌ ካፕ ፍፃሜ ተሸንፏል።

14/05/2026

የ200 ሚሊዮን ፓውንድ ፍልሚያ በዌምብሌይ ሊካሄድ ቀን ቆርጧል!
ሀል ሲቲ vs ከሳውዝሃምፕተን
በእግር ኳስ ዓለም በገንዘብ መጠኑ እጅግ ግዙፉና "ውዱ" ጨዋታ ተረጋግጧል! የሻምፒዮንሺፕ የፕሌይ-ኦፍ ፍጻሜ በዌምብሌይ ስታዲየም ሀምሌ 15 በዕለተ ቅዳሜ ሀል ሲቲን ከሳውዝሃምፕተን ጋር ያገናኛል።

አሸናፊው ቡድን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ከማደጉ ጋር ተያይዞ ቢያንስ 200 ሚሊዮን ፓውንድ ገቢ ያስገባል! ይህም ጨዋታውን በዓለም ላይ በገንዘብ ረገድ እጅግ ማራኪው ጨዋታ ያደርገዋል።
ሀል ሲቲ ሚልዎልን አሸንፎ ሲያልፍ፣ ሳውዝሃምፕተን ደግሞ በጭቅጭቅ የታጀበውንና ሚድልስቦሮን የገጠመበትን ጨዋታ ድል አድርጎ ለፍጻሜው ደርሷል። በፍፃሜው ሳዉዝሃምተን ከሃል ሲቲ ጋር ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለማደግ ግንቦት 15 በዌምብሌይ ይፋለማሉ።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address

Addis Ababa
1000