ጨፍጫፊ፣ ገዳይ እና አፋኝ የሆነው ገዳ በተግባር እየታየ ነው።
Ethio Now / ምን አዲስ
Stay Informed. Stay Ahead. Ethio What's New | ምን አዲስ: Your home for Ethiopian News Today. Stay informed with what's happening across Ethiopia.
We provide the latest Ethiopian breaking news (ትኩስ መረጃ), National Dialogue updates, and Ethiopian currency exchange rates.
‼️UPDATE ‼️
በመርካቶ 4ኛ አካባቢ የተቀሰቀሰውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው
በመርካቶ 4ኛ አካባቢ ያጋጠመውን አደገኛ የእሳት አደጋ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር የእሳት አደጋ ሰራተኞች፣ የፀጥታ ኃይሎች እና የአካባቢው ነጋዴዎች የተቀናጀ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ምሽት 2፡53 በተገኘው መረጃ መሠረት በስፍራው ያለው የጋራ ርብርብ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ አደጋውን በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ይቻላል ተብሎ ይጠበቃል።
#መርካቶ
05/09/2026
መርካቶ ከባድ የ እሳት አደጋ ምሽት 2:30
እሳቱን ለማጥፋት ጥረት እየተደረገ ቢሆንም በፍጥነት መዛመዱ አስቸጋሪ አድርጎታል።
ምሽት 2:30 ገደማ የጀመረው እሳት መነሻ ምክንያት እነደደረሰን ከዝርዝር መረጃ ጋር እናደርሳችኋለን።
#መርካቶ
05/09/2026
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካን ትክክለኛ ስፋት የሚያሳይ አዲስ የዓለም ካርታን ለማጽደቅ ድምጽ ሰጠ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን አህጉር ትክክለኛ መልክዓ-ምድራዊ ስፋት የሚያሳይ አዲስ የዓለም ካርታን ለመጠቀም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ።
በቶጎ አቅራቢነትና በአፍሪካ ህብረት አጋርነት የቀረበው "ካርታውን ማስተካከል" (Correct the Map) የተሰኘው ይህ የውሳኔ ሀሳብ በ164 ሀገራት ድጋፍ ሲጸድቅ፣ አሜሪካ ብቻ ተቃውማዋለች፤ 6 ሀገራት ደግሞ ድምፅ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
አዲሱ "Equal Earth Projection" የተሰኘው ካርታ በ2018 እ.ኤ.አ. የተሰራ ሲሆን የየአህጉራቱን ትክክለኛ የመሬት ስፋትና ተመጣጣኝነት ጠብቆ የሚያሳይ ነው። ከ16ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ አገልግሎት ላይ የዋለው የቆየው "Mercator" ካርታ ግን ከምድር ወገብ ርቀው የሚገኙ አካባቢዎችን አግዝፎ በማሳየት አፍሪካን ከግሪንላንድ ጋር እኩል ያህል አነስተኛ አድርጎ ያቀርብ ነበር። በገሃዱ ዓለም ግን አፍሪካ ከግሪንላንድ በ14 እጥፍ ትበልጣለች።
ይህ ውሳኔ ህጋዊ አስገዳጅነት ባይኖረውም በትምህርት ቤቶች፣ በሚዲያዎችና በዓለም አቀፍ ተቋማት አዲሱ ካርታ ጥቅም ላይ እንዲውል ያበረታታል።
የቶጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮበርት ዱሴ "ፍትሃዊ ዓለም የሚጀምረው ከፍትሃዊ ካርታ ነው" ሲሉ የውሳኔውን አስፈላጊነት ገልጸዋል። የአፍሪካ ህብረት በበኩሉ ውሳኔውን "ታሪካዊ እርምጃ" ሲል የተቀበለው ሲሆን፣ የውሳኔ ሀሳቡን ብቸኛ ተቃዋሚ የሆነችው አሜሪካ ግን ውሳኔው የፖለቲካ አጀንዳ ያዘለና ድርጅቱን ከዋና ዋና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች የሚያሳይስ ነው ስትል ኮንናዋለች።
05/09/2026
በኢትዮጵያ በኩል ባለው የዳልኦል አካባቢ ከኤርትራ ግዛት የተቃጣ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጠ።
በአብርሃም ኦስማን መሪነት ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱት ኡጉጉሞ የተባለኡ ታጣቂዎች ጥቃቱን ማካሄዳቸው የተገለፀ ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ በአፋር ዳሎል አካባቢ የሰው ህይወት እና የንብረት ጉዳቶች መከሰታቸው ተዘግቧል።
#አፋር
05/09/2026
የህወሓት የድሮን ስልጠና የወሰዱ ከ15 በላይ ሰዎችን ወደ ራያ አላማጣ እና ቅልሻ አካባቢዎች ማሰማራቱን የሚገልጹ መረጃዎች ተሰራጨ።
ከተሰማሩት ሰዎች መካከል የተወሰኑት "አረብኛ የሚናገሩ ነጮች" እንደሆኑ እና በቦታው መታየታቸው ግንባር ላይ ባሉ ምንጮች ተረጋግጧል።
በሌላ በኩል የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ በህወሓት እና በፌደራል መንግስቱ መካከል ያለውን ውጥረት ለማቃለል እና ወደ ውይይት ለማምጣት አሁንም የማካበብ እና የማሸማገል ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።
05/09/2026
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የኢትዮጵያን ገዥ ፓርቲ “ምንም ዓይነት እውነተኛ ጥንካሬ፣ የህዝብ መሰረት ወይም የፖለቲካ ጥልቀት የሌለው” ሲሉ ገለፁ።
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲ የሆነውን ብልጽግናን "ፖተምኪን ፓርቲ" ሲሉ በመጥራት፣ የፓርቲው ልሳኖች እና ከፍተኛ የፖለቲካ እንዲሁም የወታደራዊ አመራሮች በኤርትራ ላይ የከረረ የሀሰት መረጃ እና የጥላቻ ዘመቻ ከፍተዋል ሲሉ አወገዙ። ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው (ኤክስ) ባሰፈሩት ጠንከር ያለ መልዕክት፣ የኢትዮጵያ አመራሮች በኤርትራ ላይ የሚያካሂዱትን የስም ማጥፋት ዘመቻ መጠን በማሳደግ እንደተበላሸ የሸክላ ማጫወቻ አንድ ዓይነት ድምጽ ደጋግመው እያሰሙ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
እንደ አቶ የማነ ማብራሪያ ከኢትዮጵያ በኩል የሚሰነዘረው ዘመቻ በዋናነት በሦስት ተደጋጋሚ ጭብጦች ላይ ያተኮረ ነው። የመጀመሪያው የኤርትራን ሉዓላዊ የመንግስትነት ታሪክ ጥላሸት የሚቀባ የታሪክ ክለሳ ማድረግ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ገዥው ፓርቲ በገዛ እጁ ለፈጠራቸው ውስብስብ ሀገራዊ ቀውሶች ኤርትራን በሐሰት ተጠያቂ የማድረግ ሙከራ ነው። ሦስተኛው የዘመቻው ዓላማ ደግሞ ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ እና በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና የምትከተለውን መደበኛ የቀጠናዊ ትብብር ፖሊሲ ሙሉ በሙሉ ማጣመም እንደሆነ አስምረውበታል።
ሚኒስትሩ አክለውም እነዚህ አሳሳች የፖለቲካ ሴራዎች ዋነኛ ግባቸው የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ባህር የሚያስገባ ሉዓላዊ የባለቤትነት መብት ለማግኘት እና በቀይ ባህር ላይ ስትራቴጂካዊ ጥልቀት ያለው የባህር ላይ ኃይል ለመገንባት በሚል ላለፉት ሦስት ዓመታት ሲያሰላስለው የቆየውን አደገኛ የጦርነት አጀንዳ ትክክለኛ አስመስሎ ለማቅረብ እንደሆነ ተናግረዋል። ይህ የኢትዮጵያ ፍላጎት ደግሞ ዓለም አቀፍ ህጎችን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተርን እና የአፍሪካ ህብረትን መመስረቻ ህግን በግልጽ የሚጥስ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የገዥው ፓርቲ መግለጫ የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦችንም ሆነ ሰፊውን የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ሊያታልል አይችልም ያሉት ሚኒስትሩ፣ ለዚህ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ የአስመራ ምላሽ ፋይዳ ቢስ እና ምንም ውጤት የማያመጣ ወሬ መሆኑን የሚገልጽ "ዘረባ ኣደይ ለቱ፡ ኣየውፍር ኣየእቱ!" የሚል የትግርኛ አባባል በመጠቀም መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።
05/09/2026
የሃይማኖት አባቶች፣ አቅመ ደካሞች፣ ሕጻናት እና ነፍሰጡር እናቶች ያለርህራሄ መገደላቸው ተገልጿል
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ ሰሞኑን በተከሰቱ ግጭቶችና በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሲቪሎች መገደላቸውን፣ ንብረቶች መውደማቸውን እና በርካቶች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የተጎጂ ቤተሰቦች ገለጹ።
ይህን ጥቃት ተከትሎ የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች፣ የገዳ ኮማንዶ እና የአካባቢው ሚሊሻዎች ወሰዱት በተባለ "ደግሞ በርካታ ንጹሐን ዜጎች መገደላቸው ተገልጿል። ከተገደሉት መካከል የሃይማኖት አባቶች፣ አቅመ ደካሞች፣ ሕጻናት እና ነፍሰጡር እናቶች ይገኙበታል።
በተለይም በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ሲያገለግሉ የነበሩት ቆሞስ አቡሀይ ታደሰ ከአገልግሎት ቦታቸው ተወስደው ከተገደሉ በኋላ አስከሬናቸው ከቀናት በኋላ በጫካ ውስጥ ተገኝቶ መ የተቀበረ ሲሆን፣ በሚካኤል ቤተክርስቲያን ተጠልለው የነበሩ ከ20 በላይ ሰዎችም የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል።
ጥቃቱ በተፈጸመባቸው በአንዶዴ ዲቾ፣ ቱሉ ሌንጫ እና ሌሎች መንደሮች በርካታ መኖሪያ ቤቶች፣ መጋዘኖች እና የንግድ ተቋማት በእሳት የወደሙ ሲሆን ንብረቶችም ተዘርፈዋል። በአሁኑ ወቅት በርካታ ነዋሪዎች ወደ ጫካ እና ቤተክርስቲያናት ተሸሽገው ያለ ምንም የምግብና የመድኃኒት አቅርቦት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል።
በጥቃቶቹ እና በቀጣይ ስጋቶች ላይ ከክልሉ ባለሥልጣናት አስተያየት ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ቢደረግም እስካሁን ምላሽ አልተገኘም።
03/09/2026
ኢሕአፓ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤውን ውጤት አልቀበልም አለ
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) በቅርቡ የተጠናቀቀውን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በገዢው ብልጽግና ፓርቲ ዘዋሪነት የተከናወነ፣ ነጻና ገለልተኛ ያልሆነ በመሆኑ ምንም ዓይነት እውቅና እንደማይሰጠውና ተቀባይነትም እንደሌለው ባወጣው ወቅታዊ መግለጫ አስታወቀ።
ፓርቲው ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ ሂደቱ ገዢው ፓርቲ ሥልጣኑን ለማራዘም የተጠቀመበትና ወገንተኝነት ያበዛበት ነው ሲል ኮንኗል። ሀገሪቱ በጦርነት፣ በዜጎች መፈናቀል፣ በማንነት ተኮር እስራትና በከፍተኛ የኢኮኖሚ ውድቀት ውስጥ በምትገኝበት ወቅት የተካሄደው ይህ ምክክር፣ የፖለቲካ ችግሮችን ዘላቂ በሆነ መንገድ ከመፍታት ይልቅ ገዢውን ኃይል ለማጠናከር ያለመ ነው ብሏል።
በተጨማሪም እንደ ሕገ መንግሥት፣ የአዲስ አበባ ባለቤትነት፣ የክልሎች አከላለልና ወሰን ያሉ በልሂቃኑ መካከል ገና እልባት ያላገኙ አጀንዳዎች በበቂ ውይይት ሳይደረግባቸው የቀረቡበት መንገድ የከፋ መከፋፈልን የሚፈጥር ነው ሲል ፓርቲው ወቅሷል። በሸገር ከተማና በኮሪደር ልማት ስም የተካሄዱ የሕዝብ መፈናቀሎችን፣ ከባድ የመዋጮ ጫናዎችን፣ በድሬዳዋ የሚታየውን በብሔር ምደባ ላይ የተመሠረተ አሰራርን እንዲሁም በፖለቲካ ታማኝነት ላይ ያተኮሩ አድሏዊ አሰራሮችን መግለጫው በዝርዝር ኮንኗል።
ኢሕአፓ በሁሉም ባለድርሻ አካላት ዘንድ ተቀባይነት ያለው፣ አካታችና ከወገንተኝነት የጸዳ እውነተኛ ሀገራዊ የምክክርና ብሔራዊ እርቅ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርቧል። በሌላ በኩል የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቀደም ሲል በሰጣቸው መግለጫዎች ሂደቱ ገለልተኛ፣ አካታችና ሁሉንም ያሳተፈ እንደነበር በተደጋጋሚ መግለጹ ይታወሳል።
03/09/2026
ግብፅ ተጨማሪ 24 የራፋል ተዋጊ ጄቶችን ከፈረንሳይ ለመግዛት ፍላጎት ማሳየቷ ተገለጸ
ግብፅ በፈረንሳይ የተሠሩ የራፋል (Rafale) ተዋጊ ጄቶች ስብስብን ለማስፋፋት በሚል ተጨማሪ 24 ጄቶችን ለመግዛት የሚያስችላትን የቴክኒክ ጥያቄ «ዳሶ አቪዬሽን» ለተሰኘው አምራች ኩባንያ ማቅረቧን የፈረንሳዩ «ላ ትሪቡን» ጋዜጣ ዘገበ።
በወጣው ዘገባ መሠረት ጥያቄው አምራቹ ኩባንያ ለግዥው የሚያስፈልጉ የቴክኒክ እና የንግድ ፕሮፖዛሎችን እንዲያቀርብ የሚጠይቅ ሲሆን፣ እስካሁን በሁለቱ ወገኖች መካከል የተፈረመ የውል ስምምነት ወይም የጸደቀ ትዕዛዝ አለመኖሩ ተመልክቷል። አምራች ኩባንያው ዳሶ አቪዬሽን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።
ግብፅ እ.ኤ.አ. በ2015 የመጀመሪያዎቹን 24፣ በመቀጠልም በ2021 ተጨማሪ 31 ጄቶችን በመግዛቷ በአሁኑ ወቅት 54 የራፋል ተዋጊ ጄቶች በትዕዛዝ እና በስራ ላይ ይገኛሉ። ይህ አዲስ ጥያቄ ወደ ውል ከተቀየረ የሀገሪቱ የራፋል ጄቶች ቁጥር ወደ 78 ከፍ የሚል ሲሆን፣ ይህም ግብፅን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የራፋል ጄቶች ከሚጠቀሙ ሀገራት ተርታ የሚያሰልፋት ይሆናል።
ይህ የካይሮ አዲስ ግዥ እንቅስቃሴ የታየው ሀገሪቱ ካጋጠማት የፋይናንስ እጥረት ጋር ተያይዞ በወታደራዊ ግዥዎቿ ላይ እገዳ አድርጋ ከቆየችበት ጊዜ በኋላ መሆኑ ተጠቅሷል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Address
Addis Ababa
20304