11/01/2026
እንኳን ደስ አለን
በህዝ ተሳትፏ የተገነባው የሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲዮም የሰው ሰራሽ ሳር ንጣፍ የፊፋን ዓለም አቀፍ የጥራት እውቅና ሰርተፍኬት ተበረከተለት
በሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲዮም የተነጠፈው የሰው ሰራሽ ሳር (Artificial Turf) ከዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ከፍተኛ የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት አገኘ።
09/01/2026
የናቶሊ መድኃኒት ሾፕ የሀላባን ሴራ በዓልን በድምቀት አከበረ
ጥር 1/2018 (ሀላባ ቁሊቶ) በሀላባ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠውና የሰላም፣ የፍቅር እንዲሁም የአብሮነት መገለጫ የሆነው የ**“ሴራ”** በዓል በኖቶሊ መድኃኒት መደብር (Notoli Pharmacy) በተቋም ደረጃ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።
የተቋሙን ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ራህማን ጨምሮ ሰራተኞች የብሄሩን ባህላዊ አልባሳት በመልበስና ባህላዊ እሴቶችን በማንፀባረቅ በዓሉን ልዩ አድርገውታል። በዕለቱም የሀላባን ታሪክና የሴራን ስርአት የሚያወድሱ ዝግጅቶች ቀርበዋል።
የማህበረሰብ ትስስር ተቋሙ ከንግድ ስራው ባሻገር ለማህበረሰቡ ባህልና እሴት ያለውን አክብሮት ያሳየበት መድረክ ነው ተብሏል።
ይህ አከባበር ኖቶሊ መድኃኒት መደብር ከህዝቡ ጋር ያለውን ጥብቅ ቁርኝት የሚያሳይ ሲሆን፣ በቀጣይም መሰል ማህበራዊና ባህላዊ ኩነቶችን ለማበረታታት ቃል ተገብቷል።
በካሊድ ሀጂ ሙዘይን
የሀላባ ቲቪን ወቅታዊ፣አካባቢያዊ መረጃዎችን ለማግኘት:-
በድህረገጽችን:- https://www.halabatv.com
06/01/2026
🌀ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የደስታ እንዲሁም በሁሉም ነገር የተሟላ እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን!!
ሀላባ ሸገር ስፖርት ክለብ💙
06/01/2026
በ13ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሀ-ግብር ሀላባ ሸገር ስልጤ ወራቤን 3 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።
የሙሉ ሰዓት ውጤት
ሀላባ ሸገር 3 - 0 ስልጤ ወራቤ
06/01/2026
የቀድሞ የክለባችን ኮከብ ወሰን ጌታቸው ተሞሽሯል!
ወንድማችን ወሰን እና ባለቤቱ መልካም የትዳር ህይወት እንዲሁንላችሁ ከልብ እንመኛለን!!💙💝💙
ሀላባ ሸገር ስፖርት ክለብ💙
01/01/2026
ለወንድማችን ከይረዲን በሀሩ እና ለእህታችን ነኢማ ጃቢር መልካም የትዳር ህይወት ይሁንላችሁ!!💙💝💙
ሀላባ ሸገር ስፖርት ክለብ💙
30/12/2025
ዛሬ ረፋድ በተደረገው የኢትዮ ሊግ አንድ 13ኛ ሳምንት ጨዋታ ሀላባ ሸገር በይርጋጨፌ ቡና 2-0 በሆነ ውጤት ተረቷል፡፡
29/12/2025
ሀላባ ሽገር 🆚 ይርጋጨፌ ቡና
የኢትዮ ሊግ አንድ 14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በነገው እለት የሚካሄድ ሲሆን በፌዴሬሽኑ መረሐ ግብር መሰረትም ነገ ማክሰኞ ረፋድ 5፡00 ላይ ክለባችን ሀላባ ሸገር ከ ይርጋጨፌ ቡና ጋር ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
ድል ለውዱ ክለባችን ሀላባ ሸገር / ቆሜዎቹ💙
28/12/2025
መሀመድ አበራ የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ11ኛ ሳምንት የሶከር ኢትዮጵያ ኮከብ ተጫዋች በመሆን ተመርጧል! ጀግናው እንኳን ደስ አለህ!! በርታልን!!💙👏
25/12/2025
ሀላባ ሸገር / ቆሜዎቹ 🆚 ልደታ ክፍለ ከተማ
===========================
🌀የኢትዮጵያ ሊግ አንድ (ምድብ ሀ) 13ኛ ሳምንት መረሀ ግብር ነገ አርብ ከቀኑ 7፡00 ላይ ክለባችን ሀላባ ሸገር ከ ልደታ ክፍለ ከተማ ጋር በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም የሳምንቱን ምርጥ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡
ድል ለውዱ ክለባችን ሀላባ ሸገር / ቆሜዎቹ💙
23/12/2025
በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ 12ኛ ሳምንት ጨዋታ ሀላባ ሸገር ከ ኮንሶ ኒውዮርክ ጋር 1 - 1 በሆነ የአቻ ውጤት ነጥብ ተጋርተዋል፡፡