24/05/2025
"ጃዋር መሃመድ እና የቤተ መንግስት ሽያጭ"
መቼስ የጃዋር መሃመድ ቀልድና የጥፋት ሱስ ማለቂያ የለውም፤ "አዲሱ ቤተመንግስት ተሸጦ ለሀኪሞች ደሞዝና ጥቅማጥቅም ይከፈል" ማለቱ ቀልድ እንደማያልቅበት ያሳያል፤ በየማህበራዊ ሚዲያው "ሀኪሞች ታሰሩ፣ ስራ አቆሙ፣ አደሙ፣ ተሳደዱ፣ ተራቡ፣ ተቸገሩ . . .በሽተኞች ተጉላሉ፣ ህክምና አጡ፣ ሞቱ . . . " የሚለው ደግሞ የጥፋት ሱስ እንዳለበት አመላካች ነው። ሲደማመር የለመደው አመጽ፣ መገዳደል፣ ማቃጠል፣ ማፈናቀል . . . .የማስቀጠል አባዜ እንደተጠናወተው አረጋጋጭ ነው።
ለመሆኑ 'እሺ ይሸጥ' እንኳ ቢባል ቤተ መንግስት ዶሮ ነው እንዴ? የጓሮ አትክልት ነው?🤔 ብድግ ተደርጎ በአቅራቢያ በሚገኝ ገበያ የሚሸጥ ነው❓
ወይስ እንደቆራሌው በየአደባባዩ ወጥተን
"አዲስ ቤተ መንግስት የሚገዛ!
አለ አዲስ ቤተ መንግስት!
ሽያጭ - ሽያጭ! አለ የቤተመንግስት ሽያጭ!
አዲስ ያልተኖረበት . . . ❗"እንበል❓
" ሽያጭ❗ ያልተኖረበት❗
ንጉሥ ያልተቀመጠበት❗
ከከተማ ወጣ ያለ፣ ንጹህ አየር ያለበት❗
መሰረተ ልማት የተሟላለት ቤት መንግስት አለ❗ . . . " እያልን እንዙር❓
ይሸጥ ቢባል እንኳን ከሰነድ ማዘጋጀት እስከ ገዢ ማግኘት ምን ያህል ጊዜ ሊወስድ ይችላል❓
ታዲያ ከመንግስት ጋር ለመወያየትና ለመደራደር እንኳን ፍቃደኛ ላልሆኑ #በጃዋሪያን የአመፅ ፖለቲካ ለተጠለፉ ጥቂት አድመኛ ሀኪሞች እንዴት መፍትሄ ሊሆን ይችላል❓ ወይስ መንግስት ቤተ መንግስት ለመሸጥ ከተስማማ ወደ ሥራ ይመለሳሉ❓
ድንቄም የፖለቲካ ሳይንቲስት🤔😬
ነገሩ፣ ቤተ መንግስት መሸጥ ቀላል እንዳልሆነ ሁሉ፣ የሀኪሞችን ደሞዝ መክፈልም ቀላል አይደለም።
መፍትሄው ቀላል ነው። ሀኪሞች “ሱሪ በአንገት ነው፣ ዛሬ ካልተከፈለን ነገ አንኖርም! ህመምተኞች ከሞቱም ድፍት ይበሉ . . .” ከመሳሰሉ ኢሰብአዊ አስተሳሰብ ይላቀቁ። እነ ጃዋር ከበከሏቸው የፖለቲካ ቫይረስ ይላቀቁ፤ ወደስራም ይመለሱ። ከሁሉም ክልሎች ወኪሎቻቸውን ይላኩ። (ከዚህ በፊትም ተወካይ ላኩ ተብሎ እንደነበር መረጃ አለኝ)
ከመንግስት ጋር ሻይ ቡና እየጠጡ ጥያቄዎቻቸውን ያቅርቡ፣ ይወያዩ፣ ይመካከሩ፣ በጋራ መፍትሄ ያፍልቁ። ቤተ እምነትም ቤተ መንግስትም ሳይሸጥ የሚገባቸውን ያግኙ። (ባይሆን መንግስት በተስማሙት መሰረት መክፈል ካልቻለ ስለሽያጩ ማንሳት ይቻላል)😁
እውነት ለመናገር ቤተ መንግስት እየታነፀ ለመሆኑ አገርም አለምም ያውቃል። ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ፣ የሀገር ምልክት የሚሆን፣ የታሪክ ሀብትን የሚያጎለበት፣ የኢትዮጵያ ልዕልናን የሚገልጽ . . . ታላቅ ቤተ መንግስት እየተገነባ ለመሆኑ ህዝብም ያውቃል። በመሆኑም ማንም ብድግ ብሎ እንደጓሮ አትክልት፣ እንደ ቤት እንስሳት፣ እንደ ሱቅ ሸቀጣ ሸቀጥ . . . የሚሸጠው አይደለም። ወይም እንደ የግል ጌጣጌጥ ሲቸግር ለግብይት የሚያቀርበው አይደለም። በእውነቱ የዚህ አስተሳሰብ ተጠቂ የሆነ ሰው ነገ ሥልጣን ሲያገኝ ኢኮኖሚያዊ ችግር ቢገጥመው የአገር ደህንነትና ዘላቂ ጥቅም ቁልፍ የሆኑ ተቋማት እና መሬትን ሸጦ ሲጨርስ አገርም ከነህዝቡ ከመሸጥ አይመለስም። ይህ ጃዋር ያረጋገጠልን ሊያደርገው የሚችል እውነት ነው።
በመሰረቱ የፖለቲካ ሳይንስ በነጭ ተምሬያለሁ ከሚል ቆዳ አምላኪ የሚጠበቀው የቤተ መንግስት ሽያጭ ሀሳብ አልነበረም። የጤና ሥርዓቱ የሚሻሻልበት፣ የጤና ባለሙያዎች በድካማቸው ልክ ክፍያ የሚያገኙበት፣ በጀት ድልድል ለጤናው ዘርፍ ትኩረት የሚሰጥበት . . . የፖሊሲ ሀሳብ ማፍለቅ ነበር የሚጠበቅበት።
20/06/2022