30/08/2026
የኮርደር ልማቱ የከተማዋን ውበት በመግለጥ ለነባር ቤቶች አዲስ ዕድል መፍጠሩ ተገለጸ
በአርባምንጭ ከተማ ጋሞ አደባባይ ፊት ለፊት የሚገኘው ሆር ባርና ሬስቶንት በይፋ ተመርቋል።
በምረቃ ኘሮግራሙ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአርባምንጭ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ገዳሙ ሻንበል እንደተናገሩት ሆር ባርና ሬስቶራንት በከተማው ኮርደር ልማት ስታንዳርድ መሠረት በተሰጠው ድዛይን በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታውን እውን ማድረጉን ገልጸው የኮርደር ልማቱ የከተማዋን ውበት በመግለጥ ለነባር ቤቶች አዲስ ዕድል መፍጠሩን ተናግረዋል።
አቶ ገዳሙ አክለው እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት በአርባምንጭ ከተማ አዳዲስ የመስተንዶ ተቋማት መከፈት ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰት እንዲኖር አስተዋጽኦ ማድረጉን አውስተው ነባርም ሆነ በአዲስ መልክ እየተገነቡ ያሉ ሆቴሎችና ሬስቶራንቶች ወደ ከተማው የሚመጡ እንግዶችን የሚመጥን ደረጃው የጠበቀ አገልግልት መስጠት አንዳለባቸው አሳስበዋል።
የሆር ባርና ሬስቶራንት ባለቤት አቶ አሳምነው ኡርጌሳ በንግግራቸው እንደገለጹት ሬስቶራንቱን በኮሪደር ልማቱ ስታንደርድ መሰረት በልዩ ምህንድስና እና በዘመናዊ ዲዛይን በአዲስ መልክ ገንብተው ለምረቃ ማብቃተቸው አሰንዳስደሰታቸው ገልጸው በዚህ አዲስ ምዕራፍም የቀድሞ አገልግሎታቸውን ይበልጥ በማጠናከር የተሻለ አገልግሎት ይዘው እንደሚቀርቡ ቃል ገብተዋል።
ሆር ባር እና ሬስቶራንት ከ 2001 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 18 ዓመታት የሰላም ተምሳሌትና የቱሪዝም ማዕከል በሆነችው አርባምንጭ ከተማ እንብርት በጋሞ አደባባይ ፊትለፊት ጥራት እና ደረጃውን የጠበቀ የመስተንግዶ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱ የሚታወቅ ነው።
ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም አርባምንጭ