Ethio Football 90+

Ethio Football 90+

Share

ይህ ስለ ስፖርት ዜናዎች ፱፲+ የምተነትንበት ገፅ ነው!

Photos from Ethio Football 90+'s post 18/09/2023

አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ የ5ሺ ሜትር የአለም ክብረወሰንን ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ መልሳለች😍😍🇪🇹🇪🇹

ዛሬ በአሜሪካን ኢዩጂን ዳይመንድ ሊግ የ5 ሺ ሜትር ፉክክሯን 14:00:21 በመግባት ነው የርቀቱን ክብረወሰን ከኬንያዊቷ ፌዝ ኪፕዬገን የተረከበችው።👏👏

እንኳን ደስ አለንንን ❤️❤️ ጉዳፍ 👏👏

30/06/2022


✅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዲስ አበባ ከተማ ጋር ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ በዲኤስቲቪ ይተላለፋል
✅ ድሬደዋ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ ጋር ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ በአማራ ሚድያ ኮርፖሬሽን ቀጥታ ስርጭት ይኖረዋል
✅ አርብ በተመሳሳይ 04:00 ሃዋሳ ከተማ ከ አዳማ ከተማ ጋር አፄ ቴዎድሮስ ስታዲየም ላይ ያደርጋሉ።
✅ የዋንጫ መርሃ ግብሩ በዕለቱ አርብ ሰኔ 24/2014 ዓ.ም በባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም በሚዘጋጅ መድረክ የሚካሄድ ይሆናል ሲል ሊግ ካምፓኒው አረጋግጧል

✅ ሌሎች የ30ኛ ሳምንት የመጨረሻ የሊጉ ጨዋታዎች

✅ ሐሙስ ሰኔ 23 2014
04:00 ወላይታ ድቻ - ወልቂጤ ከተማ - ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም
10:00 ሰበታ ከተማ - አርባምንጭ ከተማ - ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም

✅ ቅዳሜ ሰኔ 25 2014
04:00 ጅማ አባ ጅፋር - መከላከያ - ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም
07:00 ሲዳማ ቡና - ሀዲያ ሆሳዕና - ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም
10:00 ኢትዮጵያ ቡና - ባህርዳር ከተማ - ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም

Ethio Football 90+

30/06/2022


✅ ከሳምንት በፊት ከደርቢ ካውንቲ አሰልጣኝነቱ የለቀቀው የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ እና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ኮከብ ዋይኒ ሮኒ በእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር (FA) ምርመራ ተከፍቶበታል
✅ ምክንያቱ ደግሞ ለደርቢ ካውንቲ ተጫዋቾች እና ሰራተኞችን የግንቦት ወር ደሞዝ በድብቅ በግሉ ወደ €1.8 ሚልየን ከፍሏል በሚል ነው
✅ መደበኛ ባልሆነ ምክንያት በተገኘ ፋይናንስ ይህን ማድረጉ ከተረጋገጠ ቅጣት ይጠብቀዋል ሲል The Telegraph ዘግቧል።

👉 ለተጨማሪ መረጃዎች ገፃችንን ይከተሉ

15/06/2022

ምጥን_መረጃዎች
ኮስታሪካ ለአለም ዋንጫ ያለፈች የመጨረሻ ሀገር ሆናለች
እንግሊዝ በሜዳዋ በሃንጋሪ 4ለ0 ተሸንፋለች
ጀርመንም ጣልያንን 5ለ2 ማሸነፍ ችላለች
ጀርገን ክሌፕ ስለ ዳርዊን ኑኔዝ ምን አሉ?
ፖል ፖግባ የቀድሞ ክለቡ ጁቬንቱስን ተቀላቅሏል
ኒማኒያ ማቲች ሮማን በነፃ ዝውውር ተቀላቅሏል
ፓውሎ ዲባላ ለኢንተር ለመጫወት ተስማምቷል
ታሚ አብራሃምን ማንችስተር ዩናይትዶች ተመኝተውታል
ቶተንሃም እና አርሰናልም የራፊንሃ ፈላጊዎች ሆነዋል
ማንችስተር ዩናይትድ ኤሪክሰንን በነፃ ዝውውር ለማግኘት
እየጣረ ነው
ቬሴንት ካምፓኒ የበርንሌይ አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል
" ዳርዊን ድንቅ ተጫዋች ነው: ቀድሞውኑ ምርጥ ቢሆንም ግን
የበለጠ የተሻለ ለመሆን ብዙ እምቅ ችሎታ አለው።
የምንፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ አሉት። ከመሀል ወደ ጎን እየተለጠጠ
ተጋጣሚን ሊያሸብር ይችላል ፣ በእንቅስቃሴው አስቸጋሪ እና
ተለዋዋጭ ነው ፣ ያለ ፍርሃትም ይጫወታል ፣ እሱ ኃይለኛ ነው።
ደጋፊዎቻችንን እንደሚያስደስትም አውቃለሁ "
ጀርገን ክሎፕ ስለ ዳርዊን ኑኔዝ የተናገሩት
_______________________________________________
እንግሊዝ በታሪኳ በሜዳዋ ጎል ሳስቆጥር አራት ሆል
ተቆጥሮባት ተሸንፋ አታውቅም ነበር ትላንት ምሽት ግን ሃንጋሪ
ይህን ታላቅ ድል ዌምብሌ ላይ አሳክታለች። እንግሊዝ በኔሽንስ
ሊጉ 4 ጨዋታ አድርጋ ያለ ምንም ድል ከምድቧ መጨረሻ ደረጃ
ላይ ተቀምጣለች
_______________________________________________
" ማንቸስተር ዩናይትድ ዳርዊን ኑኔዝን በቨርፑል ከተነጠቀ
በኀላ ፊቱን ወደ ታሚ አብርሀም ሊያዞር አቅዷል " DAILY STAR
_______________________________________________
ኬፓ አሪዛባላጋ በክረምቱ ከስታምፎርድ ብሪጅ የሚወጣ
ከሆነ ቼልሲዎች የላዚዮውን ግብ ጠባቂው ቶማስ ስትራኮሻን በነፃ
ዝውውር ለማግ እያሰቡ ነው የሚል ዘገባዎች ወጥተዋል
_______________________________________________
ፖግባ እና ማቲችን በነፃ ዝውውር ያጡት ማንችስተር
ዩናይትዶች በኤሪክ ቴን ሃግ ስር ፍሬንኪ ዴ ጆንግ እና ክርስቲያን
ኤሪክሰንን ለማስፈረም እየጣሩ ይገኛል። DAILY MAIL

13/06/2022

# ሃላንድ
✍️በይፋ የማንችስተር ሲቲ ተጫዋች ሆኗል
👉አባቱ የለበሰውን ማልያ እሱም አጥልቆታል
👉በሳምንት €375,000 ይከፈለዋል

13/06/2022

# ሃሪ_ማጓየር_ሊቀየር_ይችላል
⭐አዲሱ የማንችስተር ዩናይትድ አለቃ ቴን ሃግ ቡድኑን
በአምበልነት የሚመራ ተጫዋች ሊቀይሩ ይችላሉ። ሶስት
ተጫዋቾችም በዕጩነት ቀርበዋል
👉ዴቪድ ዴጊያ
👉ቡሩኖ ፈርናንዴዝ
👉ክርስቲያኖ ሮናልዶ
✍️ለእናንተ ለማንችስተር ዩናይትድ መሪነት ማን ይመጥናል?

13/06/2022

⭐ትላንት ምሽት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና አቡኪ በሰይፉ
ሾው
የማላዊ ህዝብ ለሰጧቸው ድጋፍ አመስግነዋል
አቡኪ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችን ይቅርታ ጠይቋል
ውበቱ አባተ ስለ ጌታነህ ማብራሪያ ሰጥቷል
" ጋርዲዮላ ይመቸኛል "
" በፊት የማን ዩናይትድ ደጋፊ ነበርኩ ነፍስ ሳውቅ ተውኩት "
" ከግብፅ የተሻለ ሊግ ሄጄ መጫወት ነው ምፈልገው "
" አይደለም ለጌታናህ ለሁሉም ተጫዋች በሩ ክፍት ነው "
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ
" ጋርዲዮላ ይመቸኛል "
" የአውበከር ግልፅ ፔናሊቲ ነበር ነገር ግን ያው ትልቅ ሃገራት
በብዙ መንገድ ወደ ፊት እንዲመጡ ስለሚፈለግ ይደገፋሉ እነሱ
ላይ ቢሆን ዳኛው ደስ እያለው ይሰጣቸው ነበር "
" ልጆቼ አሁን ደረታችንን ገልብጠን ወደ ትምህርት ቤት እንሄዳለን
እንዳሉ ባለቤቴ ነግራኛለች "
" በፊት የማንችስተር ዩናይትድ አድናቂ ነበርኩ። ነፍስ ሳውቅ ግን
ተውኩ.... ምክንያቱም የምትደግፈው ቡድን ቢሳሳትም ቢያጠፋም
ትክክል ነው ብለህ የምታስብበት ጭልም ያለ ነገር ስለሆነ
አሰልጣኝ ነኝ ብዬ ማሰብ ስጀምር ግን እንደ ባለሙያ ስለ
ማያስኬድ ተውኩት "
" በጌታነህ ኬዝ ብዙ ግፊት ነበር ማድረግ ያለብኝን Maximum
ደረጃ ድረስ ሄጃለው... ካፕቴኔ ነው የብሔራዊ ቡድኑ አምበል
ነው ፣ ወደ ናሽናል ቲም ድጋሚ ያመጣሁትም እኔ ነኝ ፣ በክለብ
ተቀጥቶ እቤት ተቀምጦ ጠርቼ አጫውቼዋለው ፣ እሱም መጥቶ
ለናሽናል ቲሙ ብዙ ነገር አድርጎልናል ግን ከዛ በኋላ የተፈጠረውን
ነገር አላውቅም ...በተደጋጋሚ ግዜ ላገኘው ሞክሬ አልቻልኩም
..መጫወት አለመፈለጉን ግን በሚዲያ ወይንም ደግሞ ትኩረት
እንደማይሰጥ ለግዜው ክለብ ላይ እንደሆነ ፍላጎቱ ሰምቻለው
ደጋግሜ ላናግረውም ሞክሬያለው ግን ስልኬን ሊያነሳ ፍቃደኛ
አይደለም ... ባህርዳር ድረስ ሄጄ ላገኘው ሞከርኩ ደወልኩ ግን
ፍቃደኛ አይደለም
ሰይፉም በመጨረሻ ይህን ጠየቀው አሁንስ ተስፋ አለው?
" በማንኛውም ግዜ እንኳን ጌታነህን የሚያክል ትልቅ ተጫዋች
አይደለም ለሁሉም ተጫዋቾች መድረኩ ክፍት ነው ። ናሽናል
ቲም ከውስጥ በሩን ገፍተህ የምትዘጋበት አይደለም "
አቡኪስ ምን አለ?
ሰይፉ :- ግብፃች ጥሪ ቢያደርጉ ዛማሊክ መጥተህ ለኛ ተጫወት
ቢሉህ ጥሩ ከከፈሉህ ግብፅ ሔደህ የመጫወት ፍላጎቱ ይኖርሃል?
" ያው አሁን ቀጣይ አመት አላህ አሳክቶልኝ ሰንዳውስ ለመጫወት
ፈርሜያለው አሁን የሰንዳውስ ንብረት ነኝ ብዬ ነው ማስበው። ግን
ለሌላ ግዜ የተሻለ ነገር ለማድረግ ከግብፅ የተሻለ ሊግ ላይ ሄጄ
ለመጫወት ነው የምፈልገው "
" ማላዊዎች ልክ የኛ ደጋፊዎች ነበር የሚመስሉት በዚህ አጋጣሚ
አመሰግናለው "
" በደርቢው ቀን ከምኞት ጋር ተጋጭቼ ተጎድቼም የጊዮርጊስ
ደጋፊዎች ሲጮሁብኝ የነበረው እኔ ላይ ነበር ፤ በዛ ሰዓት
የተመታሁት እኔ ስለነበርኩ በጣም ስሜታዊ ሆኜ ያልተገባ ባህሪ
አሳይቼ ነበረ እና የጊዮርጊስን ደጋፊዎች ይቅርታ ማለት
እፈልጋለው "

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Awassa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address

Awassa