Hawassa City S.C

Call Contact the business

Hawassa City S.C Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hawassa City S.C, Sports Team, hawassa, Awassa.

ከዛሬው ልምምድ የተወሰዱ ተጨማሪ ምስሎች...!
29/08/2026

ከዛሬው ልምምድ የተወሰዱ ተጨማሪ ምስሎች...!

ቅድመ ዝግጅቱ ተጠናክሮ ቀጥሏልቅድመ ዝግጅት ከጀመረ ሦስተኛ ቀኑን የያዘው ክለባችን ዛሬ ከሰዓት ከ9:00 ጀምሮ በሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ ልምምድ ሰርቷል።
29/08/2026

ቅድመ ዝግጅቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል

ቅድመ ዝግጅት ከጀመረ ሦስተኛ ቀኑን የያዘው ክለባችን ዛሬ ከሰዓት ከ9:00 ጀምሮ በሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ ልምምድ ሰርቷል።

ከልምምዱ የተገኙ ምስሎች...!
28/08/2026

ከልምምዱ የተገኙ ምስሎች...!

የዛሬው ልምምድ በምስል..!
28/08/2026

የዛሬው ልምምድ በምስል..!

ስለ ተጫዋቾች የጤና ምርመራ ከተለያዩ አካላት ለተነሱ ጥያቄዎች የተሰጠ ማብራሪያ​ዛሬ ጠዋት በተደረገው የተጫዋቾች የጤና ምርመራ ዙሪያ በደጋፊዎቻችን እና በተለያዩ አካላት ዘንድ የተወሰኑ ብዥ...
27/08/2026

ስለ ተጫዋቾች የጤና ምርመራ ከተለያዩ አካላት ለተነሱ ጥያቄዎች የተሰጠ ማብራሪያ

​ዛሬ ጠዋት በተደረገው የተጫዋቾች የጤና ምርመራ ዙሪያ በደጋፊዎቻችን እና በተለያዩ አካላት ዘንድ የተወሰኑ ብዥታዎች በመፈጠራቸው ይህንን በማጥራት መረጃ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።

በመሆኑም ​ተጫዋቾቻችን ከዚህ ቀደም በትልቅ ደረጃ አጠቃላይ እና ሙሉ የህክምና ምርመራ ማድረጋቸውን እያስታወስን ዛሬ በማለዳ በክለባችን የህክምና ባለሙያዎች የተካሄደው ምርመራ ቡድኑ ወደ ሜዳ ልምምድ ከመግባቱ በፊት የተጫዋቾችን የክብደት (ኪሎ)፣ የደም ሁኔታ እና ተያያዥ አካላዊ ዝግጁነቶችን ለመፈተሽ የተደረገ ቀለል ያለ መደበኛ ምርመራ ብቻ መሆኑን እንገልፃለን።

​የዛሬው አጭር ምርመራ የተደረገበት ዋና አላማም ማንኛውም ተጫዋች ወደ ልምምድ ከመግባቱ በፊት ለከባድ እንቅስቃሴ ብቁ የሚያደርገው ሙሉ ጤንነት ላይ መሆኑን ለማረጋገጥ እና ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ስጋቶችን አስቀድሞ ለመከላከል ታስቦ የተደረገ ነው።

​ስለሆነም ጉዳዩ ብዥታ የፈጠረባችሁ ውድ የክለባችን ደጋፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ይህንኑ ግንዛቤ ውስጥ እንድታስገቡ እያሳሰብን ቡድናችን መደበኛ የቅድመ-ዝግጅት ልምምዱን በይፋ መጀመሩን እናሳውቃለን።

ክለባችን ለ2019 ዓም ውድድር ዘመን ቅድመ ዝግጅት ዛሬ ረፋድ ላይ በይፋ ጀምሯል።
27/08/2026

ክለባችን ለ2019 ዓም ውድድር ዘመን ቅድመ ዝግጅት ዛሬ ረፋድ ላይ በይፋ ጀምሯል።

ክለባችን ለአዲሱ ውድድር ዘመን ቅድመ ዝግጅቱን ዛሬ ይጅምራል!!​የክለባችን ሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች ለ2019 የውድድር ዘመን የሚያደርጉትን ቅድመ-ዝግጅት በይፋ ዛሬ ይጀምራሉ።...
27/08/2026

ክለባችን ለአዲሱ ውድድር ዘመን ቅድመ ዝግጅቱን ዛሬ ይጅምራል!!

​የክለባችን ሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች ለ2019 የውድድር ዘመን የሚያደርጉትን ቅድመ-ዝግጅት በይፋ ዛሬ ይጀምራሉ።

​ትናንት ምሽት ወደ ሆቴል ገብተው ካምፕ የተቀላቀሉት ተጫዋቾቻችን ዛሬ በማለዳው አስፈላጊውን አጠቃላይ የጤና ምርመራ ያደረጉ ሲሆን ጤና ምርመራውን ያጠናቀቁ ተጫዋቾች ዛሬ ረፋድ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ የመጀመሪያ የሜዳ ላይ ልምምድ ማከናወን ይጀምራሉ።

​ለክለባችን ተጫዋቾች እንዲሁም ለአሰልጣኝ ቡድን አባላት በሙሉ መልካም የውድድር ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን።

እናመሰግናለን!​የሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከተጫዋቾቹ ሽመልስ በቀለ፣ በረከት ሳሙኤል እና ቢኒያም በቀለ ጋር የነበረውን አብሮነት ማጠናቀቁን ይገልጻል።​ተጫዋቾቹ በክለባችን ቆይታቸው ወቅ...
21/08/2026

እናመሰግናለን!

​የሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከተጫዋቾቹ ሽመልስ በቀለ፣ በረከት ሳሙኤል እና ቢኒያም በቀለ ጋር የነበረውን አብሮነት ማጠናቀቁን ይገልጻል።

​ተጫዋቾቹ በክለባችን ቆይታቸው ወቅት ያሳዩት ከፍተኛ ፍላጎት,ለክለቡ ማሊያ የነበራቸው ታማኝነት እና በየጨዋታው ያሳዩት ተጋድሎ የሚታወስ ሲሆን ላሳዩት መልካም ስነ-ምግባር እና ለክለባችን ውጤታማነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ክለባችን ትልቅ ምስጋና ያቀርባል።

​የሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አስተዳደር የመላው ስታፍ እና ደጋፊዎች ስም ለሶስቱም ተጫዋቾች ላደረጉት ሁሉ እያመሰገንን በቀጣይ የእግር ኳስ ዘመናቸው ስኬት እና መልካም ዕድል እንዲገጥማቸው ይመኛል።

​ስለ አገልግሎታችሁ እናመሰግናለን።

​ሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ

ክለባችን የሁለት ተጫዋቾችን ውል አድሷልቀደም ሲል የዳዊት ታደሰን እና የቸርነት አውሽን ውል ማራዘማችን የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾችን በክለባችን ለማቆየት ስምምነት ላ...
08/08/2026

ክለባችን የሁለት ተጫዋቾችን ውል አድሷል

ቀደም ሲል የዳዊት ታደሰን እና የቸርነት አውሽን ውል ማራዘማችን የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾችን በክለባችን ለማቆየት ስምምነት ላይ ደርሰናል።

የክለባችን የታዳጊ ቡድን ፍሬ የሆኑት ግብ ጠባቂው ደግም ተፈራ (ቻቺ) እንዲሁም ከታዳጊ ቡድን ካደገ በኋላ ከክለባችን ጋር ቆይታ እያደረገ የሚገኘው የመስመር ተከላካዩ ፊቃደስላሴ ደሳለኝ(ጫላ) ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ለክለባችን ግልጋሎት ለመስጠት ተስማምተዋል።

ለሁለቱም ተጫዋቾች ከክለባችን ጋር መልካም የውድድር ጊዜ እንመኛለን።

Address

Hawassa
Awassa

Telephone

+251911995888

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hawassa City S.C posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hawassa City S.C:

Shortcuts

Share

Category