05/04/2022
አርቴታ ይቅርታ ጠይቋል
የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ ቡድኑ ትላንት ምሽት ከሜዳው ውጭ ወደ ስልሀረስት ፓርክ አቅንቶ በፕሪሚየር ሊጉ በቀድሞ አማካዩ ፓትሪክ ቪዬራ በሚሰለጥነው ክሪስታል ፓላስ ሶስት ለዜሮ መሸነፉን ተከትሎ ደጋፊዎቹን ይቅርታ ጠይቋል።
ስብስብ ወቀሳ እና ትችቶችን ለመቀበልም ዝግጁ መሆን ያለበት ጊዜ ነው ሲል ተናግሯል።ሽንፈቱን ተከትሎ መድፈኞቹ አንድ ተስተካካይ የጨዋታ መርሀ ግብር እየቀራቸው ከከተማ ተቀናቃኛቸው ቶትንሀም ሆትስፐር በጎል ክፍያ አንሰው አምስተኛ ስፍራ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል።
አርሰናል ከፓላስ ጋር በሊጉ ካደረጋቸው የመጨረሻ ስምንት ጨዋታዎች መካከል በአንዱ ብቻ ድል ማድረግ የቻለ ሲሆን በአምስቱ ነጥብ ሲጥል በሁለቱ ሽንፈት ለማስተናገድ ተገዷል።
ንስሮቹ በበኩላቸው በሁሉም ውድድሮች ባደረጓቸው የመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎች ሰባት ጎሎችን ተጋጣሚያቸው መረብ ላይ ማሳረፍ የቻሉ ሲሆን ምንም ጎል ሳያስተናግዱም መውጣት ችለዋል።
sport
05/04/2022