25/08/2026
😭😭 #የሀዘንመግለጫ😭
የደ ብርሃን ከተማን እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ለብዙ ዓመታት በትጋትና በታማኝነት ሲመሩ የቆዩት እንዲሁም የደብረብርሃን ከተማ ተስፋ ብርሃን የስፓርት ባለሙያዎች ማህበር መስራችና ፀሀፊ የመምህር ቻለው ኃይሌ ልጅ የሆነው ወጣት ዩሃንስ ቻለው በድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶናል።
የደብረ ብርሃን ከተማ ተስፋ ብርሃን ስፖርት ባለሙያዎች ማህበር በወጣት ዩሃንስ ቻለው ድንገተኛ ህልፈት የተሰማንን እጅግ ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን ለወንድማችን ለአቶ ቻለው ሀይሌ እና መላው ቤተሰቡ፣ ዘመዶቹ፣ ወዳጆቹ ከልብ የሆነ መጽናናትን እንመኛለን።
እግዚአብሔር ነፍሱን በሰላም ያኑር፤ ለቤተሰቦቹና ለወዳጆቹ ሁሉ መጽናናቱን ይስጥ።
ተስፋ ብርሃን የስፓርት ባለሙያዎች ማህበር !!
ደብረ ብርሃን
10/01/2026
በስነምግባር የታነፁና በስፖርት የጎለበቱ የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶችን ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን ተስፋ ብርሃን የስፖርት ባለሙያዎች ማህበር አስታወቀ።
ተስፋ ብርሃን የስፖርት ባለሙያዎች ማህበር አር ሲዲ ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በስፖርት ፕሮጄክቶች ወጣቶችን በማቀፍ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ እንደተናገሩት ተስፋ ብርሃን የስፖርት ባለሙያዎች ማህበር የደብረ ብርሃን ከተማ ስፖርት እንዲነቃቃ እየሰራ ያለ ማህበር ነው ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ በርካታ ስፖርት አፍቃሪያን ያሉበት እና መወዳደር የሚፈልጉ በርካታ ወጣቶች ያሉበት ቢሆንም የግብአት እጥረቱ ስፖርቱን ማሳደግ አልቻለም ማህበሩ ከአር ሲዲ ፕሮጄክት ጋር በመተባበር ያሉ የግብአት ችግሮችን በመቅረፍ እየሰራ ያለው ስራ አበረታች ነው ብለዋል።
በቀጣይም ወጣቶች ታንፀው እንዲያድጉ እና ስፖርቱ እንዲያድግ እየሰራ ያለውን ስራ አጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ አሳስበዋል።
የአር ሲዲ ፕሮጄክት ዳሬክተር ዶ/ር ዳዊት በቀለ በበኩላቸው ሀገራችንን እና ህዝባችንን ወክለው ጥሩ ደረጃ ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ወጣቶች እንዲፈጠሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን መክፈት አስፈላጊ ነው እኛም እዚህ ላይ እንድንሰራ እድሉን በማመቻቸት ማህበሩ ያገዘን በመሆኑ ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው ብለዋል።
አያይዘውም በምንችለው ሁሉ እናግዛለን በስፖርት አካዳሚው የተካተታችሁ ወጣቶች ትምህርታችሁን በአግባቡ እየተከታተላችሁ ፕሮጄክቱ ለ30 ሳምንት የሚቆይ በመሆኑ አመርቂ ደረጃ ላይ እንድታደርሱት ሲሉ አሳስበዋል።
የተስፋ ብርሃን የስፖርት ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ብስራት ለማ በበኩሉ ማህበራችን የተቋቋመው የደብረ ብርሃን ስፖርትን ለማነቃቃትና ለመደገፍ ሲሆን አላማውም ልጆችን በፕሮጄክት በማቀፍ ፣ ስልጠና በመስጠት ውድድር እንዲያገኙ በማመቻቸት እና የተለያዩ ግብዓቶችን ከባለሃብቶች እስፖርት ወዳድ ከሆኑ ደጋፊ አካላት ግብአቶችን በማሰባሰብና በመደገፍ ማብቃት ነው ብለዋል።
በአሁኑ ሰዓትም ከአር ሰዲ ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር ተፈራርመን 85 ወጣቶችን በፕሮጄክት በማቀፍ ለ30 ሳምንታት የሚቆይ ስልጠና እየሰጠን ነው በቀጣይም ወጣቶች ካልባሌ ቦታ ተጠብቀው በስነምግባር የታነፁ እና በስፖርት የበቁ እንዲሆኑ እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋለ።