Gambella city Basketball club

Gambella city Basketball club

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gambella city Basketball club, Sports Team, Gambella, Gambela.

Photos from Gambella city Basketball club's post 31/05/2026

የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ዘንድሮ በ2018 ዓ.ም ባዘጋጀዉ ዉድድር የጋምቤላ ከተማ ቅርጫት ኳስ ክለብ በሁለቱም ፆታ አሸናፊ በመሆን ተከትሎ የተለያዩ ባለሀብቶችና ግለሰቦች በማህበርና በግል ድጋፋቸውን አድርጓል።
1) ባለሀብት ቶር ኡዳንጊ በማህበራቸው ስም (የጋምቤላ ወርቅ አምራቾች ሁለገብ የህብረት ስራ ማህበር) 500,000 ብር ለሁሉም በሊጉ ላይ ለተሳተፉትን ዘጠኝ ክለቦች ዓመት ሙሉ ስለለፉ ተብሎ ድጋፋቸውን አድርጓል። ብሩ ለሁሉም ሲከፋፈል ለጋምቤላ ከተማ ቅርጫት ኳስ ቡድን ለሁለቱ ፆታ (100,000 ብር) ድጋፍ አድርጓል። በድጋሚ ባለሀብቱ ቶር በግሉ አሁንም ለሁለቱ የጋምቤላ ከተማ ቡድኖች 200,000 ብር ድጋፉ ጨምሯል። ከዚህም በተጨማሪ የቶር ኡዳንጊ ባለቤት የሆነችው አበንግ ድዱሞ ወይም በምትታወቅበት ስም አበንጌ ቆንጆ (100,000 ብር) ለሁለቱ የጋምቤላ ከተማ ቡድኖች ጨምራ ድጋፏን አድርጋለች።

2) ባለሀብት ኡካች ታባን ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ድጋፉ ያልለየን (300,000 ብር) ለሁለቱ የጋምቤላ ከተማ ቡድኖች ድጋፉ አድርጓል።

3) ባለሀብት ኡጉል ኩዎት ለሁለቱ ቡድኖች (200,000 ብር) ድጋፍ አድርጓል።

4) አቶ ኡበንግ አብዱራዛቅ የጋምቤላ ክልል ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ኃላፊ የሆኑት በግሉ (10,000 ብር) ለሁለቱ ቡድኖች ድጋፉ አድርጓል።
በሁለቱ ቡድኖች ስም ላደረጋችሁት ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን 🙏🙏

Photos from Gambella city Basketball club's post 28/05/2026

ትዉልደ ኢትዮጵያ እና ዜግነቷ አሜሪካዊት የሆኑትን ወ/ሮ ድዱሞ አጉዋ አለሞ እና ቢተሰቦቿ ለጋምቤላ ከተማ ወንዶች ቅርጫት ኳስ ቡድን በግምት ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ የስፖርት ትጥቅ እንዳበረከቱ ይታወቃል። ከዚህ ድጋፍ ስማቸዉ የሚጠቀሱ ልጆቿ (አጉዋ ፣ አጁዳ፣ ኪሩ እና ማንነቷ መግለፅ የማትፈልገዉ አሠልጣኝ አንድላይ በመሆን ይሄ ሁሉ ወጪ በማዉጣት ድጋፍ አድርጓል። ከዚህ በተጨማሪ ለሁለቱ ቡድኖች (በወንድ እና በሴት) 30 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል። ይህ አይነት ድጋፍ ለቡድኑ ትልቅ ሞራልና አቅም የሚሰጥ ሲሆን ድጋፉ ለሌሎች ዲያስፖራዎች አርአያ የሚሆን ተግባር ስለሆነ ለሁሉም ደጋፊዎቻችንን ከዚህ ስፖርት ጎን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እያስተላለፈን የተላከልንን የስፖርት ትጥቅ እንደደረሰን ፎቶ የሚገልፅ ሲሆን ለወ/ሮ ድዱሞ እና ቤተሰቦቿ ላደረጋቹልን ድጋፍ በሁለቱ ቡድኖች ስም ከልብ እናመሰግናለን።

19/05/2026

🔥🔥

17/05/2026
Photos from Gambella city Basketball club's post 17/05/2026

በጋምቤላ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 5ኛ ዙር ሀገር አቀፍ የቅርጫት ኳስ ክለቦች ፕሪሚየሪ ሊግ ውድድር ተጠናቀቀ ።
***************************

በጋምቤላ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 5ኛ ዙር ሀገር አቀፍ የቅርጫት ኳስ ክለቦች ፕሪሚየሪ ሊግ ውድድር የጋምቤላ ከተማ ቅርጫት ኳስ ቡድን በሁለቱም ፆታ በማሸነፍ ተጠናቋል ።

የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ አቶ ቱት ጆክ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር በክልላችን የቅርጫት ኳስ ፣ በእግር ኳስ ፣ በመረብ ኳስ ፣ በአትሌትክስ እና በሌሎች ስፖርቶችም እምቅ ችሎታ ያላቸው ወጣቶች መፍለቂያ ነች ብለዋል።

የጋምቤላ ከተማን በመወከል የክልላችንን እና የሀገራችንን ስም ያስጠሩ የቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች ተተኪዎችን ከማፍራት አንጻር ብዙ ሥራ ይጠበቅብናል ብለዋል።

በስፖርቱ ዘርፍ ያሉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት መስራት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

ክቡር ዶክተር ጥበቡ እሸቴ የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌደረሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ለጋምቤለ ከተማ ሴቶች የቅርጫት ቡድን የተዘጋጀውን ዋንጫ አበርክተዋል።

ክቡር አቶ ቻም ኡበንግ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ተወካይ ለጋምቤለ ከተማ የወንዶች የቅርጫት ኳስ ቡድን የተዘጋጀውን ዋንጫ አበርክተዋል።

በመዝጊያ መርሃ ግብሩ በሁለቱም ፆታ ከአንደኛ አስከ ሦስተኛ ለወጡ የቅርጫት ኳስ ክለቦች የወርቅ ፣ የብርና ነሐስ መዳሊያ ሽልማት ተበርክቷል።

በውድድሩ በርካታ ውጤት ያስመዘገቡ እና የጨዋታው ኮኬብ አሰልጣኝ እና ኮኬብ ተጫዋቾች የዋንጫ ሸልማት ተበርከቷል።

በመርሃ ግብሩ የጋምቤላ ከተማ ምክትል ከንቲባና ፐብሊክ ሰርቭስና የሰው ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡቶር ኡኩጉ ፣ የጋምቤላ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማርቆስ ጉደታን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም መላው የቅርጫት ኳስ ስፖርት ወዳጆች ተገኝተዋል።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Gambela?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address

Gambella
Gambela
5440