Venos Ent.

Call

Venos Ent. Have fun and Entertain
Dm For Promotion
[email protected]
+251939558826

ማንችስተር ሲቲ በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ ተባለ ! ማንችስተር ሲቲ ቀርበውበት በነበሩት በርካታ የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግ ጥሰት ክሶች ጥፋተኛ ተባለ። ማንችስተር ሲቲ ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝም እስ...
25/09/2026

ማንችስተር ሲቲ በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ ተባለ !

ማንችስተር ሲቲ ቀርበውበት በነበሩት በርካታ የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግ ጥሰት ክሶች ጥፋተኛ ተባለ።

ማንችስተር ሲቲ ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝም እስካሁን የቅጣት አይነቱ ላይ ከውሳኔ እንዳልተደረሰ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

ይሁን እንጂ ማንችስተር ሲቲ ላይ የትኛውም አይነት ቅጣት ሊጣል እንደሚችል በዘገባዉ ተጠቁሟል።

ማንችስተር ሲቲ በበኩላቸው ጥፋተኛ የተባለበትን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ እንደሚጠይቁ ተገልጿል።

ክለቡ ከቀረበበት 115 የፋይናንስ ደንብ ጥሰት ክሶች በ 114ቱ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል ተብሏል።

ከዛሬ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ላልተወሰነ ጊዜ ተከለክሏል።ከኮድ 4 እና ከፖሊስ ሞተር ብስክሌቶች ውጭ ያሉ ሁሉ...
25/09/2026

ከዛሬ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ላልተወሰነ ጊዜ ተከለክሏል።
ከኮድ 4 እና ከፖሊስ ሞተር ብስክሌቶች ውጭ ያሉ ሁሉንም ይመለከታል።
የእገዳው ምክንያቶች፡
​ሞተር ብስክሌቶችን ለቅሚያ፣ ለስርቆት እና የተሰረቁ ዕቃዎችን ለማጓጓዝ መጠቀም በመበራከቱ።
​ቀይ መብራት መጣስ፣ ገጭቶ ማምለጥ፣ ሄልሜት አለመጠቀም እና የሰሌዳ ቁጥር ማደብዘዝ የመሳሰሉ የትራፊክ ደንብ ጥሰቶች በመብዛታቸው ነው ሲል የ አዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል::

25/09/2026

 በትግራይ ክልል የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ዛሬ ተቋርጧል።ሮይተርስ ፤ አራት ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ ሰዎችን እና የዲፕሎማቲክ ምንጭ ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው የስልክ እና የኢንተርኔት ...
25/09/2026



በትግራይ ክልል የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ዛሬ ተቋርጧል።

ሮይተርስ ፤ አራት ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ ሰዎችን እና የዲፕሎማቲክ ምንጭ ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ያደረጉት የህወሓት መሪዎች ናቸው።

ምንም እንኳን ህወሓት በይፋ ያለው ነገር ባይኖርም አንድ ከህወሓት ጋር ቅርበት ያላቸው ምንጭ " ህወሓት ነው ያቋረጠው " የሚለውን መረጃ አስተባብለዋል።

ህወሓት ኔትዎርኩን እንዳቋረጠ የገለጹ የሮይተርስ ምንጭ፤ " የሞባይል እና የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ያዘዘው የመንግሥት ወታደሮች በውጊያ ድሮኖችን ሲጠቀሙ የሞባይል ኔትዎርኮችን እንዳያገኙ የተጠቀመበት ስልት አካል ሳይሆን አይቀርም " ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የስምረት ፓርቲ አመራር ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሐለፎም ንርኣ " የስልክ እና ኢንተርኔት ግንኙነት (ኔትዎርክ) እንዲቋረጥ ያደረገው ህወሓት ነው " ብለዋል።

" ካሁን በፊትም ትግራይ ክልል ላይ ካለው ዋናው መስሪያ ቤት ሄደው ነበር የቆረጡት። ቆርጠው በክልሉ ባሉ ከተሞች እንዳይሰራ፣ እዛው ያሉበት ከተማ ግን እንዲያገናኝ አድርገውት ነበር በ2013 ዓ/ም " ሲሉ አስታውሰዋል።

" ስለዚህ ስለሚያውቁት ቴሌም በየብራንቹ መቆጣጠሪያ ስላለው እሱን ነው ያጠፉት " በማለት አሁን የተዘጋበትን መንገድ አስረድተዋል።

" የሳፋሪኮምም ከዚህ ጋር የተያያዘ መስሏቸው ነበር። ግን ለብቻው ነው " ብለዋል። " ዛሬ ግን 'በአስቸኳይ እንድትዘጉት' ብለዋቸዋል " በማለት ተናግረዋል።

" ህወሓት የኔትወርክ አገልግሎት እንደሚዘጋ እየተናገረ ቆይቷል። 'በቅርብ ቀን እንዘጋዋለን' እያሉ ነበር " ሲሉም አስታውሰዋል።

" ለዚህ የኔትዎርክ ማቋረጥ እንደ ዋና ምክንያት የሚያቀርቡት አንዱ ' በውስጣችን/በመካከላችን ለፌደራል መንግስት ጥቆማና መረጃ የሚሰጡ አካላት እየተበራከቱ መጥተዋል ' " የሚል ነው።

" በሌላ በኩል ' በድሮን ጥቃት እየደረሰ ያለው ጉዳት በኢንተርኔት የሚታገዝ ነው ' በሚል ነው የኢንተርኔት እና ስልክ አገልግሎት የማቋረጥ እርምጃ የወሰዱት " ሲሉ አቶ ሓለፎም የተናገሩት።

" እንደሚዘጋ አስቀድመውም እያወሩ ስለነበር እኛም ለአንዳንዶቹ የኛ ሰዎች እየተናገርናቸው ነበር " ሲሉም አክለዋል።

" የቴሌ ኔትወርክ ሲዘጋ የሳፋሪኮም አልተዘጋም ነበር። ነገር ግን ሳፋሪኮምንም የጸጥታ አካል የሆኑትን እነፍስሃ ማንጁስንና አንድን ሌላ አካል ወደ ዋናው መስሪያ ቤታቸው ሄደው እንዲዘጉት አዘዋል። ቴሌ ከተዘጋ በኋላ ሰዎች በሳፋሪኮም ለመጠቀም ሲም ካርድ ለማውጣት ዛሬ ወረፋ ይዘው ነበር። ግን የሳፋሪኮምንም ሊዘጉት ስለሆነ 'አትክሰሩ አቁሙ' ተብሏል " ብለዋል።

"' ዛሬ ሳፋሪኮም ይዘጋል። ከዛሬ እንዳያልፍ' ተብሏል " ሲሉም ያጣሩትን መረጃ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም

25/09/2026

ኸቢድ ጊዜ!

24/09/2026

ሰበር
አብ መላእ ትግራይ ኔትወርክ ተቋሪፁ።
በመላዉ ተግራይ ኔትወርክ ተዘጋ።

24/09/2026

Grand Mom boss

አማኑኤል ገብረሚካኤል ወደ ከፍተኛ ሊጉ ክለብ ድሬዳዋ ከነማ ፈረመ
24/09/2026

አማኑኤል ገብረሚካኤል ወደ ከፍተኛ ሊጉ ክለብ ድሬዳዋ ከነማ ፈረመ

🇪🇹✈️ወደ ላሊበላ የሚደረግ ጉዞ በግዚያዊነት ታገደ❗️✈️የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ የሚያደርገው በረራ ሙሉ ለሙሉ መቆሙ ታወቀ።✈️ላሊበላ ዙሪያ ትናንት ጀምሮ የከባድ መሳሪያ ተኩስ...
24/09/2026

🇪🇹✈️ወደ ላሊበላ የሚደረግ ጉዞ በግዚያዊነት ታገደ❗️

✈️የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ የሚያደርገው በረራ ሙሉ ለሙሉ መቆሙ ታወቀ።

✈️ላሊበላ ዙሪያ ትናንት ጀምሮ የከባድ መሳሪያ ተኩስ እየተሰማ ይገኛል።
ይህንን ተከትሎ ከትናንት ጀምሮ ወደ ላሊበላ በረራ አለመደረጉን ከፍላይት ራዳር ለማረጋገጥ ተችሏል።

Address

Pape Avenur

M4K3W5

Telephone

+251946481853

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Venos Ent. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Want your business to be the top-listed gym/sports facility?

Share