01/02/2021
WSC
01/02/2021
30/10/2019
ጤና ይስጥልኝ!!
01/12/2018
ጤና ይስልኝ ወልድያ
እንዴት ናችሁ የወልድያ ስፖርት ክለብ የስፖርት ቤተሰቦች!
አጫጭር መረጃወችን ለመወርወር ብቅ ብለናል!!
=================================
ወልድያ ስፖርት ክለብ በዚህ አመት በከፍተኛ ሊግ ውድድሩር የሚሳተፍ ሲሆን ነገ እሁድ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከአቃቂ ቃሊቲ ጋር በ9:00 ሰአት ከሜዳው ውጭ ያደርጋል!!
ወልድያ ከጥቅምት 2 ጀምሮ ዝግጅቱን በወልዲያ ከተማ ሲያደርግ ቆይቶ ከ ህዳር 1 ቀን ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ በማቅናት በርከት ያሉ የወዳጅነት ጨዋታወችን በማድረግ ዝግጅቱን ሲያካሂድ ቆይቷል!!
ወልድያ ስፖርት ክለብ
#ከውሃ ስራ
#ከጉለሌ
#ከመድን
#ከመከላከያ
#ከየካ
#ከቅዱስ ጊዮርጊስ
#ከአራዳ ክ/ከ
ቡድኖች የወዳጅነት ጨዋታዎችን አድርጓል
*****************************
ወልድያ ስፖርት ክለብ ላይ በዚህ አመት ያሉ ለውጦች
*በአዲስ አሰልጣኝ እና ኮቺንግ ስታፍ አባላት ተጠናክሮ ቀርቧል
*የዛሬ አመት ክለቡ ጋር የነበሩ ተጨዋቾችን 80% ቱን በአዲስ ተጨዋቾች ቀይሯል
*በዚህ አመት አንድም የውጭ ሃገር ተጨዋች አላካተተም
*ሶስት ተጨዋቾች አሳድጓል
*የክለቡ ከ50% በላይ ተጨዋቾች የአካባቢው ልጆች ናቸው
*ክለቡ የተጨዋች መኖሪያ ካንፑን ወደ ስታዲየሙ ቀይሯል!!
************************************
የወልድያ ስፖርት ክለብ ተጨዋቾች ዝርዝር!!
1. አንተነህ አሳየ
2. ተስፋሚካኤል በዛብህ
3. ነጋ በላይ
4. ሙሉቀን አከለ
5. ዳንኤል ዝናቡ
6. ሞገስ ዝናቤ
7. ፍሬው ብርሃን
8. ዮናስ ወንዳጥር (ቻይና)
9. ሐብታሙ ሲሳይ (ቃሪያው)
10. ሃይሌ ጌታሁን
11. እንድሪስ ሰይድ
12. ተስፋየ ነጋሽ
13. ከፍያለው ሃይሉ
14. ሰለሞን ወ/ጻድቅ
15. ቢኒያም ጌታቸው
16. አብይ ቡልቲ
17. አብርሃም ተስፋ
18. አለማየሁ ፍስሐ
19. በልስቲ ቀረብህ
20. ሲሳይ ሚደቅሳ
21.ይግረማቸው ተስፋየ
22. ተስሉች ሳይመን
23. በረከት አፈወርቅ
24. ሃብታሙ ንጉሴ
25. ብርሃን አንለይ ናቸው!!
********************
የወልድያ ስፖርት ክለብ የኮቺንግ ስታፍ አባላት
አረጋይ ወንድሙ = ዋና አሰልጣኝ
ያዕቆብ አብርሃ = ም/አሰልጣኝ
በኃይሉ ሰፊው = የግብጠባቂ አሰልጣኝ
ዳዊት አለሙ = ቡድን መሪ
ሰለሞን ሰጠ = ፊዚዮቴራፒስት
ዮናስ አለሙ = ኪት ማናጀር
**********************
ገረመው ካሳ = የክለቡ ስራ አስኪያጅ
አህመድኑር ደስታ = የክለቡ ፕሬዝዳንት
***************************
ወልድያ ስፖርት ክለብ ነገ እሁድ ህዳር 23 ቀን በ9:00 ሰዓት የመጀመሪያ ጨዋታውን ከ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ጋር ከሜዳው ውጭ ይጫወታል!!
#መልካም የውድድር ዘመን!!
#ድል ለወልድያ ስፖርት ክለብ!!!
=> facebook.com/woldiasportclub
10/10/2018
የወልድያ ስፓርት ክለብ ለ2011 የውድድር ዘመን 14አዳድስ ተጫዋቾችን በማስፈረም
የፊታችን አርብ ወደ ካምፕ በመግባት ሌሎችን የጎደሉትን ጨምሮ ለውድድር ቅድመ ዝግጅቱን ይጀምራል
የፈረሙትን ተጫዋቾችና ሌሎችንም ጨምረን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን
LOADING............wsc
17/07/2018
አኑ የወልዲያ ልጅ
ሰላም እንደምን አላችሁ ዉድ ወልዲያዊያን እንደሚታወቀው ክለባችን ወልዲያ ስፖርት ክለብ በሆዳሞችና እራስ ወዳድ ጅቦች ከሀገራችን ትልቁ መድረክ ዝቅ እንድንል ተደርገናል ለዚህም ሁሉም በቅርቡ ዋጋውን እንደሚያገኝ እርግጠኛ ነኝ ክለባችን ከዚህ መድረክ ይዉረድ እንጂ ክለባችን ትልቅ መስዋዕትነት ከፍሏል እራሱን ሰዉቶ የኢትዮጵያን ህዝብ ከፍ አድርጓል ይሁንና ወደ ዋናው ጉዳይ ስገባ ስለወደፊቱ ምን ታስቧል? ጥያቄዉ ለሁሉም ነዉ!
1. #አመራሩ ፦ በመጀመሪያ ደረጃ አንድን ነገር ለተሻለ ደረጃ ለማድረስ ጠንክሮ መስራት ነዉ ጠንክረህ ለመስራት ደግሞ አላማ ይኖርሃል አላማህን ለማሳካት እውቀት ያስፈልጋል ስራህን ግብ ለማድረስ መሪ ያስፈልጋል ምን ለማለት ነዉ አመራሩ በእዉቀትና በአላማ የተደገፈ ሊሆኑ ይገባል ዝም ብሎ የፖለቲካ የከሰረ ፖለቲካ ለማስፈፀም እየተመረጡ የህዝብ ሳይሆኑ የአንድ ወገን ተልዕኮ አስፈፃሚ የሚሆን ሊሆን አይገባም ለስፖርቱ ተቆርቋሪ ፍላጎት ታማኝ የህዝብ አገልጋይ ሊሆን ይገባል ዝም ብሎ የህዝብን ገንዘብ ለመዝረፍና ከተጨዋቾች ጋር አየተደራደረ የተሰጠውን አደራ የሚያባክን አመራር አያስፈልገንም አሁንም ስፖርቱን ሊያሳድግ የሚችል ከፕሮጀክቶችና በአከባቢው ያሉ የከተማው ቡድኖች ከታችኛው ቢ ወይም የጁ ከነዚህ ጋር አብሮ መስራትና አሁን ለተፈጠረው ክፍተት መሸፈን የሚቻለው በዚህ ስለሆነ አነዚህ ላይ ሊሰራ የሚችል መሆን አለበት በሌላ በኩል በቅርቡ የዉይይት መድረክ ሊዘጋጅ ይገባል ሰለ ወደፊት አላማችሁን ልታሳዉቁን ይገባል፡፡
2. #ደጋፊ፦ ከደጋፊዉ ምን ይጠበቃል የሚለውን በቀጣይ ፅሁፌ እመለከታለሁ ........................ይቀጥላል!
11/07/2018
የ30ኛ ሳምንት የወልድያ ስፖርት ክለብ ጨዋታ አሁንም ከሜዳው ውጭ ወላይታ ዲቻ ጋር ይጫወታል!!
ወልድያ ስፖርት ክለብ በመርሃግብሩ መሰረት የ30ኛ ሳምንት ጨዋታውን ወልድያ ላይ እንደሚያካሂድ ፕሮግራም የወጣ ኮቺንግ ስታፉ ተጨዋቾችን ወደ ወልድያ ለመውሰድ ቢሞክርም እና ወደ ከተማቸው እንዲሄዱ ለማግባባት ያወያየ ቢሆንም ከ 4 ተጨዋቾች ውጭ ወደ ወልድያ አንሄድም በማለታቸው እና አለመሄዳቸውንም በፊርማ ማረጋገጣቸውን ተከትሎ ጨዋታው ሰበታ ስታዲየም ይካሄዳል!!
ክለቡ ጨዋታው በሜዳው እንዲካሄድ እንደሚፈልግ በመጥቀስ ከ4 ቸጨዋቾች በስተቀር ሌሎቹ ተጨዋቾች ወልድያ ሂደው እንደማይጫወቱ የፈረሙበትን ቃለ ጉባኤ በማያያዝ ለፌደሬሽን ደብዳቤ ጽፎም አሳውቋል!!
ተጨዋቾቹ ወደ ወልድያ ካልተመለሱ እና በሚመለሱት 4 ቸጨዋቾች ብቻ ጨዋታውን ማካሄድ ስለማይቻል ውጤቱ ፎርፌ ቢሰጥ ሌሎች የወልድያን ውጤት የሚጠብቁ ክለቦች ስላሉ ውጤቱ ሌሎች ክለብ ላይ ተጽእኖ ሊያሳርፍ ስለሚችል በወልድያም ይህን ተከትሎ ሌላ ቅጣትም ሊያስቀጣው ይችላል ቅጣቱም እስከ 500,000 ብር ቅጣት እና አንድ ደረጃ ወደታችኛው ሊግ ወርዶ እንዲጫወት የሚደርስ ቅጣት ሊያስቀጣው የችላል!!
ፌጀሬሽኑ በነዚህ ምክንያት የተነሳ ይህንን ጨዋታ ሰበታ ላይ ከሌሎች ወሳኝ ጨዋታወች ጋር በተመሳሳይ ሰአት እንዲካሄድ ወስኗል!!
የወልድያና የ ወላይታ ዲቻም ጨዋታ ቅዳሜ በ9:00 ሰአት ሰበታ እንደሚካሄድ መወሰኑን እየገለጽን ዝርዝር ሁኔታውን የምናሳውቅ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን!!
19/06/2018
ይሄ የምንመለከተው ልጅ ሀይሉ ጓንጉል ይባላል በወልድያ ከተማ የገነት ፍሬ ስፓርት
ቡድን የታዳጊወች አሰልጣኝ ነው፡፡ስለሱ ብዙ አልናገርም ምክኒያቱም ሁሉ ነገሩ
መልካም ሰው ነው በአጭሩ
ዛሬ አንድ ደስ የሚል ሀሳብ ስለነገረኝ እኔም ሀሳቡን ወድጀው ፓሰትኩት
ሀሳቡ በወልድያና አካባቢው ያሉት ወጣቶች ለማሰባሰብ በፍቅር አንድ ለመሆን
ችግሮቻችንን ለመፍታት ለመነጋገር በወልድያ በአራቱም አቅጣጫ አንድ አንድ የስፓርት
ቡድን አቋቁመን ውድድር እናዘጋጅና በደንብ እንፋቀር እንገናኝ አንድ እንሁን ፍቅርን
መሰባሰብን ከሚኒስተራችን እንማር የሚል ሀሳብ ነው፡፡፡እስኪ በዚህ ላይ ሀሳብ
አስተያየት እንስጥበትና እንደት በምን ሁኔታ የሚለውን ቀጣይ እናወራለን ፡፡፡፡