04/10/2026
🚨 💣 የኦልድ ትራፎርድ ትልቁ የልብ ስብራት፦ ወደ ሪያል ማድሪድ ያመራው የትኛው ኮከብ የበለጠ አሳዘናችሁ? 💔⚪️🔴
በማንቸስተር ዩናይትድ ታሪክ ውስጥ በርካታ የአለም ታላላቅ ከዋክብት በኦልድ ትራፎርድ ደምቀው ወደ ሪያል ማድሪድ ያደረጉት ዝውውር ለደጋፊዎች ሁልጊዜም መራራ እና የልብ ስብራት የሆነ ትዝታ ነው!
▪️ 🎯 ዴቪድ ቤካም (2003)፦
ከክለቡ አካዳሚ የወጣው፣ የክለቡ ፍቅር እና የደጋፊዎች የልብ ትርታ የነበረው ቤካም ከሰር አሌክስ ፈርጉሰን ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ወደ ማድሪድ ሲያመራ የኦልድ ትራፎርድ ደጋፊዎችን በከፍተኛ ሁኔታ አዝኗል።
▪️ ⚽ ክርስቲያኖ ሮናልዶ (2009)፦
በ2008 የባሎንዶር እና የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን በዩናይትድ ቤት ያሸነፈው ሮናልዶ፣ በወቅቱ የአለም ውድ ዝውውር በሆነው £80m ወደ ማድሪድ ሲያመራ ዩናይትድ በአለም እግርኳስ የነበረውን የበላይነት እና ገዳይ የማጥቃት ኃይሉን ያጣበት አጋጣሚ ነበር።
▪️ ሩድ ቫን ኒስቴልሮይ (2006)፦
በ150 ጨዋታዎች 95 ግቦችን ያስቆጠረው ገዳዩ አጥቂ ሩድ፣ በድንገት ከፈርጉሰን ጋር ተጣልቶ ወደ ማድሪድ ማመራቱ ሌላው ያልተጠበቀ መራራ ስንብት ነበረ።
እነዚህ ሶስቱም ተጫዋቾች በሪያል ማድሪድ ቤት ድቅ ታሪክ ቢጽፉም፣ ለዩናይትድ ደጋፊዎች ግን የሮናልዶ እና የቤካም ዝውውሮች ከክለቡ ታሪክ እና ስሜት ጋር በተያያዘ ሁልጊዜም በልዩ ሁኔታ የሚታወሱ የልብ ስብራቶች ናቸው።
👇 የእናንተ ድምፅ (Reds)፦
በእርሶ ህይወት የትኛው ተጫዋች ወደ ሪያል ማድሪድ መሄዱ የበለጠ ልቦትን ሰበረው?
🎯 ቤካም? ⚽ ሮናልዶ? ወይስ ሩድ? ወይስ ሌሎቹ ማን? ሀሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን! 👇