09/07/2026
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት ተስፋ አዲስ ፓረንትስ የህፃናት ካንሰር ማዕከልን ጎበኙ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት ከኢ/እ/ፌ ፕሬዝዳንት፣ የካፍ የሥራ አሰፈፃሚ ኮሚቴ እና የፊፋ ቋሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ ዋና ሥራ አስፈፃሚአቶ ባህሩ ጥላሁን፣ የህክምና ዳይሬክተርና የስትራቴጂ አማካሪ ዶ/ር ሳሙኤል የሺዋስ ጋር በመሆን ተስፋ አዲስ ፓረንትስ የህፃናት ካንሰር ማዕከልን ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የህክምና አጋሩ ከሆነው ከውዳሴ ዳያግኖስቲክ ማዕከል ጋር በመተባበር የጳጉሜ የበጎ አድራጎት ወርን በማስመልከት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች እና የአሰልጣኝ ቡድን አባላት ተሳታፊ በሆኑበት በዚህ መርሐ ግብር ከካንሰር ታማሚ ህፃናቱ ጋር ከኳስ ጋር እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ስታዲየም ትንሿ ሜዳ ሲያከናውኑ የካንሰር ታማሚ ህፃናቱ ከካንሰር ጋር እየታገሉ ህመሙን ለማሸነፍ ነገን ተስፋ በማድረግ በሜዳ ላይ ከብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ጋር ሲደሰቱ ማየት ከእርካታም በላይ ነው።
ከዚህ ሁነት በመቀጠል የብሔራዊ ቡድኑ አባላት ከእለቱ እንግዶችና ከውዳሴ ዳያግኖስቲክ ማዕከል አባላት ጋር በመሆን በተስፋ አዲስ ፓረንትስ የህፃናት ካንሰር ማዕከል ጉብኝት አካሂደዋል። በተስፋ አዲስ ፓረንትስ የህፃናት ካንሰር ማዕከል በነበረው ጉብኝት ላይ ክቡር ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ "የህፃናቱ ሁኔታ እጅግ ልብ ይነካል። ይሄ ስራ ለተወሰኑ ሰዎች የሚተው አይደለም። እኛም እንደፌዴሬሽን የበኩላችንን እንወጣለን የብሔራዊ ቡድን አባላትም ካላችሁበት አንፃር ሰፊ ስራ ይጠበቅባችኃል። ሌሎችንም በማስተባበር ግዴታችሁን መወጣት ቸለባችሁ። ሜዳ ላይ ልጆቹን ሳይ ስሜታዊ ሆኜ ነበር አሁን ደግሞ ይሄን ሳይ ተስፋ ፈጥሮብኛል። ከዚህ ድነው ጥሩ ተማሪ ጥሩ ኳስ ተጫዋች ጥሩ ዜጋ እናገኛለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ያን ማድረግ የምንችለው እጅ ለእጅ ተያይዘን ስንሰራ ነው ስለዚህ የብሔራዊ ቡድን አባላትም እዚህ መምጣት ብቻ ሳይሆን የቤት ስራም ይዛችሁ ነው የምትመለሱት ትኩረት ልትሰጡት ይገባል፡፡ ድጋፋችንን በተግባር ማሳየት አለብን አሁን ቃል የምገባው ተግባራዊ የሚሆነው እዚህ ያላችሁ በሙሉ ስትሳተፉበት ነው በጋራ ሆነን ማህበራዊ ግዴታችንን እንወጣለን ይህንንም ፕሮግራም ያዘጋጁትን በሙሉ አመሰግናለው።" ብለዋል
የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሳራ ኢብራሂም በበኩላቸው "ድርጅታችን በዋናነት በህፃናት ካንሰርና ወላጆቻቸውን ማገዝ ነው ስራው። የህፃናት ካንሰር በከፍተኛ ደረጃ መዳን የሚችል ስለሆነ ከተጋገዝን ከዚህ የተሻለ መስራት እንችላለን። በተቋማችን በአሁኑ ሰዓት ለህመምተኞች የሚሆን ማደሪያ አለን። ታክመው ድነው ትልቅ ደረጃ የደረሱም አሉ። ይህንንም ሥራ የምንሰራው ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ነው። ዛሬም የመጡትን እንግዶች ፌዴሬሽኑንና የብሔራዊ ቡድን አባላት ይህንን እድል ስለሰጣችሁን እጅግ በጣም እናመሰግናለን። በቀጣይ ያለባችሁን ጨዋታ በድል እንድትወጡ ምኞቴን አገልፃለሁ።"
ወ/ሮ ውዳሴ እንቁብርሃን በበኩላቸው "እንዴት እንደሚኖሩ ማየት ዓይን ይገልጣል። እውነትም ተስፋ ይሰጣል የማለዳ ፀሃይ ስትወጣ አዲስ ተስፋ አዲስ ቀን ነው። ስለዚህ በአዲስ ተስፋ በአዲስ ዓመት ደግሞ አብራችሁን እንደምትቆሙ ቃል እየገባችሁልን ስለሆነ በጣም ደስተኛ ነኝ። ምስጋናዬንም በውዳሴና በአጋሮቻችን ስም አመሰግናለው " ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን ባስተላለፉት መልእክት " ከውዳሴ ጋር መሰል ሀላፊነትን ስንወጣ ቆይተናል አሁንም የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችም ከእግር ኳስ ጎን ለጎን እንደዚህ አይነት የበጎ አድራጎት ስራ መሳተፍና ተቀባይነታቸውን ተጠቅመው የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ላይ መሳተፍና መሰል ልጆችን መንከባከብና ማገዝ ከኛ ይጠበቃል ማድረግ በምንችለው በሙሉ እንሳተፋለን ይህንንም ፕሮግራም የዘጋጁትን እናመሰግናለን።" ያሉ ሲሆን በመጨረሻም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያዘጋጀውን ድጋፍ የኢትዮጵያ አግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ አበርክተዋል፡፡
Ethiopian Football Federation
09/07/2026
ሆሞሻ ሸንጋ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም ከስምምነት ላይ ደርሷል !
ሆሞሻ ሽንጋ እግር ኳስ ክለብ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከኢትዮጵያ ሊግ አንድ ወደ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ማደጉ የሚታወስ ሲሆን በከፍተኛ ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ አሰልጣኝ ጋሻው መኮንን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ለመሾም ከስምምነት ላይ ደርሷል።
ሆሞሻ ሸንጋ የኢትዮጵያ ሊግ አንድ ውድድር አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን ማጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን በነገው ዕለት በኢሊሌ ሆቴል በሚካሄደው የኮከቦች ሽልማት መሐመድ አብዱልአዚዛ በዓመቱ ኮከብ ተጨዋች ዕጩ እና ለዓለም ጥላሁን ኮከብ ግብ ጠባቂ ዕጩዎች ውስጥ የተካተቱ ተጨዋቾች ሆነዋል።
Telegram T.me/Dagu_Sport
Telegram T.me/DaguLive
09/07/2026
መንጌ ቤላሻንጉል እግር ኳስ ክለብ ለ2019 የከፍተኛ ሊግ ውድድር ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ በርካታ አዳዲስ ተጨዋቾችን ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል !
ከዝህ ቀደም በአርባ ምንጭ ከተማ ፣ ባህር ዳር ከተማ ፣ ወላይታ ድቻ ፣ ወልቂጤ ከተማ ፣ ሻሸመኔ ከተማ ፣ አዳማ ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ ተጫውቶ ያሳለፈው አጥቂው ስንታየሁ መንግስቱ ፣ ከዝህ ቀደም በወልዲያ ከተማ ፣ ሀዲያ ሆሳዕና እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተጫውቶ ያሳለፈው ግብ ጠባቂው ስንታየሁ ታምራት ፣ ከዝህ ቀደም በዶሬ ባፋኖ ያለፉትን ዓመታት በቢሾፍቱ ከተማ ያሳለፈው የአማካይ ስፍራ ተጨዋች አየነው ሰለሞን ፣ በተጠናቀቀው ዓመት በሶሎዳ ዓድዋ በግሉ ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረግ የቻለው የፊት መስመር ተጨዋች ዓለምሰገድ አድማሱ ፣ ከዝህ ቀደም በእንጅባራ ከተማ ባህር ዳር ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈው አጥቂው ዮሐንስ ደረጄ ፣ ከዝህ ቀደም በሱሉልታ ክ/ከተማ ፣ ሶሎዳ ዓድዋ እና ያለፉትን ዓመታት በመቐለ 70 እንደርታ ተጫውቶ ያሳለፈው የመስመር አጥቂው መሐሪ አመሃ ፥ ከዝህ ቀደም በነቀምቴ ከተማ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በቢሾፍቱ ከተማ ያሳለፈው አጥቂው አዳሮ ሰሙኤል ፣ አማካዩ መሐመድ አብዱልከሪም እና ሌላኛው የአማካይ ስፍራ ተጨዋች አዲሱ አድኃኖም ከመቐለ 70 እንደርታ መንጌ ቤላሻንጉልን ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ የደረሱ ተጨዋቾች ናቸው።
Telegram T.me/Dagu_Sport
Telegram T.me/DaguLive
09/07/2026
ዋናው ስፖርት x ሽሮ ሜዳ ሰመር ካፕ
ዋናው ሽሮ ሜዳ ሰመር ካፕ በሚል ስያሜ ለ1ወር ተኩል ሲዘጋጅ የነበረው የጤና ቡድኖች ውድድር ትላንት በጨፌ ሜዳ በ19 ቀበሌ እና 23 ቀበሌ የጤና ቡድኖች ጠንካራ ፉክክር ፍፃሜውን በ19 ቀበሌ 3-2 አሽናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን ዋናው ስፖርት ይህንን ዝግጅት በ 1.2 ሚሊዮን ብር ስያሜውን ተጋርቶ ስፖንሰር ሲያደርግ ዋና አላማው ወጣቶችን ከአልባሌ ነገር ከማራቅ ባሻገር ማህበረሰቡ ደግሞ የነበረውን ወዳጅነት በጠበቀ መልኩ አንዲያስቀጥል በማሰብ ነው::
🔗ማህበራዊ ገጾቻችን🔗
Instagram|Facebook |TikTok |X|Youtube
⭐️|
09/07/2026
ድሬዳዋ ከተማ ሶስት አዳዲስ ተጨዋቾችን ለማስፈረም ስምምነት ላይ ሲደርስ የሁለት ነባር ተጨዋች ውል ለማራዘም ተስማምቷል !
በከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ የሆነው ድሬዳዋ ከተማ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለመመለስ አዳዲስ ተጨዋቾችን ወደ ቡድኑ በመቀላቀል እንድሁም የነባር ተጨዋች ውል በማደስ ላይ ይገኛል፡፡
ከዝህ ቀደም በሲዳማ ቡና ፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ ንብ ( አየር ኃይል ) እና በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫውቶ ያሳለፈው የአማካይ ስፍራ ተጨዋቹ ብርሃኑ አሻሞ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋችሁ ናትናኤል ተክለ ሌላው ከምድረ ገነት ሽረ ብርቱካናማዎቹን የተቀላቀለ ተጨዋች ሲሆኑ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ድሬዳዋ ተስፋ ቡድን ተጫውቶ ካሳለፈ በኃላ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ሲመለስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካደረጉት ተጨዋቾች አንዱ የሆነውና በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በመቻል ቆይታ ማድረግ የቻለው ሚኪያስ ካሳሁን ዳግም ወደ ድሬዳዋ ከተማ ለመመለስ ከስምምነት ደርሷል።
ውላቸውን ለማደስ ከስምምነት ላይ ከደረሱ ተጨዋቾች መካከል ባለፉት ዓመታት በክለቡ ቆይታ የነበራቸው የመስመር አጥቂው ዘራይ ገ/ሥላሴ እና የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጨዋቹ ሄኖክ ሀሰን በድሬዳዋ ከተማ ለመቆየት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
Telegram T.me/Dagu_Sport
Telegram T.me/DaguLive
09/06/2026
ዋናው ስፖርትን የውድድር አጋርዎ ሲያድርጉ!
ውድድርዎት ከመድመቁ በላይ ብዙ ያተርፋሉ
✔️ ጥራት ያላቸው ማሊያዎች
✔️ ልዩ ስጦታዎች
✔️ ፈጣን አገልግሎት
📞 8289 | +251901138283 |
🛒ወይም በቀጥታ👇ይህን በመጫን
👉 (Shop Now) 👈
09/06/2026
የስልጤ ዞን ጦራ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከኢትዮ ናሽናል ስፖርት አካዳሚ በጋራ በመሆን ያዘጋጁት 3ኛው ኢትዮ ሰመር ስልጤ ዞን ጦራ ካፕ በማዕበል እግር ኳስ ክለብ አሸናፊነት ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል !
⌚️የሙሉ ሰዓት ውጤት !
ማዕበል 0-0 ፋያ ጎልድ
ጨዋታው ያለ ግብ በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የመለያ ምት ማዕበል 5-3 ፋያ ጎልድን በማሸነፍ የውድድሩ አሸናፊ መሆን ችሏል ።
የውድድሩ ኮከቦች ሽልማት
ኮከብ ተጨዋች ሪያድ ከማዕበል
ለኮከብ ግብ ጠባቂ አብዱለጢ ከማዕበል
ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ዳዊት ለማ ፋያ ጎልድ
የውድድር ኮከብ አሰልጣኝ
ቶፊቅ ሁሴን ከማዕበል
የውድድሩ ምስጉን ዳኛ ሙኽድን ጀማል
Telegram T.me/Dagu_Sport
Telegram T.me/DaguLive
09/05/2026
የ2019 ኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ
የመጀመሪያ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር
ውድድሩ በደርሶ መልስ (በሜዳና ከሜዳ ውጭ) የሚካሄዱ ሲሆን ሜዳዎችን አስመዝግበው ያላጠናቀቁ ቡድኖች በጊዜ እንዲያጠናቅቁ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሳስቧል።
ውድድሩ መስከረም 7/2019 የሚጀመር ይሆናል።
Telegram T.me/Dagu_Sport
Telegram T.me/DaguLive
09/05/2026
የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ
⌚️ የሙሉ ሰዓት ውጤት'
ኤግሎንስ 0-0 ሲዳማ ቡና
Telegram T.me/Dagu_Sport
Telegram T.me/DaguLive
09/05/2026
የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ
⌚️ 90'
ኤግሎንስ 0-0 ሲዳማ ቡና
Telegram T.me/Dagu_Sport
Telegram T.me/DaguLive