31/12/2025
🇺🇸🇪🇹 ከዲቪ ሎተሪ እስከ ግሪን ካርድ ፤ ከአሳይለም እስከ ሪፊውጂ በ2026 ምን እንጠብቅ? 9 የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ጉዳዮች Life in America
Navigating US Immigration in 2026: DV Lottery, Asylum & More | 9 Key Changes & Updates DV Lottery, Green Card, Asylum, Refugee, US ImmigrationGreen Card Up...
31/12/2025
(ዘ-ሐበሻ ዜና) "ፑቲን ጠላት ነው፣ ነገር ግን በ2026 ጦርነቱን እናቆማለን" ሲሉ ዘለንስኪ ተናገሩ፡፡ የዩክሬይኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ከአሜሪካው ፕሬዝደንት ጋር ያደረጉት ውይይት ‹‹በጣም ጠቃሚና ፍሬያማ›› መሆኑን ገልፀው ለዚህም በአሜሪካና በዩክሬይን ተወካዮች መካከል ለወራት የተደረገውን ንግግር አመስግነዋል፡፡
ባለ20 ነጥቡን የሰላም እቅድ በተመለከተ ሲገልፁ ደግሞ ዩክሬይን ከቀረቡት ነጥቦች ላይ ከአንድ ጉዳይ በስተቀር ከሞላ ጎደል መስማማቷን አስረድተዋል፡፡ ሲናገሩም ‹‹መሬቶችን በተመለከተ ከሩሲያዊን ጋር ልዩነት አለን፡፡ ልብ በሉ ልዩነት ያለን ከአሜሪካዊያን ጋር ሳይሆን ከሩሲያዊያን ጋር ነው›› ያሉት ዘለንስኪ እነዚህ መሬቶችም በአራቱ ሩሲያ በጠቀለለቻቸው ግዛቶች ማለትም ዶኔስክ፣ ሉሀንስከ፣ ዣፓሮዢያና ኬርሰን ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
ማናቸውም ግዛትን የሚመለከቱ ውሳኔዎች የዩክሬይንን ህግና የህዝቡን ፈቃድ ማግኘት እንደሚገባቸውም አስረድተዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹እኛ ከእነዚህ ግዛቶች ለቀን አንወጣም፡፡ ምክንያቱም የህግ ጉዳይ ከመሆኑም በላይ ጠላት እዚያ ውስጥ ይገኛል›› ያሉት ዘለንስኪ በእነዚህ መሬቶች ላይ ህዝበ ውሳኔ ማካሄድ ምናልባትም ተቀባይነት ያለው መንገድ ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ በቃለምልልሳቸው ‹‹ማንም ሰው ሰላም ይፈልጋል፡፡ እኛም የምንፈልገው እውነተኛ ሰላም ነው፡፡›› በማለት ያስታወቁት ዘለንስኪ ይሁንና የሩሲያውን ፕሬዝደንት ፑቲንን ዩክሬይንን ስኬት የማይፈልጉ ናቸው ብለዋቸዋል፡፡
ሲቀጥሉም ‹‹ፑቲን ሰላም እንደሚፈልግ የሚገልፅ ቃል ለትራምፕ ሊናገር ይችላል፡፡ ነገር ግን ውሸቱን ነው›› ያሉት ዘለንስኪ ትራምፕ ከፑቲን ጋር ውይይት ከማድረግ ጎን ለጎን በማእቀብ ጫና ማድረግ እንዳለባቸውም ምክር ለግሰዋል፡፡ ጦርነቱን በተመለከተ ዩክሬይን ሽንፈት ገጥሟታል በሚለው ሀሳብ ላይ እንደማይስማሙ ያስታወቁት ዘለንስኪ ለዚህ አባባላቸውም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በጦርነቱ ሩሲያ በመሬት ላይ ሰፊ ድል ማግኘቷን በማመን ሲያብራሩም ‹‹በዚህ አመት ሩሲያዊያን 3 ሺህ ኪሎ ሜትር መሬታችንን ለመቆጣጠር 400 ሺ ወታደሮቻቸውን ሰውተዋል፡፡ በየወሩ 31 ሺ ሩሲያዊያን ሲገደሉ ነበር ማለት ነው›› ብለዋል፡፡
ዩክሬይን በአሜሪካ የአየር መቃወሚያና ጦር መሳሪያዎች ላይ የተመረኮዘች መሆኗን ገልፀውም ካለእነዚህ ድጋፍ አየሯን መከላከልም ሆነ በጦር ግንባር ማሸነፍ እንደማትችል ጠቁመዋል፡፡ ዘለንስኪ በመጪው አዲስ አመት 2026 ይህ ጦርነት ሊቆም ይችላል የሚል ግምት እንዳላቸው ገልፀው ለዚህም የሰጡት ምክንያት ለመጀመሪያ ጊዜ ሩሲያ የጦር ሀይሏን ማሳደግ ማቆሟን ነው፡፡
ባለፉት አመታት የሩሲያ ጦር ሀይል በየወሩ 43 ሺ ሰዎችን ይቀጥር እንደነበር አውስተው ባገባደድነው አመት ግን ይህ መቀየሩንም አስረድተዋል፡፡ ከፎክስ ኒውስ በቀጥታ ለፕሬዝደንት ፑቲን መልእክት እንዲያስተላልፉ የተጠየቁት ዘለንስኪ ሲመልሱ ‹‹እኔ በግሌ ፑቲንን የምመለከተው እንደጠላት ነው፡፡ ነገር ግን ተጨማሪ ግጭትን ለመግታት ውይይት አስፈላጊ ነው›› ብለዋል፡፡
21/12/2025
ከሞት ጋር የተደረገ የመጨረሻ ውይይት | አሳዛኝ እውነተኛ ታሪክ
🇺🇸🇪🇹 የመጥፋቴ ስጦታ - የሞት ሹክሹክታ | የሉሊት አወቀ እየሞቱ መሆኑን እያወቁ መኖር ታሪክ Life in America | Motivational Stories
Motivational and Inspiring Short Stories | Green Card Dv Lottery | Protected Status in US Life Style, News, Music,...
19/12/2025
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የዓለም ትኩረት በምስራቅ አውሮፓ እና በመካከለኛው ምስራቅ ግጭቶች ላይ ባረፈበት በዚህ ወቅት፣ በቀይ ባህር እና በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና "ድምጽ አልባ" ነገር ግን አደገኛ የሆነ ጂኦ-ፖለቲካዊ ሽግግር እየተካሄደ መሆኑን አፍሪካ ሪስክ ኮንትሮል የተሰኘ ተቋም ባወጣው አዲስ የስትራቴጂክ መረጃ ትንታኔ አስታወቀ።
ተቋሙ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ፤ የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት፣ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ውጥረት፣ እንዲሁም እየጨመረ የመጣው የአሜሪካ፣ የሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ የግብፅ፣ የኢራን፣ የሩሲያ እና የቻይና ጣልቃ ገብነት ከአሁን በኋላ እንደ ተናጠል ክስተቶች የሚታዩ አይደሉም። እነዚህ ጉዳዮች በአለም አቀፍ የንግድ መስመሮች፣ በወደብ ተደራሽነት እና በስትራቴጂካዊ ጥምረት ዙሪያ ወደሚያጠነጥን "አንድ ወጥ የሽኩቻ ስርዓት" እየተዋሃዱ መምጣታቸውን ትንታኔው አመላክቷል።
የቅርብ ጊዜ ክስተቶች ይህንን አደገኛ ሽግግር እንደሚያሳዩ ሪፖርቱ ጠቅሷል። የሳውዲ አረቢያ መንግስት ለዋሽንግተን ባቀረበው ጥሪ፣ የሱዳን ጦርነት እንደ ሩቅ የአፍሪካ ቀውስ ሳይሆን "የቀይ ባህር ደህንነት ስጋት" ተደርጎ እንዲወሰድና አሜሪካ ጣልቃ እንድትገባ መጠየቁ የለውጡ አንዱ ማሳያ ነው ተብሏል።
በተመሳሳይ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቅርቡ በፖርት ሱዳን ያደረጉት ከፍተኛ ጉብኝት፣ በዚህ ወሳኝ ወቅት ግልጽ የሆነ የፖለቲካ አሰላለፍን ያሳየ ነው ሲል ጥናቱ ገልጿል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ተደራሽነት እና በቀጠናዊ ተጽዕኖ ዙሪያ ካለባት ፍላጎት ጋር ተያይዞ ውስጣዊና ውጫዊ ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎች እያረፉባት መሆኑ ተጠቅሷል።
የቀይ ባህር መስመር ከፍተኛ ድርሻ ያለው የዓለም የኮንቴይነር ንግድ የሚተላለፍበት በመሆኑ፣ በሱዳን የሚፈጠር ግጭት ወይም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የሚፈጠር ስህተት የሚያስከትለው መዘዝ ከአፍሪካ ቀንድ የዘለለ እንደሆነ የARC ትንታኔ አመልክቷል። የአሁኑ ውጥረት በዓለም አቀፍ የመርከብ መስመሮች ላይ መስተጓጎልን፣ የኢንሹራንስ ወጪ መጨመርን እና የአቅርቦት ሰንሰለት መዘግየትን እያስከተለ ይገኛል።
የARC ትንታኔ በጥብቅ እንዳስጠነቀቀው፤ ቀጠናው ቀደም ሲል በየመን ወይም በሶሪያ እንደታየው ዓይነት "የውክልና ጦርነት" ባህሪያትን ማሳየት ጀምሯል። ይህም የውጭ ኃይሎች የአካባቢውን ተዋንያን በመጠቀም ፍላጎታቸውን የሚያስፈጽሙበት፣ ቀጥተኛ ያልሆነ ድጋፍ የሚሰጡበት እና ለረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ የበላይነት የሚፋለሙበት ሂደት ነው። እንዲህ ዓይነቱ ስርዓት አንዴ ስር ከሰደደ ለመቀልበስ አስቸጋሪ እና ዋጋ የሚያስከፍል እንደሚሆን ተጠቁሟል።
በመሆኑም ለኢንቨስተሮች፣ ለልማት አጋሮች እና ለፖሊሲ አውጪዎች የሚቀጥሉት ከ6 እስከ 18 ወራት ወሳኝ መሆናቸውን የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ በቀጠናው የነበረውን የቀድሞ መረጋጋት ታሪክ መሰረት ያደረጉ ውሳኔዎች አሁን እንደማይሰሩ አሳስቧል።
17/12/2025
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአፍሪካ ህብረትና ተመድ በሱማሊያ ለተሰማሩ ሰላም አስከባሪ ሀይሎች አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የሱማሊያ መንግስት፣ የአፍሪካ ህብረትና ተመድ ዛሬ በሰጡት የጋራ መግለጫ ለሱማሊያ ሰላም አስከባሪ ሀይሎች አፋጣኝ ድጋፍ መደረግ እንዳለበት አሳስቡ፡፡
እነዚህ ተቋማት ይህንን ማሳሰቢያ የሰጡት ‹‹የሱማሊያ ፀጥታ ሀይሎች ትረስት ፈንድ›› ዛሬ በሞቃዲሾ ይፋ በሆነበት ወቅት ነው፡፡ የሱማሊያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የተቋማቱ አመራሮች በተገኙበት በተሰጠው መግለጫ ላይ እንደተገለፀው ትረስት ፈንዱ የሱማሊያን የፀጥታ ዘመቻ ዘላቂ ማድረግ የሚያስችል ይሆናል፡፡
በመግለጫው ላይ እንደተገለፀው በሱማሊያ ውስጥ ለሚደረገው ሰላም የማስከበር ዘመቻ በወር ውስጥ ቢያንስ 540 ሜትሪክ ቶን ሬሽን፣ 180 ሺ ሊትር ነዳጅና 24 ሰአት ዝግጁ የሆነ የአውሮፕላን አምቡላንስ ያስፈልጋል፡፡ ይህም የሰላም አስከባሪው ወጪ በአንድ ወር ውስጥ ከሁለት ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሚሆን የተነገረ ሲሆን ከዚህ ቀደም ድጋፍ ያደረጉም ሆኑ አዳዲስ በጎ አድራጊዎች በትረስት ፈንዱ በኩል ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡
17/12/2025
(ዘ-ሐበሻ ዜና) "የሱዳንን ጦርነት ለማስቆም የአርኤስኤፍን የአቅርቦት ሰንሰለት መቁረጥ ያስፈልጋል" ሲሉ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተናገሩ፡፡ የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሱዳን ያለውን ጦርነት ለማስቆም የሚደረገው ጥረት የአርኤስኤፍን የአቅርቦት ሰንሰለት ከመቁረጥ መጀመር እንዳለበት አሳሰቡ፡፡
ለአርኤስኤፍ የጦር መሳሪያና ቅጥረኛ ወታደሮች በገፍ እየቀረቡለት በሱዳን ውስጥ ተኩ አቁም ለማድረግ መሞከር ‹‹ትርጉም የለሽ ነው›› ሲሉም ገልፀዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ ይህንን የገለፁት ባለፈው ሳምንት በሳኡዲ አረቢያ በነበሩበት ወቅት አል ታያር ከተሰኘው የአገሪቱ ጋዜጣ ጋር ባደረጉትና ዛሬ ለንባብ በበቃው ቃለምልልስ ነው፡፡
ከአልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር በነበራቸው ቆይታ በሱዳን ውስጥ ባለው ቀውስ፣ በአፍሪካ ቀንድ እየጨመረ በመጣው ወታደራዊ እንቅስቃሴና በቀይ ባህር ደህንነት ላይ ውይይት ማድረጋቸውን የተናገሩት ፕሬዝደንቱ ጨምረውም ‹‹የሱዳን ጦርነት እየተራዘመ የመጣው የውጭ ጣልቃ ገብነት በመኖሩ ነው›› ብለዋል፡፡
በዚህ ቃለ ምልልሳቸው ለተቀናቃኙ አርኤስኤፍ በጎረቤት አገራት በኩል በምድር፣ በባህርና በአየር ጦር መሳሪያዎችና ቅጥረኛ እየገቡ መሆኑን ያስታወቁት ፕሬዝደንት ኢሳያስ በዚህ የተነሳም በሱዳን ውስጥ የጅምላ ግድያ፣ የሴቶች ጥቃት፣ ዝርፊያና ሌሎችም ውድመቶች መከሰታቸው መቀጠሉን አስረድተዋል፡፡
ሲቀጥሉም ‹‹የሱዳን ቀውስ አሁን በተጀመረው አይነት ተነሳሽነት አይፈታም›› ያሉ ሲሆን አለም አቀፉ ማህበረሰብም ከተፋላሚዎቹ ለአንደኛው የሚደረገውን ወታደራዊ ድጋፍ ቸል ማለቱ ታማኝነቱን ጥርጣሬ ውስጥ እንደሚከተው አስታውቀዋል፡፡ ፕሬዝደንት ኢሳያስ በቃለምልልሳቸው ‹‹ሳኡዲ አረቢያ በአፍሪካ ቀንድና ቀይ ባህር አካባቢ ያለውን ውጥረት ለመፍታት ገለልተኛና ወሳኝ ሚና መጫወት ይገባታል፡፡ አመራሩም ትንንሽ የሚመስሉ ነገር ግን በቀጠናው ትልቅ አፍራሽ ሚና ያላቸውን አካላት ለመለየት ይኖርበታል›› ብለዋል፡፡
ከመሀመድ ቢን ሰልማን ጋር በነበራቸው ቆይታ በሱዳን ጉዳይ በቂ ቁጥጥር ያልተደረገባቸውን የውጫዊ ጣልቃ ገብነቶችን በተመለከተ በዝርዝር መወያየታቸውንም አስታውቀዋል፡፡
15/12/2025
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ትራምፕ በሶሪያ ለተገደሉት አሜሪካዊያን ‹‹ከባድ የበቀል እርምጃ ይወሰዳል›› አሉ፡፡ የአሜሪካ ማእከላዊ እዝ ትላንት ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ በሶሪያ ተሰማርተው የነበሩ 2 ወታደሮቹ መገደላቸውንና ሌሎች 3 ደግሞ መቁሰላቸውን አስታውቋል፡፡ ጥቃቱን የፈፀሙት ከአይኤስ ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች መሆናቸውንም አስረድቷል፡፡
የበሽር አልአሳድ መንግስት ከተወገደ ወዲህ በአሜሪካዊያን ላይ በሶሪያ እንዲህ አይነት ግድያ ሲፈፀም ይህ የመጀመሪያ ጊዜው ሲሆን በድርጊቱ የአሜሪካ ባለስልጣናት ከፍተኛ ቁጣቸውን ገልፀዋል፡፡
የፔንታጎን አለቃ የሆኑት ፔት ሄግሴት ድርጊቱን የፈፀሙትን ‹‹ጨካኝ›› በሚል ጠርተዋቸዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹በየትኛውም የአለም ክፍል ቢሆን አሜሪካዊያንን ኢላማ ካደረጋችሁ እድሜ ልካችሁን አሜሪካ እንደምታሳድዳችሁና በመጨረሻም እንደምትገድላችሁ እወቁት‹‹ ብለዋል፡፡
ፕሬዝደንት ትራምፕ በበኩላቸው ‹‹በሶሪያ ውስጥ 3 ታላላቅ አሜሪካዊያን አርበኞችን በማጣታችን እናዝናለን›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ጥቃቱ የተፈፀመበት አካባቢ እጅግ አደገኛ መሆኑን የገለፁት ትራምፕ በድርጊቱ የሶሪያው ፕሬዝደንት አህመድ ሻራ መቆጣታቸውና መረበሻቸውን አስረድተዋል፡፡ ለተፈፀመው ጥቃት ‹‹በጣም ከባድ የሆነ የበቀል እርምጃ ይኖራል›› ሲሉም ዝተዋል፡፡
13/12/2025
(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) የኢትዮጵያ ሙዚቃ የናፍቆትና የትዝታ ቋት... አንጀት አርስ ድምፃዊው ዳዊት መለሰ፤ የብዙዎችን ልብ በሰረቀውና "ምስጢር" በተሰኘው አዲሱ አልበሙ ታሪክ ሊሰራ፣ የቨርጂኒያ ሰማይ በጉጉት ደመና ተሞልቷል።
ለዘመናት በልዩ የድምፅ ቅላጼው የፍቅርን ጥልቀት... የትዝታን ስፋት ሲለካ የኖረው ይህ የሙዚቃ ፈርጥ፤ ነገ ቅዳሜ ዲሴምበር 13 ቀን 2025 ዓ.ም. በስፕሪንግ ፊልድ በሚገኘው በታዋቂው "ዋተር ፎርድ ኤቨንት ሴንተር" ታሪካዊ ምሽት ሊፈጥር ዝግጅቱን አጠናቋል።
ዳዊት መለሰ ለዘ-ሐበሻ እንደገለጸው፤ ይህ አልበም እንዲሁ የተዘፈነ ሳይሆን፣ የነፍስን ጥልቅ ስሜት የሚዳስስ፣ በምርጥ ዜማና ግጥም የተዋበ "ምስጢር" ነው። ታዲያ ይህ ምስጢር ነገ በይፋ በሙዚቃ ኮንሰርት ሲመረቅ፣ ምሽቱ በናፍቆት ሲጠበቅ የነበረው የዳዊት ድምፅ እንደ ወራጅ ውሃ የሚፈስበት እንደሚሆን ይጠበቃል።
ነገ የሚካሄደው ይህ የሙዚቃ ድግስ የዳዊት ብቻ አይደለም፤ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የከበሩ ማዕድናት የሚፈሱበትም ጭምር እንጂ!
የዳዊትን ጣፋጭ ዜማዎች በብቃት አጃበው የሙዚቃውን ጣዕም ወደ ከፍታ ለመስቀል ዝነኛው "ራስ ባንድ" መሳሪያውን ወልውሎ ዝግጁ ሆኗል። መድረኩን ይበልጥ ለማድመቅ ደግሞ፣ አድናቂዎቿ "የዘላለም ወጣት" የሚሏት ተወዳጅ ድምጻዊት ኩኩ ሰብስቤ፣ የአባቱ ልጅ ድምፃዊ ግርማ ተፈራ፣ እንዲሁም ተወዳጆቹ ፍጹም መሃድሬ እና እያደገ የመጣው ኮከብ ድምጻዊ አዲስ ሙላት ተካተዋል። ይህ ስብስብ ራሱ በዋሽንግተን ዲሲ፣ ሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ ምድር እምብዛም የማይገኝ የጥበብ ድግስ ነው።
የዚህ ታላቅ ምሽት በር ከምሽቱ 3፡00 (9:00 PM) ጀምሮ ይከፈታል። ዳዊት መለሰ የናፈቀውን ህዝብ ሊያገኝ፣ ህዝቡም በ "ምስጢር" አልበም ሊረካ ቀጠሮው ነገ ነው።
ቨርጂኒያ ለዚህ ታላቅ የሙዚቃ ካሊፕሶ ተዘጋጅታለች።
13/12/2025
አትደናገጡ፣ ለTPS ቪዛ መፍትሔ አለው | በአሜሪካ በTPS ያሉ የኢትዮጵያ የቀድሞ፡ባለስልጣናት አሳይለም ይከለከላሉ ወይ? - Life in America
Life Style, News, Music, Ethiopian Comedy, Ethiopian Wedding, and All Things Ethiopian Subscribe Here:Chebe Media | Senselet | Diaspora ...