Zobel media / ዞብል ሚዲያ

Zobel media / ዞብል ሚዲያ

Share

official Amanuel Belete page

Photos from Zobel media / ዞብል ሚዲያ's post 27/08/2026

ሻለቃ ሲሳይ አሸብር ወንድሞቹን ተቀበለ

አፋብን በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ 305ኛ ጎቤ ኮር
ከአንድ አመት የስራ ስምሪት ቆይታ በኃላ ወንድማማቾች ሲገናኙ ናፍቆታቸዉን ተቃቅፈዉ ሲገልፁ

ሻለቃ ሲሳይ አሸብር
አርበኛ ደራሲ አንተነህ ድረስ
አርበኛ ኢ/ር በየነ አለማዉ እና ሌሎች በወልቃይት ጠገዴ አርማጭሆ ዳዊ አዳኛገር ጫቆ መተማ ዮኃኒስ ጠያይሞቹ አንገት በጣሹቹ ዛሬ ፍቅር በፍቅር ሁነዋል ናፍቆታቸዉን ከፊታቸዉ ላይ ሲነበብ በዛሬቱ ቀን ነሐሴ 20/12/2018 ዓ.ም የሻለቃ ሲሳይ አሸብር ናፍቋቸዉ የከረሙትን ወንድሞቹን እጁን ዘርግቶ ሲቀበላቸዉ ሁሉም ደስታቸዉን መቆጣጠር አቅቷቸዉ በሚገርም ሁኔታ ደስታ ወደ እብድነት ይቀየራል እንዴ ሳቅና ፈገግታ ሲቃ ተጨምሮበት የተደበላለቀ ስሜት ይታይባቸዋል በቦታዉ የተገኘዉ አባሉ እና አመራሩ እስኪጨንቀዉ ድረስ ተፍነሸነሹ

ሻለቃ ሲሳይ አሸብር ብዙ ጊዜ በየ ሰዓቱ እየደዉለ እራሳችሁን ጠብቁ በማለት ሲጨነቅ ቆይቶ ዛሬ ከዛ ሁሉ ዉጣ ዉረድ አልፈዉ በአካል ወንድሞቹን ሲያገኛቸዉ ደስታቸዉ ወደር አልነበረዉ በተጨማሪ የኮርና የክፍለ ጦር አመራሮችና አባላት እንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አድርገዉላቸዋል።

የትግል መስራች ወንድሞቸ አንድነታችሁን አፅንታችሁ ይህ ብዙ ጀግና ወንድም ያጣችሁበት ትግል ለፍሬ በቅቶ ለማየት ያብቃች ደስታችሁ ይብዛላችሁ የናንተን ደስታ ስናይ የራበዉ ሆዳችን ይሞላል እንኳን ደስ አላችሁ ።

ህልዉናችን በተባበረዉ ክንዳችን

አርበኛ ባንዴራዉ ግርማይ ከ305ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ

ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም
ከትግል ሜዳ

14/08/2026

አንደኛው ተሸኝቷል ፣ 4ቱ እየተፈለጉ ነው !!

በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ አማራ በመሆናቸው ብቻ የፋኖ ደጋፊዎች ናችሁ ተብለው ከመኪና አስወርዶ የጥይት ናዳ ያዘነበባቸው ሰይጣን የብልፅግና ተላላኪ ፖሊስ በፋኖ እና በጉራጌ ዘርማ የደህንነት ኃይሎች የተቀናጀ ስራ ሆቴል በር ላይ ወደ ማይቀረው አለም ተሸኝቷል ።

Photos from Zobel media / ዞብል ሚዲያ's post 05/08/2026

በጀግኖቻችን ደም የተመሰረተውን አንድነታችንን እናጸናለን!

​ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ንስር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክፍለ ጦር አመራሮችና አባላት ሐምሌ 05/2018 ዓ.ም በተበሰረው የጎንደር አንድነት የተሰማቸውን ላቅ ያለ ደስታ የዕዝ አመራሮች በተገኙበት ገልጸዋል።

​ስለሆነም ለወደቁት ጀግኖቻችን ክብርና ለፈሰሰው ደም ስንል፣ ማንኛውም ዓይነት ቅሬታና ጥያቄ ቢኖር እንኳ ከወንድሞቻችን ጋር በአንድ ጥላ ስር፣ በገነባነው የአንድነት ቤት ውስጥ ሆነን በመወያየት መፍትሔ መስጠት እንደምንችል አጥብቀን እናምናለን ሲሉም አጋርተዋል።

​በቀን 28/11/2018 ዓ.ም ውይይት ያደረጉት አመራሮቹ፣ የጎንደርን አንድነት ለማምጣት በየግንባሩ የተከፈለው የወንድሞቻችን የሕይወት መስዋዕትነት እጅግ ከባድና ውድ በመሆኑ ይህን ማጽናት ደግሞ ታሪካዊ ግዴታችን ሊሆን ይገባል ያሉ ሲሆን፣ ለሚሰጠን ማንኛውም ግዳጅ ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን ብለዋል።

​በመሆኑም የጠላትን አጀንዳ በመሸከም ለግል ጥቅማቸው ሲሉ አንድነትን ለማፍረስ የሚታትሩና የሕዝቡን ትግል የሚጠልፉ ፀረ-አንድነት ግለሰቦች ድርጊታቸውን በአስቸኳይ ሊያቆሙ ይገባል ብለዋል።

​በውይይቱ የተገኙት የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ አመራሮች ለታላቁ የጎንደር ሕዝብና ላለፉት ጀግኖች የማይመጥኑ፣ ከየቁጥቋጦው ስር የሚሰጡ አደናጋሪ መግለጫዎች በአስቸኳይ ቆመው፣ ማንኛውም "ታጋይ ነኝ" የሚል አካል አለኝ የሚለውን ችግርና ጥያቄ በተገነባው ጠንካራ ቤትና መዋቅር ስር ብቻ ማቅረብ እንዳለበት አምኖ ወደ ቤቱ እንዲቀላቀል ሲሉ እናሳስባለን ብለዋል።

​ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!

Photos from Zobel media / ዞብል ሚዲያ's post 22/07/2026

Stop AMHRA genocide 🛑
july 21 London fano

Photos from Zobel media / ዞብል ሚዲያ's post 14/07/2026

የ ጎንደር ፍኖ ወደ አንድነት💪🏽💪🏽💪🏽

11/07/2026

🛑 stop Amhara genocide

23/06/2026

የጀግኖቹ የመጨረሻ ስንብት !

''እናንተ ውጡ እኛ መውጣት አንችልም፤ ከቻልን ጠላትን ተራምደነው እንመጣለን፣ ካልሆነም እንደ ቴዎድሮስ እርሳሳችንን ጠጥተን እንሰዋለን'' የጎንደርን ትግል ግን አደራ ..

አማራ በሁሉም ግንባር የህልውና ትግል በሚደርግበት፣ እያንዳንዱ ሰው ነፍሱን ለማዳን በሚሯሯጥበት በዚያች የጭንቅ ሰዓት... እነ አማረ አቸንፍ፣ እነ ሳምሶን አማረ እና መቶ አለቃ አበረ አግማስ ግን ለጎንደር አማራ በክብር ቆሙ።

የብልፅግና ታንክ እና የዲሽቃ እሩምታ ሰማዩን ሲያናውጠው፣ የክህደት መረቡ በዙሪያቸው ሲያንዣብብ እየተመለከቱ ወደ ኋላ አላፈገፈጉም።

ፊታቸውን ወደ ጠላት፣ ልባቸውን ወደ ወገን አድርገው ስናይፐራቸውን ከደረታቸው ደግነው የመጨረሻዋን የነፃነት ስጦታ ለጓዶቻቸው አበረከቱ።

መውጣት እየቻሉ ''እናንተ ውጡ፣ እኛ መውጣት አንችልም'' አሉ። ይህ ቃል የሽንፈት አልነበረም፤ የሞት ድል ነሸነት የቴዎድሮስ ልጅ የመሆን ማረጋገጫ እንጂ ..

የጎንደርን አንድነት ለማወጅ እና የሕዝብን ነፃነት ለማስከበር ደፋ ቀና ሲሉ የነበሩት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በላይ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች ለጥቃት የተጋለጡት በውስጥ ባንዳዎች በተደረገ ጥቆማ እና ክህደት ነው።

አርበኛ አማረ አቸንፍን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ያሉበትን መሬት ላይ ያለ መረጃ በመጠቆም ከበባው እንዲፈፀም ያደረገው ፀረ-ጎንደር የሆነው የኦህዴድ ክንፍ እና ከእርሱ ጋር የተናበቡ የውስጥ ባንዳዎች ናቸው።

ጀግኖቹ አርበኞች ህይወታቸው ከማለፉ በፊት "እናንተ ውጡ፣ እኛ መውጣት አንችልም" በማለት ጓዶቻቸውን ተሰናብተው ከከበባቸው የጠላት ኃይል ጋር ፊት ለፊት ተናንቀው በሞታቸው የጓዶቻቸውን ሕይወት አትርፈው በግብር ቴዎድሮስን ሆነው አልፈዋል።

ጥቃቱ የተከፈተው ከጎንደር አዘዞ በልዩ ሁኔታ በተነሳ 3 ቢጫ ኦራል ሙሉ የጦር ኃይል እና በዙሪያው ከሚገኝ ወታደራዊ ሰራዊት በተውጣጣ ስምሪት መሆኑም ተረጋግጧል።

አርበኞቹ ለሕዝብ አንድነት መስዋዕት በሆኑበት ወቅት ቤተኛ የብአዴኑ ክንፍ እና ፖለቲካ ሞዐ'ው ተናበው ጀግኖችን እንዴት እንደሚያስበሉ አስቀድመው እቅድ ሲያወጡ እንደነበር ተጋልጧል።

ይህ ቡድን ራሱ ያስመታቸውን፣ በሴራ እና በጥቆማ ያስገደላቸውን አርበኞች አሳቢ እና ለጎንደር የሚጨነቅ መስሎ መድረክ ላይ የሚተውን አደገኛ ኃይል ነው።

የአርበኞችን ሞት ለፖለቲካ እና ለውስጥ ጥቅማጥቅም መነገጃ ያደረገው ይህ ስብስብ ትግሉን ተሸናፊ ለማድረግ እና ለመበተን ተልዕኮ ወስዶ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው።

ጎንደር በአሁኑ ወቅት በጠላቶቿም ሆነ ወንበር በናፈቃቸው የውስጥ ባንዳዎች የምትከፍለው መከራ በዚህ መንገድ አይቀጥልም።

ጎንደር ዛሬ ዋጋ ያስከፈሏትን የውስጥ እና የውጭ ጠላቶች ሁሉ በታሪክ መዝግባ ትይዛለች፣ ነገ ግን ለሴረኞች ሁሉ ተገቢውን ብድሯን ትከፍላለች።

የውስጥ ባንዳዎች የጠላት መንገድ መሪዎች ናቸው። ታሪክ ግን ክህደትንም ጀግንነትንም እኩል መዝግቦ ይይዛል።

የአንበሳን መውደቅ አይቶ ጅብ አይሳቅ፣ አንበሳ ቢወድቅም ያው አንበሳ ነው።

ወንድሞቼ ነፍሳችሁ በሰላም ትረፍ!

"My brother, you were a hero, you were brave. You made the ultimate sacrifice for the Amhara people and the people of Gonder. The people of Amhara and Gonder will always remember you for what you did. May your soul rest in peace."

04/06/2026

😭😭😭የአርሲ ክርስቲያኖች ስደት😭😭😭
+የተወለዱበትን ቦታ ትተው
+የሰሩት ቤታቸው ተቃጥሎባቸው
+የሚያመልኩበት ክርስትና የተነሱበት ሲሞቱ የሚቀበሩበት ቤተ ክርስቲያናቸው ተቃጥሎባቸው
+ዘመዶቻቸው ተገድለውባቸው
በአንድ ጊዜ 4 ነገር አጥው እየተሰደዱ ነው
1 መኖሪያ ቤታቸውን
2,ማምለኪያ ቤተ ክርስቲያኖቸውን
3 የኖሩበት ሰፈራቸውን
4 የሚያውቋቸው ወገኖቻቸውን አጥተው
ስደት ላይ ናቸው
የራሄልን እንባ ያበሰ አምላክ እንባቸውን ያብስልን

04/06/2026

🚨

Photos from Zobel media / ዞብል ሚዲያ's post 01/06/2026

204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር
ከሌሎች አጋር ኮሮች ጋር በመሆን!
💪እብናት
💪 አዲስ ዘመን
💪 ደብረታቦር

ዳስ እያስጣለ ነው!!
አቤት ወንድማማችነት
አቤት መናበብ

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Gondar?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Gondar