01/23/2024
#ስፖርት #ነፍስይማር #ኢትዮጵያ #ዜና 😥💐
ስመ ጥሩ ጋዜጠኛ ባደረበት ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ማክሰኞ ጥር 14/2016 ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።
ገነነ መኩሪያ ይሠራበት የነበረው 'አሻም' የተሰኘው የቴሌቪዥን ጣቢያ የጋዜጠኛውን ሕልፈተ-ሕይወት በፌስቡክ ገፁ አረጋግጧል።
አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) በአሻም ቴሌቪዥን “የገነነ” እና “ጥቁር እንግዳ” የተሰኙ ፕሮግራሞችን አዘጋጅ እና አቅራቢ ሆኖ እንዳገለገለ ጣቢያው ገልጧል።
ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ለበርካታ ዓመታት ለተለያዩ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ተወዳጅ የሆኑ ዝግጅቶችን በማቅረብ ሠርቷል።
ገነነ መኩሪያ እግር ኳስ እና ፖለቲካን እንዲሁም ታሪክን የሚዳስሱ በርካታ መጽሐፎችን ያሳተመ ሲሆን፣ “ኢሕአፓ እና ስፖርት” እና ሌሎች መፃሕፍትን ለአንባቢ አቅርቧል።
ሊብሮ ከስፖርት ጋዜጠኝነት ሕይወት ባሻገር በወጣትነት ዘመኑ ለበርካታ የእግር ኳስ ክለቦች በመሠለፍ ተጫውቷል።
የመንግሥት ባለሥልጣናትን ጨምሮ የሙያ ባልደረቦቹ እና ታዋቂ ሰዎች በሊብሮ ሕልፈተ ሕይወት ሐዘናቸውን እየገለጡ ነው።
-አማርኛ
07/17/2023
06/07/2018
11/17/2017
07/07/2016
06/27/2016