BizuAthletics

BizuAthletics Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from BizuAthletics, Sport & recreation, Toronto, ON.

ብዙአትሌቲክስ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ላይ በማተኮር የሀገር ውስጥና የውጭ ውድድሮችን እና ተዛማጅ ዜናዎችን የሚያቀርብ ድህረ ገጽ ነው።
BizuAthletics is news website that provides coverage of both local and international competitions, and athletics related news with a special focus on Ethiopian athletics.

የዓለም አትሌቲክስ ደረጃዎች ለውጥ፡- ትግስት አሰፋ በሴቶች አጠቃላይ ደረጃ ወደ አምስተኛ ደረጃ ከፍ ብላለች፡፡በዓለም አትሌቲክስ ደረጃዎች (World Rankings) የአጠቃላይ ደረጃ እስከ ...
10/01/2026

የዓለም አትሌቲክስ ደረጃዎች ለውጥ፡- ትግስት አሰፋ በሴቶች አጠቃላይ ደረጃ ወደ አምስተኛ ደረጃ ከፍ ብላለች፡፡

በዓለም አትሌቲክስ ደረጃዎች (World Rankings) የአጠቃላይ ደረጃ እስከ ሴፕቴምበር 29-2026 ድረስ በተመዘገቡ ደረጃዎች በበርሊን ማራቶን አስደናቂ ውጤት ያስመዘገበችው ኢትዮጵያዊቷ ትግስት አሰፋ በሴቶች አጠቃላይ ደረጃ ከአስራ አንደኛ ወደ አምስተኛ ደረጃ ከፍ ለማለት በቅታለች። በበርሊን ማራቶን ሁለተኛ የወጣችው ኢትዮጵያዊቷ በዳቱ ሂርጳ በማራቶን ሴቶች ከ25ኛ ወደ 10ኛ ደረጃ ስትሸጋገር፣ የወንዶች የበርሊን ማራቶን አሸናፊው ጉዬ አዶላ ደግሞ በማራቶን ወንዶች ከ27ኛ ወደ 7ኛ ደረጃ ከፍ ብሏል።

በ2026 ቫሌንሲያ ግማሽ ማራቶን ላይ ስድስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይሳተፋሉ፡፡ የውድድሩ አዘጋጆቸ ይፋ ባደረጉት ስም ዝርዝር መሰረት በቫሌንሲያ ግማሽ ማራቶን ላይ በሴቶች አራት በወንዶች ...
10/01/2026

በ2026 ቫሌንሲያ ግማሽ ማራቶን ላይ ስድስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይሳተፋሉ፡፡

የውድድሩ አዘጋጆቸ ይፋ ባደረጉት ስም ዝርዝር መሰረት በቫሌንሲያ ግማሽ ማራቶን ላይ በሴቶች አራት በወንዶች ሁለት በድምሩ ስድስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይሳተፋሉ፡፡ እ.ኤ.አ. ዕሁድ ኦክቶበር 25 ቀን 2026 ዓ.ም. በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ የሚሳተፉት ኢትዮጵያውያን በሴቶች ያለምዘርፍ የኋላው፣ ፅጌ ገብረሰላማ፣ ፍታው ዘራይ፣ እና ሚዛን አለም፤ በወንዶች ጀማል ይመር እና ታደሰ ወርቁ ናቸው፡፡

Medio Maratón Valencia

ኢትዮጵያውያኑ ግዜአለው አያና እና ማሪቱ ከተማ በ2026ቱ የቲሲኤስ ቶሮንቶ ዋተርፍሮንት ማራቶን ላይ ይሳተፋሉ::የማራቶን ሯጮች የሆኑት ኢትዮጵያውያኑ ግዜአለው አያና በወንዶች እና ማሪቱ ከተ...
09/29/2026

ኢትዮጵያውያኑ ግዜአለው አያና እና ማሪቱ ከተማ በ2026ቱ የቲሲኤስ ቶሮንቶ ዋተርፍሮንት ማራቶን ላይ ይሳተፋሉ::

የማራቶን ሯጮች የሆኑት ኢትዮጵያውያኑ ግዜአለው አያና በወንዶች እና ማሪቱ ከተማ በሴቶች፣ እ.ኤ.አ በኦክቶበር 18 ቀን 2026 በሚካሄደው የቲሲኤስ ቶሮንቶ ዋተርፍሮንት ማራቶን ውድድር ላይ ይሳተፋሉ። በውድድሩ አዘጋጆች እንደተገለጸው ሁለቱም በቶሮንቶ በሚካሄደውና የዓለም አትሌቲክስ ‹‹Elite Label›› ደረጃ ባለው የማራቶን ውድድር ላይ ብርቱ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብለው ከሚጠቀሱት አትሌቶች መካከል ናቸው።

ከሁለት ዓመት በፊት ያስመዘገበውን የስድስተኛነት ደረጃ ስለማሻሻል እና አሸናፊ ስመሆን እያለመ ወደ ቶሮንቶ የሚመለሰው ግዜአለው

ግዜአለው አያና ዘንድሮ በቶሮንቶ ማራቶን ላይ ለመወዳደር የሚመለሰው ከሁለት ዓመት በፊት በውድድሩ ላይ ያስመዘገበውን ስድስተኛ ደረጃ ለማሻሻል በማለም ነው፡፡ በዘንድሮው የውድድር ዓመት እስካሁን ባደረጋቸው ሁለት የማራቶን ውድድሮች በኦታዋ ማራቶን ላይ ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀ ሲሆን በየካቲት ወር መጀመሪያ ላይ በዱባይ 2:06:48 የሆነ የግል ምርጥ ሰዓት ማስመዝገብ ችሏል፡፡ ወደ ቶሮንቶ የሚመጣውም በጥሩ የአካል ብቃት ደረጃ ላይ ሆኖ ነው። በአሰልጣኝ ንጋቱ ወርቁ የሚሰለጥነው እና ልምምዱን ከባህር ወለል በላይ ከ2,300 –2,500 ሜትር ከፍታ ላይ እያደረገ የሚገኘው ግዜአለው የውድድሩ አሸናፊ መሆንን ዋነኛ ግቡ አድርጓል። በሴቶች ውድድር የምትሳተፈውንና እንዲሁ በአሰልጣኝ ንጋቱ ወርቁ የምትሰለጥነውን አይንአዲስ ተሾመን ጨምሮ፣ በርካታ ጠንካራ የኢትዮጵያ አትሌቶችም በቶሮንቶ ከእሱ ጋር እንደሚፎካከሩ አዘጋጆቹ ጠቁመዋል።

በአሸናፊነት ማጠናቀቅን እና የውድድር ቦታውን ክብረወሰን ማሻሻል ግቧ ያደረገችው ማሪቱ ከተማ

በሴቶቹ ውድድር የምትሳተፈው ማሪቱ ወደ ውድድሩ የምትመጣው የማሸነፍ እና የውድድሩን ክብረ ወሰን የመስበር ዓላማን አንግባ ነው፡፡ በዘንድሮው ዓመት መጀመሪያ ላይ በዱባይ ባደረገችው ውድድር የግል ምርጥ ሰዓቷን በከፍተኛ ሁኔታ በማሻሻል 2:21:52 ማስመዝገብ ችላለች፡፡ ምቹ ሁኔታዎች ከተሟሉላት ውድድሩን ወደ 2:18:40 አካባቢ በሆነ ሰዓት ማጠናቀቅ እንደምትችልም ታምናለች፡፡ ይህም ማለት አሁን ካለው የቶሮንቶ ዋተርፍሮንት ማራቶን ውድድር ክብረ ወሰን (2:20:44) በእጅጉ የተሻለ ሰዓት የሚሆን ነው።

በአዲስ አበባ በታዋቂው አሰልጣኝ ገመዱ ደደፎ ስር በሚሰለጥነው ቡድን ውስጥ እንደ ትግስት አሰፋ እና የቶሮንቶ ዋተርፍሮንት ማራቶን የሶስት ጊዜ አሸናፊ ከሆነችው ሹሬ ደሚሴ ካሉ ምርጥ አትሌቶች ጋር የምትለማመደው ማሪቱ በተከታታይ ካጋጠሟት ጉዳቶች በኋላ ከ3000 ሜትር መሰናክል ሩጫ ወደ ማራቶን ውድድር ያደረገችው ሽግግር አስደናቂ ነው። ጠንካራ ተወዳዳሪዎች በሚሳተፉበት በቶሮንቶው ውድድር ላይ ትኩረቷ ምርጥ ብቃቷን በማሳየት አዲስ የግል ምርጥ ሰዓት ማስመዝገብ ላይ መሆኑንም ማሪቱ ለአዘጋጆቹ ገልጻለች።

The Ethiopians Gizealew Ayana and Maritu Ketema will participate in the 2026 TCS Toronto Waterfront Marathon.

According to information released by the race organizers, Gizelaw Ayana (men's category) and Maritu Ketema (women's category) are among the other Ethiopian athletes who will participate in the TCS Toronto Waterfront Marathon, scheduled for October 18, 2026.

Ayana returns to Toronto with the goal of improving on her sixth-place finish two years ago and becoming a winner.

Ethiopian marathoner Gizealew Ayana is returning to compete in this year’s Toronto Marathon, aiming to improve on the sixth-place finish he recorded in the race two years ago. In the two marathons he has contested this season, Ayana finished second at the Ottawa Marathon and set a personal best of 2:06:48 in Dubai in early February. Coached by Nigatu Worku and training at elevations of 2,300–2,500 metres above sea level, Gizealew is expected to arrive in Toronto in strong physical condition, with victory his primary objective.

Maritu Ketema Targets Victory and Toronto Waterfront Course Record

Maritu, a participant in the women's race, is entering the competition with the aim of winning and breaking the event record. Earlier this year, she significantly improved her personal best time to 2:21:52 at a race in Dubai. She believes that, given favorable conditions, she can complete the race in approximately 2:18:40, a time that would be substantially faster than the current Toronto Waterfront Marathon record (2:20:44).

Maritu, who trains in Addis Ababa under renowned coach Gemedu Dedefo alongside elite athletes like Tigst Assefa and three-time Toronto Waterfront Marathon winner Shure Demise, has made a remarkable transition from the 3,000m steeplechase to the marathon following a series of injuries. She has told the race organizers that her focus for the Toronto event, which features a strong field of competitors, is to deliver a top-tier performance and set a new personal best time.

09/29/2026
ትግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን ላይ በደረሰባት ጉዳት ምክንያት በሙኒክ የአኪሊስ ጅማት ቀዶ ጥገና ታደርጋለች።ትግስት አሰፋ በቀኝ እግሯ ላይ የባት ጡንቻዎችን ከቁርጭምጭሚት አጥንት ጋር የሚያ...
09/28/2026

ትግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን ላይ በደረሰባት ጉዳት ምክንያት በሙኒክ የአኪሊስ ጅማት ቀዶ ጥገና ታደርጋለች።

ትግስት አሰፋ በቀኝ እግሯ ላይ የባት ጡንቻዎችን ከቁርጭምጭሚት አጥንት ጋር የሚያገናኘው ጠንካራ የሕብረ ሕዋስ ማሰሪያ የሆነው የአኪሊስ ጅማት በከፊል መላቀቅ (Achilles tendon partial rupture) ጉዳት ስላጋጠማት ነገ በሙኒክ ቀዶ ጥገና ታደርጋለች።
በውድድሩ ላይ ያገጠማት የቀኝ እግር አኪለስ ጅማት በከፊል የመላቀቅ ጉዳት የዓለም ሪከርድ ፍጥነቷን አሰናክሎ ከውድድሩ በኋላ በድንገተኛ በረራ ለሕክምና ወደ ሙኒክ እንድታመራ አስገድዷታል።

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት በ2026 በርሊን ማራቶን አብዛኛውን የውድድሩን ክፍል የዓለም ክብረ ወሰንን መስበር (ከ2:09:56 በታች መግባት) በሚያስችል ፍጥነት ስትሮጥ ቆይታለች። ሆኖም በውድድሩ የመጨረሻ ክፍል ባጋጠማት በዚህ ጉዳት ምክንያት ፍጥነቷ በመቀነሱ ውድድሩን በ2:11:04 ሰዓት ለማጠናቀቅ ተገዳለች። በውድድሩ መጨሻ አካባቢ የገጠማትን ከባድ ጉዳት በአስደናቂ ጽናት ተቋቁማ ያሸነፈችበት መንገድም እጅግ የሚያስገርም ነበር።

የአትሌቷ ማናጀር ጂያኒ ዴማዶና ስለገጠማት ጉዳት ለ Pura Vida Sports Africa በሰጡት ልዩ መረጃ፤ የቀኝ እግሯ አኪለስ ጅማት በከፊል መላቀቁን እና ከውድድሩ በኋላ የቀዶ ጥገና ህክምና ለማድረግ በአስቸኳይ ከበርሊን ወደ ሙኒክ እንደተላከች ጠቅሰው “ነገ (ሰኞ) በሙኒክ በአዲዳስ ሙሉ ድጋፍ በጀርመን ካሉ ምርጥ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች አንዱ በሆኑት በዶክተር ዮሃንስ ጋቤል አማካኝነት ቀዶ ጥገና ይደረግላታል” ብለዋል።

አትሌቷ በ52ኛው የቢኤምደብሊው በርሊን ማራቶን ላይ የዓለም ክብረወሰን በመስበር ታሪካዊ ድል ለማስመዝገብ ያደረገችው ሙከራ በደረሰባት ጉዳት ምክንያት በአሳዛኝ ሁኔታ ተስተጓጉሏል። ምንም እንኳን በ2፡11፡04 ሰዓት አንደኛ ወጥታ በመጨረሻ መስመሩ ላይ በጀግንነት መውደቋም ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት ቢሆንም፣ የውድድር ዘመኗ ትልቁን ግብ ልታሳካ ከጫፍ ደርሳ በጉዳት ምክንያት የመሰናከሏ አስከፊ እውነታም በአሉታዊ መልኩ መታወሱ የማይቀር ነው። ከቀዶ ጥገናው በኋላ የሚኖረው የማገገም ሂደት ከስፖርቱ ለስድስት ወራት ያህል ሊያርቃት እንደሚችል ተጠቁሟል።

ለትግስት አሰፋ ስኬታማ ቀዶ ጥገና፣ ፈጣን የማገገም ሒደት እና በጠንካራ ብቃት ዳግም ወደ ውድድር ጎዳና መመለስን እንመኛለን።

Tigst Assefa will undergo Achilles tendon surgery in Munich due to an injury at the Berlin Marathon.

Tigist Assefa is scheduled to undergo surgery in Munich tomorrow (Monday) due to a partial tear in her right Achilles tendon (the strong tissue connecting the calf muscles to the heel bone). The injury, sustained during the 52nd BMW Berlin Marathon, abruptly halted her pursuit of a world-record pace and necessitated her travel to Munich for urgent medical attention immediately after the race.

During today’s (Sunday) Berlin Marathon, the Ethiopian athlete ran most of the race at a pace that would have allowed her to break the world record (finishing under 2:09:56). However, due to the injury sustained in the final stages of the race, her pace slowed, forcing her to finish with a time of 2:11:04. The way she overcame the severe injury she sustained near the end of the race with remarkable resilience was truly extraordinary.

Speaking exclusively to Pura Vida Sports Africa about the injury, the athlete's manager, Gianni Demadonna, indicated that she had suffered a partial tendon tear in her right leg and had been urgently transferred from Berlin to Munich for surgery. He stated, "Tomorrow (Monday), she will undergo surgery in Munich, with the full support of Adidas, performed by Dr. Johannes Gabel, one of Germany's top surgeons."

The injury tragically thwarted the athlete's attempt to achieve a historic victory by breaking the world record at the 52nd BMW Berlin Marathon. Although she finished first in 2:11:04, heroically collapsing at the finish line, the bitter reality remains that the injury derailed her season just as she neared her goal. Indications suggest that the post-surgery recovery process could sideline her from the sport for approximately six months.

We wish Tigist Assefa a successful surgery, a speedy recovery, and a strong return to competition.



📸 Demadonna Athletic Promotions

በስፔን ማዮርካ በተካሄደው የፖየንሳ የሩጫ ፌስቲቫል የወንዶች 5 ኪሎ ሜትር ፉክክር ኢትዮጵያውያኑ አዲሱ ይሁኔ (13:18) እና ገመቹ ጎዳና (13:18) አንደኛ እና ሁለተኛ በመሆን አጠናቀዋ...
09/27/2026

በስፔን ማዮርካ በተካሄደው የፖየንሳ የሩጫ ፌስቲቫል የወንዶች 5 ኪሎ ሜትር ፉክክር ኢትዮጵያውያኑ አዲሱ ይሁኔ (13:18) እና ገመቹ ጎዳና (13:18) አንደኛ እና ሁለተኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡



📷 .com

በትላንትናው ዕለት (ቅዳሜ ሴፕቴምበር 26/2026) በጣልያን ትሬንቶ በተካሄደው የጂሮ አል ሳስ የወንዶች 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያዊው ጥላሁን ሀይሌ ሶስተኛ በመሆን አጠናቋል፡፡    ...
09/27/2026

በትላንትናው ዕለት (ቅዳሜ ሴፕቴምበር 26/2026) በጣልያን ትሬንቶ በተካሄደው የጂሮ አል ሳስ የወንዶች 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያዊው ጥላሁን ሀይሌ ሶስተኛ በመሆን አጠናቋል፡፡



🥇 የማነብርሀን ክሪፓ 🇮🇹 28:09
🥈 ብሪያን ኪፕምዌቲች 🇰🇪 28:24
🥉 ጥላሁን ሀይሌ በቀለ 🇪🇹 28:34

📷 Demadonna Athletic Promotions

የ2026ቱ የበርሊን ማራቶን የኢትዮጵያውያን የበላይነት እጅግ ጎልቶ የታየበት ውድድር ነው፡፡  በወንዶቹ ምድብ ከመጀመሪያዎቹ 10 አሸናፊዎች መካከል 8ቱ፣ እንዲሁም በሴቶቹ ምድብ ከመጀመሪያዎ...
09/27/2026

የ2026ቱ የበርሊን ማራቶን የኢትዮጵያውያን የበላይነት እጅግ ጎልቶ የታየበት ውድድር ነው፡፡
በወንዶቹ ምድብ ከመጀመሪያዎቹ 10 አሸናፊዎች መካከል 8ቱ፣ እንዲሁም በሴቶቹ ምድብ ከመጀመሪያዎቹ 10 አሸናፊዎች መካከል 7ቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው። በሽልማት መድረኩ ላይ ለመቆም ከኢትዮጵያውያን ውጪ ቦታ ያገኘው ብቸኛው አትሌትም በወንዶቹ ምድብ ሶስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው የታንዛኒያው ጋብርኤል ጄራልድ ብቻ ነው።



📸 World Athletics and BERLIN-MARATHON

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የነገሱበት የ2026 በርሊን ማራቶን በትግስት አሰፋ (2:11:04) እና ጉዬ አዶላ (2:02:50) አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ የሴቶቹ አሸናፊ ትግስት 40ኛውን ኪሎ ሜትር...
09/27/2026

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የነገሱበት የ2026 በርሊን ማራቶን በትግስት አሰፋ (2:11:04) እና ጉዬ አዶላ (2:02:50) አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

የሴቶቹ አሸናፊ ትግስት 40ኛውን ኪሎ ሜትር ስታልፍ የዓለም ክብረ ወሰኑን በ12 ሰከንዶች የሚቀድም ሰዓት ማስመዝገብ በምትችልበት ሁኔታ እየሄደች የነበረ ቢሆንም በመጨረሻው ኪሎ ሜትር እያነከሰች ለመሮጥ ተገዳ ነበር። ያም ሆኖ ወደ መጨረሻው መስመር ጉዞዋን አላቋረጠችም፡፡ ባሳየችው ጽናትም ውድድሩን የግሏ ምርጥ እና የውድድር ቦታው ሪኮርድ በሆነ 2:11:04 ሰዓት በማጠናቀቅ አሸናፊ ሆናለች፡፡ ትግስት በበርሊን ያሸነፈችበት ሰዓት በሴቶች ማራቶን ታሪክ የምንግዜም ሦስተኛው ፈጣን ሆኖ የሚመዘገብም ነው።

በበርሊን ማራቶን ሁለተኛ ድሉን ያስመዘገበው ጉዬ አዶላ ሶስተኛ አስደናቂ አፈጻጸምን አሳይቶ አሸንፏል። እ.ኤ.አ. በ2017 የመጀመሪያ የማራቶን ውድድሩን በበርሊን ሲያደርግ አስደናቂ ብቃት በማሳየት ዓለም አቀፍ እውቅናን አግኝቷል፤ በዛ ውድድር ላይ የወቅቱን የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት ኤሊዩድ ኪፕቾጌን በቅርበት በመፎካከር 2:03:46 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። በ2021 ወደ በርሊን ተመልሶም በሞቃታማ የአየር ሁኔታ ውስጥ 2:05:45 በሆነ ሰዓት አሸናፊ ሆኗል። በዛሬው ወድድር ላይም በመጨረሻዎቹ ሰባት ኪሎ ሜትሮች ከሌሎች ተወዳዳሪዎች ተነጥሎ በመውጣት 2:02:50 በሆነ ፈጣን ሰዓት ሁለተኛውን የበርሊን ማራቶን ድሉን ለማስመዝገብ በቅቷል።

ዕሁድ መስከረም 17/2019 በሚካሄደው የ2026 በርሊን ማራቶን ላይ 20 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይወዳደራሉ፡፡የ2026 በርሊን ማራቶን አዘጋጆች ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ከ84,000 በላይ...
09/25/2026

ዕሁድ መስከረም 17/2019 በሚካሄደው የ2026 በርሊን ማራቶን ላይ 20 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይወዳደራሉ፡፡

የ2026 በርሊን ማራቶን አዘጋጆች ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ከ84,000 በላይ ሯጮችን በማሳተፍ ክብረ ወሰን ለሚሰብሩበት ሳምንት ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል። እሁድ ሴፕቴምበር 27/2026 በሚካሄደው ዋናው የማራቶን ውድድር ላይ 20 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይወዳደራሉ፡፡ ከ56,000 በላይ ሯጮች በማራቶን ውድድሩ ላይ ብቻ የሚሳተፉበት የበርሊን ማራቶን፣ ከዋና ዋና ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድሮች አንዱ ነው።

በዘንድሮው የበርሊን ማራቶን ላይ ከሚወዳደሩት ታዋቂ አትሌቶች መካከል ኢትዮጵያውያን እንስት አትሌቶች ትልቅ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል። ትግስት አሰፋ እ.ኤ.አ. በ2023 በዚህ ውድድር ላይ 2:11:53 በሆነ ጊዜ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግባ የነበረ ሲሆን፣ ዘንድሮም በድጋሚ የዓለም ክብረ ወሰኑን መልሳ ስለመያዝ በማለም ወደ በርሊን አቅንታለች። ለዘንድሮው የበርሊን ውድድር በደንብ መዘጋጀቷን እና የግል ምርጥ ሰዓቷን ለማሻሻል ማቀዷንም ትናገራለች፡፡ የበርሊን ውድድር አዘጋጆችም በውድድራቸው ላይ 14ኛውን የዓለም ክብረ ወሰን ሲሰበር ለማየት ተስፋ ያደርጋሉ። ከ2:19 በታች የሆነ የግል ምርጥ ሰዓት ያላቸው ኢትዮጵያውያኑ በዳቱ ሂርጳ፣ ዴራ ዲዳ እና ዘይነባ ይመር የትግስት የቅርብ ተፎካካሪ እንደሚሆኑም ይጠበቃል፡፡ የትግስት የልምምድ አጋር እና የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ታምራት ቶላ ባለቤት የሆነችው ዴራ ዲዳ ስለውድድሩ ለአዘጋጆቹ "እርግጥ ነው፣ እርስ በርስ በደንብ እንተዋወቃለን፤ ጠንካራ ብቃት እናሳያለን ብዬም እጠብቃለሁ" ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች።

ያለፈው ዓመት አሸናፊነት ክብሯን ለማስጠበቅ የምትወዳደረው ኬንያዊቷ ሮዝሜሪ ዋንጂሩ፣ የግል ምርጥ ሰዓቷን ከ2:16:14 ወደ ከ2:15 በታች ዝቅ የማድረግ ዕቅድ ይዛ ከኢትዮጵያውያኑ ጋር ትፎካከራለች። የበርሊን ማራቶን የሴቶች ተወዳዳሪዎች ዝርዝር እጅግ ጠንካራ አትሌቶችን ያካተተ ሲሆን፣ ሰባት አትሌቶች ከ2:20 በታች እና 13 አትሌቶች ደግሞ ከ2:22 በታች የሆነ የግል ምርጥ ሰዓት ያላቸው ናቸው።

የወንዶቹ ውድድርም አሸናፊውን ለመተንበይ የሚያስቸግር እና ከፍተኛ ፉክክር የሚታይበት እንደሚሆን ይጠበቃል። በጉዳት ምክንያት እራሱን ከውድድሩ ያገለለው የአለም ክብረ ወሰን ባለቤቱ ሴባስቲያን ሳዌ በክብር እንግድነት ይገኛል፡፡ ሳዌ በሌለበት ውድድር ላይ ፉክክሩን በበላይነት ለመጨረስ የሚያስችል ብቃት ያላቸው ቢያንስ ስድስት አትሌቶች እንዳሉ ይታመናል። የሳዌን ከሁለት ሰዓት ያነሰ ክብረወሰን የመስበር ሙከራ ይደረጋል ተብሎ ባይታሰብም ውድድሩ እጅግ ፈጣን እንደሚሆን ይጠበቃል። በኤሊዩድ ኪፕቾጌ የተያዘውን የውድድር ቦታውን ክብረ ወሰን ማሻሻል ዋነኛው ግብ ይሆናል። በኬንያዊው ኪፕቾጌ የተያዘው የበርሊን ማራቶን የውድድር ቦታ ክብረወሰን 2:01:09 ነው።

ትንሽ ቀዝቀዝ ያለ የአየር ሁኔታ እንደሚኖር እና ውድድሩም ከወትሮው በ30 ደቂቃዎች ቀድሞ ማለትም በበርሊን ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 2:45 ላይ የሚጀምር በመሆኑ ዘንድሮ ከፍተኛ ፉክክር የሚታይበት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡



📸 © SCC EVENTS / Petko Beier

Address

Toronto, ON

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when BizuAthletics posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to BizuAthletics:

Shortcuts

Share