Ethiopian Tremendous

Ethiopian Tremendous

Partager

Informations de contact, plan et itinéraire, formulaire de contact, heures d'ouverture, services, évaluations, photos, vidéos et annonces de Ethiopian Tremendous, Centre de loisirs, Yaoundé.

07/02/2023

13/12/2022

አርቲስት ረቂቅ ተሾመ ምላሽ ሰጠች! ጋዜጠኛ እና ደራሲ ቴድሮስ ተ/ አረጋይ ይቅርታ ጠየቀ!Ethiopia | Ethiopian Tremendous

11/12/2022

ከአርባ በላይ የአማረኛ ፊልሞች ላይ የተወነው ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በድንገተኛ ህመም ዛሬ ጠዋት አርፏል ።

ተዋናዩ ካባለቤቱ የፊልም ተዋናይት
ቃልኪዳን ጥበቡ ጋር ከተለያየ በኋላ ድብርት ተደጋግሞ ያጠቃው እንደነበር ፊደል ፖስት ከቅርብ ወዳጆቹ ሰምቷል።

ዕድሜው በሰላሳዎቹ አጋማሽ የሚገኘው ተዋናይ ታሪኩ ተውልዶ ያደገው ተክለ ሐይማኖት አካባቢ ሲሆን የአንድ ልጅም አባት ነው።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝናን አና በብዙዎች ተወዳጅነትን ያተረፈ ተዋናይ ነው። በጉዳዬ ፊልም ላይ ደግሞ በድርሰት ፣ በዳይሬክተርነት እንዲሁም በትወና ተሳትፎበታል ፤ እጅግ በጣም ብዙ ፊልሞች ላይ ተውነዋል ።

ከተወነባቸው ፊልሞች መካከል :- 300ሺ፣ የፍቅር ABCD ፣ ብላቴና፣ ቦሌ ማነቂያ ፣ እንደ ባል እና ሚስት ፣ ኢንጂነሮቹ ፣ እርቅ ይሁን ፣ ኢዮሪካ ፣ ጉዳዬ ፣ ሀገርሽ ሀገሬ ፣ ሕይወቴ ፣ ህይወት እና ሳቅ ፣ ከባድ ሚዛን ፣ ፍቅር እና ፌስቡክ ፣ ከቃል በላይ፣ላውንድሪ ቦይ ፣ ኮከባችን ፣ ማርትሬዛ ፣ ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2 ፣ ሞኙ የአራዳ ልጅ ፣ ትዳርን ፍለጋ ፣ አንድ ሁለት ፣ ብር ርርር ፣ ወደው አይሰርቁ፣ ወፌ ቆመች፣ ወንድሜ ያዕቆብ ፣ እንደ ቀልድ ፣ ወቶ አደር፣ አባት ሀገር፣ የሞግዚቷ ልጆች፣ ይዋጣልን ፣ ዋሻው፣ ወሬ ነጋሪ ፣ ወጣት በ97 ተጠቃሽ ናቸዉ።

Ethiopian Tremendous

07/11/2022

እዉቁ እና ተወዳጁ የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አሊ ቢራ ከዚህ ከከንቱ አለም አረፈ 😔😭
ነፍስ ይማር
🙏የተሰማንን ሀዘን እየገለፅን🥹🥹😭 ለቤተሰቦቹ፣ለአድናቂዎቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን::

ነፍስ ይማር!

REST IN PARADISE LEGEND🕯🕊

02/10/2022

ከክርስቲያኑ ሮናልዶ በስተጀርባ አለምን ያስገረመው ነገር Ethiopian Tremendous CR7

Photos from Ethiopian Tremendous's post 18/01/2022


በጥምቀት ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው

?
1. ምሥጢርን ለመግለጥ፡-
ጌታችን በፈለገ ዮርዳኖስ ሲጠመቅ ምስጢረ ሥላሴ ግልፅ ሆኗል፡፡ አብ በደመና “የምወደው የምወልደው ልጄ ይህ ነው” በማለቱ አብ የወልድ አባት መሆኑ ታወቀ፡፡ መንፈስ ቅዱስም የባሕርይ ሕይወቱ መሆኑን ሲያስረዳ በአምሳለ ርግብ በራሱ ላይ ተቀመጠ ወልድም በተለየ አካሉ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ ታየ፡፡ ስለዚህ ምሥጢርን ለመግለጥ ስንል የአንድነት የሦስትነት ምስጢር በጐላ ሁኔታ እንዲታወቅ ተጠመቀ ማለት ነው፡፡ /ማቴ. 3፥16/

2. ትንቢቱን ለመፈፀም፡-
በመዝሙር 46/47/፥16 ላይ “አቤቱ ውሆች አዩህ፣ ውሆችም አይተውህ ፈሩ ጥልቆች ተነዋወጡ ውሆችም ጮኹ፡፡” ተብሎ በቅዱስ ዳዊት የተነገረውን ትንቢት ለመፈፀም ተጠመቀ፡፡

3. አርአያ ሊሆነን፡-
ተጠምቆ እንድንጠመቅ አደረገን ሥርዓትን ሠራልን ቀድሞ በአርአያውና በአምሳሉ እንደፈጠረን አሁንም አርአያ ምሳሌ ሆነን፡፡ ለዚህም ነው ምሳሌን ከእኔ ተማሩ ያለን፡፡ /ማቴ 11፥29/ ለትምህርት ለአርአያ /ዮሐ. 13፥1-17/

4. የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ፡-
አዳምና ሔዋን ፍዳው በፀናባቸው መከራው በበዛባቸው ጊዜ የሚያቃልልላቸው መስሏቸው ዲያብሎሰ ስመ
ግብርናችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ ባላቸው ጊዜ አዳም ገብሩ ለዲያቢሎስ (አዳም የዲያብሎስ የወንድ አገልጋይ) ሔዋን ዓመቱ ለዲያብሎስ (ሔዋን የዲያብሎስ ሴት አገልጋይ) ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ዲያብሎስም ይህንን ደብዳቤ አንዱን በሲኦል አንዱን በዮርዳኖስ አስቀመጠው፡፡ በዮርዳኖስ ያስቀመጠውን ጌታችን ሲጠመቅ እንደሰውነቱ ረግጦ ደምስሶታል፡፡ ይህንን ጽሕፈት ለመደምሰስ ነው ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተፃፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፡፡” ያለው ቆላ 2፥14

?
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በ5531 ዓመተ ዓለም ዘመነ ሉቃስ ማክሰኞ ጥር 11 ቀን ከሌሊቱ በ10ኛው ሰዓት ነበር፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 19 በተጠመቀም ጊዜ ዕድሜው 30 ዓመት ከ13 ቀን ነበር፡፡ /ሉቃ. 3፥23/

?
በብሉይ ኪዳን ሥርዓትና ልማድ ካህናት ለቤተ እግዚአብሔር ተልእኮ እና መንፈሳውያን አገልግሎቶች ከ30 ዓመት ዕድሜ በፊት አደባባይ አይወጡም ነበር፡፡ እጅግ አስፈላጊ እንኳ ቢሆን ከ20 እና 25 ዓመት አስቀድሞ ለአገልግሎት መሰየም ልማድ አልነበረም፡፡ የቤተ እግዚአብሔር አገልጋዮች በዕድሜና በዕውቀት የበሰሉ፣ በጠባይና በሥራ ልምድ የተፈተኑ ተልዕኳቸውን በብቃት ለመወጣት በተገልጋዩ ሕዝብ ዘንድ የተመሰከረላቸው መሆን ነበረባቸው፡፡ /ዘፀ. 4፥3፤1ዜና መዋ. 23፥24፤ 1ጢሞ. 3፥6-10/ ያንን ሥርዓት ለመፈጸም ጌታችን የተጠመቀውና ለትምህርተ ወንጌል የተገለጠው በ30 ዓመቱ ነበር፡፡

ዮሐንስ መጥምቅም የጌታን መምጣት ለማወጅ በዮርዳኖስ ይሁዳ ምድረ በዳዎች ወጥቶ የታየው ከ30 ዓመት ዕድሜው በኋላ ነው፡፡ ሌላው ዐቢይ ምክንያት የሰው ሁሉ መጀመሪያ አዳም የ30 ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ በ40ኛ ቀን ተሰጥቶት ኋላም በኃጢአት ምክንያት ያስወሰደውን ልጅነት ለማስመለስ ነው፡፡

ክርስቶስ የተጠመቀው ክብር ሽቶ ሳይሆን የአብ የባሕርይ ልጅነቱን (የባሕርይ አምላክነቱን) ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ለማስመስከር፣ ውኃውን ለመቀደስ፣ የአዳምን ልጆች የእዳ ደብዳቤ ለመደምሰስና በስህተት የጠፋውን የልጅነት ክብር ለመመለስ ነው፡፡ ጌታ ተጠምቆ ከውኃው ከወጣ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ በማረፍ አብ በደመና ‹‹ይህ ልጄ ነው›› ብሎ ሲመሰክርለት ምሥጢረ ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በጉልህ ተረጋግጧል፡፡ /ማቴ. 3፥16/

?
ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ሲሆን በአገልጋዩ በቅዱስ ዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ በፍጹም ትሕትና ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ ይህንንም ያደረገልን አብነት ሊሆነን ነው፡፡ ምክንያቱም ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስን ‹‹መጥተህ አጥምቀኝ ›› ብሎት ቢሆን ኖሮ ነገ ነገሥታቱና መኳንንቱ ካህናቱን መጥታችሁ አጥምቁን ባሉ ነበር ስለዚህ እንዲህ እንዳይሆን ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ጌታ ስሆን በባርያዬ እጅ እንደተጠመቅሁ እናንተም ወደ ቤተክርስቲያን ሄዳችሁ በካህናት እጅ ተጠመቁ›› ሲል ነው፡፡

ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው ልጅነትን የምታሰጥ ጥምቀትን ባርኮ ቀድሶ ሊሰጠን እንጂ ክብር እንዲሆነው አይደለም፡፡ ምክንያቱም፡- እርሱ እከብር አይል ክቡር እጸድቅ አይል ጻድቅ ነውና፡፡

?
ጌታችን ዮሐንስን አጥምቀኝ ባለው ጊዜ "ሌላውን በአንተ ስም አጠምቃለሁ አንተን በማን ስም ላጥምቅህ? በአብ ስም እንዳላጠምቅህ አብ አባትህ ባንተ ሕልው ነው በወልድ ስም እንዳላጠምቅህ ወልድ አንተ ነህ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዳላጠምቅህ መንፈስ ቅዱስ ሕይወትህ ባንተ ሕልው ነው ታዲያ በማን ስም ላጥምቅህ?" ብሎ ቢጠይቀው ጌታም ‹‹እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት አንተ የዓለም ካህን ብርሃንን የምትገልጥ የአብ የባሕርይ ልጅ ሆይ ይቅር በለኝ›› ብለህ አጥምቀኝ አለው፡፡

?
- ዮሐንስ በጥምቀት አከበረው /ልዕልና ሰጠው/ እንዳይባል፡፡
- መለኮትን በእጅ መንካት ስለማይቻል

?
በኢየሩሳሌም አካባቢ ብዙ ወንዞች ኩሬዎችና ሐይቆች መኖራቸው የታወቀ ነው፡፡ ጌታ ጥምቀቱን በዮርዳኖስ ያደረገው ስለዚሁ አስቀድሞ የተነገረውን ትንቢት መፈጸሙን ለማረጋገጥ ነው፡፡ ‹‹ባሕር አይታ ሸሸች ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ›› /መዝ.113፥3/ ከዚህም ጋር ከላይ ምንጩ አንድ የሆነው ዮርዳኖስ ዝቅ ብሎ በደሴት ተከፍሎ እንደገና እንደሚገናኝ በግዝረት በቁልፈት (በመገዘርና ባለመገዘር) ተለያይተው የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ መላው የአዳም ልጆች በጌታችን ጥምቀት አንድ መሆናቸውን የሚገልጽ ትርጉም አለው፡፡ እስራኤል ዮርዳኖስን ተሻግረው ምደረ ርስት ገብተዋል፡፡ ያመኑ የተጠመቁ ምዕመናንም በጥምቀት ገነት መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ፡፡ ሌላው በዮርዳኖስ ተጥሎ የነበረውን የዕዳ ደብዳቤ ይደመስስልን ዘንድ /ቈላ. 2፥14/

?
እግዚአብሔር አምላክ በዘመነ ኦሪት ሰብዐ ትካትን በንፍር ውሃ ፈርኦንና ሰራዊቱን በኤርትራ ባሕር ካጠፋ በኋላ ሰዎች ውሃ ለመዓት እንጂ ለምሕረት አልተፈጠረም ይሉ ነበርና ለምሕረት እንደተፈጠረ ለማጠየቅ በውሃ ተጠመቀ ( ዘፍ 7÷17፤ ዘጸ 14÷1-29)

አንድም ውሃ እሳትን ያጠፋል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ከገሃነመ እሳት ትድናላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም ውሃ መልክን ያሳያል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ መልክዓ ሥላሴን የአምላክን ቸርነት ርህራሔ ታያላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም በማር በወተት ቢጠመቅ ኖሮ እነዚህ ለባለጸጎች እንጂ ለድሆች አይገኝም ውሃ ግን በሁሉ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ጥምቀት የታዘዘ ለሁሉ ነው ሲል ነው፡፡

አንድም ማርና ወተት ቢታጠብበት ያቆሽሻል እንጂ አያነጣም ውሃ ግን እድፍን ያስለቅቃል እናንተም በማየ ገቦ ብትጠመቁ ከኃጢአት ትጠራላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም ማርና ወተት ተክል ላይ ቢያፈሱት ያደርቃሉ እንጂ አያለመልሙም ውሃ ግን ያለመልማል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ልምላሜ ሥጋ ወነፍስ ታገኛላችሁ ሲል ነው፡፡ (ዮሐ 19÷35)
ምንጭ፦የዮሐንስ አፈወርቅ ትምርቶች

02/01/2022

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኮከቡ ሽመልስ በቀለ ከ ካሜሮን ፀጥታ ሀይሎች ጋር ሰልፊ


29/12/2021

ተነሳሽነት (Motivation) ምንድን ነው?

የሳይንስ ሊቃውንት ተነሳሽነት (Motivation) ማለት አንድ ነገር ለማድረግ ያለን ፈቃደኝነት እና እርምጃ እንድንውስድ የሚያስችል የስነ ልቦና ኃይሎች ስብስብ ነው ይላሉ።

ለቀለም ትምሀርት ተነሳሽነት ማጣት መንስኤዎች በሦስት ዋና ዋና ምክንያቶች ሊከፋፈሉ ይችላሉ። እነሱም - ስንፍና ፣ ከሌሎች ጋር ለመመሳሰል መሞከር እና ያለንበት ሁኔታ። ለምሳሌ ፣ ተነሳሽነት ላይኖራቹ ይችላል ፣ ለረጅም ሰዐት አንድ ቦታ ላይ ትኩረት ማረግ ሊከብዳቹ ይችላል ፣ ትምህርት በሚጠሉ ጓደኞቻቹ ተጽዕኖ ሊኖርባቹ ይችላል ወይም ከትምህርት በላይ የቤተሰብ ጉዳይ ሊያሳስባቹ ይችላሉ። ሦስቱም ልክ ናቸው ፤ ነገር ግን ከእነዚህ ችግሮች ጋር ለመስራት እና ተነሳሽነትን (Motivation) ለማግኘት አሁንም መፍትሄ ማግኘት ይችላሉ።

በሚቀጥሉት ጽሁፎች የተነሳሽነት እጦት መንስኤ ምን እንደሆነ እና አለመነሳሳትን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል በዝርዝር እናካፍሎታለን።

🌟

19/12/2021

💚💛❤️

19/12/2021

💚💛❤️ Ethiopian Diaspora


Vous voulez que votre entreprise soit Gym la plus cotée à Yaoundé ?

Cliquez ici pour réclamer votre Listage Commercial.

Emplacement

Site Web

Adresse


Yaoundé