4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ

4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ

Teilen

4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ! https://t.me/Sport_433et

ማስታወቂያ ለማሰራት በ +251953333287 በመደወል ያገኙናል።

01/10/2025

ስዊድናዊው የመድፈኞቹ አጥቂ ቪክተር ዮኮሬሽ ባለፈው ሲዝን በ8 የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች 6 ጎሎችን አስቆጥሮ ነበር...

Can he delivers today ? 👀🇸🇪

Photos from 4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ's post 01/10/2025

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አረርቲ ከተማ አስተዳደር በግንባታ ላይ የሚገኝ ህንፃ ቤተክርስቲያን በግንባታ መወጣጫ መደርመስ ምክንያት ባጋጠመዉ አደጋ ቻናላችን 4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ ኀዘኑን ይገልጻል፡፡

ሕይወታቸዉን ያጡ ከ35 ሰዎች በላይ እንዲሁም ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸዉ በርካታ ሰዎች መኖራቸዉ በመሰማቱ ቻናላችን የተሰማዉን ኀዘን ይገልጻል፤ ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን፤ በሕክምና ላይ ለሚገኙት በፍጥነት ማገገምን እንመኛለን፡፡

01/10/2025

የቀድሞው ግብ ጠባቂ ህይወቱ አለፈ

በሀገራችን ትልልቅ ክለቦች እስከ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ድረስ ለረጅም ዓመት ማገልገል የቻለው እንዲሁም ወደ አሰልጣኝነትም በመግባት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሁለቱም ጾታዎች የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ በመሆን ሀገሩን በሚገባ ያገለገለው የቀድሞ ድንቅ ግብ ጠባቂ ሳዳት ጀማል ሕክምናውን በሀገር ውሰጥ እና በውጭ ሀገር ሲከታተል ቢቆይም ዛሬ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፉ ተሰምቷል።

4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ በሳዳት ጀማል ሕልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ ፣ ለወዳጆቹ እና ለስፖርት ቤተሰቡ መፅናናትን እንመኛለን።

01/10/2025

ቨርጂል ቫን ዲይክ

"መሸነፍን እጠላለሁ ሰለዚህ መሻሻል አለብን የሞኝ ስህተቶችን ማቆም እና አካሄዳችንን መለወጥ መጀመር አለብን።"

"ወደ አዲስ ቦታ፣ አዲስ ቡድን እና ወደ አዲስ ፍላጎት ከመጣህ በአእምሮ ጠንካራ መሆን አለብህ ፤ በስህተቶቻችን ምክንያት ነው የተሸነፍነው በምሽቱ ጨዋታ ላይ ትንሽ ቸልተኞች ነበርን።"

01/10/2025

በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ችግሩ አሰልጣኙ አይደለም ። ይሄንን ከ1 አመት ከ6 ወር በፊት ተናግሬዋለሁ ።

አሁንም ደግሜ እናገራለሁ በዩናይትድ ቤት ችግሩ አሰልጣኙ አይደለም !! እኔ ማንችስተር ዩናይትድን እወዳለሁ ጥሩም ነገር ለክለቡ እመኛለሁ

አሞሪም በፖርቹጋል አስደናቂ ታሪክ ሰርቷል ፤ አስቸጋሪ ነው ማእበሉ ይቀጥላል.....ሆኖም መጨረሻ ላይ ማእበሉ አብቅቶ ፀሀይዋ መውጣቷ አይቀርም ።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ

01/10/2025

አርሰናል የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ እንደሚያሸንፍ ተስፋ አደርጋለሁ ። ሚኬል አርቴታን እወደዋለሁ ፤ ይሄ አርሰናል የተለየ ነው የአእምሮ ጥንካሬያቸው ጥሩ ነው

የቀድሞ የማን ዩናይትድ ሌጀንድ ዋይን ሩኒ

01/10/2025

በዘንድሮው የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች ብዙ የግብ እድሎችን የፈጠሩ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጫዋቾች ፦

21 - ፍሎሪያን ቪርትዝ
21 - ጃክ ግሪሊሽ
18 - ብራያን ምቤሞ
17 - ብሩኖ ፈርናንዴዝ
16 - 5 ተጫዋቾች

[Opta]

01/10/2025

"ከአርሰናል ጋር በነበረን ጨዋዋ ላይ የመጨረሻዎቹን ደቂቃዎች የተሻለ መስራት ነበረብን ቢያንስ አንድ ነጥብ ማግኘት እንችል ነበር።"

"በአርሰናል የደረሰብን ሽንፈት አበረታች እንጂ ጎታች መሆን የለበትም ሽንፈቱን እንደ አዲስ መነሻሻነት ልንጠቀምበት ይገባል።"

"አሁን በቻምፒየንስ ሊጉ ላይ አለን በሚቀጥለው አመት ግን በዚ መድረክ የመኖራችን ነገር ቢቀጥልም ባይቀጥል ጊዜው ብቻ ነው የሚያውቀው ሰለዚህ ይህንን እድል በአግባቡ ለመጠቀም የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን።"

Photos from 4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ's post 01/10/2025

📆 ከ22 አመት በፊት በ2003 የምንግዜም ምርጡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በታላቁ ቻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታውን አደረገ ! 💫

ክርስቲያኖ በቻምፒየንስ ሊግ ያለው አንዳንድ ረከርዶች :-

• ብዙ ጎል: 140

• ብዙ አሲስት: 42

• ብዙ ጨዋታ ያደረገ: 183

• በ1 የቻምፒየንስ ሊግ ሲዝን ብዙ ጎል ያስቆጠረ: 17

• በጥሎ ማለፍ (Knockout) ጨዋታዎች ላይ ብዙ ጎል ያስቆጠረ : 67

• ብዙ ግዜ የቻምፒየንስ ሊግ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ : 7

• በ3 የተለያዩ የቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታዎች ጎል ያስቆጠረ ብቸኛው ተጫዋች

• በ11 ተከታታይ የቻምፒየንስ ሊገ ጨዋታዎች ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች

• በ1 የቻምፒየንስ ሊግ ሲዝን ብዙ ሀትሪክ የሰራ ተጫዋች : 3



CHAMPIONS LEAGUE ❌

CRISTIANO RONALDO LEAGUE ✅

01/10/2025

🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿7ተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች

አርብ መስከረም 23/2018

04:00 | በርንማውዝ ከ ፉልሃም

ቅዳሜ መስከረም 24/2018

08:30 | ሊድስ ከ ቶተንሀም
11:00 | አርሰናል ከ ዌስትሃም
11:00 | ማን ዩናይትድ ከ ሰንደርላንድ
01:30 | ቼልሲ ከ ሊቨርፑል

መስከረም 25/2018

10:00 | አስቶን ቪላ ከ በርንሌይ
10:00 | ኤቨርተን ከ ክሪስታል ፓላስ
10:00 | ኒውካስትል ከ ኖቲንግሃም
10:00 | ወልቭስ ከ ብራይተን
12:30 | ብሬንትፎርድ ከ ማን ሲቲ

*********

የውጤት ግምታቹን ኮመንት ላይ ይፃፉልን 👇

01/10/2025

አርቴታ ሊገብዛቸው ሰለሆኑት የRAF ተዋጊ ፕሌን ፓይለቶችን 🗣

"የነሱ ስራ ዕጅግ ከባድ ነው በህይወት የመቆየትህ ነገር ዋስትና የለውም ከነሱ የሚገርመኝ ነገር በሞት እና በህይወት መሃል ቁመው 20 ቃላት አይደረድሩም በአጭሩ ነው ግባቸውን ለመምታት የሚግባቡት እና ቅልጥፍናቸው ያስደንቀኛል።"

"ለዛም ነው ወደኛ ጋብዘናቸው ሂደታችንን እንዲገምግሙ እና ጥሩ ስልጠና እንዲሰጡን ያሰብነው ፤ ቀልጣፋ እና ብዙ ቃላት ሳናባክን በቶሎ የምንግባባቸውን ሁኔታዎች መፍጠር አለብን።"

01/10/2025

ጆዜ ሞሪኒዮ የቼልሲ ደጋፊዎች ሰለዘመሩለት መዝሙር

"ይህ የእንግሊዝ ባህል ነው በኢንግሊዝ ውስጥ ያሉ ሰዎች እንደዚህ አይነት ባህል አላቸው ከዚህ በፊት ያስደሰታቸውን ሰው አይረሱም ፤ ከተለያዩ ቡድኖች ጋር እዚህ መጥቻለሁ እና ሁልጊዜም እንደዛ ነበር ሲዘመርልኝ የነበረው ፤ ለቀድሞ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞት አክብሮት አለ።"

"በጣሊያን ቱሪን ላይ ቢሆን በእርግጠኝነት እንደዚ አይቀበሉኝም ነበር።"

Wollen Sie Ihr Service zum Top-Fitness-Studio in Cologne machen?

Klicken Sie hier, um Ihren Gesponserten Eintrag zu erhalten.

Lage

Kategorie

Adresse


Cologne