26/03/2024
የኬቨን ዴብሮይን የማንችስተር ሲቲ ቆይታ ?
ቤልጂየማዊው የማንችስተር ሲቲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬቨን ዴብሮይን በአሜሪካ እና ሳውዲ አረቢያ ክለቦች እየተፈለገ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ኬቨን ዴብሮይን አሁን ላይ ሙሉ ትኩረቱን ማድረግ የሚፈልገው የመጨረሻ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በሚገኘው የውድድር አመት ማጠናቀቂያ ወቅት ላይ እንደሆነ ተነግሯል።
በውድድር አመቱ መጨረሻ ኬቨን ዴብሮይን ከሌሎች ክለቦች ጋር ከመነጋገሩ በፊት በኮንትራቱ ዙሪያ ከማንችስተር ሲቲ ባለስልጣናት ጋር እንደሚነጋገር ተዘግቧል።
26/03/2024
ማይክል አርቴታ ዛሬ 42ተኛ አመቱን እያከበረ ይገኛል !
08/01/2021
በ ምርጥ አቀራረብ እንመለሳለን
Football News Football News updates-AmharicFootball News updates-AmharicFootball News updates-Amharic
29/05/2020
ኢትዮጵያ ከካፍ ድጋፍ ሊደረግላት ነው !
ካፍ አሁን እንዳስታወቀው ለ 54 አባል ሀገራቱ ከ 10.8 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል ፡፡
እያንዳንዱ አባል ሀገራት 200,000 የአሜሪካ ዶላር ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዚህ እርዳታ አካል እንደሚሆን ይጠበቃል ::
29/05/2020
የጣልያን ሴርያ ጨዋታዎች እንዲካሄዱ ከስምምነት ላይ ተደርሷል ::
በዚህም መሰረት የሴርያው ጨዋታዎች ከፊታችን ሰኔ 13 ጀምሮ እንዲካሄዱ ፍቃድ አግኝቷል ::
29/05/2020
ፕሪምየር ሊጉ ቀን ተቆርጦለታል. . .
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በድጋሚ ዕረቡ ሰኔ 10 እንደሚጀምር ቴሌግራፍ የዘገበ ሲሆን በዕለቱም አስቶን ቪላ ከ ሼፍልድ ዮናይትድ እና ማንችስተር ሲቲ ከ አርሰናል የሚገናኙ ይሆናል።
29/05/2020
የስፔን ላሊጋ የሚጀምርበት ቀን ተገለፀ !
የላሊጋው ፕሬዝዳንት ጃቪየር ቴባስ ላሊጋው ከሁለት ሳምንታት በሃላ ሰኔ 4 ሀሙስ ቀን እንደሚጀምር አሳውቀዋል ::
ከዚህ በተጨማሪም ላሊጋው ሀምሌ 2 እንደሚጠናቀቅ በመረጃው ተገልጿል ::
ይህንንም ተከትሎ ሲቪያ ከ ሪያል ቤቲስ በሚያደርጉት የላሊጋው ሌላኛው ታላቅ ደርቢ እንደሚጀመር ይፋ ሆኗል ::
23/05/2020
ማንችስተር ዩናይትድ በመጪው ክረምት የቅድመ ዝግጅት ጉዞ እንዳለፈው ጊዜ እንደማይካፈሉ እየተገለፀ ይገኛል፡፡
ቀያዮቹ በባለፈው የውድድር አመት የቅድመ ዝግጅት ጊዜን በአውስትራልያ ማሳለፋቸው ይታወሳል ::
23/05/2020
ባርሴሎና የወሳኝ ተጫዋቹን ውል ሊያራዝም ነው !
የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የጀርመናዊውን ኮከብ ግብ ጠባቂ ማርክ አንድሬ ቴር ስቴገን ውል ለማራዘም ከጫፍ መድረሱ ተገልጿል ::
ቴር ስቴገን በመጪው ቀናት ከባርሴሎና ጋር እስከ 2025 የውድድር አመት ድረስ የሚያቆየውን አዲስ ውል እንደሚፈራረም ይጠበቃል ::
23/05/2020
ጁቬንቱስ የምርመራ ውጤቱን አሳወቀ!
የሴርያው ሀያል ክለብ ጁቬንቱስ ከቀናት በፊት ለቡድን አባላቱ ያደረገው የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ይፋ አደረገ ::
በውጤቱም ሙሉ የቡድን አባላቱ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን ይፋ ሆኗል ::