Saint George Sport Club Families - የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፓርት ክለብ ቤተሰቦች

Saint George Sport Club Families - የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፓርት ክለብ ቤተሰቦች

Share

ይህ ገጽ የእኛ የፈረሰኞቹ ነው! እኛ ጊዮርጊስ አለ በተባለበት ቦታ ሁሉ የምንገኝ!
ሳንጃው ፈረሰኞቹ ሼባው አርበኛው አራዶቹ ሼባው Sanjaw Shebaw

08/07/2026

ወደ መሬት ባንክ ገብቷል

06/07/2026

‎እዚች ደብዳቤ ላይ . . .

‎የቅዱስ ጊዮርጊስን ማሊያ ለብሶ . . .የክለቡን መልካም ስም የሚያጠለሽ ተግባር ላይ ተሳትፎ የተገኘ ደጋፊ ላይ ክለቡ ስሙን ለመጠበቅ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ቢገለፅ😍

‎-
‎ይህን የተመለከተ አንቀፅ መተዳደሪያ ደንቡ ውስጥ ቢካተት ሸግዬ ነው🙏

‎-
‎በነገራችን ላይ . . .የግለሰቦችን እና የተቋማትን አቋም መለየት ለማይችሉ ጥበብን😁 እየቻሉ ሆን ብለው ሴራ ለሚጠነስሱ ደግሞ አስተዋይ ልቦና እንዲሰጥልን . . .የእግር ኳሱን አማልክት እንለማመናለን😁

ዴቭ ቅዱስ ጊዮርጊስ

06/07/2026

#የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር
የአቋም መግለጫ

በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር እና በፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ መካከል ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. የተደረገውን የእግር ኳስ ጨዋታ ተከትሎ፣ ከሁለት ወገን በተወሰኑ ግለሰቦች ስፖርታዊ ሥነ ምግባርን በማይመጥን መልኩ በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጩ የነበሩ ሥነ ምግባር የጐደላቸው መልዕቶች አጠቃላይ የስፖርት ማህብረሰቡን የማይወክሉ እና ሊወገዙ የሚገባቸው መሆኑ ስለማያከራክር ብዙም ማብራሪያ አያስፈልገውም፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በሁለቱም ወገኖች ተሰራጭቷል የተባሉትን ተገቢ ያልሆኑ መልዕክቶችን በጥብቅ የሚቃወም ሲሆን፣ ክለባችን ከእነዚህ ድርጊቶች ጋር ምንም ዓይነት ተሳትፎም ሆነ ተባባሪነት እንደሌለው ለማህበረሰቡ በግልፅ ማሳወቅ ይፈልጋል፡፡

ስፖርት የፍቅር፣ የአንድነትና የመከባበር መድረክ በመሆኑ፣ ሁሉም የስፖርት ቤተሰብ አባላት ለእነዚህ እሴቶች ተገቢውን ክብር እንዲሰጡ ክለባችን በዚህ አጋጣሚ አጥብቆ ያሳስባል፡፡

በመሆኑም ክለባችን ከእነዚህ ድርጊቶች ነፃ መሆኑን በድጋሚ እየገለፀ፣ በሌላ በኩል በሁለቱም ወገኖች የተፈፀሙት ስፖርታዊ ሥነ ምግባርን የማይመጥኑ ድርጊቶች ወደፊትም እንዳይደገሙ በማሳሰብ አቋሙን ይገልጻል፡፡

06/07/2026

የውድድር አመቱ በትናንትናው እለት በይፋ ተጠናቅቋል፡፡በብዙ ተግዳሮት ውስጥ ሆነው ያገለገሉንን ተጫዋቾች ፥ አሰልጣኞች ፥ የጸህፈት ቤት እና የአካዳሚ ሰራተኞች ፥ የመንግስት ተቋማት ፥ አጋር ድርጅቶች ፥ የሊጉን አክስዮን ማህበር እና ፌደሬሽኑን ፥ ኦ ቢ ኤን እና ሌሎች በሙሉ እናመሰግናለን!!

ከሁሉም በላይ እናንት ክቡራን ደጋፊዎችን እናመሰግናለን!

እናንተም ምስጋና ይገባዋል የምትሉትን በሙሉ በአስትያየት መጻፊያው ላይ እንድታመሰግኑ እንጋብዛለን!

04/07/2026

ወደድክም ጠላክም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀገር አልፎ የአፍሪካ ቅርስ እና የጥቁሮች ነጮችን የማሸነፍ ተምሳሌት ሆኖ የተመዘገበ ታሪካዊ ክለብ ነው። ማንም ይሔን ታላቅ ክለብ ማክበር አለበት ማክበር እንኳን ባይችል የሚያስከብር የሚያኩራራ እንጂ የሚያሰደብ ታሪክ ስለሌለው ይሔን ታላቅ ክለብ መሳደብ ሀጥያትም ነውር ነው። ሲቀጥል የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊ ቤተሰብ ሆነህ ማሊያውን እስከለበስክ ድረስ አንተ አንቺ የክለቡ አባሳደር ነክ ማሊያውን ለብሰክ ወይም የታላቁን ክለብ ስም እያነሳህ የምታረገው ነገር ጥሩ ከሰራህበት አንተንም ክለብህንም በበጎ ታስጠራበታለክ ነገር ግን ማሊያውን ለብሰክ የክለብክን ስም እየጠራህ የምታደርጋቸው እያንዳንዱ መጥፎ ነገር ከራስክ አልፎ ታላቁን ክለባችንን በመጥፎ ስለሚያስነሳው መጠንቀቅ አለብህ። ሁልክም ታላቁ ክለባችን ይሔን ስም ለመገንባት በትውልድ ቅብብሎሽ ዘመናትን ለፍቷል ስኬቱም ጨዋነቱም በደም የተገነባ ነው ብዙ ተከፍሎበታል ስለዚህ የታላቁን ክለባችንን ስምን ታሪክ እዲህ ብለህ ነበር እያለ በመጥፎ እዳያነሳው ሁሉም ሊጠነቀቅ ይገባል። ጊዜው የዋይፋይ ነው እያንዳንዱ የምትላት ነገር በሰከድ ነው የሚሰራጨው፣ ሪከርድ ሆኖም ተቀምጦ ካለፈ በሗላ ያስጠላል ስለዚህ ሁላችንም እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊና ቤተሰብ ለክለባችን ብራንድ ለሆነ ስም መጠንቀቅ የውዴታ ግዴታ ነው። በተለይ ክለባችንን ከሀይማኖት ከዘር ከብሔር ጋር የሚያነካካ ነገር እዳይኖር መጠቀቅ ያስፈልጋል። ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስ ያለምን ጾታ ዘር ብሔር ሀይማኖት ልዩነት የሚደገፍ የመላው ኢትዮጵያውያን ክለብ ነው!✌️❤
#በመጨረሻም
ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለባችን አሁን ላይ መሪ ካለው ወተው አንዳንድ ነገሮችን ያስተካክሉ ✌️❤

Heni Ye Giorgis

04/07/2026
04/07/2026

በነገራችን ላይ 5ተኛ ወጥተን 20 ሚሊዮን ብር ሽልማት ተጫዋቾቻችን ተሸልመዋል።

እስካሁን ዋንጫ በልቶ እንኳን ይህንን ያህል ብር የሸለመ የለም ።

ለማኝ የተባለው ክለብ ቀጣይ የስቴዲዬም ባለቤት ይሆናል

04/07/2026

‎እነዚህ ተጨዋቾች ከ90 በመቶ በላይ ልምድ የሌላቸው እና ወጣቶች . . .በወቅታዊው የእግር ኳስ ገበያ ውድ ዋጋ ያልተለጠፈባቸው አንዳንዶቹ ጨርሶ የማይታወቁ ተጨዋቾች ናቸው. . .በእንቅርት ላይ . . .እንዲሉ ጭራሽ ለሞራላቸው ማነቃቂያ ቀርቶ . . .ላባቸውን የሚያብሱበት ምግብ ቀርቶ ጥማቸውን የሚቆርጡበት ውሃ እንኳን ተቸግረው ነበር. . .

‎-
‎ተጋጣሚዎቻቸው ደግሞ በሊጉ ውድ ተከፋዮች. . .ቅንጡ ሆቴል ተመጋቢዎች ሁሉ የተሟላላቸው ነበሩ. . . ሆኖም እነዚህ በብዙ ችግር ውስጥ ቢሆኑም . . .ከሁሉ በክብሩ የሚልቅ ዘመናትን በአሸናፊነት መድረክ ላይ የተንፏለለ ቢጫ ቀይና ብርቱኳንማ ቀለም ያለው የድል ኳባ ደርበው ሜዳ ይገቡ ነበር . . .መግባት ብቻ አይደለም በክብር ለታላቁ ክለብ ተዋድቀው እነዛ ከውድድሩ በፊት ብዙ የተባለላቸውን ቀድመው ከፊት ተሰልፈው ተገኙ. . .
‎ይህ የሆነው . . .ምን አልባት የሚሆነውም በቅዱሰ ብቻ ነው!

‎-
‎ይህን ለክብር ስለተደረገ ፍልሚያ ብዙዎች ቢያደንቁትም ሃያ ሚሊዮን በማውጣት በርቱ ያለው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ MIDROC Investment Group ሚድሮክ ነውና ማመስገን ያስፈልጋል


‎-
‎ቀጣይ ምን ላላችሁ እነ ጭንቀቴ. . .መልሳችን👇

‎እኛን ነው ማየት. . . እንላለን😁😁

ዴቭ ቅዱስ ጊዮርጊስ

04/07/2026


‎ነጯን እንነጋገር?

‎-
‎ሶስት መሰረታዊ ነገሮች በመጠየቅ እንጀምር👇

‎1- ለሚድሮክ እና ለሼሁ በዘመቻ መልክ የተፃፈው እውነታ ቅሬታ በተነሳባቸው ሁለት ደጋፊዎች ነው?

‎-
‎2-ሁለቱ ደጋፊዎች እንደ ሌላው ሁሉ ክለባቸውን ባሻቸው እና በገባቸው መንገድ ከመደገፍ ውጪ አንዳችም በክለቡ ውስጥ ሃላፊነት እንደሌላቸው ሳያውቁ ቀርተው ነው?

‎-
‎3- ለምን ይሄን ያህል ነገሩን ማጦዝ ተፈለገ?

‎-
‎ለዚህ ምላሽ . . .በዘመቻ የተጋሩትን ፅሑፎች እና የፅሑፉ ደጋፊ ኮሜንቶችን እንዲሁም ተቃውሞ የተነሳባቸውን ሁለቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ያጋሯቸውን እና ብዙዎች እየተቀባበሉት ያለውን መልዕክቶች በሚገባ ተመልክቻለው

‎-
‎አጠር አድርገን ምላሹን ስናየው. . .

-
‎1ኛው. . .ለሚድሮክ እና ለሼኩ የተፃፈው የዘመቻ ፅሁፍ አላማው ለሼኩ መልካም ስም ተቆርቋሪ በመምሰል. . .እንዲሁም ለሚድሮክ ደግሞ ቢዝነሱ ላይ ኪሳራ እናመጣብሃለን በሚል ማስፈራሪያ ሰበብ . . .ከቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲርቁ እና ለክለቡ ድጋፍ እንዳያደርጉ ለማድረግ የታቀደ ሴራ ነው!

‎-
‎2ኛው. . .እዚህ ጋር ደጋፊዎች በክለቦቻቸው ዙሪያ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የደጋፊዎች አተያይ ይለያያል . . .አንዳንዱ ለክለቡ ስትቀርብ የክለቡ ባለቤት አድርጎ ሊያስብህ ይችላል . . .አንዳንዱ ደግሞ የክለቡ ተቀጣሪ ሊያደርግህ ይችላል . . .ሆኖም እኔ የማውቃቸው ጥቂት ይሄን ነገር እያጦዙት ያሉት የፋሲል ደጋፊዎች ሁለቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ተራ የክለቡ ደጋፊዎች እንደሆኑ ጠንቅቀው እንደሚያውቁ እርግጠኛ ነኝ! ስለዚህ ይህ ሃሳብ ልጆቹን መነሻ አድርጎ ቅዱስ ጊዮርጊስና ሚድሮክን ያላቸውን ግንኙነት ለማበላሸት የተጠቀሙበት እንደሆነ በግልፅ መረዳት ይቻላል


‎-
‎3ኛው- ይህ ነገር ሲጦዝ ማን ይጠቀማል?
‎ፋሲል ዘንድሮ ከነበረው የተጨዋቾች ስብስብ እና የገንዘብ አቅም አንፃር በሊጉ ቀጥተኛ የዋንጫ ተገማች እና ተጠባቂ ቡድን ነበር . . .ይህ ለምን አልተሳካም የሚሉ. . .እንዲሁም በክለቡ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ጥያቄ የሚያነሱ ደጋፊዎች እንደነበሩ ይታወቃል. . .ስለዚህ ይህ ጉዳይ እንደ አጀንዳ ማስቀየሪያ ለመጠቀም ወርቃማ አጋጣሚ መሆኑ ክርክር የሚነሳበት አይደለም!

‎-
በአጠቃላይ ‎ለፋሲል ደጋፊዎች ያለኝ መልዕክት . . .ነገሩን ተረጋግታችሁ መርምሩ መልዕክቴ ነው! ለጥቂቶቹ ሴረኞች ግን . . .ቅዱስ ጊዮርጊስን በዚህ መንገድ አታሸንፉትም . . . እቺ ብዙዎች ቀድመው ሞክረዋታል ግን አለሆነም😁😁


‎-
‎ምስል:- የፋሲል ደጋፊ ነው ሳይሸፋፍን የእውነት ፍላጎታቸውን ፅፏል😁. . .

ዴቭ ቅዱስ ጊዮርጊስ

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Addis Ababa