30/08/2022
⚽የወዳጅነት ጨዋታ⚽
Friendly Match
ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል ።
⚽ ቅዱስ ጊዮርጊስ 3 -1 አል ሜሪክ ⚽
⚽አማኑኤል ተርፋ 24'
⚽ቢኒያም በላይ 41'
⚽ኢስማኤል ኦሮ አጎሮ 42'(ፍ)
📆 ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 24/2014
🕗 10:00
🏟 በክቡር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ
29/08/2022
✌የአቋም መፈተሻ ጨዋታ✌️
🐎ቅዱስ ጊዮርጊስ[Eth] ከ አል ሜሪክ[Sud]
🗓 ማክሰኞ ነሀሴ 24
⏰10:00 ሰዓት
🏟 ክቡር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ
👉ሁለቱ ቡድኖች ለመጨረሻ ጊዜ በተገናኙባቸው ሁለት ጨዋታዎች በአንደኛው አል ሜሪክ ሲያሸንፍ በአንደኛው ጨዋታ ደሞ ነጥብ ተጋርተው መውጣት ችለዋል
27/08/2022
የታላቁ ቅዱስጊዮርጊስ እንስት ደጋፊዎች በዛሬው እለት የክለባችን የልብ ደጋፊ በነበረችው እናታችን ካሰች መስቀሌ ስም በተሰየመው "ዝክረ ካሰች" በተሰኝው የደም ልገሳ መርሃ ግብር ላይ በቀይ መስቀል ተገኝተው የደም ልገሳ ሲያከናውኑ ውለዋል።
27/08/2022
የፈረሰኞቹ ስፖርት ባር ተገቢውን ጥገና ተደርጎለት ወደ ስራ ገብቶ ለክለባችን ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ሚሆንበት መንገድ
መሰራት አለበት እንቅስቃሴዎችም እንደተጀመሩ የደረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ
የፈረሰኞቹ ስፖርት ባር በኢድ አከባበር ላይ በተፈጠረ ረብሻ ጉዳት ከደረሰባቸው ህንፃዎች መካከል አንዱ መሆኑ ይታወቃል።
27/08/2022
ሌላ የወዳጅነት ጨዋታ።
በኣፍሪካ ቻምፕ.ሊግ ቅድመ ማጣርያ ከጅቡቲው ሻምፕየን ኣርታ ሶላር 7 የደረሰው .. ሌላኛው ሀያል የሱዳን ቡድን የሆነው ኣልሜሪክ .. ለጨዋታው የሚረዳውን ዝግጅት ለማድረግ .. ዛሬቅዳሜ ኣዲስ ኣበባ የገባ ሲሆን .. ከዘንድሮ የኢትዮጵያ ሊግ ሻምፕየን ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋርም 2 የወዳጅነት ጨዋታዎችን እንደምያደርግ ክለቡን ላይ ኣተኩረው የሚፅፉ ገፆች ያሳወቁ ሲሆን .. ኣጠቃላይ የዝግጅት ነገሮችን ለማመቻቸትም የክለቡ ምክትል የስፖርት ጉዳዮች ሀላፊ ረቡዕ እለት ሸገር ገብተዋል።
26/08/2022
አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ
የ2014 ኮከቡ አሰልጣኝ ከሻምፒዮኖቹ ፈረሰኞች ጋር በዋና አሰልጣኝነት ይቀጥላል
በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ፈረሰኞቹን በጊዜያዊነት እየመሩ የቆዮት አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የቡድናችን ዋና አሰልጣኝ በመሆን ተሹመዋል።
ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስ ለ2014 የውድድር ዘመን ዝግጅት በጀመረበት ወቅት ሰርቢያዊውን አሰልጣኝ ዝላትኮ ክራምፓቲችን በዋና አሰልጣኝነት ቢሾምም አሰልጣኙ ከተጫዋቾች ጋር የነበረባቸው የተግባቦት ችግር ተከትሎ የክለቡ አመራር አሰልጣኙን በማሰናበት አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ቡድኑን በጊዜያዊነት እንዲመሩ መደረጉ አይዘነጋም።
26/08/2022
ፈረስኞቹ በክቡር አቶ ይድነቃቸውተሰማ አካዳሚ ልምምዳቸውን እያደረጉ ይገኛሉ
ለብሄራዊ ቡድን ግዳጅ ከሄዱት ተጫዋቾ ውጪየያዘው ስብስብ
የፊታችን መስከረም 1 በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ላለበት ጨዋታ ጠንካራልምምድ በመስራት ላይ ይገኛል።
24/08/2022
"ለዘንድሮ ስኬታችን የፅ/ቤት ሰራተኞች የከፈላችሁት መስዋዕትነት የሚዘነጋ አይደለም"
አቶ አብነት ገብረመስቀል
====//////=====/////====
የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የፅ/ቤት ሰራተኞች የ2014 ዓ.ም የውድድር ዘመን መጠናቀቅን ምክኒያት በማድረግ በክለቡ መዝናኛ ማእከል የሠራተኞች የጋራ የደስታ ፕሮግራም አሠናድተዋል።
በፕሮግራሙም ሰራተኞች የዚህ አመት የጉዞ ትዝታዎቻቸውንና ያልተነገሩ ገጠመኞችን በማውሳት ከአመራሩና አጠቃላይ የጊዮርጊስ ቤተሰቦች ጋር በጋራ የተሰራው ስራ ለዋንጫ ድል እንዳበቃን ገልፀዋል።
በፕሮግራሙ መሀል የክለባችን ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገብረመስቀል በስልክ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን " የፅ/ ቤት ሰራተኞች የሚያጋጥሙ ችግሮችን በትዕግሥት እና በፅናት በማለፍ ለምታከናውኑት ተግባር ክብር አለኝ ፤ ብዙውን ነገር ችላችሁና ታግሳችሁ ለውጤታማነታችን የሠራችሁት ጊዮርጊሳዊ ማንነት ስላላችሁ ነው፤ አሁንም ከፊት ያለው ይበረታልና በትዕግሥት ታላቁን ጊዮርጊስ አይታችሁ በአብሮነትና በህብረት እንድትቀጥሉ አደራ እላለሁ፤ በራሳችሁ ወጪ ደስታችሁን በጋራ ማክበራችሁ ተጠናክሮ ይቀጥል " ብለዋል።
በምሽቱም ፕሮግራም ሰራተኛው በአርአያነታቸው የጎሉ ግለሰቦችን አመስግኗል።
22/08/2022
ወቅታዊ ዜናዎችን በተሻለ አቀራረብ የምናደርስ ይሆናል
01/10/2021
የ2014 ቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር መርሀ ግብር
26/05/2021
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ጨዋታ ዉጤት
✌️ቅዱስ ጊዮርጊስ 3⃣➖2⃣ወልቂጤ
⚽️⚽️⚽️ሀይደር