For more info about Realfevr join https://t.me/RealfevrFantasyEthiopia
Realfevr Fantasy Ethiopia
Fantasy football, where you can create your dream team. Be the manager you always wanted and win ama
03/03/2022
03/03/2022
ፋንታሲ በትላልቅ ሽልማቶች መጥቷል !
♨️ Realfevr Fantasy Ethiopia ተወዳጁ የአለማችን እግር ኳስ ጨዋታ ፋንታሲ ስፖርትን በሀገራችን ለየት ባለ መልኩ "Realfevr" በተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ አፕልኬሽን ከአስራ አንድ በላይ ሊጎችን አካቶ ቀርቧል ።
የድሉ ጊዜ እየቀረበ ነው ፤ ለጊዜው በእንግሊዝ ፋንታሲ ተጫውተው አሸናፊ በመሆን የትም ያልተነዳ 00 ሱዙኪ ዲዛየር መኪና እንዲሁም ሌሎች አጓጊ ሽልማቶችን ይሸለሙ ።
እንደ ምርጫዎ በአራት እርከኖች በተከፈለው የፋንታሲ ውድድር ላይ በመሳተፍ የሽልማቱ ተቋዳሽ ይሁኑ !
1⃣ የመጀመሪያው 100 ብር በመክፈል ከአምስት መቶ ሰዎች ጋር የሚደረግ ውድድር ሲሆን አሸናፊው 20,000 ብር የሚያሸንፍበት ከ 2-10 ደረጃን የሚይዙት አንድ ሺህ ብር የሚሸለሙበት ውድድር ነው ።
2⃣ ሁለተኛው 300 ብር በመክፈል ከ አምስት መቶ ሰዎች ጋር የሚደረግ ውድድር ሲሆን አሸናፊው 50,000 ብር የሚያሸንፍበት ከ 2-10 ደረጃን የሚይዙት ሁለት ሺህ ብር የሚሸለሙበት ውድድር ነው ።
3⃣ ሶስተኛው 500 ብር በመክፈል ከአምስት መቶ ሰዎች ጋር የሚደረግ ውድድር ሲሆን አሸናፊው 100,000 ብር የሚያሸንፍበት ከ 2-10 ደረጃን የሚይዙት ሶስት ሺህ ብር የሚሸለሙበት ውድድር ነው ።
4⃣ አራተኛው 990 ብር በመክፈል ከ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሰዎች ጋር የሚደረግ ውድድር ሲሆን አሸናፊው አዲስ ሱዙኪ ዲዛየር 2021 መኪና የሚሸለምበት ከ 2-10 ደረጃን የሚይዙት አስር ሺህ ብር የሚሸለሙበት ውድድር ነው ።
⚠️ ክፍያውን በንግድ ባንክ እንዲሁም በአቢሲኒያ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 102030 አልያም በ ቴሌ ብር ላይ Merchant ID 530160 ላይ ማስገባት ይችላሉ ። አልያም ከኤጀንቶቻችን የፋንታሲን ጌም ካርድ መግዛት ይችላሉ።
⏳በመቀጠል
ወደ Realfevr Fantasy Ethiopia የቴሌግራም Bot () በማቅናት የቡድኖን ስም እንዲሁም የክፍያ ማረጋገጫዎን (slip screenshot, transaction number, Fantasy game card code...) ማስገባት ይኖርብዎታል ።
✅ ክፍያዎ ከተረጋገጠ በኋላ ማረጋገጫውን በላኩበት Bot ላይ የውድድሩ ተሳታፊ የሚያደርግዎ የ Private League League Token ይደርሶታል ።
⚽️ የደረስዎትን token number በመያዝ "Join" Private League የሚለውን አማራጭ በመጫን ኮዱን በማስገባት የውድድሩ ተሳታፊ ይሆናሉ ።
📲 የሞባይል መተግበሪያ አፕልኬሽኑ ስም Realfevr ሲሰኝ በ Playstore እና Appstore ላይ ይገኛል !
03/03/2022
የነጥብ አሰጣጥ
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት፤ ተጫዋቾች በገሃዱ አለም ጨዋታ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች እና በዚያ ላይ ተመስርቶ የሚያሰጣቸው የፋንታሲ ነጥቦች ናቸው።
➡️ ለሁሉም ተጫዋቾች በሜዳ ላይ ከ59 ደቂቃ በታች የመጫወቻ ጊዜን ካገኙ 1 ነጥብ፣ ከ60 ደቂቃ በላይ የተጫወቱ ተጫዋቾች 2 ነጥብን የሚያገኙ ይሆናል።
➡️ ለሁሉም ተጫዋቾች በራሳቸው ላይ ግብ ሲያስቆጥሩ 2 ነጥብ ይቀነስባቸዋል፣ ቢጫ ካርድ ሲያዩ 1 ነጥብ እንዲሁም ቀይ ካርድ 3 ነጥብ ያስቀንሳል።
➡️ ፍፁም ቅጣት ምት መሳት ለ2 ነጥቦች ያስቀንሳል፣ ፍፁም ቅጣት ምት የሚያሰጥ ጥፋት መስራት 1 ነጥብን ያስቀንሳል እንዲሁም ፍፁም ቅጣት ምት ማዳን 5 ነጥብ ያሰጣል።
➡️ ኢላማቸውን የጠበቁ 2 ሙከራዎችን ማረግ 1 ነጥብን ከግብ ጠባቂ ውጪ ለሁሉም ተጫዋቾች ያስጨምራል።
➡️ ለግብ ጠባቂዎች ጎል ካስቆጠሩ 10 ነጥብ፣ ጎላቸውን ሳያስደፍሩ ከወጡ 4 ነጥብ፣ ፍፁም ቅጣት ምት ካዳኑ 5 ነጥቦችን ያገኛሉ።
➡️ ለተከላካዮች ጎላቸውን ሳያስደፍሩ ከወጡ 4 ነጥቦችን፣ ጎል ካስቆጠሩ 6 ነጥቦችን የሚያገኙ ሲሆን 2 ጎሎችን ሲያስተናግዱም 1 ነጥብ የሚቀነስባቸው ይሆናል።
➡️ አማካኝ ተጫዋቾች ጎል ሳይቆጠርባቸው ከወጡ 1 ነጥብን ሲያገኙ ጎል ካስቆጠሩ 5 ነጥቦችን የሚያገኙ ይሆናል።
➡️ አጥቂዎች ጎል ሲያስቆጥሩ 4 ነጥቦችን የሚያገኙ ይሆናል።
03/03/2022
እንዴት ነው የምንጫወተው?
የሞባይል መተግበሪያ አፕልኬሽኑን app store ወይም playstore ላይ Realfevr ብላችሁ ሰርች በማድረግ በቀላሉ አፕልኬሽኑን በማውረድ መጠቀም ትችላላችሁ።
ወይም ለአንድሮይድ ስልክ ተጠቃሚዎች በዚህ ሊንክ በቀላሉ አፕልኬሽኑን ማውረድ ትችላላችሁ።
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.realfevr.fantasy
ለአይፎን ስልክ ተጠቃሚዎች በዚህ ሊንክ በቀላሉ አፕልኬሽኑን ማውረድ ትችላላችሁ።
https://apps.apple.com/us/app/realfevr-fantasy-sports/id1111611723
ቡድን እንዴት ነው የሚዋቀረው?
በዚህ ጨዋታ ቡድን ሲገነቡ 15 ተጫዋቾችን የመምረጥ ሀላፊነት አለብዎ። በዚህ ምርጫ ከአንድ ቡድን ውስጥ ከሶስት በላይ ተጫዋቾች መምረጥ አይቻልም ። እነዚህን ተጫዋቾች መርጦ ቡድኖን ለማሟላት የ100 ሚሊዮን ብር ($) በጀት የተመደበ ሲሆን አብቃቅተው 2 ግብ ጠባቂዎችን፣ 5 ተከላካዮችን፣ 5 አማካኞችን እና 3 የፊት መስመር አጥቂዎችን መግዛት ይጠበቅባቹሀል።
የመጀመሪያ ጊዜ ቡድኖን ሰርተው ካስገቡ በኋላ በቀጣዩ ሳምንት ለሚደረጉ ጨዋታዎች ከ2 ተጫዋች በላይ ማዘዋወር አይፈቅድም፤ ካዘዋወሩ ለእያንዳንዱ ያዘዋወሩት ተጫዋች 4 ነጥብ ከነጥብዎ ላይ ቅነሳ ይደረግቦታል። የገነቡትን ቡድን ለማስገባት የጨዋታ ሳምንት ከመጀመሩ 60 ደቂቃዎች በፊት ሙሉ ዝውውር አርገው ማጠናቀቅ ይጠበቅብዎታል። ቀነ ገደቡ ካለፈ ያለፈው ሳምንት የነበረውን አሰላለፍ ይዞ የሚቀጥል ሲሆን ለቀጣዩ ሳምንት ግን አንድ ተጨማሪ ዝውውር የማድረግ እድልን ያገኛሉ። ይሄም ማለት በቀጣዮ ሳምንት ሶስት ተጫዋቾችን ማዘዋወር ይችላሉ ማለት ነው።
ቡድንዎን ሰርተው ከጨረሱ በኋላ ቋሚ 11 ተሰላፊዎችን መርጠው 4 ተጠባባቂ ተጫዋቾችን ተቀያሪ ወንበር ላይ የሚያስቀምጡ ይሆናል። ቋሚ ተሰላፊ አርገው ያሰለፏቸው 11 ተጫዋቾች ብቻ በየጨዋታ ሳምንቱ በሚያገኙት የአቋም ነጥብ ድምር የቡድኖ ውጤት ሆኖ ይመዘገባል። auto-sub የሚለው ON ሲሆን ፤ ቋሚ አሰላለፎ ላይ ያሉ ተጫዋቾች ካልተሰለፉ ከተቀያሪ ወንበር ላይ ያሉ ተጫዋቾች ለእርሶ ነጥብን ለማስገኘት የሚጀምሩ ይሆናል። በተቃራኒው ኦን ካልሆነ እና manual substitution ከሆነ ይህ አገልግሎት አይሰራም።
አንበል የሚያረጉት ማንኛውም ተጫዋች ያገኘውን ነጥብ እጥፍ የሚያገኝ ሲሆን አንበሎ በጨዋታው ካልተሰለፈ ምክትል አንበሎ የዚህ እድል ተጠቃሚ ይሆናል። ሁለቱም ካልተሰለፉ ይሄ እድል የሚያመልጦ ይሆናል።
How to download and register
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Addis Ababa