16/09/2024
🚨 ሰበር ክለባዊ ዜና
ጥቁር አንበሳ የእግር ኳስ ክለብ በ 2017 አ.ም የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጃቸው የአዋቂ እና ታዳጊ ወንዶች የውድድር አይነቶች ተሳታፊ መሆናችንን እናሳውቃለን።
ጥቁር አንበሳ የእግርኳስ ክለብ በተለያዩ የእድሜ ዕርከኖች የአዳዲስ ተጫዋቾች ምልመና በቅርብ ቀናት ስለሚጀምር በምልመላ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫዋቾች ከስር የተቀመጠውን የቴሌግራም ሊንክ በመጫን ክለቡ የሚያወጣውን መርሃ ግብሮችን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::
https://t.me/Blacklionfootballclub
08/10/2023
🚨 ጥቁር አንበሳ የእግር ኳስ ክለብ ለ 2016 አ.አ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጃቸው ውድድሮች በአዋቂ ወንዶች እና U-13 ይሳተፋል በመሆኑም ክለባችን ከአምና ተሳትፎው ይበልጥ ለማጠናከር የአዳዲስ ተጫዋቾችን ምልመላ ጀምሯል ::
🚨 ይህን ታላቅ ራዕይ ያለው የእግር ኳስ ክለብ ለመቀላቀል የምትፈልጉ ቀጣይ የምልመላ ቀን ...
⏩ ማክሰኞ መስከረም 29
🏟️ ዊንጌት አደባባይ ኖክ ማደያ አጠገብ የሚገኘው ሜዳ
⏰ 2:00 ጠዋት
📞 +251911893818
11/09/2023
🦁 HAPPY ETHIOPIAN NEW YEAR 2016 E.C 🦁
ለመላው ደጋፊዎቻችን ለውድ ተጫዋቾች እና የክለባችን አመራሮች አመቱ ፍሬማ ሰላም ከጤና ጋር እንዲሆንላችሁ እንመኛለን 🌿🌻🌼
08/09/2023
🚨 ሰበር ክለባዊ ዜና 🚨
🦁 ጥቁር አንበሳ U-13 የአዲስ ከተማ ዋንጫን በዛሬው አንስቷል 🦁
የጥቁር አንበሳ ደቦሎች ለክለባችን የመጀመሪያ የሆነውን ዋንጫ ያስገኙ ባለታሪክ ሆነዋል 👍
ጥቁር አንበሳ የእግር ኳስ ክለብ በተመሰረተ በጥቂት ወራት በአዋቂ ወንዶች እና ከ13 አመት ቡድኖቹ ድልን እየተጎናፀፈ የክለባችን ታላቅ ህልም ወደሆነው የኢትዮጵያ ዋናው ፕሪሚየር ሊግ እየተንደረደረ ይገኛል ‼️
አብሮነታችሁ ሁሌም የሚያበረታን የክለባችን ደጋፊዎች ፤ ውድ ተጫዋቾች እና አመራሮች እንኳን ደስ አላችሁ ‼️
20/08/2023
🚨 2015 በአዲስ አበባ ፌዴሬሽን ሲካሄድ የቆየው የአንደኛ እና የከፍተኛ ሊግ ውድድሮች ፍፃሜ ተጠናቀዋል
ጥቁር አንበሳ የእግር ኳስ ክለብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዋቂ ወንዶች እና ከ 13 በታች ቡድኖቹ ተሳትፎ አበረታች ውጤቶችን ማስገንዘብ ችሏል 🦁
የ አ.አ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ደረጄ በመዝጊያው እንደተናገሩት ውድድሮቹን ለማካሄድ ከፍተኛ ፈተና ማለፋቸውን እና በተለይም ከፌዴሬሽኑ ጋር የስፓንሰር ሺፕ ስምምነት የፈፀሙ ድርጅቶች ክፍያ ባለመክፈላቸው የኮሚሽነሮች ክፍያን ጨምሮ ውድድሮችን በጥራት ለማካሄድ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን መክፈል ስላልቻሉ የቡድኖች ውጤት ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን በመጥቀስ በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል ::
30/07/2023
🦁 በቅርቡ በዜማ ለደጋፊዮቻችን በይፋ የሚለቀቀው የጥቁር አንበሳ እግር ኳስ ክለብ አዲስ ዝማሬ 🦁
የጀግኖች ተምሳሌት የነፃነት አርማ
የአይበገሬነት የድል ብስራት ዜማ።
የጥንካሬነት ሀያል ብርታት ተስፋ
በውስጣችን አለ በጥቁሮቹ
አንበሶች መቼም የማይጠፋ።
ትልቅ ነው ህልማችን
ትልቅ ነው ግባችን
የሀገር ኩራት መሆን በአንበሶቻችን።
ጥቁር አንበሳ
መጣ እያገሳ።
በእግር ኳሱ ሜዳ፣
በሰላሙ መንደር፣
ሊፋለም ሊያሽንፍ፣
ታሪክን ለመስራት፣
እንደ አያቶቻችን፣
ተሰልፏል ዛሬም፣
በወኔ በኩራት።
ትልቅ ነው ህልማችን
ትልቅ ነው ግባችን
የሀገር ኩራት መሆን በአንበሶቻችን
........
22/07/2023
🚨🚨 ታላቅ የምስራች 🚨🚨
ጥቁር አንበሳ የእግር ኳስ ክለብ አዲስ አበባ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጃቸው አመታዊ ውድድሮች በተለያዩ የእድሜ እርከኖች ተሳትፎውን በማጠናከር ለሚቀጥሉት አመታት የውድድር ተሳታፊ ቡድኖቹን ይበልጥ ለማጎልበት - የተስፋ ታዳጊ ተጫዋቾችን ለ 6 ወራት የሚቆይ ልዩ የእግር ኳስ ስልጠና አዲስ በከፈትነው ደቦል አካዳሚ ለማካሄድ ከ አ.አ ስፓርት ቢሮ ሙሉ ፍቃድ አግኝተናል 🦁
ደቦል ጥቁር አንበሳ አካዳሚ በእግር ኳስ ሙያ በቂ እውቀት ባላቸው አሰልጣኞች እና የተሟላ የስልጠና ትጥቆችን በማዘጋጀት አዲስ አበባ ለምትገኙ ተስፈኛ ተጫዋቾች U-13 U-15 U-17 ልዩ ስልጠና ያሰናዳን ሲሆን የምዝገባ ሙሉ መስፈርቶችን እና የስልጠና ሜዳዎችን በሚቀጥሉት ቀናት እናሳውቃለን 🦁
12/06/2023
🔥 የጨዋታ ውጤት 🔥
🦁 ጥቁር አንበሳ 3️⃣ - 0️⃣ ተስፋ ሊግ ⚽️
⏰ ሰኞ 01/11/2015
⌚️5:00
🏟️ ጀል ሜዳ
⚽️ አ.አ አንደኛ ዴቪዚዮን 23 ኛ ሳምንት ጨዋታ
https://t.me/Blacklionfootballclub
09/06/2023
🚨 ሰበር ክለባዊ መረጃ 🚨
የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አንደኛ ሊግ የመጀመሪያው የውድድር ወቅት አጋማሽ ተጠናቀቀቀቀ 🦁
🦁 ጥቁር አንበሳ U-13 አጠቃላይ የሊግ ውጤት 🦁
7️⃣ ጨዋታ
5️⃣ አሸነፉ
1️⃣ አቻ
1️⃣ ሽንፈት
ደቦሎቹ በ 16 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ከመሪው ወይራ ሰፈር እግር ኳስ ቡድን በ 3 ነጥቦች ብቻ ርቀው ሊጋቸውን አጠናቀዋል በቀሪ ጥቂት ጨዋታዎች የአንደኛ ደረጃን እንደሚቆጣጠሩ ባለሙሉ ተስፋ ነን 🦁
🦁 ምንግዜም ጥቁር አንበሳ 🦁
08/06/2023
🔥 የጨዋታ ውጤት 🔥
🦁 ጥቁር አንበሳ ❹ - ❶ አቢሲኒያ ⚽️
⏰ ሀሙስ 01/10/2015
⌚️5:00
🏟️ ጀሞ ሜዳ
⚽️ አ.አ አንደኛ ዴቪዚዮን 22 ኛ ሳምንት ጨዋታ
https://t.me/Blacklionfootballclub