Girmachew Eniyew/DC Sport

Girmachew Eniyew/DC Sport

Share

this page used to sport news

31/03/2021

ጨዋታው ለምን ተቋረጠ እንዴትስ ቀጠለ?
********************************
የኮትዲቯር እና የኢትዮጵያ ጨዋታ ሊጀመር 3 ሰዓት ሲቀረው የእለቱ ዋና ዳኛ በኮቪድ መያዛቸውን ተከትሎ የጨዋታው ኮሚሽነር ከካፍ ጋር በመነጋገር 4ኛ ዳኛው ጨዋታውን የመምራት ሚና ሲሰጠው፤ ጨዋታው ያለ 4ኛ ዳኛ እንዲጀመር የጨዋታው አስተባባሪ እና የጨዋታው ኮሚሽነር ወሰኑ። ጨዋታው በ31 ዲግሪ ሴሊሽየስ እና humidity 82 የተካሄደ ሲሆን፤ የውሃ እረፍት እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ብንጠይቅም በውድድሩ በካፍ የተመደቡት ዶክተር እምቢታን በመምረጥ ጨዋታው የቀጠለ ሲሆን 81ኛው ደቂቃ ላይ ጨዋታውን ሲመሩ የነበሩት ዳኛ በነበረው የአየር ሁኔታ ተዝለፍልፈው በመውደቃቸው ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ፤ ጨዋታው ያለ 4ኛ ዳኛ ሲመራ ስለነበር ጨዋታው 81ኛው ደቂቃ ላይ ተቋርጧል። በመቀጠል ሌላ ኮትዲቯራዊ ረዳት ዳኛ እንዲመጣ ተደርጎ ጨዋታውን የመስመር ዳኛው እዲመሩ የሳቸውን ቦታ ደግሞ ኮትዲቯራዊው ተተክቶ ጨዋታው ከተቋረጠ ከአንድ ሰዓት በኋላ ዘጠኙን ደቂቃ እንድንጫወት ተድርጎ ጨዋታው በኮትዲቯር 3ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
Via፦ EFF

Photos from Girmachew Eniyew/DC Sport's post 30/03/2021

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ ።

ትላንት ሰኞ መጋቢት 20/2013 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ግቢ ውስጥ የተደረገውን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህገወጥ ብሎ የጠራውን ምርጫ በሚመለከት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ በኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር፣ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ አሰልጣኞች ማህበር በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸውን እንዲሁም የፌዴሬሽኑ ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫ እና የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር መግለጫ በዝርዝር ይህንን ይመስላል ።

1. የኦሎምፒክ ኮሚቴም ሆነ ብሄራዊ ፌዴሬሽኖች የሚመሩበትን መመሪያ ካለም አቀፍ የስፖርት ማህበራት ዋና ዋና የህግ ምሰሶዎችን በመውሰድ በዋናነት በሃገሪቱ መንግስት በተወከለ የስፖርት ኮሚሽን ከሚያወጣው የስፖርት ማህበራት መመሪያ በመነሳት መሆን ሲገባው መንግስት ሆነ ስፖርት ኮሚሽን አያገባውም በሚል ንቀትና ከአለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ህግና ደንብ የሚቃረኑ የህግ አንቀፆችን በመጨመር የተፈፀመ ሲሆን በአንድ ሃገር ውስጥ ያሉ የስፖርት ማህበራት ከሃገሪቱ የልማት ስትራቴጂና ፖሊስ በመነሳት ተጨባጭ ሁኔታዎችን በሚቃኝ መንገድ መሆን ሲገባው የፌደራል ስፖርት ምክር ቤት የሰጠውን አቀጣጫ ወደ ጎን በመተው የተከናወነ ምርጫ በመሆኑ ተገቢ አለመሆኑን እንገልፃለን ይንንም የሃገራችን መንግስት ጉዳዩን በማጣራት አስፈላጊ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን፤

2. ታህሳስ 25/2013 ዓ.ም. በሃዋሳ በተካሄደው 45ኛ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ጠቅላላ ጉባኤ ስለ ቀጣይ ምርጫ በኦሎምፒክ ኮሚቴው ፕሬዝዳንት ሞሽን ቀርቦ የጠቅላላ ጉባኤው አባላት ሃሰብ በመስጠት ምርጫ ከቶኪዮ ኦሊምፒክ 2020 በኋላ እንዲሆንና ያለው ስራ አስፈፃሚ እስከ መስከረም 2014 ዓ.ም. ድረስ እንዲቀጥል በሙሉ ድምፅ ውሳኔ ካገኘ በኋላ ምርጫ ማካሄድ ተገቢነትና
ህጋዊነት የለውም እንላለን፤

3. አንድ የስፖርት ማህበር (የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ) ጉባዔ ማካሄድ የሚችለው በዓመት አንድ ጊዜ ወይም አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥም አንድ አስቸኳይ ጉባዔ ማካሄድ ሲኖርበት ተደጋጋሚ ጉባዓዎችን በማካሄድ የአትሌትንና የህዝብን ገንዘብና የስፖርት ትጥቅ በከፍተኛ ደረጃ ለብክነት የዳረገ በመሆኑ በሚመከተው የመንግስት አካል ሊመረመር ይገባዋል እንላለን፤

4. ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የቅርጫት ኳስ ፕሬዝዳንትነታቸው በጠቅላላ ጉባዔ ምርጫ ያልተከናወነና ያልፀደቀ በመሆኑ ለኦሎምፒክ ኮሚቴ ለፕሬዝዳንትነት በእጩነት ቀርበው ሊመረጡ ስለማይችሉና ህጋዊነት የሌለው በመሆኑ እንደገና በሚመለከተው አካል ሊፈተሸ ይገባዋል፤

5. በህገወጥ ምርጫው ላይ ከተመረጡ ስራ አስፈፃሚዎች መካከል የክብደት ማንሳት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆኑት የስፖርት ማህበራት የሚፈቅደውን አገልግሎት ዘመናቸው ስምንት ዓመት ያለፈ በመሆኑ የተመረጡበት አግባብ ህገወጥ በመሆኑ ሊሰረዝ ይገባዋል፤

6. የሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴና የአትሌት ብርሃኔ አደሬ በኦሎምፒክ ኮሚቴ ከፍተኛ አመራርነት መግባታቸው ካደረጉት የሃገርን ሰንደቅ ዓላማ ማስከበር አንፃር ተገቢ ቢሆንም ሊወክላቸው የሚገባው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አንጋፋ አትሌቶች ማህበር ወይም ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ አትሌቶች ማህበር የተወከሉ ባለመሆናቸው ህጋዊ መስመሩን ያልተከተለ ነው፤

7. አንድ ሃገራዊ የስፖርት ማህበራት ምርጫ መካሄድ ያለበት በግልፅና የሚዲያ አካላት ባሉበት መሆን ሲገባው በድብቅ በኦሎምፒክ ኮሚቴ ግቢ ውስጥ በተተከለ ድንኳን መካሄዱ ግልፅነት የጎደለውና ከጥቅማ ጥቅም ጋር የተያያዘ ስለሚያስመስለው እና ህጋዊ መሰረት ስለሌለው የሚመለከተው የሃገራችን መንግስትና ስፖርት ኮሚሽን መርምሮት ምርጫው እንዲሰረዝ ለዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ደብዳቤ እንዲፅፍ እንጠይቃለን፡፡

በአጠቃላይ አሁን ባለው የኦሎምፒክ ኮሚቴው አሠራርና አደረጃጀት የምናስበውና የምንጠብቀውን የቶኪዮ 2020 ጨዋታ የሚያደብዝዝና የአትሌቶቻችንን ስነ-ልቦና በመጉዳት ውጤት እንዲበላሽ ስለሚያደርግና ያለን ግንኙነት ከአለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የሚላኩ የተለያዩ ሰርኰላሮችና ፌዴሬሽኑ የሚልካቸው የምዝገባና ሌሎች መሠል ደብዳቤዎች እየደረሱ ባለመሆኑ በገለልተኛ ኮሚቴ የኦሎምፒክ ኮሚቴው እንዲመራና የአገራችን የኦሎምፒክ ወጤት እንዲቀጥል በጋራ አንጠይቃለን፡፡

ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አቋም መግለጫ በመቀጠል ከኢትዮጵያ አትሌቲክ አትሌቶች ማህበር የተሰጠ የአቋም መግለጫ፣

መጋቢት 21/2013 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ህገ-ወጥ ምርጫ ላይ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ አትሌቶች ማህበር የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አትሌቶች ማህበር እየተካሄደ ባለው የአትሌቲክስ ስፖርትን የሚጎዳ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ያላትን ስምና ክብር የሚቀንስ ለተተኪ ትውልድ የምንወርሰው መጥፎ ሁኔታ እልባት ካላገኘ እንዚህ ነገሮች ሊያደርሱብን ይችላሉ፡፡ የአለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ኢትዮጵያን ከኦሎምፒክ ውድድር እንዳያግዳት ስጋት አለን፡፡

በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እየተካሄደ ያለውን ህገወጥ አሰራር እንዲቆም እያስገነዘብን ኮሚቴው እያደረገ የሚገኘውን ህገወጥ እና አላግባብ የሆነ አሰራርን በመቃወም በቶኪዮ 2020 ሃገራችንን በአትሌቲክስ የሚወክሉ አትሌቶች፣ አሰልጣኞች፣ የቀድሞ አትሌቶች የፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የሌሎች ሀገር አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽን አመራሮች በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጽ/ቤት በግቢ ውስጥ በመግባት ስርዓት ባለው ሁኔታ በፀጥታ ኃይሎች በተገኙበት በኦሎምፒክ ኮሚቴው አየተካሄደ ያለው ህገ-ወጥ አሠራሮችና አካሄዶች በጽኑ በመቃወም ድርጊቱን በአስቸኳይ እንዲቆምና የሚመለከተው አካል በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ ጠይቀዋል፡፡

እንደሚተወቀው በታህሳስ 25/2013 ዓ.ም በሃዋሳ በተደረገ ጉባዔ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ መስከረም ላይ ከቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ማግስት እንዲደረግ ቢወሰንም ቢሾፍቱ ላይ በተጠራ ጠቅላላ ጉባዔ በባህርዳር ጠቅላላ ጉባዔ አካሂዶ ምርጫውን ለማከናወን ቢንቀሳቀስም በባህርዳር ለማካሄድ ሲከለከል በሃዋሳ ለማድረግ ሞክረው የነበረውን የኦሎምፒክ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባዔ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫን እንዳይካሄድ በፀጥታ ኃይሎች ቢታገድም ለሌቱን ከሃዋሳ የተወሰኑ የክልል ኮሚሽነሮችንና የስፖርት ማኀበራት እንዲሁም አሶሴሽኖችን ይዞ በትናትናው ዕለት በኦሎምፒክ ኮሚቴው ቅጥር ግቢ ድንኳን በመጣል በድብቅና ግልጽ ባልሆነ ሕገ-ወጥ ምርጫ አካሂዷል፡፡

ከዚህ ቀደም 13 የስፖርት ሃገር አቀፍ የስፖርት ፌዴሬቨኖችና አሶሴሽኖች ተቋውሟቸውን ለዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና ለሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት በጽሁፍ ማሳወቃቸው ይታወቃል፡፡

ስለዚህ ማኀበሩ ይህንን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቃወም መሆኑን ለህብረተሰቡ እያሳወቀ መንግስትም ጉዳዮን በትኩረት አይቶ አቅጣጫ እንዲሰጥበት እንጠይቃለን፡፡

መላው የኦሎምፒክ ተሳታፊ አትሌቶችና አሰልጣኞች እንዲሁም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አትሌቶች ማኀበር

Photos from Girmachew Eniyew/DC Sport's post 30/03/2021

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ታሰሩ በሚል በአንዳንድ ማህበራዊ ድረገፅ ትናንት የተወራው ወሬ ፍፁም ሀሰት መሆኑን ኦሎምፒክ ኮሚቴ ገለፀ ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ እርስ በርስ ለማነጋገር ዶ/ር አሸብርን እና ኮማንደር ደራርቱን ይዞ በሄደበት ወቅት ዶ/ር አሸብር ታሰረ በሚል የተሳሳተ መረጃ ለቀዋል ። ይሁን እንጅ ዶ/ር አሸብር ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር ተወያይተው ወዲያውኑ ወደቤታቸው መመለሳቸውን ኦሎምፒክ ኮሚቴ አስታውቋል ።

30/03/2021

ቡምቡምቡምቡምምምምምም……….
የተከበራችሁ የግርማቸው እንየው ቻናል ተከታታዮች እንዴት ናቹ? ዛሬ 10 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ከ አይቬሪኮስት የሚደረገውን አጓጊ ፍልሚያ በዚሁ በዩቱብ ቻናላችን በቀጥታ ወደናንተ እናደርሳለን አብራችሁን ሁኑ፡፡ሀሳብ አስታየታችሁን እንዲሁም ግምታችሁን ላኩልን፡፡ቻናላችንንም share,Like,SUBSCRIBE ማድረጎን አይርሱ፡፡እናመሰግናለን፡፡

Photos from Girmachew Eniyew/DC Sport's post 30/03/2021

ዛሬ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በቅጥር ግቢው ውስጥ ምርጫ አድርጎ እንዳጠናቀቀ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱቱሉ ፣ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንተ አትሌት ገዛሃኝ አበራ እና የኦሮሚያ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ፍስሃ ገ/ሚካኤል የቅጥር ግቢውን በር በመኪና ጥሰው በመግባት ረብሻ መፍጠራቸውን የኦሎምፒክ ኮሚቴ ዋና ፀሀፊ አቶ ዳዊት አስፋው ተናግረዋል ። ኮማንደር ደራርቱ ፊትለፊት ያገኘቻትን አትሌት ብርሀኔ አደሬን ፀያፍ ስድብ ከመሳደብ ባለፈ ለመደባደብ ተጋብዛለች ብለዋል አቶ ዳዊት ። የአዲስ አበባ ፖሊስ ወደ ቅጥር ግቢው በመግባት ለ6 ሠአታት አግቶናል ሲሉ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ አንድ የጉባኤው አባል ለዝግጅት ክፍላችን ነግረውናል ። ኮማንደር ደራርቱ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሠራተኞችን እና አትሌቶችን በመያዝ በተለያዩ መፈክሮች ተቃውሞዋን ገልፃለች ። ደራርቱ ምርጫው ህገወጥ ነው ስትል የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በበኩሉ በብርሀኔ እና ሀይሌ መሸነፏን አለማመኗን ያሳያል ብሏል ። ደራርቱ ከቀናቶች በፊት ወደ አለምአቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የፃፈችው ደብዳቤ ኢትዮጵያን ለማስቀጣት ያለመ ቢሆንም ብዙ ተፃፅፌ አገሪቷ በኦሎምፒክ እንዳትቀጣ አድርጌያለሁ ይላሉ ዶ/ር አሸብር ።

Photos from Girmachew Eniyew/DC Sport's post 29/03/2021

ሰበር ዜና
=====================
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤውን በሃዋሳ እንዳያካሂድ ታገደ ። የታጠቁ የሲዳማ ፖሊስ አባላት ወደ ሀይሌ ሪዞርት በመግባት ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጉባኤውን እንዳያካሂድ ከልክለዋል ። የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በበኩሉ የደቡብ ክልል ፍቃድ ሰቶኝ እያለ ጉባኤው መከልከሉ ትክክል ያልሆነ እና አገርን በኦሎምፒክ ለማስቀጣት የሚደረግ ሩጫ ነው ብሎታል ። በኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ለሚመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወገንተኝነት በማሳየት የኢፌዴሪ ምክትል ኮሚሽነር ዱቤ ጁሎ የጉባኤው አባላት እንዳይገኙ ሲያግባቡ የነበረ ቢሆንም በርካታ የጉባኤው አባላት ይህንን ሴራ እቁብ ሳይቆጥሩ በመገኘታቸው ዶ/ር አሸብር አመስግነዋል ። ይሁን እንጅ ዛሬ ጠዋት ጉባኤው ሊደረግ ሲል መሳሪያ የያዙ የሲዳማ ፖሊሶች የጉባኤውን አባላት ከአዳራሽ አስወጥተዋል ። የተወሰኑትንም ለሠአታት ያክል አስረው ፈተዋል ። ይህ ድርጊት መፈፀሙን የአለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የሚያውቅ ከሆነ የመንግስት ጣልቃ ገብነት በሚል ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ የሚያሳግዳት ይሆናል ። ይህ የሀዋሳው የኦሎምፒክ ኮሚቴ ጉባኤ በተከለከለበት በዛሬው እለት ኮማንደር ደራርቱቱሉ ራሷ በምትመራው አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በስካይ ላይት ሆቴል እውቅና እየተሰጣት ይገኛል ። ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤየን እንደማደርግ እየታወቀ ይህንን የደራርቱን እውቅና ማድረግ የሴራ ነው ሲል አጣጥሎታል ። እውቅናው መሰጠት ካለበት ለደራርቱ ብቻ ሳይሆን ለሀይሌ ፤ ቀነኒሳ ፣ ሚሊዮን ፣ መሠረት ፣ ጥሩነሽ ፣ ቲኪ ገላና ፣ ገዛሃኝ አበራ እና ለሌሎቹም ኦሎምፒያዶች በጋራ ሊሆን ይገባ ነበር ብሏል ።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Addis Ababa